Telegram Web Link
በታገተው ፓስታና ማኮሮኒ ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶች፡-

👉 በዕውቀቱ ሥዩም፡- ‹‹ጅብ›› የሚለው ሥም የመጣው ከጅቡቲ ነው ብዬ ስናገር ያመነኝ አልነበረም፡፡

👉 አቶ ንጉሱ፡- በዛሬው እለት ጅቡቲ ሁለት መርከብ ፓስታና መኮሮኒ የማገት
አዝማሚያ አሳይታ የነበረ ቢሆንም፣ መንግሥታችን ባደረገው ድርድር ከፓስታና መኮሮኒው በተጨማሪ አንድ መርከብ ሩዝ ማስመለስ ተችሏል፡፡ የቀረውን የማስመለስ ሒደቱም ተጠናክሮ የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

👉 ታምራት ነገራ፡- የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊቱን ልኮ ከፓስታና መኮረኒውን በተጨማሪ ጅቡቲን ማስመለስ አለበት፡፡

👉 ዶክተርዬ፡- ዛሬ ከወንድሜ እስማኤል ኦመር ገሌ ጋር በስልክ ተደዋውለን ሁለቱ አገራት ፓስታና መኮሮኒውን በጋራ መቀቀል እንደሚኖርባቸው ተነጋግረናል፡፡ ብሎም ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ፓስታውን ለመብላት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ጅቡቲ የሹካ ድጋፍ ታደርጋለች›› በማለት ፕሬዝዳንቱ ቃል ገብተውልኛል፡፡

👉 ሥዩም ተሾመ፡- ጅቡቲ ላይ ለተራገፈው ፓስታና መኮሮኒ ከእስራኤል
ያገኘውን ዶላር ሰጥቶ የማራገፊያ ወጪውን የሸፈነው አብን ግማሹን ሊካፈል የተወሰኑ አመራሮቹን ወደ ጅቡቲ መላኩን የሚገልጽ አፈትላኪ መረጃ ደርሶኛል፡፡

👉 ከንቲባችን፡- ፕሬዝዳንት ኦመር ገሌ ጆንያ ተሸክመው የተነሱትን ፎቶ ሶሻል
ሚዲያ ላይ ባለጠፉበት ሁኔታ የእኛ ፓስታና ማኮሮኒ ጅቡቲ ላይ ተራግፏል
ለማለት እቸገራለሁ፡፡

👉 አንዱዓለም ቡኬቶ፡- ‹‹መለስ ዜናዊ አሰብን አሳልፎ ባይሰጥ ኖሮ ፓስታውም
ባልተራገፈ፣ እሱም በሰላም ባረፈ ነበር››
ሳባዊ ደሳለኝ፡- ወያነን እኮ አለማድነቅ አይቻልም! ይሄን የጅቡቲን ባሕርይ
ስለምታውቅ ነበር ከፕላስቲክ የተሰራ ሩዝ ስታስገባ የነበረው!

👉 ቬሮኒካ መላኩ፡- ‹‹የሚቀቅለውን የተነጠቀ ሕዝብ ቀቃዩን ይበላል›› በማለት ማካቬሌ እንደተናገረው… የኢትዮጵያ ሕዝብ ፓስታና መኮሮኒው ከመቁላላቱ በፊት ያለ ምንም ጦር መሣሪያ በሹካ ብቻ ጅቡቲን ቀቅሎ የተወሰደበትን ማስመለሱ አይቀርም፡፡

👉 ጌታቸው ረዳ፡- ሼፍ መሆን ሲገባቸው የአገር መሪ መሆን የቻሉ ወፈፌዎች ፓስታና መኮሮኒ ባስወሰዱ ቁጥር ሥራችንን ትተን ስለ እንዲህ አይነት ትርኪ ምርኪ የምናወራበት ጊዜ የለንም፡፡ እኛ ዘንድ ሹካ የማኮሮኒ መብሊያ ሳይሆን መቆፈሪያ ሆኖ ሸሚዛችንን ሰቅስቀን የአርሶ አደራችንን ማሳ እያለማንበት ነው፡፡ 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii
ባህላዊ
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይዘሮ አልጣሽ ስመጥር የባህል ህክምና አዋቂ ናቸው ፤ አምስት መቶ በላይ ብራናዎችን መርምረዋል:: ከምስጢራዊ ጠቢባን ተምረዋል- ይባላል፤ የሆነ ጊዜ ላይ ወደ ቤታቸው ሄድኩ፤ ለካርድ አምስት መቶ ብር አስቀድሜ ከፈልኩ፤ካርዱ ራሱ ባህላዊ እንዲሆን ታስቦ ከሰኔል የተሰራ ነው፤ ወይዘሮ አልጣሽ ደርበብ ያሉ ውብ ሴትዮ ናቸው፤ አፈወርቅ ተክሌ ስእል ውስጥ ከሚታዩት እናቶች አንዲቱን ይመስላሉ::
“ምንህን ነው የሚያምህ?” ሲሉ ጠየቁኝ::
“ ራሴን! ራሴን በጣም ያመኛል”
“ ህምም …መች መች ነው እሚነሳብህ?”
“ማለዳ ከንቅልፌ ስነሳ"
ወይዘሮ አልጣሽ በዙፋን ቅርፅ በተሰራው ሶፋቸው መከዳ ላይ ተለጥጠው ተመቻቹና እንዲህ አሉ፤
“ በሰው ልጆች ታሪክ የመጀመራው ራስ ምታት ታማሚ ናምሩድ ነው፤ ናምሩድ የተወለደው ባቢሎን ውስጥ ነው ይላሉ ፤ ስተት ነው ፤ትውልዱ ፊንቃዊ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም!! እስከ ሰላሳ ዘመኑ ድረስ ኢትዮጵያ መጥቶ ተቀምጦ ነበር:: ባመመው ቁጥር በራሱ ዙርያ እሚጠመጥማት ነጭ ሻሽ ለብዙ ዘመን ባክሱም ኖራለች:: ልኡል ራስ መንገሻ ዮሀንስ ጠምጥመዋት ፎቶ ተነስተዋል፤ በነገርህ ላይ የልኡሉ ማእረግ ንጉስ ነው! ራስ መንገሻ ይባሉ የነበሩት ጥኑ ራስ ምታት ስለነበረባቸው ነው:: አጤ ምኒልክ ራስ መገሻን ድል ካደረጉ በ ሗላ ሻሺቱን ራሳቸው ይጠመጥሟት ጀመር! "
እምለው ቸግሮኝ ዝም አልኩ::
“ አባትህ ራስ ምታት አለባቸው”?
“ የለበትም ” ብየ መለስኩ::
አልጣሽ ቀጠሉ:-
“ ህምም! ንጉስ ናምሩድ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ አንደኛው ዱርየ ሲሆን ፤ ሌላኛው ጭምት ነበር ዱርየው ልጅ አባቱ ለዘመቻ በወጣ ቁጥር የቤቱን እቃ ጆሮውን እያለ ፈጀው ፤ ጭምቱ ልጅ ግን ዱርየው የሸጠውን እቃ እንደገና በውድ ዋጋ ገዝቶ ወደ ቤቱ ይመልሳል፤ ናምሩድ ሊሞት ሲል ለጨዋ ልጁ ዘውዱን ከራሱ አውልቆ ሲሰጠው ለዱርየ ልጁን ደግሞ ራስ ምታቱን አወረሰው ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መንግስትም ራስ ምታትም በዘር እሚተላለፉ ሆነዋል! ይህንን ነገር መፅሀፈ ኩፋሌ አምልቶ አስፍቶ ፅፎታል፤ ለመሆኑ ራስህን ሲያምህ ምን ታደርጋለህ?”
“ ቡና ጠጣለሁ”
“ ቡና ይቅርብህ! “ አሉ ወይዘሮ አልጣሽ “ በነገራችን ላይ በሰው ልጆች ታሪክ የመጀመርያው የቡና ሱሰኛ አፄ ሱስ-ንዮስ ነበር፤ ኢሉምናምንቴዎች ፖርቱጋሎች የቡናን አመል ከታች ማዶ አምጥተው አለመዱት! ሱስ-ንዮስ አገራችንን ለፖርቱጋሎች ትቶ : ቡናውን አስፈልቶ ፤ ፈንድሻውን አስቆልቶ፤ አጫጭሶ ከልጁ ጋር አብሮ ፏ-ሲል ይውል ነበር፤ፏ-ሲል የሚለው አነጋገር በጊዜ ብዛት " ፋሲል "ሆኗል“ ራስ ምታቴ እየጨመረ ሲመጣ ይሰማኝ ጀመር! በመጨረሻ በጉጉት ስጠብቀው የነበረውን መዳኒት የሚያዙልኝ ጊዜ ደረሰ ፤ የሆነ የሰለሞን እፅ ይሰጡኛል ብየ ጠብቄ ነበር፤ ፓራሲታሞል እንዳዘዙልኝ ስመለከት ግን ውሃ ሆኘ ቀረሁ::
" ምነው?" አሉኝ መደናገጤን አጢነው፤
“ ባህላዊ መድሃኒት ነበር ከርስዎ የጠበኩት”
“ ጃኖ ወይም በርኖስ ለብሰህ ከዋጥከው ባህላዊ መሆኑ መች ይቀራል?”

@wegoch
@wegoch
#ቢዋሹ ቢዋሹ ከፈጣሪ አይሸሹ!!

አንድ ሃብታም የማይመስል ሃብታም ሰው ነበር ኑሮው ሁሉ ከድሃ ያንሳል የአካባቢው ነዋሪ ሁሉ የሆነ የሃብቱ ብዛትና አኗኗሩ ሰማይና ምድር የሆነ ችጋራም ሃብታም ይለዋል… ከቤተሰቡ ጀምሮ ለማንም ለምንም ነገር ቢጠይቅ ምንም ነገር አይደማውም የለኝም ቸግሮኛል ብሎ ማማረር ብቻ ነው የሚያውቀው።

ታዲያ ይህ ሰው አንድ ቀን ቁጭ ብሎ እንዲህ ብሎ ፀሎት ያደርጋል … “ጌታዬ እንደምታየኝ ቡቱቶ ቆሻሻ ለባሽ ደሃ ባርያህ ነኝ ሰዎች እንደሚሉት ሃብታም አይደለሁም ከማንም የማልሻል ደሃ ፉጡርህ ነኝ ሰዎች የሚሉትን አትስማቸው እኔ ምንም የሌለኝ ደሃ ነኝ እርዳኝ"


ሲል ጎረቤቱ የሆኑቱ ሰሙትና ከተለመደባቸው በላይ ጮክ ብለው እየሰቁበት… “ስማ አንተ ሰው አትሳሳት ያለህን የለኝም ማለት የሰጠሀን አልሰጠሀኝም እንደማለት ይቆጠራል ጌታህ የሰጠህን ያለህን አንተ ከምታውቀው ከሚገባህ ባላይ ያውቀዋል

ሁሉም ሰው ጌታውን ስለሚለምን ሁሉም ፀሎት አድራጊ ችግረኛ ስለሆነ አለም የችግር ውጥንቅጥ ውስጥ ስለተዘፈቀች አምላክ ችግረኛን ብቻ ነው የሚያውቀው ብለህ ችግርህን ብቻ አትንገረው ችግርህንም

ድሎትህንም ደስታህንም ሁሉንም ነገርህን ያውቃል ቢሆንም ቢሆንም ንገረው የሚያውቀውን ንገረው ከሁሉ በላይ ባለህ ነገር አመስግነው ለሰጠሀኝ ነገር ተመስገንልኝ በለው እያለህ እየሰጠህ የለኝም ስትል አልሰጠሀኝም እንደማለት ነው እሱ ደሞ ክፋት ነው

ያለህን እንዳይነጥቅህ ተጠንቀቅ… እኛ ሰዎች ሲሰጥህ አላየንም ምን እንዳለህም አናውቅም ስትቸገርም ችግርህን አናየውም ልንረዳህም አንችልም አንተም ልትረዳንም አትችለም የሰጠህን ያለህን የሚሰጥህን

የሚወስድብህ ጌታህ ነው ለሱ እንኳን ታመንና ለምነው እራሱ የሰጠህን ከራሱ ትደብቃለህ ተው እንጂ" ብለውት ሰውየው ሄደ።

ነጋዴው ሲሸጥ ገዢን ሲያጭበረብር ገዢው ስላላውቀ ጌታህም ማጭበርበርህን አያውቀምን? ውይስ ገዢው እኮ አላውቀም ብለን ፈጣሪንም አላወቀም ልንል ነው?

እንሰርቃለን፣ እናጭበረብራለን፣ እንዋሻለን እኛ ይሄን ስናደርግ የተደረገበት ሰው ላያውቅ ይችላል የሁለታችንን ልብ የሚያውቀው ፈጣሪስ አያውቅም?

እሱን አንፈራም?
ከሰዉ ተደብቀን ልናልፍ እንችላለን ሁሉንም ከሚያየው ፈጣሪ በምን እናልፈዋለን ማጭበርበር ማወናበድ ፋሽን ከሆነብን በጣም ቆየ ከላጭበረበርክ ካልሰረክ አያልፍልህም ብሎ ሰባኪ… አልሰረኩም

አልጨበረበርኩም ሰዎቹን አትመናቸው ብሎ የሚፀልይ ከበዛ ነገን መፍራት አለብን በአፋችን በስራችን ከገባንበት በላይ አዘቅት እንዳንገባ መፍራት አለብን… ለሁሉም ከጠፋነው ያለማነውን ይይልን (ካለ ማለት ነው)።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Audio
#የአንድ_እብድ_ትንቢት
( ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት )
@wegoch
@wegoch
@wegoch
★★★ ሞቴን ቀማኝ………#3★★★
(ሜሪ ፈለቀ)

በህይወቴ የሚመጡ ሰወች ሁሉ ኮከቦች ሊሆኑ አይችሉም። ወይ የማያደምቁ ወይ የማይሞቁ ሰወች በምን ስሌት ኮከቦቼ ይሆናሉ? ብዬ ማሰብ ጀመርኩ።

ያሬድ እንደዚያ አይነት ሰው ነው። ምን ያህል እንደሆነ የማላውቀውን የአባቱን ንብረት ስለተካፈልኩት እምብርቴ ላይ ቆሟል። …… አየኸኝን ላስታምመው የተስማማሁት ንብረቱን ከልጁ ጋር እኩል እንደሚያካፍለኝ ከማወቄ እጅግ አስቀድሞ ነው። …… ቀድሞ ነገር ንብረት ይኑረው አይኑረውም አላውቅም። …… ለጥቆ ነገር ከንብረቱ በላይ የመኖር ተስፋዬን ያለመለመ ሰው ነው። …… ሰልሶ ነገር ንብረት ምኔም ያልሆነ ሴት ነኝ። ……

አየኸኝ አዲሳባ መጥቶ ብዙም ሳይቆይ ሆስቲታል ገባ…… የከተማው ድንግርግር፣ ለማየው ነገር ሁሉ እንግዳ መሆኔ…… ሳይለቀኝ የህይወቴ ፈርጥ ኮከብ የህይወት ክሩ ጫፍ ላይ መሆኑን አወቅኩ። …… ህይወት ተለዋጭ ብትሆን የምለውጠው ሁሉ ይመስለኛል። …… አዲስአበባ እንደደረስን ያለውን ንብረት በሙሉ ከልጁ ጋር እንዳካፈለን ነገረን። …… ከዚያች ዓረፍተ ነገር በኋላ ያሬድ ቃል አልተነፈሰም። …… ሆስፒታል በቀን አንዴ ብቅ እያለ አባቱን ያየዋል። …… አያናግረውም። ……

"ከአባቴጋ ያላችሁ ግንኙነት ምንድነው?" አለኝ የሆነ ቀን

"ልጄ ሲለኝ አልሰማህም? ልጁ ነኛ!" መለስኩለት

"እንቦቃቅላ ጨቅላ አደረግሽኝ እንዴ አንቺው? ተሱ እንዳልተወለድሽ አውቃለሁ! ምን ሲሆን አየሽው በይ? እንደየት እንደየት ብለሽ አጠመድሽው? ንብረቱን ብለሽ እንጂ መቼም……" ……  የገጠር አነጋገር ለዛው ያዝ እያደረገው ……  አልጨረሰውም

"በናትህ ተወኝ! ከፈለግክ ሁሉንም ንብረት ውሰደው!! አንተ አባትህ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ የሚያስጨንቅህ ንብረት ነው?" አልኩት አልመለሰልኝም።

"እንኳን እኛ የወረስነው የለፋበትም አልኖረበት!" ቀጠልኩ

"ምንድነው የምዘላብጂው?" ብሎ ትቶኝ ሄደ።

አየኸኝ አፉ ሲያዝ ብዙም አልቆየም። ሀኪሞቹ ሆስፒታል መቆየቱ ምንም ጥቅም ስለሌለው ወደ ቤት እንዲሄድ ነገሩት። …… ቁጭ ብሎ ሞትን መጠበቅ እንዴት ያማል? ለኔ ስቃይ ሆነብኝ። አየኸኝ ግን በስቃይ ውስጥ ሆኖ እንኳን ፈገግታው አልከሰመም።……

"ካልተሻለው ለምን ወደ ቤት አመጣሽው?" አለኝ ያሬድ በሆነው ቀን

"የሚሰጡት ህክምና ስለሌለ እዛ መተኛቱ ምንም ጥቅም የለውም።" መለስኩት

"ታዲያ የተሻለ ሀኪም ቤት ይሂዳ?"

"ቀልድ ነው የያዝከው? ምን ያለኸው ክፉ ነህ? ሲሆን ባለቀች እድሜው በፍቅር ልትሸኘው ሲገባህ……" ብዬ መጨረስ አቃተኝ። ከእንባዬ ግብ ግብ መግጠም አልፈለግኩም። ተሸነፍኩ። አነባሁ።

"ይታከም ማለት ክፋት ነው?" አለ ለዘብ ብሎ

ይሄኔ ግራ ተጋባሁ። አንድ ያልገባኝ ነገር መኖሩ ተገለጠልኝ። ……

"ለመሆኑ በሽታው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?" አልኩት። በጭንቅላቱ ውዝወዛ አለማወቁን ነገረኝ። ይሄኔ ሁሉም ግልፅ አለልኝ። አባቱ እንደሚሞት አያውቅም።

"አባትህ ሀብቱን የተናዘዘው ለምን መሰለህ ታዲያ?" አልኩት

"ሲሻለው ገዳም እንደሚገባ ነው የነገረኝ።"
ግራ ተጋባሁ። ለምን ደበቀው? አየኸኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ያሬድ ማወቅ እንዳለበት አሰብኩ። …… ከአባቱጋ እንዴት እንደተዋወቅን ስነግረው… …

"አንድ ቀን ካያት ሴት እኩል ንብረቱን ያካፍለኛል?" ሲል ውስጤ ሲረግብ ተሰምቶኛል።

"በማየት ከሆነ እኮ እንደውም ካንተ ቀድሞ ነው ያየኝ። እውቂያችን ብዙም አይራራቅም።" አልኩት ብስጭት ብዬ

"ልጁ ነኝ‘ኮ" አለኝ ጥርሱን ነክሶ……

"አባትህ ከሳምንት ያለፈ እድሜ የለውም። ይሞታል። …… የጭንቅላት እጢ ነው ያሉት በሽታውን……" ስላበሳጨኝ ሌላ ቦታ እያየሁ ነው ያወራሁት። እስከምን እንደሰማኝም አላውቅም። ከአጠገቤ ተነስቶ ወደአባቱ ክፍል ሮጠ። …… ተከተልኩት። ……

"ለምንድን ያልነገርከኝ?" እያለ በሩን በርግዶ ገባ። አየኸኝ እስከዛሬ ያላየሁት መመሳቀል ፊቱ ላይ ታየኝ። …… አፍን ሊከፍት ታገለ…  ቃላቶቹ እዛው ከንፈሩ ላይ ድምፅ ሳይሆኑ ይዋጣሉ። እጁን ሊያነሳ ሞከረ…… ጣቱን ከማንቀጥቀጥ ያለፈ ማድረግ አልቻለም። ……

"25 ዓመት እስኪሆነኝ ሳትፈልገኝ… … ልትሞት ስትል ለምን ፈለግከኝ? ሀዘን ልታሸክመኝ? ለምንስ እውነቱን አልነገርከኝም? በፀፀት ልትፈጀኝ?"

እውነቱን ለማውራት አነጋገሩ ያሳዝናል። ደረቱን እየደቃ ጮክ ብሎ ነው የሚያወራው። …… እየሰማሁት እያለቀስኩ መሆኔ የገባኝ እንባዬ የአገጬ ደርዝጋ ሲደርስ ነው።

"ለምን አገኘኸኝ? አባት እንደሌለኝ አምኜ እየኖርኩ ነበር። ለምን መጣህብኝ? ለምን እንደተውከኝ አልቀረህም? ለምን አገኘኸኝ?" እያለቀሰ መሆኑን ሳይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋባሁ። የአየኸኝ ስቃይ አሰቃየኝ። እንባዬን ጠርጌ ያሬድ አጠገብ ደረስኩ። እጁን ያዝኩት። መነጨቀኝ። አጥብቄ ድጋሚ ያዝኩት።

"ምን?" አለኝ እያፈጠጠ

"ያሬድ መናገር አይችልም እኮ እያስጨነቅከው ነው።" አልኩት… … አልሰማኝም መንጭቆኝ ሄዶ አባቱ አልጋ አጠገብ በጉልበቱ ተነጠፈ።

"ታውቃለህ? ትልቅ እስክሆን የሆነ ቀን አባቴ ሊፈልገኝ ይመጣ ይሆናል ብዬ እጠብቅህ እንደነበር? አታውቅም! ታውቃለህ እናቴ ብዙ ሆና እንዳሳደገችኝ? አታውቅም! ታውቃለህ አባቴን ብዬ ባስጨነቅኳት ቁጥር እንደምትንሰቀሰቅ? አታውቅም!! ምንም አታውቅም!! በዛ ሁሉ የናፍቆት ጥበቃዬ ዝር አላልክም። ልትሞት ስትል ግን አገኘኸኝ። ለምን? ምን አደረግኩህ? ለምን ሌላ ናፍቆት ትደርብብኛለህ? ምናለ ክፋትህን እንዳመንኩ ብኖር?" …… ስርቅታው አላናግር አለው። ……

"ወየው…… ወየው…… ወየው ፈጣሪዬ ምን በደልኩህ?" ብሎ ሲጮህ እሪ ብዬ አብሬው መጮህ አምሮኝ ነበር። …… ጭንቅላቱን ይዞ እሪታውን አስነካው። አየኸኝ የአንድ አይኑ እንባው ወደጆሮው ሲሄድ አየሁት። …… ያደረግኩትን ያወቅኩት ካደረግኩት በኋላ ነው። …… እሱ እንዳደረገው መሬቱ ላይ በጉልበቴ ተንበረከኩ። …… አጥብቄ አቀፍኩት። …… አልታገለኝም። ድምፁን አውጥቶ ተንሰቀሰቀ። ……
……
………
አሁንም አልጨረስንም……

@wegoch
@Wegoch
@paappii

#meri_feleke
የኔ ቀን 🙏
........የቤተስኪያኑ ደፍ የሰው ዳና እና ኮቴ ናፍቆ እምባን ባቆረዘዘ አይኑ ተመለከተኝ።
ዜማና ማህሌታይ የተራበው ምኩራብ በዝምታው ውስጥ ህመሙን ላከብኝ።
የደጀ ሰላሙ ዕድሞ በአርምሞ እንደተያዘ የገዳም ካህን ፀጥ ብላል። ረጭ! ላብ የጠገበው የደወል ቤት ገመድ የሚያንገላታውን እጅ ተመኝቶ ትክዝ ብሏል።
እጣን ያማረው ምኩራብ ......ዜማ.....ቅኔ....ማህሌት መስማት ያሰኘው የቤተስኪያኑ ዕድሞ ምእመኑን ታዝቦ ከፍቶታል። የካህናት ወረብ እና ቅዳሴን የተጠማው መንደሬ ከሰማዩ ጋር ተኳርፎ ፊቱን አዙሯል።
አለወትሮም በእረኞች ትንፋሽ የሚዘወረው ዋሽንት ጣእሙ ተለውጦ ሮሮን ማሰማት ጀምሯል። ከዱሩ የሚሰማው የእረኞች ጅራፍም ለእግዜር እንደሚያለቅስ ደሀ ድምፁ ተቀይሯል።
እንደ ልብ የሚቦርቁ የጥጆች ድምፅ በመንደሬ ኩርፊያ ተውጧል። ነገን የዶሮ ኡኡታን ሳልሰማ እንዳይነጋ ሰጋው። ያኔማ እኔ ልሙት ያመኛል።(ከሞት ወዲያ ህመም)
አምላክ ስማን እባክህ ይህቺ መንደሬ ያኮረፈችው ፤ ምኩራብህ በምዕመናኑ እና በቅዳሴ እጦት የተከፋው በኮሮና ነውና ምህረትህን አዝንብልን!!።
እኛ አቅም የለንም ምህረትህን ላክልን እባክህ የኔ ጌታ!
ስማን የኛ ጌታ የቀን ጉርሳችንን የምንሸፍንበት ስባሪ ሳንቲም ለሌለን ለኛ ለድሆችህ ስትል ታረቀን🙏
መሶባችን ተራቁቶ ውሃን እንደተጠማ የበረሃ ተጓዝ አይጩህብን እባክህ🙏
በምህረትህ ሙላት ይህቺን ጊዜን አሻግረን።
ትውልዴ ሆይ ስማኝ አለመፀለይ እርድና አልያም ስልጣኔ አይደለም። ይልቅ አራዳ ይፀልያል።
በፀሎትህ ቤተሰብህን ሀገርህን አስብ!!።
የዛች የመንደሬ ኩርፊያ እኔኑ ከእራሴ ጋር ሲያኳርፈኝ ጊዜ ሆድ ባሰኝ።
በቡና ድምድምታ አመሻሹን ከጨረቃዋ ጋር የምትጨፍረው መንደሬ ክንፏን እንደተመች እርግብ ቅዝዝ ፣ ትክዝ ፣ ፍዝዝ አለችብኝ።
አቤቱ ምህረትህ ቃኘን 🙏
ሀገር ስትታመም ለካ ተራራው ፣ ጋራው ፣ ወንዙ ተረተሩ ሳይቀር ይታመማል። ሀገር ማለት ሰው ነውና ስለሰው ብለን እንፀልይ.. እንጠንቀቅ ...አንፍራ..
የደባያት ውዳሴችን አርያም ድረስ የሚሰማው፣
በቀላያት ፍልስምና በቀንጃችን ያልታረሰው፣
ልቦናችን ደፍርሶ ነው ምህላችን ያልደረሰው።
ፀሎታችን ያልተሰማው።
#ሻሎም_ለኢትዮጵያ
#ሲራክ @siraaq
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሒሳብ አዋቂው ፈረስ ›

አሌክስ አብርሃም

የሆነ ጊዜ አንድ የስነልቦና ሊቅ ፈረሱን እየጎተተ ወደአንድ ዩኒቨርስቲ ሄደና ‹‹ ፈረሴ አራቱን የሒሳብ ስሌት ከማወቅ አልፎ ውስብስብ የሂሳብ ስሌቶችን ውጤት እስከማወቅ ደርሷል ካላመናችሁ ፈትኑት›› አለ …በነገሩ የተገረሙ ሙሁራን ዳኛ ሰይመው ፈተና አዘጋጁ …እንግዲህ አፈታተኑ እንዲህ ነው ለምሳሌ 2 ሲደመር 2 ተብሎ ፈረሱ ይጠየቃል ….ከዛም የተለያዩ ሰዎች ቁጥር የተፃፈበት ሰሌዳ ይዘው ይቆማሉ ፈረሱ ቀጥ ብሎ 4 ቁጥር ወደያዘው ሰው ይሄድና በአፍንጫው ይጠቁማል(ምርጫ እንደማለት ነው) ….በቃ ማባዛት ነሽ ማካፈል መደመር ነሽ መቀነስ ውጤቱን በሰከንዶች ውስጥ ቁጭ ያደርገዋል ፈረሱ ….እናም ‹‹እውነትም ፈረሶች ከተማሩ ከሰው ልጆች እኩል ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ›› ብለው ደመደሙ ምሁራኑ !!

ባለፈረሱ ግን እንዲህ አለ ‹‹ እናተ የማትረቡ ….ፈረስ መቸም ቢሆን ሒሳብ አይችልም …. ፈረሱ መልሱን የሚያውቀው በልብ ትርታችሁ ነው … ቁጥር ይዘው ከተደረደሩት ሰዎች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘው ሰው የልብ ትርታ የተሳሳተ መልስ ይዘው ከቆሙት ሰዎች ጋር ሲነፃፀር የተረጋጋ ነው ...እንስሳት ደግሞ የሰውን ስሜት ጠረን በማሽተት ከፍተኛ በሆነ የማድመጥ ችሎታና የእንቅስቃን ፍጥነት በመመልከት የመረዳት ፈጣን ተሰጥኦ አላቸው።

በዚች ምድር እውነት ይዛችሁ በቆማችሁ ቁጥር እንኳን አእምሯቸውን የሚጠቀሙ ሰብአዊ ፍጥረቶች እንስሳት በደመነፍስ ይለዩዋችኋል … ፈረሱ የመረጠው የእናተን ዝባዝንኬ ቁጥር አይደለም … እውነት ያረጋጋው ልባችሁን እንጅ !! ወደመልሱም የመራው እውነት ያረጋጋው ልባችሁ ነው !!
ልባችሁ !!❤️
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

   ክፍል - ፩

    ጲላጦስ ነኝ - የጀግና አዝማሪ የሙዚቀኛ ልጅ ነኝ
ዜማ እስካሁን በመጣሁበት የህይወት ጎዳና ያልተለየኝ የኔ የምለው ቀረኝ የምለው ወዳጄ ነው
ብዙ ነገር ስላጣሁ ነው ዜማን አሁን ላይ ቀረኝ ያልኩት
ኑ እስቲ በውብ ሙዚቃዎች የህይወቴን ውብ ትዝታዎች ላጋራችሁ
መቼም በትዝታ አድማስ ወደ ኀላ ልወስዳችሁም አይደል
      
         ውሎ አድሮ ነበረ ከተወኝ ፍቅርሽ
          አስቸገረኝ እንጂ ዛሬ ትዝታሽ
        በትዝታ አትጋርጂኝ አይኔን ልግለጥበት
       ፍቅርሽን አንሺልኝ አልጨነቅበት
                          ሙሉቀን መለሰ ነው
ለመጀመሪያ ማጫወቺያዬን ከፍቼላቹሀለሁ አቤት ድምፅ እኔም በሱ ልሳን ወደ ኀላ ተመለስኩ
ዜማውን እያጣጣማችሁ
ይህ ነው የሚባል የህይወት ታሪክ ስለሌለኝ ለኔ ውድ ስለሆነው የፍቅር ታሪኬ ላጫውታችሁ
ለካስ ታሪክ የሚባለው በኖርንበት አለም ውስጥ አንስተን ምንሰጠው ስያሜ ነው
እኔ የኖርኩበትን ምዕራፍ ታሪኬ አልለውም ብቻ ዳሽ በዳሽ አድርጌዋለሁ
ኑ ለማንኛው ከትዝታዬ ጋር የኀሊት እንፍሰስ

የሙዚቃዋን ስንኝ አትርሷት
ውሎ አዳድሮብኛል አረ ሰነባብቶም ከርሞብኛል
ያው እንደ ዘፈኑ ፍቅርሽ አሁን ላይ ለቆኛል ብያለሁ እንግዲህ
 ግና ትዝታዋ ሙሉ ትውስታዬን ተቆጣጥሮት የመርሳት በሽታ እንደገጠመው ሰው እሷ የገባችበትን ህይወቴን ብቻ ነው የማውቀው ሌላው ከትውስታ ማህደሬ ተሰርዟል
ሁሉም .......
በአካል መታ ከምደነግጠው በላይ ትዝታዋ ይበልጥ ያስደነግጠኛል ለምን እንደሆነ እንጃ
ሙልዬ እኮ መዝፈኑን ቀጥሏል ቆይ ጨመር ላድርግላችሁ
እኔም ፋታ ልውሰድ ሁሉን ሳስታውስ የማይቆም ነስር ስላለብኝ ከአፍንጫዬ ሚንጠባጠበውን ደም ልጥረገው
በስቃይ..... 
             ቀኑን እያቃዠ
             ሌት የሚያባንነኝ
             ትዝታሽ መሆኑ
            ዛሬ ነው የገባኝ
                  ሙዚቃዋ ቀጥላለች እያጣጣማችሁ እኔም ይህን የደም ጠብታዬን አፅድቼ ተመልሻለሁ ሌላ ጠብታ እስኪመጣ እቀጥላለሁ
ስለ አፈቅርኩዋት ጉብል ትንሽ ልበላችሁ......

በየቦታው እየተንከላወሱ እያቀነቀኑ ከመዞር ሌላ ምንም ስራ የለኝም ሀሳብ አላማ ነገን የሚሉ ነገሮች ከህይወት መዝገቤ ላይ በጭራሽ የሉም ነበር
አረ እንደውም ግምሹ የእድሜ ዘመኔን በመዞር ነው ያለፈው ማለት ይቻላል
ግን እንዲ ስል ነፍፍፍፍፍ አመት የኖርኩ አይመስልም እድሜይንም ላስጠጣ ሆነ እኮ

ስለሷ ላወራ ብዬ ሌላ ነገር ምቀባጥረው ባሰብኳት ቁጥር ትልቅ ሀይል ያለው ነገር አናቴን ስለሚነድለኝ ነው መቆጣጠር ስለማልችል ቦታዬ ከመሬት ነው እራሴን እስክስት ድረስ ምቱ አይምረኝም
ለነገሩ ይበለኝ.....   

በመዞሬ ጎዳኝ የምለው አንድም ነገር የለም ብዙ ነገር አትርፌበታለሁና ከምላችሁ በላይ ብዙ ነገር አይቼበታለሁ
ተፈጥሮን መርምሬበታለሁ እግሬ መሄድ ብቻ አይደለም ጭንቅላቴም ብዙ አይሽሬ ትዝታዎችን ስለያዘበት
አሁን ይህን ምፅፈው ትውስታዬን ለመመለስ ነው
...........
ስንከላወስ ብዙ ማልጠግባቸው ጓደኞች አጊቻለሁ
ፍቅሬን ግን ከህይወት ትልቁ ሰአታችንን ከምናሳልፍበት ት /ቤት ነው ያገኘሁዋት
ፊያሜታ.......
የበአሉ ግርማዋን የኦሮማይ ድምቀት ፊያሜታ ጊላይ እናንተ እሷን ይሆናል የምታውቁት አይደል
እኔ ስለኔዋ ፊያሜታ ላወራችሁ ነው ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ነው በጀብድ የተሞሉ የጥቁር አሜርካኖችንና የኮሎምቢያ የእፅ አዘዋዋሪዎችን ፊልም መመልከት የጀመርኩት
 ቆይ አንዴ ዘፈኑን ልቀይርላችሁ
                    ቀዘብዬ የኔ ቀዘባ
                    ቀዘብዬ የኔ ቀዘባ
                    ስልሽ ጥላዬ የማለዳ ሲሳይ
                   የጠዋት እጣዬ ነይ ወለባዬ
                            ቴድዬ ነፍሴ መቶላቹሀል እኔም ጠብታዎቼን ላፅዳ እናንተም .....  
ቀዘብዬን የከፈትኩት ለፊያዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀነቀንኩላት ዘፈን ነበር አሁንም እሷው ናት ብዬ ነው
አይ ፍቅር አሁን ድረስ ፊያዬ ነው የምላት እና ትውስታዬን መላሾች እናንተ በሰማችሁኝ ቁጥር ነው ትውስታዬን ምመልሰው
ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ስኮመኩመው የነበረው ነገር ሙሉ ለሙሉ ጭንቅላቴን ተቆጣጥረው በቃ ሀሳቤ ሁሉ Drug diller መሆን ሆነ እንደ እነሱ የራሴን ቡድን አቋቁሜ ሁሉን መስራት አማረኝ
ሀሳቤ አይሎ አይሎ የፈነዳው 11ኛ ክፍል ከገባን በኋላ ነው
ምን እንዳረኩ አሁን ትዝ ባይለኝም በሆነ ነገር ከነበርኩበት ትምህርት ቤት ወጥቼ ፊያዬን ወዳገኘሁበት አዲሱ ት/ቤት የገባሁት
እንግዲህ አዲስ የህይወት ጅማሬ ጀመርኩ በዚች ትንሽ ትውስታዬ ማረሳው አንድ ሀቅ በጣም ደስተኛ እንደነበርኩኝ ነው
                    ጀንበር ተሰናብታ ሰማዩም ጠቆረ
                    ደሞ እንደ ልማዴ ይጨንቀኝ ጀመረ
                                    ሙዚቃው ቀጥሏል
ለኔ ደስታ የፈጠረለኝ የመሰለኝ ነገር ለካ የህይወቴን ሰማይ እያጠለሸው እያጠቆረው ነበር
ይሄን የምላችሁ ካለሁበት የሰመመን ህይወትና ከንሰሀው መንገዴ ላይ ሆኜ ነው
ኑዛዜ አይደለም ግን ስም ያልሰጠሁትን ዳሽ በዳሽ ያልኩት ምዕራፌን እያወጋዋችሁ ነው

  እቀጥላለሁ......
            ብላቴናው በደም ቀለም

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
የዶሮ_ላባዎች_ሲበተኑ

አንድ ወጣት ወደ አንድ ታላቅ አባት ዘንድ ይሄድና "አባት እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን ስም በማጥፋት የጎዳሁ መሆኔ አሁን ታወቀኝ። እና ስለ ሀጢያቴ ምን ላድርግ?" ብሎ ጠየቃቸው።

እኛም ጥበበኛ አባት "የዶሮ ላባ ፈልገህ ሰብስበህ አምጣ" አሉት። ሄዶ ሰብስቦ ይዞ መጣና "ይኸው" አላቸው። "ሂድና በአሉባልታ ወሬ በጎዳሀቸው ሰዎች በር ላይ አስቀምጠው" አሉት።

እሱም ሄዶ አስቀምጦ መጣና ያሉኝን "አድርጌያለው" አላቸው። ከዛ እሳቸውም "በል ሂድና ያስቀመጥከውን ላባ ሰብስበህ አምጣ" አሉት። እሱም "እንዴ ይሄማ አይሆንም፤ ይሄኔ ንፋስ በትኗቸዋል" አላቸው።

እሳቸውም "አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ አንተ የበተንከው የሀሜትና አሉባልታ ወሬ በከተማ ሁሉ ስለ ተሰራጨ መልሶ መሰብሰብ ከባድ ነው" በማለት ከመለሱለት ቡሃላ "አየህ ሀሜተኛ አትሁን። ዳዊት 'አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር' እንዳለው ጠባቂ በሌለው ምላስ በሀሜት ትዳራቸው የፈረሰ ፣ ቢዝነሳቸው የከሰረ ፣ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ፣ ከሚወዱት ሰው የተለዩ ፣ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት የሀሜትን ጦር ፈርተው የራቁ ብዙዎች ናቸው። ሀሜተኞችና አሉባልታ አውሪዎች የሚያጠፉት ጥፉት እሳትና ሰይፍ ከሚያጠፉት ይበልጥ ፈጣንና አደገኛ ነው።

ሀሜተኛ ምላስ በክፉ ጠባዩ አያሌዎችን የገደለ ብዙዎችን የደም እንባ ያስለቀሰ መልካም ኑሮን ያናጋ መርዘኛ እባብ ነው። ብዙዎች በሀሜተኛ ምላስ ጅራፍ ተገርፈው ቆስለው ደምተዋል። ሀሜተኞች ወላጅና ልጅን ወንድምና እህትን ፣ ባልና ሚስትን ፣ አሰሪና ሰራተኛን አቃቅረው አጣልተዋል።"

ስለዚህ እስቲ እራሳችንን እንመርምር ስለምናወራው ነገር እንጠንቀቅ፡፡
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
መንታ መልክ

📖📖📖

ሊዮናርዶ ዳቪንቺ የመጨረሻው ዕራት የሚለውን ሥዕሉን በሚሰራበት ወቅት አንድ ችግር ገጠመው። ከአሥር ዓመታት በላይ በፈጀው በዚህ የስዕል ሥራ ላይ ሁለት ሞዴል መሆን የሚችሉ ሰዎች ጠፉ። ኢየሱስን እና የአስቆሮቱ ይሁዳን...


ዳቪንቺ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊዎችን ጭቅጭቅ መታገስ ከአቅሙ በላይ ሆነበት። ስዕሉን እንዲጨርስ የተሰጠው ጊዜ እየተገባደደ ነው። ...የትም ፍጭው...አይነት መርህ።

🗒🗒🗒

ከእለታት በአንዱ ዳቪንቺ ሞዴል ፍለጋ ወደከተማ ወጣ። በአራት ማእዘን መተላለፊያዎች ጥግ ቆሞ ክርስቶስንም ይሁዳንም ወክሎ መሣል የሚችል ሞዴል አጣ። ከብዙ ፍለጋ በኋላ ድንገት አንድ ሰው ብቅ አለ ከገበያ መሃል...

የአጥንት አወራረዱ፣ የዓይኖቹ ውበት እና ጥልቀት፣ ቁመናው፣ የአፍንጫው አወራረድ፣ ፂሙ፣ ርጋታውና አትኩሮቱ ቁጭ ኢየሱስን። ወደ ስቱዲዮው ይዞት ገባ... ቀለሙን በጠበጠ፣ ሽርጡን ታጠቀ፣ ሰውየውን ከፊቱ አስቀመጠና ስሎ ጨረሰ።

🗒🗒🗒

አሁን የመንፈስ መረጋጋት እየተሰማው ነው። ነገር ግን አንድ ሰው መገኘት አለበት፤ ይሁዳን የሚመስል ። የአስቆሮቱ ይሁዳን ሰብዕና መወከል የሚችል ሰው በሀገሩ ጠፋ። አሥራ ሁለቱም ተስለዋል፤ የይሁዳ ቦታ ግን ባዶ ነው። የመጨረሻው እራት ከይሁዳ ውጪ ባዶ ነው። ኢየሱስን ወደ ደረቱ ቀርቦ የሚያነጋግረው ዮሐንስ አለ። ሌሎቹም እንዲሁ። ነገር ግን እጁን ወደ ወጪቱ ከመሲህ እጅ ጋር የሚያጠልቀው ይሁዳ ግን የለም፤ እርሱን የሚመስል ሞዴል አላገኘም ነበርና...እነሆ ሶስት ዓመት አለፈ። ይሁዳን ፍለጋ...

🗒🗒🗒

ከሶስት ዓመት በኋላ ከቀናት በአንደኛው ዳቪንቺ ወጪና ወራጁ በሚመላለስበት መንገድ መሃል አንድ ሰው አስተዋለ። ፊቱ በመጠጥ ብዛት የተመጠጠ፣ ዓይኖቹ ከጉድጓዳቸው ወጥተው ሊወድቁ የደረሱና ሁሉንም የሚመለከቱ መረጋጋት የተሳናቸው የሚመስሉ፣ ያለ ዕረፍት የሚንቀጠቀጡ ቅንድቦች ያሉት፤ መልከ-መልካም የነበረ የሚመስል የአካሉ ጉስቁልና የመንፈሱን መታወክ የሚሰብክ አንድ ሰውን ተመለከተ፤ ቀርቦም...

"እኔ ሰዓሊ ነኝ ለምስለው ስዕል ያንተ ገዕታ ያስፈልገኛልና ብስልህ ምን ይመስልሀል?" ሲል ጠየቀው ዳቪንቺ ሰውዬው በስላቅ እየሳቀና በጥርጣሬ እየተመለከተው "መልካም እኔ ምን ቸገረኝ ሳለኝ ነገር ግን ትከፍላለህ" አለው
ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ....

🗒🗒🗒

እንዴት መቀመጥ እንዳለበት ለይሁዳ ስሜት በሚቀርብ ሁኔታ ሰውዬውን ካሰናዳ በኋላ ስዕሉን ጀመረ... ከሰዓታት በኋላም ስዕሉን ጨረሰ። የእፎይታ ስሜት የሰዓሊውን መላ አካል ወረረው። አሁን የሚጨቀጭቀው፣ የሚነዘንዘው አይኖርም።
የተሳለው ሰው ገንዘቡን ተቀብሎ ሊወጣ ካለ በኋላ ተመልሶ ስዕሉን ማየት እንደሚችል ጠየቀ።

🗒🗒🗒

ስዕሉን ወደሰውዬው አይኖች አዞረለት። እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ ለበርካታ ሰዓታት ምስሉን ያስተውለው ገባ። እናም በጥርጣሬ አይነት አነጋገር "ይህን ስዕልከዚህ በፊት ሳላየው አልቀርም" አለ "በፍፁም አይተኸው አታውቅም ይህ ስዕል ገና አደባባይ ያልወጣ ያልታየ የራሴ ብቸኛ ስራ ነው" ሰውዬው አቋረጠው "ቢሆንም ይህንን ስራ ከዚህ በፊት በእርግጠኝነት አውቀዋለሁ"
"የት?" ዳቪንቺ ጠየቀ
"እዚሁ ከተማ ከዚህ በፊት አንድ ሰዓሊ ይመስለኛል ከሶስት ዓመት በፊት ክርስቶስን ትመስላለህ ብሎኝ ያውቃል ዛሬ ደሞ አንተ ይሁዳን ትመስላለህ አልከኝ" ብሎ "ወይ የሰው ልጅ" እያለ በመገረም በተሰጠው ዲናር ወይኑን ለመጎንጨት መንገዱን ጀመረ...

📖📖📖

ምንጭ 📖 የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎችም ወጎች
ደራሲ ኤፍሬም ስዩም

፨ በኛ ሕይወት ውስጥም በየቀንና በየሰአቱ የሚቀያየርና የማይጨበጥ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ስንት ይሆኑ...? ጥዋት እንደ ኢየሱስ በየዋህነት የሚቀርቡን ከሰአት እንደ ይሁዳ አስማምተው የሚሸጡን ስንት ይሆኑ?...ቤቱ ይቁጠራቸው...!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

      ክፍል - ፪

ቀጥያለሁ......

team jungle boyz በትምህርት ቤታችን ታዋቂ ሆነናል
በስራችን ውስጥ የሌለ ተማሪ የለም ሁሉንም በኔትወርካችን ስር አድርገን ተደራሽነታችንን እስከ አስተማሪ ድረስ አድርሰነዋል በቃ ሁሉም ነገር ጭስ በጭስ ሆኑአል በኛ ምክንያት
አላማዬ መሉ በሙሉ ወደ ምፈልገው ቦታ ሄዶልኛል በዚ ዘመን ላለምነው አላማ መሳካት ያለምነው ነገር ሰውን ጎጂ መሆን አለበት
ሁሉም በር ካለምንም ልፋት ስለሚከፈትልን
ስለኛ ማያወራ ስለኛ ማያነሳ በኛ ስራ ማይቀና ሰው የለም
እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ ሳየው የነበረው ነገር በተግባር በመፈጸሜ ከኔ በላይ የጀግንነት ስሜት የሚሰማው ሰው አልነበረም
በቃ ጀግና ነኝ....
ባለሁበት ትምህርት ቤት ውስጥ ካለው የተማሪ ብዛት 60% በላይ የሚህኑት ሴቶች ነበሩ በኔ የስራ አለም ውስጥ ፆታ ቀለም የሚባል ነገር የለም ሁሉንም ተደራሽ ማድረግ ነው ፍላጎቴ
ግን አብዛኛዎቹ ወንዶች በመሆናቸው ያን ያህል ተደራሽ እንዳሎንኩኝ ውስጤ በተደጋጋሚ ለጀግናው ስሜቴ ይነግረዋል
ሄዋንስ........  
ሄዋንን ወደኔ ለማምጣት ሌላ ብልህ  ሄዋን በጣም ታስፈልገኛለች እሷም ነይ ሳትባል ነው የመጣችው
ነገሩ ወዲህ ነው
አንድም ቀን ከጆሮዬ ኤርፎን ተለይቶኝ አያቅም #ኢስኮባር መጣ ኢስኮባር እንዲህ ሆነ ...
ኢስኮባር ነበር የሚሉኝ
ኢስኮባር ታዋቂ የኮሎምቢያ ሀሺሽ ነጋዴ ነው ኢስኮባር እሹ እራሱ አንድ መንግስት ነው ማለት ይቻላል
እኔም በሱ ስም በመጠራቴ ከፍ ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ
አዎ ኢስኮባር ነበርኩ ትንሹ ኢስኮባር
አባቴ በአዝማሪነቱ የማያውቀው ሰው ያላካለለው ሀገር ያልዞረበት የባህል ቤት የለም
እኔም የማያውሸኝ ሰው በስራዬ ሙሉ የአዲስ አበባን ትምህርት ቤቶች እና ኩታራው የሚዝናናባቸውን ክለቦች በጠቅላላ ተቆጣጥሬ ነበር
የአዝማሪ ልጅ መሆኔን ለማሳወቅ ነው ሁሌ በሄድኩበት ሙዚቃ ማይለየኝ
በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ሲሰማ የነበረው ሙዚቃ ይቀየራል ሁሉም ነገር ወደ ድሮ ይመለሳል
አንድም ሰው አያጉረመርምም
ፀጥ ረጭ ...... ኢስኮ ነኛ
ከአባቴ ቀጥሎ ያለኝ ነገር ሙዚቃ ነው አባቴም ከባቲ እና አምባሰል ካንቺሆዬን ትዝታ ቀጥሎ የምሰማው እሱ እራሱ አንዱ ሙዚቃዬ ነው
አባት አለሜ ለኔ የሰጠኝ ትልቁ ሀብት ሙዚቃ ነው
           ሙዚቃ ህይወቴ አለ ቴዲዬ ነፍሴ
ወደ ፊያሜታ ልመልሳችሁ (ማንም ሳይጠራት መጣች)
አንዳንዴ ፍቅርን ከየት እንደምናገኝ አናውቀውም ስንዳክር ለኛ ባልተሰራ ሰው ስነንደክም ቆይተን ባላሰብነው ሰአት የኛ ሰው ከጎናችንን እናገኘዋለን
የኔ ...... ባትሆንም የኔ ነበረች
ትዝ ይለኛል መማር ያለመደው ጎኔ ዛሬም በተለመደችው ቦታ ቁጭ ብያለሁ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ብቻዬን ነበርኩኝ
                    ገና ስመጣ ወደዚች ምድር
                     አሳደገችኝ ቀብታ ፍቅር
                     በልጅነቴ ከእቅፋ ሰርቃ
                    ነፍሴን ወሰደች ያቺ ሙዚቃ
                                          ሳሚ ዳን ነው ብዙ አወጋዋችሁ እኔም የምፅፍበት ሉኬን ያበላሸውን ጠብታዬን ለፅዳ ድምጿን ጨመር አርጉት እኔም አንዴ ሰላም ያለው አየር ልውሰድ .......
ሰላም በሌለው ክፉ ትዝታ ውስጥ አፋኝ አየር እንጂ ንፁ ነገር የለም
ስቃይ ........
ለምን እንዲህ እንደሆንኩ አላቅም ጥግ ድረስ የልባችንን በራፍ ወገግ አርገን ስንከፍት የከፈትንለት ሰው ብቻውን መግባት ይፈራል መሰል ብዙ የልብ ምት አዋኪ ነገሮች ከልባችን ስር ይቀመጣሉ
ደም መዘዋወሩን አቁሞ በገባው ነገር ተደናግጥ እዛው ባለበት ይረጋል
ሌላ ደም ስለማይመጣ ልባችን ትቀዘቅዛል እራሷ ከፍታ ያስገባችውን አካል መልሳ ለማስወጣት ቅዝቃዜው ያስቸግራታል ለመሞቅ የትዝታዋን እሳት ስለለኩስ የረጋው ደም መፍላት ይጀምራል ይበልጥ ስቃይ
ትነቱ አእምሮ ጋ ሄዶ ይደልቀዋል ያኔ ያ ህመም ከህመሞች ሁሉ የባሰው ይሆናል
ምክንያቱም........
ማሰብ ቆሞ ልብ የምትሰጠንን ምስል ብቻ ማውጠንጠን ስለምንጀምር
ማሰብ ማቆም ነው የህመም ሁሉ ህመም
ልብ ሲተክዝ ሰወነት ይቆማል
ሰውነትም ሲቆም ማሰቡ የጠፋል
                 የኔ ሀሳብ ባንቺ ፍቅር ተመርዞ
                 ቢያስቸግረኝ ፍፁም ልቤን አስተክዞ
                ተረታሁኝ ባንቺ ፍቅር ተይዤ
                አሃ አሃ አሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ
               ቁጭ ብዬ ቀረሁልሽ ተክዤ
               አሃ አሃ አሀሀሀሀሀሀሀሀ
              ሀሳብ ብቻ በልቤ ውስጥ ተመርኩዤ
                                ግርማ ነጋሽ ቀጥሏል ከዚ ዜማ በላይ ሊገልፀኝ የሚችለው ነገር የለም
የልብ ስብራት እንደ ጉልበት ስለማይታሽ እንደ ፀባዩ መያዝ ነው
አቃተኝ እናነተዬ ደምና እንባ እየጠከስኩ ነው ምፅፈው አቅሙ አጥሮኛል እጄ ተንቀጥቅጦ ቃላቱን በአንዱ ቃል ላይ እየደረበ ነው
ስቃይ.....

                          እቀጥላለሁ
                   ብላቴናው በደም ቀለም
          
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
"የኮረና ቫይረስ በምግብ ይተላለፋል ወይ?"

Dr Solomon Kibret (ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ)

ጋዜጠኛ Tesfaye Woldesilassie ይህን ጥያቄ አብራርቸ እንድመልስ በጠየቀኝ መሰረት እንደሚከተለው አስረዳለሁ።

የኮረና ቫይረስ መተላለፊያ መንገዱ በትንፋሽና በንክኪ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ነው ንክኪ መቀነስ፤ እጅን በሳሙና መታጠብና ማህበራዊ ፈቀቅታ የሚመከረው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚጠየቅ ጥያቄ ግን ምግብን በተመለከተ ሆኗል። "የኮረና ቫይረስ በምግብ ይተላለፋል ወይ?" ይህን ለመመለስ የተለያዩ ጥናቶችን ለመዳሰስ ሞክሪያለሁ።

የአሜሪካ የበሽታ መከላከል ማዕከል (CDC) ይህንን ጥያቄ በማስመልከት ማርች 17 በሰጠው መግለጫ; "There is no evidence that food has been associated with the transmission of the virus although more research is still required. Foodborne exposure to this virus is not known to be a route of transmission”

"እስካሁን ያለው መረጃ የሚያሳየው የኮረና ቫይረስ በምግብ ምክንያት አንደማይተላለፍ ነው። ቫይረሱ ከምግብ ጋር በመግባት የበሽታ መተላለፍ መንስኤ አይሆንም" በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በቫንደርቢልት ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ዊልያም ሻፍነር ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ "የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ነው እንጂ ሆድ ውስጥ ያሉ የምግብ መፍጫ አካላትን የሚያጠቃ አይደለም ስለሆነም በመተንፋሻ አካላት በኩል ዘልቆ ካልሆነ ከምግብ ጋር አብረን ስለተመገብነው በሽታው አይዘንም። ሆድ ውስጥ ቢገባ እንኳን የጨጓራ አሲድ ሲሳይ ይሆናል።" ይልቁንስ ይላሉ ፕሮፌሰር ዊልያም "ምግቡ ሲዘጋጅ ንክኪ ከተፈጠረ፤ ለምሳሌ በቫየረሱ የተያዘ ሰው ምግቡን ሲያዘጋጅ ቢያስነጥስበት ወይም እጁን ሳይታጠብ ካዘጋጀውና እኛም ምግቡን ወይም ምግቡ የታሸገበትን እቃ በእጃችን ነክተን ከዛም ከፊታችን ጋር ንክኪ ስናደርግ ቫይረሱን ቀጥታ ወደ መተንፈሻ አካላችን እንዲገባ እናመቻችለታለን። ይህ ንክኪ በተለይ በእጃችን በቀጥታ በመንካት የምንመገባቸው ምግቦችን (ምሳሌ፤ ፍራፍሬዎች፤ ሳንድዊች፤ ጥሬ ስጋ) ቫይረሱ ቀደም ሲል ምግቡን ከነካው ሰው ወደ እኛ እጅ በተወሰነ መልኩ (አነስተኛ እድል ቢኖረውም) የመተላለፍ እድሉን ሊፈጥር ይችል ይሆናል።"

ስለዚህ ምን ማድረግ አለብን?

መዘንጋት የለለብን ነገር ይህ ቫይረስ የሚተላለፈው በንክኪና በትንፋሽ መሆኑን ነው። ስለዚህ፤

1. ማንኛውም ምግብ የሚያዘጋጅ ሰው እጁን በሳሙና ታጥቦ [እና የፊት መሸፈኛ ማስክ አድርጎ] ምግብ ያዘጋጅ፤ አስታውሱ ምንጊዜም ምግብ ዝግጅት ከመጀመራችን በፊት እጃችንን በሳሙና በደንብ መታጠብ አለብን።
.
2. ከምግብ ተራ የገዛናቸውን ፍራፍሬዎችና አትክልት በተለያዩ ሰዎች ተነካክተው ስለሚሆን በሚፈስ ውሃ [running water] አጥበን እንጠቀም፤ [በሳሙና ወይም በኮምጣጤ ማጠብ አይገባም፤ ውሃ በቂ ነው](በእቃ ላይ የታቆረ ውሃን ሳያፈሱ ለብዙ ሰዓት ለማጠቢያነት መጠቀም ከማጠብ ተግባሩ ይልቅ ከአንዱ ወደ አንዱ የመበከል ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል ምንጊዜም የሚወርድ ውሃን እንጠቀም]
.
3. ምግቡ የታሸገ ከሆነ የታሸገበትን ካርቶን/ወረቀት ካነሳን በኋላ በትክክል ማስወገድና ወዲያውኑ እጃችንን በሳሙና መታጠብ ይገባል [ለማስታወስ ያህል በቅርብ የተደረገ ጥናት ኮሮና ቫይረስ በካርቶን ላይ እስከ 24 ሰዓት መቆየት ይችላል]
.
4. ምግብን አብስሎ መመገብ የተለያዩ በሽታ አምጭ ተህዋስያንን ስለሚገልልን ልናዘወትረው ይገባል።
.
References:
1. Kutter JS, Spronken MI, Fraaij PL, Fouchier RA, Herfst S. 2018. Transmission routes of respiratory viruses among humans. Current opinion in virology 28:142-151.
2. NPR. How Safe Is It To Eat Takeout? April 8 2020; https://www.npr.org/…/822903…/how-safe-is-it-to-eat-take-out
3. US News. Coronavirus and Food Safety. March 31, 2020. https://health.usnews.com/…/art…/coronavirus-and-food-safety
4. FDA. Food Safety and the Coronavirus Disease 2019 (COVID-19). April 14, 2020.
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ርቀት መጠበቅ ይወዳል ቤቱ፤
ከጥንት ነው ከመሰረቱ

( በእውቀቱ ስዩም)
አካላዊ መራራቅ የሚባለው ነገር ለብዙ ሰዎች ሲከብዳቸው ሳይ ይገርመኛል ! ለኔ ደግሞ አካላዊ ርቀት የሚባለው ነገር አብሮ አደጌ ነው!
የሆነ ጊዜ ላይ አያቴ በነበረው አስተዳደር ተማረረና ሸፈቶ ጫካ ገባ ፤ አልፎ አልፎ፤ ቀን በደመና ማታ በጨለማ ተሸሽጎ ይመጣና ቤቱ ያድራል ! ሁሌም ሲተኛ መውዜሩን እንደ አራስ ልጅ ታቅፎ ነው ! አንዴ ለቁርስ ልቀሰቅሰው አስቤ፤ የተከናነበውን ቡልኮ ብገፈው “ ይቺን ይወዳል ” ብሎ ፎክሮ በሰደፍ ለጥቂት ሳተኝ፤ እኔን የሳተኝ ሰደፉ ካጠገቤ የነበረውን ግድግዳ ነደለው ! የሚገርማችሁ ነገር ሰደፉ የነደለውን ቀዳዳ በተጠባባቂ መስኮትነት ሲያገለግለን መኖሩ ነው :: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አያቴን ለመቀስቀስ ስፈልግ: ከቤት እወጣና -በረጅም አጣና በምኝታቤቱ መስኮት አሻግሬ ብብቱን እኮረኩረዋለሁ ፤ ልጅ እያለሁ ላጭር ጊዜ ካያቴ ጋር ኖርያለሁ! አያቴ ሁሌም ከአደን ሲመለስ ቆንጆ ቁርስ ይሰራለታል፤ መጀመርያ የገብስ ዳቦ በአጋዘን ወተት እያማገ ይበላል፤ ቀጥሎ የዥግራ መላላጫ ይመጣለታል ፤ በመጨረሻ እጁን ወደ ውጭ ሰደድ አድርጎ መስኮቱን ታክኮ ከበቀለው ቁጥቁዋጦ ውስጥ እንጆሪና ቀጋ ሸምጥጦ ይበላል ፤ ታድያ በየጣልቃው፤ ከጉሬዛ ፀጉር በተሰራ ናፕኪን አፉን መጥረግ አይዘነጋም ! እሱ ምግቡን በጨበጣ ሲያጠቃ ‘ እኔና ወንድሜ ባስር ሜትር ርቀት ላይ ቆመን በጉምዥት እናየዋለን ፤
አንድ ቀን ያያቴ የጭን ገረድ ፤” ልጆች እየተቁለጨለጩ ነው ምናል ትንሽ ቢያቀምሷቸው ?” አለቺው አያቴ አፉ ውስጥ የሚንጉዋለለውን ጉርሻ አጣድፎ ዋጠና እንዲህ አላት ;-“ ልጅ መቁለጭለጩን ሰማይ መብለጭለጩን አይተውም፤ ይልቅ ወሬውን ትተሽ ሽንብራ ቁይላቸው ” ያምስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ እንኮየ የምትባል የክፍላችን ቆንጆ ልጅ ወደድኩ! ስምንት ወራት ያክል በትጋት ካፈቀኳት በሁዋላ አንድ ቀን ስሸኛት ፤ ስፈራ ስቸር በጣቴ ከንፈሯን ነካሁት! ከዚያ ወደ ቤቴ ገሰገስሁ ! ከንፈሯን የነካሁበት ጣቴ እንዳይረክስ በመንገዴ ላይ ማንንም አልጨበጥሁም፤ ሊጨብጡኝ የሚቃጡትን ሁላ “ ይቅርታ አርጉልኝ፤ እከክ አለብኝ እያልሁ፤ ለእንኮየ ፍቅር ስል “ እከካም “ እየተባልሁ ቤቴ ደረስሁ ! እቤት ገብቼ በእንኮይ ከንፈር የተጠመቀ ጣቴን ጨመጨምኩት! አንድ ቀን እንኮየን አስቁሜ ስምንት ወር ሙሉ አፈቀርኩሽ አላማሽ ምንድነው አልኩዋት! እየተሽኮረመመች አደባባይ ላይ ከሚሆን ቤት ሄደን አይሻልም አለችኝ፤ ቤት ሄደን በባዶ ሆድህ አትችለውም ብላኝ ትንሽ ነገር ቀምሰን ስናበቃ፤ ተነስታ የሳሎኑን መስኮት መጋረጃ ዘጋች! ስንሳሳም ከውጭ ያለው ህብረተሰብ እንዳያይ አስባ ነው ብየ ገመትኩ፤ መሳሳቴን ያወቅሁት ታላቅ ወንድሙዋ ዶልቻ ከምኝታ ቤት ሲወጣ ሳይ ነው! ከዚያ በሁዋላ ያለው አይነሳ! ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስስ ብልቴን ብቻ ሳይሆን ሸካራ ብልቴን ተመትቻለሁ ! በቅዱስ ሚካኤል ስእል ውስጥ እንዳለው ጠይም ሰይጣን ክንዴን ተንተርሼ ወድቂያለሁ ፤ ዶልቻ እንደ ልስን ጭቃ ‘ ደረቴ ላይ ጭድ እየነሰነሰ ደጋግሞ ረገጠኝ ፤ በመጨረሻ ቤቴ ደጃፍ ላይ አምጥቶ ሲጥለኝ “ ከእህቴ አርባ ክንድ ካልራቅህ የጋሽ አስፋውን ጋሪ ተከራይቼ ነው እምድጥህ “ ያለው አይረሳኝም!
ከዚያ ክፍል ቀየርኩ ! በማስከተል ትምርት ቤት ቀየርኩ ! በመጨረሻ ከተማ ቀየርሁ፤ የእንኮየን ወንድም ከብዙ ዘመን በሁዋላ ሚኒሶታ የሚባል ከተማ ያበሻ የሙዚቃ ፌስቲባል ላይ አገኘሁት ፤ በልጅነቴ ያደረሰብኝን ረስቶታል ፤ እኔ ግን ደረቴ ላይ የተመላለሰውን የጫማውን ቁጥር ሳይቀር አልረሳሁለትም! ያም ሆኖ አብሬው መጨፈር ጀመርሁ ! ዶልቻ ሁለቴ እስክስታ ይመታና ሶስት ጊዜ ዙርያ ገባውን ገልመጥ ገልመጥ እያለ በስጋት ይሾፋል ! ምክንያቱን ጠየኩት! ምላሹ ባጭሩ እንዲህ ነው! ሚስቱን በድሎ ፍርድ ቤት Restraining order አውጥቶበታል! ከቀድሞ ሚስቱ በተገኘችበት ቦታ ሁሉ በሶስት መቶ ጫማ እንዲርቅ ተወስኖበታል፤ ይህንን ርቀት ጥሶ ከተገኘ ይታሰራል !
“ ያቺ ሰላቢ እዚህ ከመጣች ደውላ ታሳፍሰኛለች “አለኝ
የዶልቻ የቀድሞ ሚስት መጥታ ፌስቲቫሉን እንድትቀላቀል በልቤ እየፀለይሁ ጭፈራየን ቀጠልኩ፤

@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፫
ቀጥያሉ.....

ከታፈንኩበት አየር ተመልሻለሁ ትንጋዬንም ጠረግ ጠረግ አድርጌዋለሁ
ቅድም ከተሰቃየሁት በላይ ስቃይ መሰቃየት ልጀምር ነው መሰለኝ
ማብቂያ የሌለው ስቃይ የእቶን ቃጠሎ ከበርባሮስ በጠለቀ ፅልመት ውስጥ ነኝ
ፊያ.....
ኢስኮ ኢስኮ አለቺኝ ሰምቻታለሁ ግን እንደሌሎቹ ወይ ሰላም ለማለት ወይ እንደተለመደው .......
መጣራቱ ቆሞ ከአጠገቤ መታ ጀርባዬን ደለቀቺኝ
ምን አይነት ድፍረት ነው ደሜ ፈላ ብዙ ነገር ልናገር የተነሳሁት ልጅ አፌ ፀጥ ረጭ አለ
አነሳሴ አስደንግጡአት ነው መሰለ ትናንሽ እጆቹአን ቀሚሷ ላይ አርጋ አንገቱአን ደፋች
ያ የደለቀኝ ድፍረቷ የት ገባ
እእእእእእእእ ምድነው አልኳት
ቀና ብላ አየቺኝ ረጅሙ ፀጉሯ አንድ አይኗን እስከ ግማሽ ከንፈሯ ሸፍኖታል
የጎደለ የፊት ገፅታ ግን ምንኛ ታምራለች በአባባ ሞት
ፈጠን ብላ
እኔ ካንተ ጋ መቀላለቀል እፈልጋለሁ ምንም አታስብ ጭራሽ ሀሳብ አይግባህ የሰጠኸኝን ዛሬውኑ
አየር እንኳ አቶስድም ስታወራ ከንፈሯ ላይ የተጣበቀው ፀጉሯ ለማውራት ስላዳገታት ሙሉ ጸጉሯን በአለንጋ ጣቶቹአ ወደ ኀላ አሸሸችው
ያ ግማሽ ውበት አሁን በሙሉ ሆኖ ደሜን ያራውጠው ጀመር
እእእእእ በናትህ ኢስኮ ቃጭል ድምጿ ከሀሳቤ አነቃኝ
ምን አለ በደንብ በሀሳቤ ብከትሽ
ምንም ሳላቅማማ ከቀኑ የቢዝነስ ስራ የተረፈውን 5 ክርታስ ሰጠሁዋት
ዘላ ተጠመጠቺብኝ ትንፋሿ ይፋጃል ገና ከመመሰጤ ጥላኝ ሄደች ......
ከመሄዷ አይኔን አንከራተተችው ልፍለፋዋ ዝም ብሎ ይታወሰኝ ገባ
ለነገ የሰጠሁዋትን ትሽጥም አትሽጥም እሷን ማግኘት ለኔ ከብሩ በላይ አጓጊ ሆኑአል
አዳሬን ሙሉ እሷን ማሰብ ሆነ ከዚ በፊት ለብዙ ሴቶች እንዲ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ያውቃል ይሄም ስሜቴም ብዙ እንግዳ አሎነብኝም
መጣ መሄዷ ስለማይቀር......
                     ይገርማል ቁመናና ዛላ
                     ልዩ ነው የፀጉሯ ዘለላ
                    ጥርሶቿ አቀማመጣቸው
                    ይገርማል አቤት ንፃታቸው
                                       ጥልዬ ደሞ መቷል በተራው በጣም ይገልፃታል ይሄ ዜማ በሉ በምናባችሁ የኔ ፀጉረ ዘለላ ምን እንደምትመስል እየሳላችሁ ጠብቁኝ
እኔም እንደለመደብኝ ...........
አይነጋ የለ አዲሷ የቢዝነስ አጋሬ ስታቃዠኝ አድራ ከመኝታ ቤቴ ከምተገባው ጮራ ጋ ውብ ፊቷ ድቅን ይል ጀመረ
 ገና በጠዋቱ ....
አባቴ ተነስቶ ወዲ ወዲያ ይላል እንደለመደው ሬዲዮኗ ተከፍታ ጥዑም ዜማ እያደረሰችን ነው
                    ማለዳ ፀሀይ ስቶጣ ደማምቃ
                     ከእንቅልፌ ድንገት ባንኜ ስነቃ
                     ፈጣሪን በቀኝ አውለኝ እላለሁ
                     አምላኬን ስሙን ሳነሳ እውላለሁ
                                      ቴዎድሮስ ታደሰ ነው አባቴ ነፍሱ እስኪወጣ ነው ሚወደው
ዘፈኑ ለአመስጋኝ እንጂ ለኔ አይነቱ ተራሰው እንደማይሆን ባውቅም ቀኑን ሙሉ ምለሴ ላይ ዋለ
መማርን አላማ አድርጌ ወደ ምማርበት ቦታ ሄጄ አላውቅም
ዛሬም ማለዳ ከምላሴ ያቺ ውብ ደሞ ከጭንቅላቴ ተጣበቀው ዋሉ
ዛሬ ከመጣችልኝ ቀኔ ነው በቃ ምን አልባትም ዜማው ሳይረዳኝ አልቀረም መሰል
ፊያሜታ ከፊት ለፊቴ .........

                      እቀጥላለሁ
                  ብላቴናው በደም ብዕር

                  
@wegoch
@wegoch
@wegoch
★★ ሞቴን ቀማኝ…… #4★★
(የመጨረሻ ክፍል)

"እታባ ‘አባትህ ጥሩ ሰው ነው። አንዳች እክል ካልገጠመው በቀር እንዲህ አይጨክንብንም።‘ ትለኝ ነበር "

ያሬድ ለአየኸኝ እየነገረው ነው። ……የማንጎ ጭማቂ በማንኪያ ሊያጠጣው እየሞከረ…… ማብቂያ የሌለው ከሚመስል የሰዓታት ዝምታና ብቸኝነት በኋላ ከአባቱ አጠገብ ተቀምጦ ስለ እናቱና ስለራሱ ማውራት ሆኗል ልምዱ…… አየኸኝ ባይመልስለትም ልጁ አጠገቡ ተቀምጦ እየደባበሰ ያለማቋረጥ ሲያወራው ፊቱ ይፈግጋል። ………

"…… እኩያዬ እኮ ነው። …… ስላሸነፍኩት አባቱ ተደርቦ ገፈተረኝ እና እግሬ ወለም አለኝ።…… ከዛ አባቴን ካልወለድሽ ብዬ እህል አልቀምስም አልኳት።……" በትውስታው ፈገግ ብሎ ቀጠለ "…… አለቀሰች። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ በአንተ ስትመረር የሰማሁት ያኔ ነው። …… አሳዘነችኝ። ……"

በሩ ላይ ቆሜ እሰማዋለሁ። ……

"በቃ እረፍ ትንሽ…… በወሬ አደከምሁህ" ብሎ ሊነሳ ሲል አየኸኝ ፊቱ ተከፋ……

"ትንሽዬ ተኛና ደግሞ አጫውትሃለሁ።" ብሎ የአባቱን እጅ ሳመው……

የተቀሩት ቀናት እንደዚህ አለፉ። ……

"ወንድሞች እንደነበሩህ ነግሮህ ነበር?" አልኩት የሆነ ቀን

"ምንም አልነገረኝም። ምንም አልጠየቅኩትም ነበር።" መለሰልኝ በጉጉት ። ያጫወተኝን በሙሉ ነገርኩት። ቃል ሳይተነፍስ ሰማኝ።

"ምስኪን አባቴን!" አለ ተነስቶ ወደ አባቱ ክፍል እየሄደ። ……

"የሰው ልጅ ተፈጥሮ ፈጣሪውን ነው የሚመስል፣ መልካም ነው። በህይወቱ በሚያልፋ ክፉና መልካም ተጎዳኝ ክስተቶች ክፉ ይሆናል እንጂ በተፈጥሮ የከፋ ሰው የለም።" ይለኝ ነበር አባዬ

ያሬድን አስቤ የገባኝ ይሄ ነው።በህይወቱ ያለፉ መከራዎች ሁሉ መንስኤ የአባቱ እናቱን ማስረገዝ እንደሆነ ነው የሚያምነው። …… ላለመማሩ እና የገጠር ወጣት ሆኖ ለመቅረቱ መንስኤ አባቱ እሱን አለመፈለጉ እንደሆነ… …… እሱ አቅሙ ደርሶ አርሶ መዝራት እስኪችል ከእናቱ ጋር በጥልቅ ድህነት ዘመናቸውን ገፍተዋል። …… ለሁሉም ምክንያት የሚያደርገው አባቱን ነው። ……

አባቱ ሊሞት መሆኑን ሲሰማ ምሬቱን ረሳው፣ ያለፈ መከራውን ተወው…… መከፋቱን ዘንግቶ ለአባቱ አለቀሰለት።……

ድምፁን የሰማሁ ስለመሰለኝ ተነስቼ ወደ አየኸኝ ክፍል ገባሁ። ያሬድ መሬቱ ላይ ተንበርክኮ ድምፅ አልባ ለቅሶ ሲያለቅስ ደረስኩ። …… ያንን ሞቴን የቀማኝን የአየኸኝ ለቅሶ የመሰለ መንሰቅሰቅ…… ያን እንባ የሚቀማ ለቅሶ የመሰለ ፍቅፍቅታ… … እራሱን አባቱን ይመስላል። …… አንጀት የሚያላውስ አይነት… …  የተፈጠረው ገባኝ። …… እሪ አልኩ። …… ድንኳን ተቀምጦ የቅርብ ወዳጁ እያለቀሰ እንደደረሰው ለቀስተኛ የኔን እሪታ ሲሰማ የሚይዘው አሳጣው። …… ኡኡ ብሎ አለቀሰ። …… በለቅሶና በእንባ ብዛት የራስን ሀዘን ያራግፉታል እንጂ ለአየኸኝ የነፍስ ስንቅ አይሆን ነገር ተላቀስነው……

ይህ የአየኸኝ ህይወት ፍፃሜ ነበር። የእኔ ህይወት ጅማሬ…… የያሬድም ሌላ የህይወት ምዕራፍ ጅማሬ…… ወዳጅ ነኝ ያለ በተሰበሰበበት ተቀበረ። ……
………
………
……
አየኸኝ ከሞተ ወዲያ አዲሳባ መቀመጡ ምንም ስላልተመቸኝ ወደ ቀዬዬ ከተመለስኩ ሰነባበትኩ። ያሬድም ጠበቃው የንብረት ክፍፍሉን ጉዳይ ፈር እስኪያሲዝ እናቱን ይዞ ሊመለስ ወደ ቀዬው ወረደ። ጠበቃው እንደነገሩኝ ከሆነ እውነት የማይመስል ንብረት ባለቤት ሆኛለሁ። በእርግጥ ምንም ላልነበራት ሴት ይሄ ሁሉ ምኗ ይሆናል?  ……

አዲስ ህይወት እጀምራለሁ? አዲስ አበባ እገባለሁ? የምጀምረው ህይወት ደስተኛ ያደርገኛል? አዲስ የኑሮ ልምድን ካልተለማመድኩ ይሄ ሁሉ ንብረት በዛች በእርምጃ በምትለካ ቀዬዬ ምን አደርግበታለሁ? …… የቱንም አውቆ መወሰን አቃተኝ እና ማሰቡንም ተውኩት።……
……
……

ጠበቃው ያዘመመች ጎጆዬ ድረስ ሲመጣ ወራት መንጎዳቸው ገባኝ። …… የነገረኝን የገንዘቤን መጠን የኔታ አላስቆጠሩኝም። … እንኳን ልሾፍረው አዲስ አበባ ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳፈርኩበትን መኪና… … የመኪና ባለቤት መሆኔን ነገረኝ። ……
…… የአየኸኝ ኑዛዜ ያለውን ንብረት በሙሉ እኩል ካካፈለ በኋላ ቤቱንም እንድንካፈል ያዛል። ……

"ያሬድ ሊያማክርሽ ይፈልጋል ወደ አዲስ አበባ መሄድ አለብን!" አለኝ ጠበቃው… 

እዚህም ብቀመጥ የምፈትለው ጉዳይ ስላልነበረኝ ተስማማሁ። ……
……
……
………
ያሬድን ሳገኘው እንደ አብሮ አደግ ወዳጅ ተሰማኝ። በሰፊ እጆቹ አጀብ ደረቱ ላይ ቆየሁ። …… የምን እንደሆነ ያለየሁት ለቅሶ አለቀስኩ። አባበለኝ። …… እናቱ ተቆጥተው ለቅሶዬን አስቆሙኝ… …

"ምን አሰብሽ?" አለኝ በሁለተኛው ቀን ሲመሻሽ ገደማ

"ምን ላስብ?"

"የሌላው ንብረት በግልፅ ስለተካፈለ አስቸጋሪ አይደለም። ቤቱን እንዴት እናድርገው?" አለኝ

"ኸረ ሌላው ገንዘብ ይበቃኛል። ቤቱን ከእናትህ ጋር ኑሩበት። አይሸጥም።" መለስኩለት

"እንዲህ እንድትዪኝ አይደለም።" አለኝ ቅር እየተሰኘ

"ያለው መፍትሄ ምንድነው? ሸጦ መካፈል አይደል? ወይም አንዳችን የአንዳችንን ድርሻ ከፍሎ ቤቱን መጠቅለል? እኔ ካንተ ገንዘብ ተቀብዬ ቤቱን አልሸጥልህም። ተቃራኒውንም አላደርግም። ……"

"ሌላ መላ አይኖርም?" አሉ እናትየው የያሬድን አይን አይኖች እያዩ… … አስቀድመው የፈተሉት ወግ እንዳለ ያስታውቅባቸዋል።

"ምን አስባችሁ ነው?" አልኳቸው ተራ በተራ እያየኋቸው።

"ለምን አብረሽኝ አትኖሪም?" ሲል አይኖቹ አላዩኝም። ድምፁ ውስጥ ጥያቄ አይደለም ያለው… … ልመና ነበር። …… አብሮ መኖር…… አብሮ ከያሬድ ጋር መኖር……

"ባክሽ አትመለሽ?" አለ ቀጠለና… …

"በኔ ይሁንብሽ ልጄ… … ሞክረሽ ካልሆነ የፈለግሽው ይሆናል።" አሉኝ እናትየው

"እሺ!!" አልኩኝ በደመነፍስ ወዲያው ‘ምኑን?‘ ብባል መልሱን የማውቀው አይመስለኝም።

ያሬድ ከተቀመጠበት ተነስቶ እጆቼን እያገላበጠ ሳመኝ። እናትየው በእልልታ ቤቱን አቀወሱት። ይሄኔ እዚህ ቤት አብሮ ከመኖር ያለፈ የተጨዋወቱት ፈትል እንዳለ ገባኝ። ……
……
………
አሁን ጨርሰናል።
(ከበዛ ክብርና ነፍፍፍፍፍ ፍቅር ጋር!!!!!)

@wegoch
@wegoch
@paappii
#ስቅለት ወ ኮሮና

በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም
እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው
ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል
እረ ወዲያ......
ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ
ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር
ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው
ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ
ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል
የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች
ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ
ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን
እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ
በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ
ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል
መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ
ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ

በጌቴ ሴማኒ
ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል
እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ......
የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል
የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል
ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን
በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል
በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው
ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ
አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ
እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ
ይህን ካልኩ ይበቃኛል
መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን
በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው
                 መልካም ስቅለት
                    ብላቴናው
----Edited----
#ስቅለት ወ ኮሮና

በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም
እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው
ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል
እረ ወዲያ......
ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ
ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር
ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው
ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ
ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል
የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች
ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ
ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን
እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ
በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ
ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል
መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ
ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ

በጌቴ ሴማኒ
ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል
እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ......
የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል
የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል
ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን
በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል
በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው
ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ
አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ
እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ
ይህን ካልኩ ይበቃኛል
መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን
በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው
               መልካም የስቅለትበዓል
                    ብላቴናው
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፬
ቀጥያለሁ ......

የዛሬዋ ማለዳ ምንኛ ትለያለች ካየሁዋቸው ማለዳዎች ይቺ ለየት ሳትል አትቀርም
በማለዳ ዜማ ገና በማለደው እንደ ማለዳዋ ጮራ የፈካችው ልጅ ከፊት ለፊቴ ቆማለች
ዛሬም ያ እረጅም ፀጉር ይበልጥ አምሮበታል ከለበሰችው ጥቁር ጃኬት ጋ በቃ ዝም ነው
በዛች ትንሽ ንግግር ውስጥ እኔጋ ብዙ ስሜቶች ገብተዋል እኔም እንደመጣች ከእቅፌ አስገባሁዋት
ሌላ ስሜት ወደ ውስጤ ሲገባ ተሰማኝ
 እቅፍ አደረኩዋት
ጠረኗ ዛሬም አልተቀየረም እራሷ ተጠምጥማ ያሸተትኩትን ጠረን ዛሬ እኔ ተጠምጥሜባት መልሼ እያሸተትኩት ነው
በጣቶቹአ የያዘችውን ብር ከደረት ኪሰ ከተተችልኝ
መተቃቀፉ አበቃ     
ኤጭ.....
     እየው ኮሚሽኔ ከዛሬ ጀምሮ ይታሰብልኝ ደሞ ወደህ ነው ማታስብልኝ እኔ በአንድ ስራ ብቻ ትንሽ ነገር መውሰድ ስለማልፈልግ ነው እሺ ሙሉ ብሩን የሰጠሁህ
ያ የማውራት ፍጠነቱአ ዛሬም አልቆመም
አይኔ ከንፈሯ ላይ ነው
እና አጋሮች ሆነናላ ተስማምተናል አይደል 
አፌን ምን እንደለጎመኝ አላውቅም አይኔን ከከንፈሯ ነቅዬ አይኗ ላይ ተከልኩት ትክ ብዬ እያየሁዋት አንገቴን በአዎንታ ነቀነኩላት
በኔ ዝምታ ውስጥ ትልቅ ጩኸት አለ
መልሴ አስደሰታት መሰለኝ ደስ የሚል ትንሽዬ ፈገግታ ሰታኝ ቻው አለቺኝ
እቅፉአን ናፈኩት
ድንገት ከሄደችበት ተንደርድራ መታ ከንፈሯን ጉንጮቼ ላይ አሳረፈቻቸው
ኡፋ በአባባ ሞት
በዚች ማለዳ ውስጤን ያጠልቀለቀ ሀሴት ሲገባ ተሰማኝ
እርቃ ሳቴድ ታድያ ምሳ ልጋብዝሽ አልኩዋት
ቡና ይሁንልኝ ..... መለሰችልኝ
አቤት ፍጥነቷ
ፍጥነቷን ተጠቅማ ሳይሆን አይቀርም ከስሜቴ ዘላ እንዲህ በፍጥነት የገባችው
እጄ ከንፈሯ ያረፈበት ጉንጬ ላይ ነው አጣብቄው ቀርቻለው
ፍዝዝ ድንዝዝ ........
የልቤ በራፍ ሰተት ብሎ ሲከፈት ተሰማኝ በልቤ አዳራሽ እንድትገባ እኔም ፈቀድኩላት
በሩን ቶሎ አልዘጋሁትም
ምን ልበላችሁ በቃ ልዩ ሆነቺብኛ ምን አባቴ ላርግ
በፍላጎቴ ሰው ለመውደድ ስሞክር ታወቀኝ
ብዙ ጊዜ ፍቅር ሲይዘን ሁሌ ሳናስበውና ሳናስተውለው ስለሆነ ፍቅር እሱ እራሱ ሚታዘበን ይመስላል
እንዲህ ደሞ በፍላጎት ሲሆን በረከቱ እራሱ ሚበዛ ይመስለኛል
እናንተዬ ብዙ አሶራችሁኝ እኮ
እስቲ እቺን ጀባ ልበላችሁ እኔም ጠብታዎቼን ላፅዳ
                   የልቤን አዳራሽ መኖሪያ አርገዋለች
                  ወይስ የምሯን ነው ወይ ትቀልዳለች
                  ከልቤ አዳራሽ ውስጥ ሰተት ብላ ገብታ
                  ውስጥ የነበሩን በሙሉ አሶጥታ
                             መልካሙ ተበጀ ነው በፍላጎቴ አዳራሼን ከፍቼ ልቤን ልበላ ነው
ከትዝታዬ ተመልሻለሁ
ትንሽ የሙዚቃዋን ድምፅ ቀነስ አድርጉአት
ልቤም የአዳራሹን በር መክፈቱን እንጂ በየትኛው ቁልፍ ተዘግቶ ቁልፉን ከየት እንደጣለው ማያውቀው
ለዛም ነው በዘህ አሁን ባለሁበት ሁኔታ የልቤን አዳራሽ ከፍቼ ውስጡ ያለችውን ሰው ጎትቼ ማውጣት ያቃተኝ
ምክንያቱም ቁልፉ እኔጋ ስለሌ
አንዴ ከተዘጋ የልብን በር መክፈቻ ቁልፍ ማግኘት ይከብዳል
ቁልፉም አንዴ ብቻ ነው መሰል ለመክፈቻነት ሚያገለግለው
ለዛም ነው ብዙ ከፋቾች ወደ በራችን በር ሲመጡ በሩን መክፈት ሚከብዳቸው
የዘጋው መልሶ ከፍቶ ካልወጣ ከውጪ ሆኖ ማንም ሊከፍተው አይችልም
እሷም መልሳ እንዳቶጣ ከዚ ዘንድ የለችም
እሷ ግን የት ናት ወደትዝታዬ ስመለስ አወጋቹሀለሁ
   
                 
                እመለሳለሁ.....
            ብላቴናው በደም ቀለም
         
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ታሪከ ብዙ በሆነችዉ መንደሬ ሳዘግም አለማየዉ ቤቱን ያቀፈዉ ዉሃ ልክ ለይ
ቁጭ ብሏል። የመንደራችን ቤቶች አጥር ስለሌላቸዉ የየቤቱ ዉሃ ልክ እንደ
ባለጌ ወንበር ቁጭ ብሎ መቆዘሚያ፤ መገርመሚያ ነዉ። "ምነዉ ብቻህን?" ሁሌም ብቻዉን እንደሚቀመጥ ባዉቅም እንደመግቢያ ጠየኩት፤ እስክደነግጥ ድረስ ትክ ብሎ ካየኝ በኃላ " ሰዉ ብቻዉን ሆኖ አያዉቅም!" አለ ክርር ባለ ድምፅ። በዝምታዬ እንዲያወራ ጋበዝኩት "አየህ የእኔም ያንተም ማንነት ከሌሎች ሰዎች ተዋጥቶ ነዉ እኛን የሰራን ፤የሌሎች ስብዕናን ቅንጥብጣቢ የተሸከምን ነን። እንዴት በለኝ?" ካልጠየኩት እንደማይቀጥል ከልምዴ ስለማዉቅ " እንዴት ?" አልኩት ፤ " አየህ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ዉስጥ እኛነታችን የሚዋቀረዉ ፤ ቀድማ ጭንቅላትህ ዉስጥ በተፈጠረች ትንሽዬ ጄኔቲክሳዊ እዉቀት ለይ ተንተርሰህ ከሰዎች ባህሪን በሶስት መንገድ ትቀዳለህ። የመጀመሪያዉ እንዳለ መቀበል ሲሆ ን ፤ልክ እንደመዉረስ በለዉ ። ሁለተኛዉ መቃወም ሲሆን ካየሀዉ ባህሪ ዉጭ የሆነ ተቃራኒ ባህሪን መከተል ነዉ። ሶስተኛዉ ደሞ ከመቀበልም ከመቃወምም ዉጭ በሆነ አማራጭ ማዝገም ነዉ።" ቀና ብሎ አይቶኝ ቀጠለ። "አየህ እኔ ዉስጥ በዚህ መልክ የተቀበልኳቸዉ የተደላደሉ የሌሎች ሰዎች ባህሪዎች አሉ። እኔ የጭምቷእናቴ፤ የኮስታራዉ አባቴ፣ የጉራማይሌ ቤተሰቤ ፤
የጉራማይሌ ጎረቤቴ ፤ የጉራማይሌ መንደሬ፣ የጉራማይሌ ሀገሬ ፣ የጉራማይሌ አለሜ... የነዚህ ሁሉ ድምር ነኝ። ብቻዬን ሆኜ አላዉቅም! ብቸኝነቴ ዉስጥ የተከተቱ ፤የትየለለሌ ሰዎች አሉ፤ህልቆ መሳፍርት የሆኑ ።ምናልባት ማዉቃቸዉ ምናልባትም ማላዉቃቸዉ፣ ምናልባት እያወቅኩ ማላዉቃቸዉ ፣ ምናልባት ሳላዉቅም ማዉቃቸዉ ... ብቻ እነሱ ሁሉ እኔ ዉስጥ ተከተዋል። 'እኔ' የሚባል ነገር ካለ ከነሱ የስብዕና ትብታብ ለይ ሰበዝ እየተመዘዘ ነዉ ፤ 'እኔ' 'እኔ' የሆንኩት።እና ሰዉ ብቻዉን ሆኖ አያዉቅም! " ለአንድ ጥያቄ እንዲህ ያለ ሰፊ መልስ ሲሰጠኝ አንዴ እያዛጋዉ፣ አንዴ መሬት አንዴ ሰማይ ሳይ ቆይቼ(ሰማይ ግን ለምን ሰማያዊ ሆነ? ጥቁር የሀዘን፤ ነጭ የደስታ ፤ ቀይ የመስዋዕትነት... ሰማያዊስ?) እንደ ጨረሰ ተነስቼ ሄድኩ። ምናባቱ ይለፋደዳል! ብሽቅ

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#nicola nas
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፭
ቀጥያለሁ.....

ወደ ትዝታዬ ሚገፋኝ እህህህ ብሎ ሚሰማኝ ስለሆን አብራችሁኝ ፍሰሱ
ከዚ ዘንድ የሌለችው የኔ አለም ከየትኛው ቦታ ወደ የትኛው ሌላ አለም እንደገባች በደንብ አውቃለሁ
አዎ ከኔ አለም ወደ ሌላ አለም
እሷ ያለችበትን አለም ቶሎ መናገር አልፈልግም የሷን አለም መገኛውን ምነግራችሁ እኔም ወደዛ ለመሄድ መንገድ ስጀምር ነው
ለጊዜው ብዙ ምነግራችሁ ውብ ትዝታዎች አሉኝ
ወደ ትዝታዬ ተመልሻለሁ
ቅደም የተለያየንበት ቦታ ሁለታችንም እኩል ተገናኝተናል እሷም ወደ እኔ እኔም ወደ እሷ በፍቅር መላእክቶች ጠሪነት
ቁጥብ ፈገግታዋና ችኩልነቷ ተደምረው በቃ መፍዘዝ ሆኑአል ስራዬ
ወደ ቡናችን እንሂድ ፈጠን ብላ አነቃቺኝ
የቅደሚ እጄን ወደ ፊት ዘረጋሁላት ግድ የለም ቅደም ወደ ፊት ገፋችኝ
ታስገርመኝ ጀምሯል አይኔ አይኗ ላይ ነው
ጀርባዬን ትመታኛለች ከደረጃዎቹ ስንወርድ እጆቼን ትጎትተኛለች በቃ
ደስ የሚል ስቃይ.......
ባለፍንበት መንገድ ሁሉ ኢስኮና ፊያሜታ ሆኑአል ወሬው
እስከ ዚች ሰአት ድረስ ስሟን አልጠየኩዋትም ፊያሜታ መሆኑአን ያወኩት ጓደኛዬ ጠበቅ አርጋት የወንዱ ሁሉ አይን እሷ ላይ ብሎ የነገረኝ ሰአት ነው
ቡናችንን አዘን ቁጭ ብለን ደስ የሚል ጨዋታ ላይ ነን
ቆንጆ የቡና ሱሰኛ ናት ለነገሩ እኔም ካልጠጣሁ አይሆንልኝም
ስምሽ ግን ማነው በወሬያችን መሀል እንዳላወቀ ሆኜ ጥያቄዬን ወረወርኩላት
ፊያሜታ እባላለሁ ችኩል ብላ ተነስታ እጇን ዘረጋችልኝ
ምን አይነት እብደት ነው በጣም አሳቀቺኝ
ደስ አለኝ በቃ
እጄን ዘርግቼ ሰላምታዬን ስሰጣት መልሳ ከጎኔ ተቀመጠች
አይኖች ሁሉ ወደ እኛ ናቸው በቃ
የተማሪው አፍ በእኛ ወሬ ተጠምዶ ቡናው በስቅታ ነው የጨረስነው
እኔ ምልህ አይኗን ወደ አይኔ ተክላ እንዲህ ታዋቂ ነህ እንዴ ደሞ ተወዳጅ በዛ ላይ ቆንጆ
አቤት አቤት አረ አታሽኮርምሚኝ ጨዋታችን ሳቅ ብቻ ሆነ
ይልቅ አሁን ወደ ስራ በል ተነስ ተነስ የጠጣንበትን ሲኒ መልሰን ተነስተን ሄድን
ወደ ክፍሏ ይዛኝ ሄደች
ገባን በሩን ጥርቅም አደረገችው
ቡናው አስክሯት ነው መሰል ዝም ብላ ትስቃለች
ቁጥብ ፈገግታዋ ተቀይሮ እንዲህ ስትስቅ ሳያት ማላውቀው ስሜት ይነዝረኝ ጀመር
ዴስኮቹ ላይ ተቀመጥን በስራዬ ቀልጣፋና ፈጣን መሆኔን በባለፈው ስራዬ ተረድተሀል አይደል
ምንም እንደታስብ ጭራሽ በቃ 60% የትምህርት ቤቱን ሴት በእቅድህ አስገባልሀለሁ
በባለፈው የሰገሁሽ ሙሉ በሴቶች ነው ያለቀው ገርሞኝ ጥያቄዬን ወረወርኩላት
አዎና አለቺኝ.....
አንተ ከላይ አለክ ከበታችህ ብዙ ሰዎች እኔ ግን ከሁሉም በላይ አስፈልግሀለሁ በራስ መተማመኗ አስገረመኝ
ስለዚህ ሀሳብ አይግባህ ኢስኮዬ የሸሚዜን ኮሌታ ጨምድዳ ይዛ ይበልጥ ተጠጋችኝ ከመቀራረባችን የተነሳ በአይኗ ብሌን መልኬን አየሁት አይኗ ውብ ነው የሆነ ሀይል ያለው አካል
ትንፋሿ አጋለኝ ይበልጥ ተጠጋጋን አፍንጫዎቻችን እስኪነካኩ ድረስ መጠጋጋታችን አላቆመም ቀይ ፊቷ እዛው እያየሁት በርበሬ መሰለ እጆቼን ወደ አንገቷ ላኩት
እንቅ አደረኩዋት
አየር ሳንስብ ሁለታችንም አየር ተሰጣጠን ትንፋሽ የለም ቆዳዬን ትኩሱ ትንፋሿ ይገርፈው ጀመር
ያንን ከንፈር በቃ.......
እናንተዬ ኑ ተመለሱ በቃ ስቃዬን አበዛችሁት እኮ ትንሽ ዜማ እንስማ እንጂ እኔም ጠብታዎቼን እንደተለመደው ላፅዳ
                    ድንቅ ልጅ ድንቅ ነው ውበትሽ
                    ከዋክብት ናቸው አይኖችሽ
                   አቤት ቅርፀ ስራው የከናፍርሽ
                  ፈገግማ ስትይ ሌላ ነው ጥርስሽ
                          መሀሙድን ከፈትኩላችሁ
አዎና ማንም ምንም ብዬ ባልሰየምኩአት ልጅ የማላውቀው ስሜት ውስጥ ተወርውሬያለሁ
ማን ምን ብለን ሳንጠይቅ ሚሰማን ፍቅር ነው ሌላ ልዩ አለም ውስጥ ሚከተን በቃ እኔም እዛ ልዩ አለም ውስጥ ነበርኩኝ እንዲህ ትዝታን ብቻ ታቅፌ ከመቀመጤ በፊት
አሁንማ ልዩ አለም ውስጥ ሳልሆን ልዩ ስቃይ ውስጥ ነኝ
ወደ ትዝታዬ እመለሳለሁ ......

                 እቀጥላለሁ
        ብላቴናው በደም ቀለም
 
@Wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/25 09:17:31
Back to Top
HTML Embed Code: