Telegram Web Link
..ደብዳቤ ለሄዋኔ..
[አብርሃም የሙሉ]

ሰላም ላንቺ ባለሽበት ካለሁበት፡፡ ሄዋኔ እንደምን አለሽ? እኔ በቸርነቱ እንደ ክፋቴ እየኖርኩ አለሁኝ፡፡ አንቺስ እንደኔ ከፍተሽ ይሆን? ለፈጣሪሽ አስቸግረሽ ይሆን? ለመልካም፡፡

እኔ ጋር ሂወት መራራ ናት፡፡ ፍሬም የላትም፡፡ እኔም አንቺን እንጂ ሂወትን አልወዳትም፡፡ እልፍ ሂወት ባይኔ ሽው ብላለች፤ ልቤን ነካክታኛለች፤ በውበቷ ጥላኝ ውበቴን ንቃለች፤ እንደሌለኝ አውቃ እንዳትኖረኝ ሄዳለች፡፡ እኔ ጋራ ሂወት አላፊ ሁና አልፋለች፡፡

አንቺ ጋራ ሂወት እንዴት ነው? ፍሬ ቢስ ሆነብሽ? እኔን እንጂ ሂወትን እንደማትወጂው አውቃለሁ፡፡ እልፍ ሂወት በአይንሽ ላይ ሽው ብሏል?፤ ልብሽን ነካክቶታል?፤ በውበቱ ጥሎሽ ውበትሽን ንቆታል?፤ እንደሌለሽ አውቆ እንዳይኖርሽ ሄዷል? አንቺ ጋራም ሂወት አላፊ ሁኖ አልፏል? ለመልካም፡፡

ሄዋኔ የቀይ ዳማ ሁኚ፤ ጠይም ሁኚ፤ ወይም ጥቁር፤ የ'ኔም መልክ ከሰው የተለየ አይደለም፡፡ ሰውነቴ ሰውነትሽን ይናፍቃል፡፡ ንፁህ ልቤ ንፁህ ልብሽን ሲጠብቅ፤ ይነጋል ይመሻል፡፡

ሄዋኔ ምን ያህል ከናፍሮች ያንቺን እንደሚመስሉ ታውቂያለሽ? ከናፍሮችሽን ከንፈሮቼ ተርበዋል፤ አፍንጫዬ የጡትሽን መዓዛ ለመታጠን ጓጉቷል፤ እጆቼ ወገብሽ ላይ ለመጠምጠም ቸኩለዋል፤ አካላቴ ጭኖችሽ ውስጥ ለመገኘት ይሻል፤ ከዚ ሁሉ በላይ ግን አይኖቼ አይንሽን ለማየት፤ ጆሮዎቼ ድምፅሽን ለመስማት ቸኩለዋል፡፡

አዳምሽ ነኝ። ሄዋኔ ነሽ፡፡
እናፍቅሻለሁ። ትናፍቂኛለሽ፡፡

እስክንገናኝ፤ እስክንተያይ ሰላምሽ ለሰላሜ ይብዛ፡፡ ባለሽበት ካለሁበት ቸር ቆይኝ፡፡🌹


@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን!
💚

“የይቅርታ ጫፍ!” በለቅሶ ድንኳን
ውስጥ!
Written by ደ.በ


ድሬደዋ በዓመት የተወሰኑ ቀናት ቢዘንብ እንኳ፣ እንደዚህ የከበደና
ከተማውን ያጨለመ ዝናብ ታይቶም አይታወቅ፡፡ ሰው ሁሉ ግራ ተጋባ፣
ሀዘንተኛው የሚለው ጠፋው፡፡ አንዳች እርም ነገር ያለበት፣ ጠማማ ሰው
ቢሆን - ምናልባት ፈጣሪም ቁጣውን ሊያሳይ ነው ይባል ነበር፡፡ ደግሞስ
ድሬዳዋ ገብቶ እኛሁን ሳይነቅል፣ አውሬነቱን ሳይጥል የሚወጣ የታለና፡-
ድሬዳዋ እንደ አሜሪካ ናት፡፡ ሰው ሁሉ ከያገሩ ይዞት የመጣውን መሰሪነትና
ጠማማነት፣ በዚያች ከተማ እህል ውሃ ታጥቦ፣ በሽንቱም በላቡም
ይወጣለትና እንዳገሬው ሰው ገራምና ደግ ይሆናል፡፡
የሰላማዊት እናትም ያው የድሬደዋ ሰው ናቸው:: ገደቆሬ ተወልደው ከዚራ
ያደጉ፡፡ ታዲያ የእኒህ ደግ ሴት ቀብር እንዲያምር፣ ዝናቡ ለምን አልቆም አለ?
ሰላማዊት ዝናብ እየዘነበ፣ የርሷም ጉንጮች ላይ እንባዋ እንዳይዘንብ
አልከለከለችውም፤ “እማ ገመናዬ!!... እማዬ ጓዳዬ!” ትላለች፡፡
ከፊሉ ሰው እርሷን እያየ አብሯት ያለቅሳል:: ሌላው ደግሞ እንዳታለቅስ የቆ
የባጡን ያወራል:: “ተዪ-- የእግዜርን ዐይን አትውጊ! ስንት ወጣት ባጭር
በሚቀጭበት ሀገር! … ስንቱ ሞቶ አስከሬን በሚቃጠልበት ዘመን … በቃ
አስታምመሻል … በቃ!”
እርሷ ግን ትንሽ እንደማቆም ትልና፤ “እማ አጋለጥሺኝ … እማዬ ገመናዬን …
ገለጥሺው!” እያለች ትቀጥላለች፡፡
ቤቱ ሰው በሰው ሆኗል፣ ድንኳኑም በሰው ታጭቋል፡፡ የእናቷ ልከኛ ቪላ ቤት፣
ሰርክም ሰው አያጣም፡፡ ጎረቤት እንደ ቤቱ ገብቶ በልቶ የሚጠጣበት ቤት
ነው፡፡ ይህ ቀድሞ የነበረ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በሙስሊም ፆም፣
ጎረቤቶቻቸውን ሾርባ ሰርተው፣ ሳንቡሳ ቴምር ገዝተው፣ ቤታቸው ይጋብዙ
ነበር፡፡ ደግ ሴት ነበሩ፡፡ ጨዋታስ ሲያውቁበት!
“ጉድ አደረግሺኝ! ጉድ አደረግሺኝ!”
ለቅሶው መሀል የስምንት ዓመት ልጇ ስልኳን ይዛ እየሮጠች መጣ፤ “እማዬ
ስልክ?”
ቁጥሩን አየት አድርጋ፤ “ሄሎ! … ሄሎ! እንዴት ነህ!” ድምፅዋ ተለውጧል
“እንደዚህ ራስሽን አትጉጂ! … የናንተ ሀገር ሰው ልቅሶ ያበዛል!” አላት
“እናቴ ኮ ናት! …” አለች፤ ለስለስ ብላ፡፡
ብዙ ዐይኖች ወደርሷ አፍጥጠዋል፡፡ አንዳች ነገር ቀይ ፊቷ ላይ ማንበብ
ከጅለዋል፡፡ ቀጥ ብሎ ቁልቁል የወረደው አፍንጫዋን፣ አስሬ ስታልበው
ሳያቋርጡ ያያሉ፡፡ ለጊዜው እነርሱም ለቅሶውን አቁመዋል፡፡
“የናንተ ሀገር ሰው ልቅሶ የሚያበዛው በቁም ስለማይረዳ ነው፤ ፀፀት ነው!”
ይላታል፡፡
“አንቺ ግን እናትሽን የምትችይውን ሁሉ አድርገሽላታል፤ በቃ ያለ ነው፡፡
በርግጥ ጌጡ ልዩ ሰው ነበረች፤ ግን በቃ ፈጣሪ ደግ ሰው አይሞትም! ወይም
ዕድሜ ይጠግባል” አላለም፡፡ ብዙ ደግ ሰዎች ያለ ዕድሜያቸው እንደተቀጩ
ቅዱስ መጽሐፍም ይናገራል፡፡ የማቱሳላን እድሜ አልመኝላቸውም!” ሲላት
የወትሮ ንግግሩ ትዝ አላትና ወደ ሳቅ ልትገባ ነበር፡፡ ደስ ሲለው የሀገሩ
ደራስያን መጽሀፍት ውስጥ ያሉትን ገፀ ባህርያት ህይወት ሊጠቅስላት
ይችላል ወይም ከሼክስፒር ቴአትር፣ አሊያም ከጆን ሚልተን ስንኞች፣ ከጆን
ኪትስ ሶኔቶች … ፀባዩን ስለምታውቅ ገርሟት ዘጋችው፡፡ ይልቅስ ቀን ስለሆነ፣
እናቷንም አንድ ሁለቴ መጥቶ ስላገኛቸው በሀዘን የሚሰበር መስሏት በነበር፡፡
… የፈረንጅ ነገር! ብላ ዝም አለችው፡፡ ሰባት ዓመት ሙሉ አብረው ኑው፣ ፀባዩ
ለምን እንደገረማት ራስዋን ገረማት፡፡
ከአሁን በኋላ ምን ዓይነት ህይወት፣ ምን ዓይነት ትዳር ይኖራቸው እንደሆነ
እያለመች ወደ ልቅሶው ገባች፡፡ እናትዋን የሚያውቁ በዝምድና የሚገናኙ፣
ጎረቤት ሆነው ብዙ ዓመታት ያሳለፉ ሁሉ እያለቀሱ ይገባሉ፡፡ አንዳንዶቹ
ለእርሷ ብሰው ስለሚያለቅሱ እንዲተዉ ይለመናሉ፡፡ በዚያ ዝናብ፣ በዞያ ዶፍ
ውስጥ እንኳ የልቅስተኛው ቁጥር እየጨመረ መሄዱን አላቋረጠም ነበር፡፡
ወንዱም ሴቱም እያለቀሰ፣ ወይም አንገቱን ዝቅ እንዳደረገ ይገባል፡፡
በውጭ ስንዴ ለቀማው፣ ድስት መጣዱ፣ የተለያየ ነገር ማዘጋጀቱ ለእድር ብቻ
አልተተወም፡፡ ወንዱ እንጨት ፈለጣ፣ ሴቱ ማዕድ ቤትና እልፍኝ ውስጥ
ስራውን ቀጥሏል፡፡ በሞቃቱ ወራት ቢሆን ብዙ ነገሩ ከባድ ይሆን ነበር፡-
ዝናቡ ቀስ እያለ ሲያባራ የቀብሩ ጉዳይ የማይቀር ሆነ፡፡ እዚያም በተመሳሳይ
የሚያለቅሰው አልቅሶ፣ ዝም ብሎ ሀዘኑን በሆዱ የያዘውም ይዞ፣ ቀሳውስቱ
የቀብሩን ስነ ስርዐት አስፈፅመው ተመለሱ፡፡ አሁን ፈተናው የሰላማዊት
የብቻዋ ነበር፡፡ ከባለቤትዋ ጋር ስላላት የትዳር ጉዞ ማሰብ፣ ማውጣት፣
ማውረድና መወሰን አለባት፡፡ እናትዋ ጋ የሚኖሩትን ሁለት ልጆቿን ጉዳይ ምን
እንደምታደርግ ግራ ገብቷታል:: ባለቤትዋ የማያውቀው የሁለት ልጇቿ ጉዳይ፣
አደባባይ የሚሰጣበት፣ገመናዋ የሚወጣበት ቀን እየደረሰ ነው፡፡
ባልዋ የምድር ባቡር ሰራተኛ ሆኖ ድሬደዋ ሲሰራ፣ ራስዋን እንደ ልጆች እናት
አድርጋ ስላልነገረችው ግር ብሏታል፡፡ ሁለት ጓደኞቿ ለባሎቻቸው ሳይነግሩ
አግብተው፣ በመጨረሻ ነገሩ ሲገለጥ የደረሰባቸውን አበሳ ታስታውሳለች፡፡
ሁለቱም በባሎቻቸው ተደብድበው፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው ተሰኝተዋል::
“አታለልሺኝ” የሚል ሙሾ ተሟሽቶባቸዋል፡፡ ለዚያውም የእነርሱ አንድ ልጅ
ነው፡፡
“እማዬ ገመናዬን ዘረገፍሺው!” አለች፤ አመለጣትና፡፡
ብዙ ሰዎች ኑሮዋ ለንደን መሆኑንና ፈረንጅ ባል እንዳላት እንጂ ሌላ ብዙ ነገር
አያውቁም፡፡ ሁሉንም የሚያውቁት እርሷና እናቷ ናቸው፡፡ ፈረንጁ ሁለት ጊዜ
ከእርሷ ጋር ሲመጣ፣ ልጆቿን ጅጅጋ ያሉት አክስቷ ጋ አስቀምጣቸው ነበር፡፡
ደግነቱ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ስለነበረ ብዙም አላስጨነቃት፡፡ ጊዜውን
በክረምት ያደረገችውም አውቃ ነበር፡፡ አሁን ግን ልጆቿን ለማን ጥላ፣ በምን
አንጀቷ ትኖራለች! … ያበጠው ይፈንዳ! … ፈረንጁ ከእነ ልጆቿ ከተቀበላት
ተቀባለት፡፡ አለዚያም አንደ ሁኔታው ትኖራለች፡፡ ግን ያዝንባታል፣
ያሸማቅቃታል፡፡
በዚህ ዓይነት መሳቀቅ ከቆየች በኋላ አጅሬው ከተፍ አለ፡፡ ከአየር ማረፊያ፣
ወደ ቤታቸው ሲመጣ፣ ትንሽም አልተደናገረም፡፡
በሚገባ ተቀበለችው፡፡ እርሱም “መጽሀፍቱን፣ ቅዱሱን እርኩሱን እየጠቀሰ
ሊያፅናናት ሞከረ:: አንዳንዴ የሚጠቅሳትን ሀሳብ ጠቀሰላት፤ በጥሩ ጊዜ ስለ
paygmalion አወራት፡፡ ዕድለኛው የግሪክ ንጉስ አፈታሪክ፡፡ አንዲት ቆንጆ
ልጅ ሀውልት አድርጎ ሰርቶ፣ ያችን ደረቅ ሀውልት ላይ ያያትን የራሱን ፍጡር
ቢያደንቅ፣ የፍቅር አምላክ የምትባለው አፍሮዳይት ህይወት ዘራችባትና ሚስቱ
አድርጓት፣ በተድላ ስለኖረው ዕድለኛም ቆጥሮ ነገራት፡፡ ራሱን እንደ ዕድለኛ
ቆጥሮ፣ከራሱን ጋር ሊያወዳድረው ሞከረ፡፡
ዛሬ ይህንን ለምን እንዳነሳበት ባታውቅም ውስጧ እየተናጠ፣ ነፍሷ ባንዳች
ሞገድ እየተናወጠ ነበረ:: አሁን ግን የቁርጡ ሰዓት እየመጣ ነው:: ከጎረቤት
ያሉትን አንድ የዕድሜ ባለፀጋ መምህር አስቀምጣ፣ ከዚህ ቀደም ልጆች
እንዳሏት ሳትነግረው ስለ ፈፀመችው ጋብቻ መፀፀቷን ልትገልጽለት አሰበች፣
ከዚያም ወደ መኝታ ክፍል አስገብታው ልትወጣ ስትል፣ አፈፍ አድርጎ ያዛት፡፡
ከጎረቤት ሰው ልትጠራ እንዳሰበች ነገረችው፡፡
“አያስፈልግም! … አያስፈልግም!”
ደነገጠች፡፡
“እኔ ፕያግማሊን ነኝ፤ ዕድለኛ ነኝ ብዬሻለሁ!”
ግራ ተጋባች፡፡
“አንቺን በመምረጤ ዕድለኛ ነኝ፡፡ አደራሽን! አንቺ ግን ራስሽን እንደ
ፍራንካንስቴን አትቁጠሪ!”
ምን ማለቱ እንደሆነ ቀድሞም ታውቀዋለች፡፡ ሰው ራሱ በሰራው ስራ መከራ
እንደሚያይ አትቁጠሪ እያላት ነው፡፡ ይህ ፍራንካንስቴን የሼሌ ገፀ ባህሪ ነው፡፡
የሜዲካል ኮሌጅ ተማሪ ፈጥሮት፣
ፈጣሪውን የገደለ፣ ህይወቱን የበላ ገፀ
ባህሪ! ተገረመች፡፡ ራስሽን ዕድለ ቢስ አታድርጊ እያላት ነው፡፡
“Keep up our pious love!”
ድንቄም አለች፡፡
ስሚኝ “ሁለቱን ልጆችሽን አምጫቸው፣ ካገባሁሽ ቀን ይልቅ፣ የወደድኩሽ ዛሬ
ነው፡፡ አንቺ ድንቅ ሴት መሆንሽ ዛሬ ከአየር ማረፊያ ስመጣ ነው የሰማሁት!
ዛሬ የእናትሽ ልቅሶ ላይ ባትሆኚ፣ ሼሌ ገዝቼ ደግሜ እሞሽርሻለሁ!
ሰላማዊት ድንገት መሬት ምንጣፉ ላይ ወደቀች፡፡
“እኔን ስለምታፈቅሪኝ፣ እኔን ከማጣት ይልቅ የምትወጃቸውን ሁለት ልጆችሽን
ህይወት፣ ለኔ ለጣዖትሽ ሰዋሽ!! ፍቅር ከዚህ በላይ የሚገለጥበት መስቀል
የለም!” ብሏት አብሯት ዝብ አለ፡፡
ወገቧን ይዞ ሲያነሳት አዲስ የሚናኝ የፍቅር መዐዛ፣ የነፍሱን እልፍኝ
እያላወሰው ነበር፡፡ እርሷ በጉንጯ ከሚወርደው እንባ በቀር ቃል
አልነበራትም፡፡

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!💚

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!💚

የዛሬ 90 አመት የወጣ የአውዳመት ዜና!


ከመጠጥ የሚገኝ ጉዳት


ታህሳስ 29 የክርስቶስ ልደት እለት አቶ ……… የሚባል እንጦጦ ራጉኤል ገዳም ውስጥ
የነበረ ሰው በልደት በዓል ቀን አራዳ አረቄ ሲጠጣ ውሎ ወደ ማታ በፈረስ ተቀምጦ ወደ
ቤቱ ሲወጣ ራጉኤል አፋፍ በደረሰ ጊዜ ሰውነቱ በመጠጥ ዝሏልና ተኮርቻ ተገልብጦ
ወደቀ፤ እነሳለሁ መስሎት እየተንከተከተ /እየሳቀ/ አረሀ ላረሀ ሲንደባለል አሽከሩ እንደ እሱ
አልባሰበትም ነበርና ከቤቱ ሄዶ ሰዎች ይዞ እስቲመጣ ድረስ እሱ አረፋ ደፍቆ ሆዱ ተነፍቶ
ሞቶ ተገኘ። ብዙ ሞኞች ጋኔን ገደለው እያሉ ያወራሉ ግን ካረቄ የበለጠ ጋኔን እንደሌለ
ባያውቁ ነው።


ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ

ጥር 6 ቀን 1918 ዓ.ም

@wegoch
@wegoch
ጡ...ጡ....ጡ..ጡ..ጡጥ! 

ያልሰማህ ስማ ፣ የሰማህ ላልሰማ አሰማ !

ነገ ነሀሴ 28 ካሲዮፒያ የበጎ አድራጎት ማህበር በብሄራዊ ቲያትር የጥበብ ምሽት አዘጋጅቷል ። 

የጥበብ ምሽቱም ዓላማ አቅም የሌላቸውን ታዳጊ ተማሪዎች በመማርያ ቁሳቁሶች መርዳት ሲሆን መግቢያውም አንድ ደርዘን ደብተር ይሆን ዘንድ ተወስኗል ። 

በ 11።30 ፕሮግራም ላይ ሲሆን ብዙ የምንወዳቸው ገጣሚዎች እና የጥበብ ሰዎች ስራዎቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ይሆናል ። 

ወገኔ እነሆ ይሄን ፕሮግራም ታልመጣህ ዘንዳ ማርያምን አይማረኝ አልምርህም !

...
ጡ....ጡ....ጡ....ጥ!

ያልሰማህ ስማ! ...የሰማህ ላልሰማ ሼር በማድረግ አሰማ !!
@wegoch
Forwarded from ኢትዮ ሳቅ በሳቅ
ለረፋዳችን
💚


~~ ቢሊዬነሩ
~~
ድርሰት፡- ማክሲም ጎርኪ ትርጉም፡- ኢዮብ ካሣ
~~ ~~ ~~
በብረታ ብረትና በነዳጅ ንግድ የነገሱ ባለጸጎች እንዲሁም ሌሎች የአሜሪካ ከበርቴዎች
ሁሌም የምናብ አቅሜን በከፍተኛ ደረጃ ያነቃቁት ነበር፡፡
እነዚህ ተዝቆ የማያልቅ ገንዘብ ያላቸው ባለፀጎች፣ እንደ ሌሎች ሟች ፍጡራን ሊሆኑ
እንደማይችሉ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡
እያንዳንዱ ሚሊዬነር (ለራሴ ሹክ አልኩት) ቢያንስ የራሱ ሶስት ሆድና 150 ጥርሶች
አያጣም።
ሚሊዬነር ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ እስከ ቀትር ሌሊት ድረስ ያለ እረፍት
እንደሚያሻምድ አልተጠራጠርኩም፡፡
ምግቦቹ እጅግ ጣፋጭና ውድ እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው! መቼም አመሻሽ ላይ
በፈታኙ የማኘክ ሥራ መደካከሙ አይቀርም፡፡
ከመድከሙ ብዛትም (በምናቤ ሳልኩት) ቀን አጣጥሞ በጉሮሮው የላካቸውን ምግቦች
ይፈጩለት ዘንድ ለአሽከሮቹ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
መላወስ የተሳነው፣ ላብ ያጠመቀውና መተንፈስ ዳገት የሆነበት ሚሊዬነሩ፤ አሽከሮቹ
ደጋግፈው አልጋው ላይ ያወጡትና እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ያለበለዚያ በነጋታው ጠዋት 12
ሰዓት ላይ ዳግም የመብላት ሥራውን መወጣት አይችልም፡፡
ለእንዲህ ያለው ሰው - የቱንም ያህል ስቃይ ቢያስከትልበትም - የሃብቱን ግማሽ ብቻ
መጠቀም የሚሞከር አይደለም፡፡
ሃቁን ለመናገር እንዲህ ያለው ህይወት ቀፋፊ ነው፡፡ ግን ደግሞ አንድ ሰው ሚሊዬነር
ከሆነ፣ ይቅርታ---ቢሊዬነር…ምን ምርጫ አለው?
ከተራ ተርታው ሟች ብዙ እጥፍ የበለጠ ምግብ ካላሻመደ ቢሊዬነርነቱ ምኑ ላይ ነው ? ይሄ
የታደለ ፍጡር፣ የወርቅ ካኔቴራና ሙታንታ እንደሚለብስ፣ በወርቅ ምስማሮች ያጌጠ ጫማ
እንደሚጫማ፣ ጭንቅላቱ ላይ በባርኔጣ ምትክ የአልማዝ አክሊል እንደሚያጠልቅ ….
በምናቤ ስየዋለሁ፡፡
ልብሱ እጅግ ውድ ከሆነ አጥላስ የተሰራ፣ ቢያንስ 50 ጫማ ርዝመት ያለውና በ300
የወርቅ አዝራሮች የተያያዘ ነው፡፡ በበዓላት ወቅትም ስድስት ውድ ጥንድ ሱሪዎችን ደራርቦ
ለመልበስ መገደዱ አይቀርም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አለባበስ ጨርሶ ምቾት እንደሌለው
አያጠያይቅም፡፡
ግን ደግሞ አንድ ሰው ያን ያህል ባለጸጋ ከሆነ፣ እንዴት እንደተቀረው ህዝብ ይለብሳል?
የማይሞከር ነው!
የቢሊዬነር ኪስ በጣም ሰፊና ጥልቅ እንደሚሆን ገምቼአለሁ፡፡ እዚያ ትልቅ ኪስ ውስጥ
ለአንድ ቤተክርስቲያን ወይም ለሙሉ የሴኔት አባላት የሚሆን ክፍል በቀላሉ ማግኘት
አያዳግትም፡፡
የዚህ ዓይነቱ ሰው ቦርጭ፣ ርዝመቱንና ስፋቱን ልገምተው ያልቻልኩት የአንድ መርከብ
አካል (ቦዲ) እንደሚያህል አስቤአለሁ፡፡ የሰውነቱን መጠን በተመለከተ ግን ጥርት ያለ
ምስል መከሰት አልቻልኩም፡፡
ሆኖም ለብሶት የሚተኛው የአልጋ ልብስ ከጥቂት መቶ ስኩዌር ሜትሮች እንደማያንስ
ገምቻለሁ፡፡ ትምባሆ የሚያኝክ ከሆነ ምርጡን ብቻ እንደሚያኝክ አልተጠራጠርኩም።
አንዴ ወደ አፉ የሚልከውም ሁለት ፓውንድ የሚመዝን ትምባሆ ነው፡፡
እርግጥ ነው ገንዘብ መውጣቱ አይቀርም!
በሚገርም ሁኔታ የዚህን መንዲስ የሚያህል ሰውዬ ጭንቅላት በተመለከተ ለራሴ ግልጽ
ያለ ምስል መፍጠር አልቻልኩም፡፡
ለዚህ ከማንኛም ነገር ውስጥ ገንዘብ ጨምቆ ለማውጣት ከተዘጋጁ ግዙፍ ጡንቻዎችና
አጥንቶች ለተበጀ ፍጡር፣ ጭንቅላት እምብዛም አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም፡፡
ከእነዚህ አስደማሚ ፍጡራን አንዱን ፊት ለፊት ስጋፈጠውና ቢሊዬነርም እንደ ሌላው ሁሉ
የሰው ልጅ መሆኑን አምኜ ስቀበል የሚፈጠርብኝን መደነቅ--- ማን ሊገምተው ይችላል!
የእጅ መደገፍያ ባለው ወንበር ላይ በምቾት ተለጥጦ የተቀመጠ ረዥም፣ ጨምዳዳ
ፊት፣በፀሃይ የጠቆረ ጅማታም እጁ ዓይን በማይሞላ ሰውነቱ ላይ የተነባበረ ሽማግሌ
ተመለከትኩኝ፡፡
የፊቱ ለንቋሳ ቆዳ ሙልጭ ተደርጎ ተላጭቷል፡፡ ሊወድቅ የደረሰው የታችኛው ከንፈሩ፣
በቅጡ የተዋቀሩ መንጋጋዎቹን የሸፈኑለት ሲሆን የወርቅ ጥርሶቹን አጋልጠውታል፡፡
ጠፍጣፋ፣ ቀጭንና ኩበት የሚመስለው የላይኛው ከንፈሩ፤ ሲናገር እንኳ አይንቀሳቀስም፡፡
ግንባር የለሽ ፈዛዛ ዓይኖች፤ምልጥ ያለ ጭንቅላት ነው ያለው፡፡
አለባበሱ ከተራው ሟች ፍጡር ምንም የተለየ ነገር የለውም፡፡
ቀለበት አድርጓል፤ ሰዓት አስሯል። ከጥርሶቹ ውጭ ወርቅ የለውም፡፡ እሱም ቢሆን ግማሽ
ፓውንድ እንኳን አይሞላም፡፡
መላ ገፅታው ሲታይ፣ በአውሮፓ የአንድ መሳፍንት ቤተሰብ አዛውንት አገልጋይን
ያስታውሳል፡፡
እኔን በተቀበለኝ ክፍል ውስጥ ምንም የተለየ የምቾትና የቅንጦት ነገር አይታይም፡፡ የቤት
ቁሳቁሶቹ ጠንካራ መሆናቸውን ከመግለጽ ውጭ ሌላ ሊባል የሚችል ነገር የለም፡፡
“ምናልባት ዝሆኖች ወደዚህ ቤት ያዘወትሩ ይሆናል” የቤቱን ግዙፍና በርካታ ቁሳቁሶች
ስመለከት ያለ ውዴታዬ ያሰላሰልኩት ሃሳብ ነበር፡፡
“አንተ ነህ ቢሊዬነሩ?” ጠየቅሁት፤ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ፡፡
“እንዴታ! መጠርጠሩስ?” ጭንቅላቱን በአሳማኝ ሁኔታ እየነቀነቀ መለሰልኝ፡፡
“እሺ፤ ቁርስ ላይ ስንት ኪሎ ስጋ ትጨርሳለህ?”
“እኔ ጠዋት ስጋ አልበላም” ያልጠበቅሁት መልስ ሰጠኝ “ቁራጭ ብርቱካን፣ አንዲት
እንቁላል፣ ትንሽዬ ስኒ ሻይ፣ ይሄው ነው …”
“ጥሩ” እንደገና ጀመርኩ፤ በከፊል ሳልረጋጋ “እንዳትዋሸኝ፤ ሃቁን ንገረኝ፡፡ በቀን ስንት ጊዜ
ትበላለህ?”
“ሁለቴ” አለኝ ተረጋግቶ “ቁርስና እራት ካገኘሁ በቂዬ ነው፡፡ ቀትር ላይ ሾርባ፣ ጥቂት ዶሮ
ወይም ዓሳ፣ አትክልቶችና ፍራፍሬ፣ ከዚያ አንድ ስኒ ቡና፣ ሲጋራ …”
መገረሜ በፍጥነት እየጨመረ መጣ፡፡ ትንፋሽ ወሰድኩና ጥያቄዬን ቀጠልኩ፡-
“ያልከው እውነት ከሆነ፣ በገንዘብህ ምን ታደርግበታለህ?”
“ተጨማሪ ገንዘብ እሰራበታለሁ!”
“ምን ሊያደርግልህ?”
“የበለጠ ብዙ ገንዘብ ለማግኘት!”
“እኮ ምን ሊያደርግልህ?” ደግሜ ጠየቅሁት፡፡
እጆቹን በመቀመጫው መደገፍያ ላይ በማድረግ ወደ እኔ አስግጎ፣ በገጹ ላይ የጉጉት ስሜት
እየታየበት፤
“ነካ ሳያደርግህ አይቀርም?” አለኝ፡፡
“አንተስ?” አልኩት …
ሽማግሌው ጭንቅላቱን ዘመም አደረገና፤ በወርቅ ጥርሶቹ በስሱ አፏጭቶ፤
“ካንተ ዓይነት ዝርያዎች ውስጥ የተዋወቅሁት የመጀመሪያው የሰው ልጅ አንተ ነህ” አለኝ፡፡
ከዚያም ጭንቅላቱን ወደ ኋላ አስደግፎ ለተወሰነ ጊዜ ተመለከተኝ - በዝምታና በጥንቃቄ
በመመርመር፡፡
“ሥራህ ምንድነው?” እንደገና ጀመርኩ፡፡
“ገንዘብ መስራት” በአጭሩ መለሰልኝ፡፡
“አሃ--ሃሰተኛ ገንዘብ ነዋ የምትሰራው!” በደስታ ስሜት ጮኬ ተናገርኩ፤ በመጨረሻ
የእንቆቅልሹን ፍቺ ያገኘሁት ስለመሰለኝ፡፡ ቢሊዬነሩን ግን ስሜት ፈነቀለው፡፡ መላ ሰውነቱ
ተንቀጠቀጠ፡፡ ዓይኖቹ እንደ ጉድ ተንከባለሉ፡፡
“ተሰምቶ የማይታወቅ ነገር ነው!” አለ፤ ስሜቱ ሲረጋጋ፡፡ ከዚያ ጉንጮቹን ወጠራቸው ፤
ለምን እንደሆነ ባላውቅም፡፡
ጥቂት አሰብኩና ተከታዩን ጥያቄ አከልኩለት፤
“ገንዘብ የምትሰራው እንዴት ነው?”
“በጣም ቀላል ነው፡፡ የባቡር ሃዲድ መስመሮች አሉኝ፣ ገበሬዎች ጠቃሚ ምርቶች
ያመርታሉ፤ እኔ ለገበያ አቀርባቸዋለሁ፡፡ ገበሬው እንዳይራብና የበለጠ ማምረት እንዲችል
ምን ያህል ገንዘብ ልተውለት እንደሚገባ በትክክል አሰላለሁ።
የቀረውን እንደ ትራንስፖርት ክፍያ ለራሴ አስቀምጣለሁ፡፡ ይሄ ለእኔ በጣም ቀላል ነው!”
“እና ገበሬዎቹ በዚህ ይረካሉ?”
“ሁሉም ይረካሉ ብዬ አላምንም” አለ፤በገራገር ጨቅላነት “ግን ደግሞ ሰዎች ምን
ብትሰጣቸው አይረኩም ይባላል፡፡ ሁልጊዜ በቃኝ የማያውቁ ለየት ያሉ ሰዎች አሉ…”

ምንጭ ☞ አዲስ አድማስ

@wegoch
@wegoch
ጥሬ ጨዉ
=========
መስለዉኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰዉ ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸዉ
ጥሬ ጨዉ…ጥሬ ጨዉ ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት መቀየጥ
ገና እሚቀራቸዉ
“እኔ የለሁበትም!”
ዘወትር ቋንቋቸዉ።
_______
ደበበ ሰይፉ



ደበበ ሰይፉ ጥሬ ጨው የሚላቸው.....እኔ ምን አገባኝ እኔ ላይ ካልደረሰ የሚሉትን ....እኛም ጥሬ ጨው ሳንሆን አንቀርም ሁላችንም እኔ ላይ ካልደረሰ ምን አገባኝ የምንለው ፈሊጥ አለ .....ነገ እኛ ጋር ሲደርስ እኔ ምን አገባኝ እኔ ላይ ካልደረሰ ያልናቸው እነሱም በተራቸው ይሄንንኑ እንደሚደግሙት አትጠራጠሩ ....."በራስህ ላይ ሊደረግ የማትፈልገውን በሌላው አታድርግ " የሚለው ንግግር ለኔ የሚገባኝ በአንተ ላይ ሊሆን የማትፈቅደው ነገር ሌሎች ሰዎች ላይ ሲፈፀም ምን አገባኝ ከማለት ድርጊቱን ተቃወመው......አንድ የነብዩ መሀመድ ንግግር አለ << መጥፎ ነገር በሚደረግበት ጊዜ ከቻላችሁ አስቁሙት ፣ ካልቻላቹ ድርጊቱ መጥፎ እንደሆነ ተናገሩ በመናገር አውግዙት ይሄንንም ካልቻላቹ ግን ድርጊቱን ተፀየፉት ብለዋል!! (ንግግሩን ካሳሳትኩኝ እታረማለሁኝ ) እና #እኔ ምን አገባኝ ከማለት እንውጣ !


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!💚

@wegoch
@balmbaras
ለሰንበቲታችን
💚

የጽሞና ጊዜ

ዋጋህ ያለው በሠራህ ጌታ እጅ ነውና ዋጋህ ስንት
እንደ ሆነ እርሱን ጠይቀው፡፡ አንተ የምትጥለውን ነገር
ትደክምበታለህን? እርሱም የሚደክምብህ ሊጥልህ
ሳይሆን ሊከብርብህ ነውና ደስ ይበልህ፡፡ ልብህ ታንቡር
የመታበት ቀናቶች፣ እንቅልፍ ያጣህበት ሌሊቶች ብዙ
ናቸው፡፡ እንደዚያ በመሆንህ ግን ምን አመጣህ? ዛሬም
ነገርህን ለእግዚአብሔር አስረክብ እንጂ ራስህን
አታድክም፡፡ ጭንቀት የቀረበውን ከማራቅ በስተቀር ምንም
ዓይነት መፍትሔ የለውም፡፡ «ጭንቀት ለመጣው ችግር
ወለድ መክፈል እንጂ መፍትሔ አይደለም፡፡» በጭንቀት
ውስጥ ስትሆን ቀጣዩ ቀን አይታይህም፡፡ ስለዚህ፡-
· የሚበልጠውን ተቀብለሃልና ለትንሹ
ዋስትና አለህ፡፡
· ለራስህ በመጨነቅ ከእግዚአብሔር
በላይ ደግ አትሆንለትም፡፡
· ስለ ትርፉ በጣም የሚጨንቅህ
ዋናውን ስላልያዝህ ነው፡፡
· ያንተ ቀን ዛሬ እንጂ ነገ አይደለችምና
ስለ ነገ አትጨነቅ፡፡


☞ ምንጭ የኑሮ መድህን

@wegoch
@wegoch
#ሃሳብዎን በነፃነት ይስጡ!

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዚህ በታች የቀረቡት ቃለመጠይቆችን ከመስከረም 2011 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ወይም የተከናወኑ ጉልህ አገራዊ ሁነቶች የሚመለከቱ ናቸው። ዓላማውም የቻናላችን አንባብያን የዓመቱ ምርጥ፣ ተወዳጅ፣አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተቶች በተመለከተ ሀሳባቹን ወይም አስተያየታቹን መሰብሰብ ነው።ምላሽ በመስጠት የተለመደውን ተሳትፏቹን እንጠብቃለን። እናመሰግናለን!🙏🙏


1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ


🤔 ማስታወሻ :- ስማቹን ፣ ፣ የምትኖሩበት ቦታ አብራቹ መላካቹን እንዳትረሱ 🙏🙏🙏

👇👇

@balmbaras
Èyãsû gøssäyé:👇👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል" ፕሬዝዳንት :musxefa Ali(Somali)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም: tele
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም:elpa
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም:no one
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት:-hagerawi megbabat
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ:- chigign tekela
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት:-ye bejet gudlet😂
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት:- no one
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ:- Dr. Abiy
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ:-asham
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ:- bisrat
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ:no
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት:no
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ:Ethiopian (real ones)
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ:9gnaw shih
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ:- no
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም:- no
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ:ye asham TV documentary aqrabiw Girma assef
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ:-sayxaxamu megenxel mebalu
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ:-memarya kusakus le temariwoch

#Ke eyasu gossaye
Debrezeit

Nikodimos Enyew:👇👇👇

Nikodimos Enyew Addis Ababa
1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
-> ዶ/ር ደብረጽዮን
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
-> Ethio Telecom
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
-> ትምህርት ሚንስትር
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
-> መከላከያ ሚንስትር
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
-> የዕዳ ቅነሳ ስምምነት ከቻይና ጋር
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
-> ሐምሌ 22
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
-> የክረምት በጎ ፈቃድ
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
-> ኦባንግ ሜቶ
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
-> ዶ/ር አብይ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
-> ፋና
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
-> ሸገር
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
-> ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
-> ጦቢያ
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
->
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
-> ውርስ
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
-> ገራገር
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
-> ጎሳዬ/አስቴር/ዘሩባቤል
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
-> ፀጋአብ ወልዴ (Tikvah)
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
-> ሰኔ 15
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ
-> ለጌዲዮ እና ጉጂ ተፈናቃዮች በታማኝ በየነ የተሰበሰበው ድጋፍ

Gedel gibu:👇👇👇

ada....ke a.a


1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት .....የሱማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም....በጣም ባይባልም ምርጫ ቡርድ
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም.....ት/ት ሚኒሰቴር
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም....ምርጫ ቦርድ
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት......ማስመሰል
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ....ችግኝ ተከላ
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት.....የዘውግ ፓለቲካ መሰራፋት
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት....?.As positively no one but negatively gawar Mohamed
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ no one
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ.....art tv
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ sheger fm
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ......ትውልድ አይደናገር.....
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት...
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ.....ታማኝ በየነ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ......ዘመን
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ.....ገራገር
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም.....ደጊ ደን
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ.....
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ ኦነግ
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ......

I HAVE DREAM!:👇👇👇

1.Mustafa Omar Somalia
2.may be ethiotelecom
3.timirt Minster
4.?
5.Ethiopia and Eritrea selam mewired
6.chigign tekelew hamile 22
7.?
8.ታማኝ በየነ
9.ልደቱ አያለው 👍👍👍👍👍👍
10.L TV
11.fana fm specilay "jilalo awol"
12.amalkit & tawotat (pilatos or halegiorgis mamo)
13.gonder university kenun alasatawism epherem syium ena lelochi
14.መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ
15.9ሺ
16.?
17.astuka chewa🙏🙏🙏
18.simeneh bayiferes walta tv
19.የአዴፓ እና የህወሀት መግለጫ
20.yesefer lijoch gar hunen 2010 lay ye akimedekama bet yeseranew

#Tewodros mengesha ke wollo raya kobo


Biniyam:👇👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት --Mustafa (somali kilil)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም--Gebiwoch minister
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም---Mebrat hayl
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም---Mircha Bord
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት---Wuyiyitin masfafat
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ--chigign tekela
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት--Chigign tekela
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት ---Jawar
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ....Dr. Abiy
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ---Fana B.C
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ---Zami FM
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ --Harrison
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት---I don't know
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ ---Dr. Abiy
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ--I don't know
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ- Gerager
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም - Gosaye's
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ- Elias Meseret
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ - coup d'etat of sene 15
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ - Sitota le addis abebaye

#Biniyam , ke A.A


እኔስ የ ማርያም ነኝ:👇👇👇

1.no one
2.ye fth tekuam
3.football federation
4.sebawi mebt komision
5. ye ethio ertra wedajnet
6.arenguade zemecha
7.ye metek sra megalet
8.no one
9.d.r abiy Ahmed(king)
10.fana TV
11.ethio FM
12.yemdrachn jegna zenebe wela
13.tobiya (gtmn be jazz)
14.Dr ab
iy Ahmed
15.9naw s

hi
16.fikir yetalesh
17.aster aweke (queen)
18.Mensur abdulkeni
19.ye adiis Ababa guday
20.yegodana ljochn mansat

#Yohans gebre ke bole



Manuel:👇👇👇

..ከመስከረም 2011 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ወይም የተከናወኑ
ጉልህ አገራዊ ሁነቶች የሚመለከቱ ናቸው።
የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት.....የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት
የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም...የለም
የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም......ትምህርት ሚንስቴር
የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት ፓርቲ.......አብን
የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት.....ችግኝ ተከላ
የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ......አረንጉዋዴ አሻራ
የዓመቱ ተስፍ የሌለው ፓርቲ....አዴፓ
የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት .....ዮኒ ማኛ
የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ...አስራት ቲቪ
የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ሙዚቃ......ገራገር
ዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም .......ጨዋ
የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ.......ስሜነህ
የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ፓርቲ.......ኢዜማ
የዓመቱ ትልቅ ውሽት........መፈንቅለ መንግስት
የአመቱ ታላቅ ውሸታም........ዶክተር አብይ
እውነቱ ይሄው ነው !

#Aman ke metu


ትዙ የ ገብርኤል:👇👇👇

ስም ፡-ትዝታ
አድራሻ፡ አ.አ

1. ደብረ ጺዩን
2. ኢቲዩ ቴሌኮም
3. ትምህርት ሚኒስቴር
4. ህህዎት
5. ኢቲዩ ኤርትራ እርቅ
6. ችግኝ ተከላ
7. ብሄር ከብሄር ግጭት (political
8. ጆሀር
9. ዳ/ር አብይ
10. ጄቲቪ
11. አሃዱ
12. የ አብይ ይልማ 666
13. ጦቢያ
14. ኦባንግ ሜቶ
15. ምን ልታዘዝ
16. ኢጌቱ ልቤ ማላ
17. ዘሩባቤል
18. ቃልአብ በሀይሉ ቃና
19. ኦነግ ያሸበራ የሚያሸብራ
20. ሜቄዶኒያ

Black ሴት:👇👇👇
Sumi
(adis ababa)

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት (ሙስጠፌ)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም(ገቢዎች)
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም(t.p.l.f)
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም (የምርጫ ቦርድ)
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት(ኢትዮ ኤርትራ እርቀ ሰላም)
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ(ችግኝ ተከላ)
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት(ዝናብ)
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት( ታማኝ)
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት መሪ)(ደመቀ መኮንን)
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ(ፋና)
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ(bsrat)
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ(የዘር ካርድ)
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት(ጦቢያ)
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ(ዶ/ር ምህረት ደበበ)
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ(ዘመን)
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ(አልጓጓም ራሄል)
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም(የአቡሽ)
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ(ሊብሮ)
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ(የተግራይ እና የአማራ ክልሎች ጥል)
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ(ካሲዮኘያ የበጎ አድራጎት)


Sem Sem:👇👇👇

sem sem from Adama

1 አ/ቶ ሙስጣፌ መሀመድ
2 ገቢዎች ሚኒስቴር
3 የፈተናዎች ኤጀንሲ
4 ምርጫ ቦርድ
5 ችግኝ ተከላ
6 ችግኝ ተከላ የተካሄደበት
7 የደብተር መሰብሰብ ዘመቻው
8 -
9 ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
10 አርት ቲቪ
11 ብስራት FM 101.1
12 -
13 -
14 የመጅሊስ መሪ ሀጂ ሙፉቲ
15 ሞጋቾች
16 የዘቢባ ( ገራገር)
17 የ ዳግ ዳንኤል ( ስሜቶቼ )
18 መንሱር /ቀኒ
19 መፈንቅለ መንግስቱ
20 የዶ/ር አብይ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ ያበረከቱት 25000 ዮሮ


Le fils de sa mere..:👇👇👇

Teklu man#

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት : Mustefa Muhamed (My prime minister)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም: Mekelakeya
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም: Press secretary of pm./ Teklay frdbet
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም: Yellem
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት:- Yellewm
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ:- Orthodox Tewahdos
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት:- Ethio Eritrea
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት:- Miky Amhara
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ:- Er. Yilkal Getnet/ Ato Getachew Reda
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ:- Asrat tv
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ:- Ahadu fm
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ:Andargachew Tsiges egnam ennager
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት:no
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ:Dr. Ambachew
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ:betoch drama
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ:- Tedy tkurara
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም:- Aster chewa
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ:Temesgen Dessalegn
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ:- kegna
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ:- Ato worku aytenew 30 million le tefenakayoch


ʧãç:👇👇👇

Isak
ke jima
1 አቶ ለማ መገርሳ
2 gebiwoch
3 timhrt minster
4 ኢህዴግ
5 industry park
6 chigign tekela
7 ethio eritrea
8 Jewar mohammed
9 PM Dr Abiy Ahmed
10 L TV
11 Sheger fm
12 ...
13 ..
14 Muferyat kamil
15 zemen
16 Gildo kassa ( lageba new )
17 gosaye tesfaye ( siyamsh yamegnal)
18 Betelhem ( L TV )
19 ጋዜጠኛ Eskindr Nega ( baladera )
20 Abebech Gobena



Betaam ameseginalew 🙏🙏

---------------------------------------------------

#እጅግ በጣም ብዙ ነው እንዳይሰለች ቀስ እያልን ካልሆነ የተወሰነውን ብቻ ለመልቀቅ እንገዳለን #ሁላችሁንም በሃይልል ነው የምናመሰግናቹ ሀሳባቹን በነፃነት በመስጠታቹ !!

@balmbaras
ከመሸ ለምስጋና ብቅ ብለናል !
🙏

#የቻናላችን ቤተሰቦች የላካቹን በሙሉ በጣም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

እውነት እጅግ ብዙ ብዙ መልክቶች ናቸው የተላከልን የሁላችሁንም መልክቶች ማቅረብ አልቻልንም ለዚህም ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን የላክናቸው ይበቃል ከማለት ነው የላካችሁሉን በሙሉ ግን ትልቅ አክብሮት አለን 🙏!!!

ሁላችሁም ሀሳባቹ በነፃነት ስለገለፃቹልን ደስ ብሎናል እናመሰግናለን !!

#አብዛኞቻችሁ ማለት እችላለሁ ልዩነቶቻችን ትንሽ ናቸው አንድ የሚያደርገን ግን ብዙ እንደሆነ ገብቶኛል ያ ደግሞ አስደስቶኛል እኛ የተለያየ ምርጫዎች ፣ ፍላጎቶች ይኖሩናል ይሄ የሚጠበቅ ነው የሚያስገርምም አይደለም .....

ሁላችንም ኢትዮጵያ በተለያየ ምልከታዎች ልንመለከታት እንችላለን ይሄ ሸጋ ነገር ነው !!መነሻችንም መድረሻችንም ግን እሷ ናት !! ሁላችንም ሀገራችን እንወዳለን የተሻለች እንድትሆን እንፈልጋለን ሀገራችን ብዙ መልካም ነገሮች እንድትሆን እንፈልጋለን አይደል.? ስለዚህ የምንፈልገውን ነገር ከመፈለግ ባሻገር ከኛ የሚጠበቀውን ማንኛውንም መልካም ነገር እናድርግላት ከመንገድ ላይ የሙዝ ልጣጭ (ቆሻሻን ) ማንሳትም ጀምሮ መፈለግ ብቻውን ለውጥ አያመጣምና !!

#በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን !! በሃይል የምወደውን የልቤን ሰው #የነብይ መኮንን ግጥም ጀባ ብያቹ ወደ አልጋዬ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር💚💛❤️ አሜን!!!

------------------------------------------------


///ነብይ መኮንን///

በዚህ ዓመት
ሳንጣላ መታረቂያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሰደጃ፡፡
ምንለበት ፤
ለምናልባት ብንተውለት !!
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ባዶ እንዋዋል ፣ ከልባችን ደግ በኩል፡፡
ለአንጎላችን መላወሻ
ትንሽ ቦታ እንተውለት
" ምናልባት " የምንልበት፡፡
ልክ እንዳምና ፣ ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብንል መታሰርያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ፡፡
በልባችን ደግ በኩል ፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ፡፡
የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለወጫ !!

((( ደግ ለሚያስቡ ))))💚💛❤️



@balmbaras
@wegoch
ለውብ ቀን
💚

* የሚበልጠውን ይዘናል! **


ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት?! ዲዮጋን የተባለው የግሪክ ፈላስፋ ኑሮው ጎርፍ
በሸረሸረው ፈፋ ውስጥ ነበር፡፡
ንብረቱም አንዲት መንቀል (የውሀ መጠጫ ቅል) ስትሆን አንዲት ውሻም ጓደኛው ነበረች፡፡
ታላቁ እስክንድር ዓለምን አስገብሮ ሲመለስ ዲዮጋን የተባለውን ፈላስፋ ማየት አለብህ
ስላሉት ሊያየው መጣ፡፡
ዲዮጋን ግን ከቤቱ አጠገብ በጀርባው ተኝቶ ፀሐይ ይሞቅ ነበር፡፡ ታላቁ እስክንድርም
አጠገቡ መጥቶ ቢቆም ማን ነው ብሎ እንኳ ዲዮጋን አይኑን አልገለጠም፡፡
እስክንድርም ‹‹ዲዮጋን ሆይ ተነስ እኔ ታላቁ እስክንድር ነኝ፡፡
ዓለምን አስገብሬ ተመልሻለሁ ፤ የምትሻውን ለምነኝ የመንግስቴንም እኩሌታ ቢሆን
እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡
ዲዮጋን ግን አይኑን እንደ ከደነ ‹‹ይልቅስ አንተ ልትሰጥ የማትችለውን ፀሀይ አትከልክለኝ››
አለው ይባላል፡፡


ንጉስ እንኳን የማይሰጠውን ብዙ ስጦታ ስለተቀበልን እግዚአብሔር ይመስገን! ሰውዬው
‹‹እግር የሌለውን እስካይ ድረስ ጫማ የለኝም ብዬ አዝን ነበር›› ብሏል፡፡


መለስ ብሎ እራሱን ሲመለከት የሚበልጥ ነገር አገኘ፡፡ ጫማን ገንዘብ ይገዛዋል ፣ እግሩን
ግን በገንዘብ አይገዛውም፡፡ ጫማም ያማረው እግር ስላለው ነው፡፡ ለማማረርም የበቃነው
በህይወት ስላለን ነው፡፡


ለማማረርም እንኳን ዕድሜ ስላገኘን ልናመሰግን ይገባናል፡፡ በሳጥናቸው ብዙ ልብስ
አጭቀው ከአልጋዬ ተነስቼ አንድ ቀን እንኳ በለበስኩት እያሉ የሞቱ ሰዎችን አውቃለሁ፡፡
የሚበላው እያለው የሚሞት ፣ የሚበላው አጥቶ የሚኖር ብዙ ሰው አለ፡፡
ባለጠጎች በገንዘባቸው ለአንድ ቀን ዕድሜያቸውን ማስረዘም አይችሉም፡፡


እናት ለምትወደው ልጇ ቀንሳ የማትሰጠው ዕድሜ ስላለንና ሰው የማይሰጠውን
ስለተቀበልን እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል፡፡ …

👉 ‹‹የኑሮ መድኅን›› መፅሐፍ ከገፅ 32 የተወሰደ!

@wegoch
@wegoch
ለሰንበቲታችን
💚

“ሀሳብ ያለ ነጻነት ግራ እንደተጋባ መንፈስ ነዉ ፣ ህይወት ያለ ሀሳብ ነፍስ እንደሌለዉ አካል
ነዉ ፣ ነጻነት ያለ ህይወት እንደ ግኡዝ አካል ነዉ፡፡”
*
*
ካህሊል ጂብራን፡

@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
2024/11/15 18:01:28
Back to Top
HTML Embed Code: