Telegram Web Link
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
ድምፃዊ #ሙሉአለም_ተክሌ ወንድማችን ነው። ከጎን ለመቆም ሁላችንም ጊዜ አንጠብቅ
ዛሬ አሁን ለምንወደው ድምፃዊ እገዛችንን እናድርግ !
ሙሌ #በኩላሊት ህመም #ዲያልሲስ ጀምሯል

ለጥያቄ እና ለመርዳት
ስልክ:- +251911572276
ንግድ ባንክ (CBE)
mulualem takele
1000182044184

ከጎን ሆናችሁ ሀሳብ ለመስጠት ይሄን
group ተጠቀሙ https://www.tg-me.com/joinchat-JSJyPhNcOTNP5V8x4LOXOw
እያንዳንዱ ሩዝ ላይ የሚበላው ሰው
ስም ተጽፏል


አንድ እጅግ ጉረኛ ሰው ነበር፡፡ ድንገት ይመጣና ‹‹አሥራ ስድስት
ቀበሮዎች አግኝቼ አንድ ላይ፣ በአንድ ጥይት ሰፋኋቸው! በጣም አስገራሚ
ገድል ነው የፈፀምኩት›› አለ፡፡
‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› አሉት፡፡
‹‹እንዴ?! የዚያን ጊዜ ተዓምር በቃላት አይፈታም››
ማሰብ ይጠይቃል፡፡ እንደው ላይ ላዩን አይተን ብቻ በመሀይም ልቦና ጉዳዩ
ውስጥ እንግባበት ብንል ከንቱ ድካም ነው የሚሆነው፡፡
ምንም ማስረጃ ሳያስፈልግ ለአገር መመስከር እንችላለን፤ ሕዝቦች ነንና!!
ይኸው ጉረኛ መንገድ ላይ ሰው አገኘና፡-
‹‹ከየት ትምጣለህ?›› አለው
‹‹አሥራ ስድስት ቀበሮዎች ሰፍቼ››
‹‹የት?››
‹‹ጫካ››
‹‹ጀግና ነህ! አንበሳ ነህ!››
‹‹ጀግንነቴ አስደማሚ አይደለም?››
‹‹እኔን ያስደመመኝ ያንተ ጀግንነት አይደለም››
‹‹ሌላ ምኑ ነው ታዲያ ያስደመመህ?›› አለው፡፡
‹‹የአገርህ ቀበሮዎች አሰላለፍ!!››
* * *
ለማንኛውም ከጥሩ ማስተዋል ጋር አሰላለፍን ማሳመር መታደል ነው!
ገጣሚውና ፀሐፌ - ተውኔቱ መንግሥቱ ለማ፡-
ቀማኛን መቀማት
ከሌባ መስረቅ
ለማቅለል ከሆነ
የድሆችን ጭንቅ
በእኔ ቤት ፅድቅ ነው
አንድ ሰው ይሙት!!
አንድ መቶ ሺህ ሰው ሲኖር በምጽዋት!››… ብለዋል፡፡
ይህ ፍንትው ያለ ዕውነት ነው!!
‹‹ውሸት ዓለምን ዞሮ ሲጨርስ፣ ዕውነት ቦት ጫማውን አስሮ አይጨርስም››
ይላሉ አበው፡፡
‹‹ጓደኛሞች መጠጥ ቤት ይገናኙና፤
‹‹የት ጠፋህ›› አለ አንዱ አንደኛውን
‹‹እንደው ባንተያይ ነው እንጂ እኔ እንኳን አለሁ››
‹‹የደበቅኸኝ ነገር አለ እንጂ እዚሁ አዲሳባ እየኖርን ልንጠፋፋ አንችልም››
‹‹ምንም የደበቅሁህ ነገር አይኖርም፤ ግን ለአንድ ለስድስት ወር አሥረውኝ
ነበር››
‹‹ምን አርገህ ብለው ነው?››
‹‹አንድ ኮርቻ ሰረቅህ ብለው ነው››
‹‹ለኮርቻ ስድስት ወር?››
‹‹ምን እባክህ ከኮርቻቸው ሥር አንዲት የማትረባ በቅሎ ነበረች››
ዋናውንና ምንዛሪውን ካልለየን አለመታመን የግድ ይመጣል፡፡ የግድ ተዓማኒ
ለመሆን ማንነትን ማጥራት ዋና ጉዳይ ነው፡፡
ማንነት ደግሞ፤
የቀናነት
የሀቀኝነት
የፍቅር
የተስፈኝነት
የዕውቀት
ሁሉም የመልካም አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ አንድ ሰው ሆድ ውስጥ ማጠራቀም ብርቱ ጥረት ይጠይቃል፤
ከልባችን እንታገል!!
ካመረርን፣ መንገዳችን ሩቅና መራራ መሆኑን ከልብ ካመንን የማናቸንፍበት
አንዳችም ምክንያት የለም!!


መልካም የፍቅር ዓመት ያድርግልን!!


(( ነብይ መኮንን ))

@wegoch
@wegoch
መልክ አልባ ኑሮ(ልዑል ሀይሌ)
50 ዓመት ያለመልክ ኖሪያለሁ። ይብላኝለት 60 ዓመት ከመልክ ጋ ለተጓዘ...አንዲቷም ወደኔ አሻግራ ሳታይ እኔ ብቻ ዓይኔን ሳልነቅል እየኮመኮምኩ በነጣነት አገር ምድሩን ስዞር ኖርኩኝ ይብላኝለት እንደ ኤግዚቢሽን ለሚጓዝ ባለመልክ በወጣ በገባ ቁጥር በቆነጃጅት ተከቦ እይታው ለተጋረደው እኔስ 1000 ማይል አሻግሬ ማየት እችላለሁ። ማንም ሰው ነጣነቴን አይጋፋኝም ምክንያቱም አገላብጬ ከእግር ጥፍራቸው እስከራስ ጠጉራቸው እያየሁ ሳደንቅ እነሱ እንደ ሂውማን ሄራቸውም አያዩኝም። በአጋጣሚ ዓይኔን ብልጥጥ አድርጌ ሳያቸው የተመለከቱኝ ቆነጃጅትም "ምን ይመስላል?!" እንዳይሉኝም ድፍረት የሚነፍጋቸውን አስፈሪ ፊቴን አይተው የግዳቸውን እንደ ኮሶ የመረረ ሳቅ ስቀውልኝ ያልፋሉ። ዕድሜ ለዚህ ብቻውን ክልል መሆን ለሚችል ለማያልቀው ፊቴ ያሻኝን ሁሉ ዓይቼ እገባለሁ። ሠፈር ውስጥ እንደገባሁ ት/ቤት አንሄድም እያሉ፣ ወላጆቻቸውን አልታዘዝ እያሉ፣ በጊዜ ቤት አንገባም እያሉ የሚያስቸግሩ ህፃናትና ጎረምሶችን እንዳስፈራራበት በተሰጠኝ ይሄ ሁሉ ዓመታትን ተሸክሜው ስዞር የነበረ ሌላ ሰው ቢሸከመው ግን አንገዳግዶ የሚጥለው ኩንታል ፊቴን ይዤ ከተጠራሁበት ቤት ገና ከመድረሴ ት/ቤት አልሄድም ብሎ ሲያስቸግር የነበረው ልጅ በቅፅበት ዩኒፎርሙን ለባብሶ ደብተሮቹን ይዞ "ከዚህ ፊትስ ትምህርት ይሻላል!.." በሚል ስሜት ውልቅ ብሎ ሲሄድ ሳይ በዚህ ማስፈራሪያ ፊቴ እኮራለሁ። ወላጆቹን አልታዘዝ ያለውም ልጅ ገና ፊቴን ሲያይ ማስታጠቢያና ውሃ አምጥቶ የወላጆቹን እግር እስከማጠብ ይደርሳል። በዚህም አገልግሎቴ በሠፈሩ ወላጆች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አግኝቻለሁ ምንም እንኳ ለአንድም ቀን ቀና ብለው አይተውኝ ባያውቁም በድምፄ ስለሚለዩኝ ግን በርከት ያለ የእግዜር ሰላምታና ውዳሴ ያቀርቡልኛል። እኔም ይሄንን ነፃነቴን ተጠቅሜ በሰፈሩ ውስጥ ሳልፍ ጮክ ብዬ መዝፈን ሁላ ይቃጣኛል ምክንያቱም ብቸኛው ከሰፈሩ ሰዎች ጋር ያስተዋወቀኝ ባለውለታዬ ድምፄ ስለሆነ ነው። ፊቴማ ሰው አርቆብኝ በሩቅ ያስከብረኛል ድምፄ ባይኖር ግን በምኔ ይለዩኝ እንደነበር እንጃላቸው። ብቻ ይሄንን ፊት ግማሽ ክፍለ ዘመን ስሸከመው ከክብርና ከነፃነት ጋር ነው። አልፎ አልፎ የሠፈር ሰዎች እያሙኝ እደርስና ድምፄን አጥፍቼ አዳምጣቸዋለሁ አንዳንዱ "ዛሬ ልጄ ሰውየውን አይቶት ሲያቃዠው አደረ...ፀበል ብረጨው ምን ባደርገው ቅዠቱን ሊያቆም አልቻለም። እንደሁ ምን ይሻለኛል?" ሌላዋም ሴትዮ ቀጠል አደርጋ "የኔ ልጅ ደግሞ ት/ቤት አልሄድም ብሎ ሲያስቸግር ሰውዬውን ባመጣው ይኸው ከት/ቤት አልተመለሰም...ት/ቤቱ አዳሪ ፕሮግራም እንዲጀምር ተማሪዎቹን እያሳመፀ ነው..."...ሌላም ሌላም ይላሉ እንደ "ነይልኝ!" እና "ነይለት!" እየተቀባበሉ። እኔም ለመመለስ ይዳዳኝና ልጃቸውን ስለማስፈራራላቸው የቤት ኪራይ መክፈሉን ምረውኝ ለብዙ ወራት የዘለቁት አንዷን ባልቴት ላለማስቀየም ስል የጀብደኝነት ስሜቴን እንደተጎናፀፍኩ ውልቅ ብዬ እወጣለሁ። 50 ዓመት ያለመልክ ኖሪያለሁ። ያለመልክ መኖርን እስከጥግ አውቀዋለሁ ፈጣሪዬን ለአንድም ቀን አማርሬው አላውቅም። እንደውም የምከበርበትን መንገድ በፊቴ ስላጎናፀፈኝ ዘወትር አመሠግነዋለሁ። ይብላኝለት 60 ዓመት ከመልክ ጋ እየተጓዘ በውበቱ ለሚመፃደቅ ...አመሠግነው ዘንድ ምክንያቴ ብዙ ነው። መልክ በመነፈጌ ነፃነትን እስከጥግ እንዳጣጥመው ረድቶኛል። በሁሉም ድክመቶቻችን ውስጥ እናመሠግንባቸው ዘንድ የተሠጡን ፀጋዎች ብዙ ናቸው። ቁጠሩ ...ፀጋችሁን ቁጠሩ 1..2...3....4...1000,000,000....እነዚህ ቢልየን ምክንያቶች ፈጣሪያችን እናመሠግንበት ዘንድ ስለተሠጡን ዘወትር ፈጣሪያችንን እናመስግን። መልካም ምሽት!! መልካም አዳር!!
13-11-2011 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@tirfeskirbitoleulhaile
ለውብ ቀን!
💚

አፍ በከፈተ አይደለም

ያዝኩትን የአልማዝ ትናንሽ የእንቁ ጠጠሮች ላጠራቅም ፈልጌ እቃ ማማረጥ ጀመርኩ።
እንዳጋጣሚ ባዶ የኪዊ ቆርቆሮ እና የአምቦ ውሃ ጠርሙስ ተዳፋቱ እኩል የሆነ ወለል ላይ
ተቀምጠው አየሁ። እንግዲህ እኔ የማያቸው ከላይ ሆኜ ነው።
ከላይ ወደ ታች ሲታዩ ለአይኔ የሚታየው የተከፈተው የኪዊ ቆርቆሮ ሰፊ መሆኑና የአምቦ
ውሃው ጠርሙስ ግን ጠባብ አፍ ያለው መሆኑ ነው። ወዲያው የደረስኩበት ድምዳሜ ሰፊ
አፍ ያለው የኪዊ ጠርሙስ ላጠራቅም የፈለግኩትን አልማዝ ከአፈ-ጠባቡ የአምቦ ውሃ
ጠርሙስ ይልቅ ሊይዝልኝ ይችላል የሚል ነው።
በመሆኑም የአልማዝ ጠጠሮቼን ወደ ኪዊው አፍ መጣል ጀመርኩ። አንድ ሁለት ከያዘልኝ
በኋላ ሶስተኛውን አፈናጥሮ ጣለው። አይኔ ፈጠጠ። አወራወሬን አስተካክዬ መወርወር
አለብኝ አልኩና አሁንም ኪዊ ቆርቆሮ ላይ እንዲያርፍ አልማዜን ጣል አደረግኩ። አሁንም
ተፈናጥሮ መሬት ላይ ወደቀ።
እንዴ? አልኩና ቆይ እስቲ የአምቦ ውሃውን ጠርሙስ ልሞክረው ብዬ አልማዜን ወደሱ
ወረወርኩ። አልማዟ ጠርሙስ ውስጥ ገባች። ይህን ሳይ እስቲ ለሁለቱም ልወርውር አልኩና
ለሁለቱም እኩል ወረወርኩ። ኪዊ ጠርሙሱ አልማዜን መሬት ጣለብኝ።
የአምቦ ውሃው ጠርሙስ ግን ቀብ አደረገና ያዘልኝ። አሁንም ወደ አፈ-ጠባቡ የአምቦ ውሃ
ጠርሙስ መወርወሬን ቀጠልኩ። እንደ አፉ ጠባብነት ሳይሆን ከወረወርኳቸው አልማዞቼ
አንድም ወደ መሬት ሳይጥል ያዘልኝ።
አሀ! አልኩ። ስህተቴ አሁን ገባኝ።የኪዊው ቆርቆር እንደአፉ ስፋት ሆዱም ሰፊ ነው ብዬ
አስቤ ነበር። የአምቦ ውሃው ጠርሙስ ደግሞ አፉ ጠባብ ስለነበር ሆዱም ጠባብ መስሎኝ
ነበር። አይኔን ሰፋ ጠበብ እያደረግኩ ሁኔታውን ለመረዳት ሞከርኩ። መጨረሻ ላይ በደንብ
ገባኝ። ለካስ የአፈ-ሰፊው ኪዊ ቆርቆሮ ወለል በጣም ቅርብ ነው።
ለዚህ ነው የተወረወረውን አልማዝ መልሶ አሽቀንጥሮ የሚተፋብኝ። የአምቦ ውሃ ጠርሙሱ
ግን ጠባቡን አፍ ላለመሳት ተጠንቅቄ አልማዜን ስጥል ብዙ ሰአት ቢፈጅብኝም ምንም
አልማዝ ወደ ውጭ አልጣለብኝም። ሆዱ ሰፊ ነው።
በርግጥ ሰፊ አፍ እና ሰፊ ሆድ ያለውን በርሜልን አውቃለሁ። ጠባብ አፍና ጠባብ ሆድ
ያለውን ባዶ የቫዝሊን እቃም እንዳለ አውቃሁ። እናም ጠባብ አፍ ያለው ሁሉ የመያዝ
አቅሙ አነስተኛ እንደሆነ እና ሰፊ አፍ ያለው ሁሉ አቅሙም በዛው ልክ ሰፊ እንደሆነ
ድምዳሜ ነበረኝ። ግን ተሳስቻሁ።
ነገርየው አፍ ባሰፋና ባጠበበ አይደለም። የሆድ ስፋትና ጥበት በአፍ ስፋትና ጥበት ላይለካ
ይችላል። ስላላወራ ምንም አያውቅም ማለት አይቻልም።
አባቶች ዝምታ ወርቅ ነው ይሉና ትንሽም መናገር እንቁ ነው ይላሉ። የሚያውቁትን ነገር ሁሉ
መለፍለፍ የሚያስገምት ነው። በተቃራኒው ዝም ዝግት ማለትም ለማንም ሲበጅ አላየንም።
ትንሽ መናገር ግን ጥሩ ነው። ከሰነፍ አያስቆጥርም። ትንሽ እንናገር።


ምንጭ☞ ትኩስ ሀሳቦች የሚወጡበት የዛሩጣ ማስታወሻ


@wegoch
@wegoch
ቫንዳም እና የቫቲካኑ ዲያቆን !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ትንሽ ዘና ማለት ነገር አምሮኝ ከፊት ለፊቴ ወደሚገኘው ባለ አንድ ፎቅ ክለብ አመራሁ። እውነቱን ለመናገር ክለብም ይሆን ካፌ ለኔ ተገቢ የመዝናኛ ቦታዎች አልነበሩም። አሁን ራሱ ምን ስል ወደ ሆቴሉ እግሬ እንዳመራ አላውቅም። ብቻ ለራሴም በማይገባኝ መንገድ የክለቡ አዳራሽ ውስጥ ተገኘሁ ። ገና መቀመጫዬና የክለቡ መቀመጫ በቅጡ ሳይገናኙ አንድ ሰጎን አንገት አስተናጋጅ መጥቶ ምን ልታዘዝ በሚል ጥያቄ ያጣድፈኝ ያዘ 🙂 አስተናጋጁ ምንም ትህትና የምትባል ነገር ያልፈጠረበት ትዕቢተኛ ነው ።
ምህ ቢራ አምጣልኝ
ምን ?
ቢራ ?
አቦ ሙዚቃው አያሰማም ምን አልክ ?
ቢራ ! (ጮክ አልሁኝ ። ) Ok ! (ጀርባውን ሰቶኝ ሄደ ) በክለቡ የተለያዩ መዳረሻዎች ላይ አይኔን ወረወርኩኝ ። ብዙ እድሜያቸው አስራ ስምንት ያልሞላ ጩጬዎች እኔ አስራ ስምንት ዓመት ቢያሰለጥኑኝ የማይገባኝን አይነት ዳንስ ይደንሳሉ ፣ ይተሻሻሉ ፣ ይላላሳሉ ፣ ያጨሳሉ ፣ ይጫጫሳሉ ። ጭራሽ ከክለቡ ሴቶች ጋር ለአጭሬ እና ለረዘምዛሜ (በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ቋንቋ 🤣🤣) ዋጋ ይደራደራሉ ። እነሱን ባየሁበት ቅፅበት ሀሳቤ ወደ ታናሽ ወንድሜ አመራ ። ታናሽ ወንድሜ ፍፁም የተለየ ልጅ ነው ። ፀባዩ ለሰፈሩ ልጆች አቃቂር በማውጣት በሚታወቁት እመት ዘርፈሽዋል ሁሉ ሳይቀር የተመሰገነ ነው ። ( በነገራችን ላይ እመት ዘርፈሽዋል እየሱስ ስትል ከሰሙ ራሱ “ቱ ! የዛች አስካለ ልጅ ሜንጤ ሆነ እና አረፈው ! መድሀኒተ ዓለምን ከዳ። መቼም ተካናዳ ለሚመጣ ስንዴ እርዳታ ብሎ ነው ።” ብለው ለሀሜት የሚጣደፉ ባልቴት ናቸው 😀 አሁን ታድያ ገና በማለዳው ከሰውነቱ የከበደ መዝሙረ ዳዊት ተሸክሞ ለጠሎት የሚጣደፈው ወንድሜና እዚህ ከእድሜያቸው በላይ የከበደ ዳሌ ለማገላበጥ የሚሻፍዱት ልጆች የአንድ ዘመን ፍጥረቶች ናቸው ለማለት ያስደፍራልን ? ከንፈሬን በሀዘኔታ መጠጥሁኝ (ምፅ ! አይነት ነገር ) ጭፈራው ቀለጠ ! ሆሆታው ደራ ! በየጠረጴዛው ላይ የውስኪ ጠርሙስ አይነት ተደረደረ ! አቤቱ ጌታ ሆይ ! እኔ እንኳ የመንግስት ስራ ከያዝኩኝ አንስቶ ውስኪ የሚባል መጠጥ በጉሮሮዬ አልፎ አያውቅም ። ከኔ በትንሹ በአራት እና አምስት ዓመታት የሚያንሱ ፈልፈላዎች ውስኪን ቀለል አድርገው ነው የሚያዙት ! የለውጡ መንግስት ያለወጠው የኔን ኑሮ ብቻ ነው ስል አጉተመተምሁ ። ይኸው ! ቀና ስል አስተናጋጁ ብላክ ሌብል ውስኪ ይዞ ከተፍ ብሏል እንዴ ? ምን አስበህ ነው ሀሎ ! ማለት ? (ገላመጠኝ ) ቢራ እኮ ነው ያልኩህ ። ብላክ ነው ያልከው ! ኸረ ቢራ ነው በህግ አምላክ ። ብላክ ነው ! ብላክ ነው ! ያልከው (ገገመ ) ጭራሽ ይባስ ብሎ በንዴት እንደ መጦፍ አደረገው ! የክንዱን ሹራብ ወደ ላይ ሰብስቦ ለቡጢ ሁሉ ይጋብዘኝ ጀመር ። ምን ሆነሀል ሰውዬ? አንተ ራሱ ምን ሆነሀል ? (እጁን አንስቶ ሊነርተኝ ሲል ከየት መጣ ያልተባለ ቦክስ አፈፍ አድርጎት መሬት ተዘረረ) ትቀይርለታለህ ! ወደህ ሳይሆን ተገደህ !!!!🙂 ቀና ስል ታናሽ ወንድሜ ደረቱን ሽሮ ክክ እንደ ተሰጣበት መሬት ገልብጦ ገጭ ብሏል ። ሁለት ትላልቅ መቀመጫ ያላቸው ቺኮች ስሩ ተሸጉጠው በወንድሜ ጀብዱ ኮርተዋል ። አይዞህ ተረጋጋ ቤብ ! ትለዋለች አንዷ እሙአ (ሌላዋ ከንፈሩን ሳመችው) እንዴ ቫንዳም ! ወንድሜ ሙቀት ተሰማው መሰለኝ ጭራሽ ሁለቴ ተገለባብጦ ፓካንድ ሰራ ። ቀኝህን ሲመቱህ ግራህን ስጥ ብሎ የሚሰብከኝ ታናሼ ቀኜ ሳይመታ የሰው ቀኝና ግራ ጉንጭ ላይ ቦክስ አሳርፎ አስተናጋጁን የጫት ተርዚና የወጠረ አስመሰለው ።
አ ውቺያ ! አይኔ እያየ ወንድሜ ለሶስተኛ ጊዜ ተገልብጦ ቆመ ። ሌላ የማላቃት ሴት መጥታ ከንፈሩ ላይ ተለጠፈች ።
እግዚኦ ስምንተኛው ሺህ !🙂

@wegoch
@wegoch
@wegoch
~~ ሞካሪና አስሞካሪ ~~
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።" አልኩት
"እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?"
"እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……"ድንግል መሆን አልፈልግም።" አልኩት
"ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? " "አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ።
ወራት ነጎዱ……… "ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ ሰማሁ። መሞከር ፈልጋለሁ።" "አይ አይ አይ…… ጥሩ አይደለም ማሬ ስሞትልሽ አትሞክሪ።" አለኝ እያንገፈገፈው "ልንገርህ ብዬ እንጂ መሞከሬ አይቀርም። እነቤቲ ዛሬ እንቅማለን ብለዋል…… "ሳልጨርስ ቀድሞ "እሺ በቃ ፍቅሬ እሺ…… መሞከር ከፈለግሽ እኔም አብሬሽ እሞክራለሁ። ከኔጋ ቃሚ…… " ጫቱንም ፍራሹንም ሰጠኝ።…… መቃም በፈለግኩ ቁጥር ከስራ እየቀረ አብሮኝ ቃመ። ወራት ነጎዱ………"ልመረቅ ስለሆነ ስክር ማለት እፈልጋለሁ ክለብ ውሰደኝ" አልኩት……
"እሺ እንደፈለግሽ ሁኚ እጠብቅሻለሁ።" አለኝ…… መጠጡን ቀዳልኝ…
እንደፈለግኩ ሆንኩ……
ሰዓታት ነጎዱ……
"ማጨስ እፈልጋለሁ።"
"እማ ስካሩ አይበቃም? ፕሊስ ጭሱ ይቅር? "ለአፉ አለኝ እንጂ የፈለግኩትን
ሳልሞክር ማቆሚያ እንደሌለኝ ያውቃል።
"እሺ ገዝቼልሽ ልምጣ? " "አልፈልግም የተጨሰ ግማሽ የደረሰ ሲጋራ ነው ማጨስ የምፈልገው።… እንደውም ያን ሰውዬ ስጠኝ እለዋለሁ።" "እሺ እሺ በቃ የተጨሰ አይደል ማጨስ የምትፈልጊው? በቃ እኔ አጭሼ ሰጥሻለሁ።…… ከሌላ ሰው ከንፈር ተውሰሽ አታጨሺም! " አጭሶ ሰጠኝ። አጨስኩ።… እስክመረቅ በጨፈርኩ ቁጥር የተጨሰ ሲጋራ አቀበለኝ። ዓመታት ነጎዱ…… ብዙ ዓመታት…… እንደተመረቅኩ ከሃገር ወጣሁ።……
ተራራቅን…… ከጊዜ በኋላ መገናኘት አቆምን።… አገባሁ…… ወለድኩ…… ለበዓል ወደሃገር ቤት ተመልሼ ሳለሁ መንገድ ላይ አየሁት።…… ደነዘዝኩ። ያ ሊነኩት የሚያሳሳ ቆዳው ከስሎ…የሚያንጠራራ መለሎ ቁመናው ጎብጦ… የሚያኮራ ደልዳላ አካሉ ኮስምኖ… አይሆንም እሱ አይሆንም! "አቁምልኝ! አቁምልኝ! "ጮህኩኝ ባሌ ላይ… ዘልዬ ወረድኩ እና እጁን ይዤ አስቆምኩት። "እማ አንቺ ነሽ ስካሬ እያስቃዠኝ ነው? " አለኝ ከቃላቶቹ እኩል የርካሽ መጠጥ ጠረን እየተፋ "አባ አንተ ነህ? ምን ሆነሃል? በየሱስም ምን አገኘህ? ታመህ ነበር? በየሱስ ስም…… ደህና ነህ? ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?" "አንቺ እማ! አንቺ ነሽ የተከሰትሽው! ሌላ ማን አለ አንቺ "… የሆነ የአዳም ረታ መፅሃፍ ውስጥ ያለሁ ገፀ ባህሪ የሆንኩ መሰለኝ። እንጂማ እኔ በእውነታው ይህችን ሴት ልሆን አልችልም። በሱስ ምክንያት በተደጋጋሚ አማኑኤል ሆስፒታል እንደነበረ ነገረኝ። በዛ ምክንያትም ስልክ ኖሮት ስለማያውቅ
ላገኘሁ እንዳልቻልኩ አብራራልኝ……
"እማ አንቺ ማለት የምትበር ቢራቢሮ ነበርሽ…… ነፃ የሆንሽ… ነፃነትሽን
የምትወጂ… ካልሞከርሽ የማታረጋግጪ…… ሁሉን ሞከርሽ እኔን ጨምሮ ሁሉን ተውሽ! ሁሉን አስሞከርኩሽ ከሁሉ ተጋባሁኝና ቀረሁ። " አለኝ።
አይ አይሆንም የአዳም አንዷ ገፀባህሪማ ሆኛለሁ።…… ነፃነት? ሌላውን የገደለ
ነፃነት? በሌላው ባርነት ላይ የቆመ ነፃነት? የአባን ገፅ ያከሰለ ነፃነት?
……… አይሆንም ውሸት ነው። እኔማ እውን አይደለሁም…

@getem
@getem
@paappii

#meri_feleke
ይሄን ሰው ምን ነካው ?
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ከእንቅልፌ በነቃሁ ቅፅበት ታናሽ ወንድሜ ከአልጋዬ ግርጌ ቆሞ ውዳሴ ማርያም ሲደግም አየሁት ። አይኔን ባለማመን ደግሜ ፣ ደጋግሜ አሻሸሁት ። ራሱ ታናሽ ወንድሜ ነው ! ያ መጠጥ ከማብዛቱ የተነሳ ዛሬ ምንም አልቀመስሁም አንድ ካሳ ቢራ ብቻ ነው ብሎ የሚሽኮረመመው ፣ ጫት ቅሞ ጉንጩ ውስጥ ሲወጥር የዛች የትግሪኛ ዘፋኟን ሪች መቀመጫ😜 የሚያሳህለው ፣ የሺሻ ጎማ በመጎተት ከኤርታሌ እስለ ሱማሌ የሚሰማ ቱርርርርርር የሚል ድምፅ የሚያወጣው ወንድሜ ነው እየፀለየ ያለው 🙂
የማየው ነገር ህልም እንዳይሆን ተመኘሁ ። ደስ ሲል ደግሞ ህልም አይደለም ! እናቴ በሁኔታው ተገርማ አይኖቿ ሲበሩ ይታወቀኛል ። በሰፈር ሽማግሌ ፣ በንሰሀ አባት ፣ በፖሊስ እና ፌደራል ተሞክሮ ጠባይ ሳይገዛ የኖረው ወንድሜ እነሆ በመጨረሻም በራሱ ጊዜ እንዲህ ለፈጣሪው ተንበረከከ ! አቤት ጠሎት ! አቤት ስግደት ! እጁን እያጣመረ ፣ ከወገቡ ሸብረክ እያለ ሲሰግድ ላየው ዛሬውኑ ጣዲኡ አቡዬን ታልሆንኩ ብሎ የወሰነ ነበር የሚመስለው ።
ደግሞ ከፀሎቱ ብኋላ በላስቲክ አድርጎ ውጭ ካስቀመጣት ፀበል ተጎነጨ ። አቤቱ ማረን ጌታችን አለ ! በስልኩ የቴዎድሮስን መዝሙር ከፈተ !
ያ በማይክል ጃክሰን ዘፈን የቤታችንን ሴራሚክ ያነቃንቅ የነበረው ፣ የሰፈሩን ከለቦች ከራሱ ሸሚዞች በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀው ፣ ዲጄ ልሆን ነው ብሎ ላፕቶፕ በጀርባው አዝሎና ጠጉሩን አንጨባሮ ሲንበጫረቅ የኖረው ወንድሜ መዝሙር አዳመጠ ። ደግሞ መዝሙሩን በቅጡ ባያውቀውም በስሜት ነበር የሚዘምረው ።
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን ! የሚለውን መዝሙር
እናታችን ነሽ ማርያም ባንቺ አይምጡብን ! 🤣🤣እያለ ይዘምራል ። ኽረ ይሄንስ ማን አየበት ? ይሁን ነው የሚያስብለው ! ደግሞ ባንቺ አይምጡብን የሚለው ባንቺ አይምጡብኝ የምትለው የናቲ ማን ሙዚቃ ትውስ እያለችው እንደሆነ እናውቃለን ። ቢሆንም ዋናው ለመዘመር በስሜት መመሰጡ ነው ። ከሀሽሽ ጡዘት ወደ መዝሙር ምሳጤ መግባት እጅጉን አስደማሚ ነገር ነው ።
ጭራሽ ይባስ ብሎ ወንድምዬ እስቲ ተነስ እና እምነት ልቀባህ ብሎ ተመለከተኝ ።
"ማታ ራሴን አሞኛል ብለህ አልነበረምን ?🙂 ና ልቀባህ ትድናለህ ! "
ጆሮዬን አላመንሁትም ። በሌባ ጣቴ ኮረኮርሁት ። የሆነ ቢጫ ኩክ ዘኝዬ ወጣሁ ። ታናሼ ያ “ ጀለስ እስቲ ለውሎ ገንዘብ ቦጭቅ “ የሚለኝ ወንድሜ እምነት ልቀባህ አለኝ ።
ተነስቼ ግንባሬን አቀረብሁለት ። በስመ ስላሴ አንጣረ ገፁን አማትቦ ቀባኝ እና የስራ ሰዓት ደረሰብኝ ብሎ ጥሎን ተፈተለከ ።
ቅፈላ ይል የነበረው ወንድሜ ስራ ሲል ............
እናቴ የምታየውን ባለማመን እንደ ፀሀይ የበራ አይኗ ይበልጡን ቦግ አለ ። እየሱስ ዳግም ሊመጣ ነው አልያም ዓለም አሁኑኑ ልትጠፋ ነው ብላ የሰጋችም ነገር መስለኝ ።
ወድያው ከሰዓታት በኋላ አንዲት ሸጋ መልከ ግቡ ወጣት ቤታችን መጣች !
አመጣጧ ወንድሜን ፈልጋ ነበር ። "ማታ ሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ስላለ ወንድምህ እንዳይቀር ንገረው" አለችኝ ። ዓይኖቿ እንደ ቤተክህነት ጉልላት የተንጎማለሉ ናቸው ። ፈገግታዋ ገዳይ ነው ። 😍
እሺ እነግረዋለሁ !
አመስግናኝ ወጣች ። ዝቅ ብላ አመስግኛለሁ ስትል ከመሬት ላይ ኮብልስቶን ነክሳ ለመመለስ ምንም ያህል አልቀራትም ነበር ። አቤት ውበት ! አቤት ትህትና !
ወንድሜ እሷን አይቶ መሆን አለበት ሀይማኖተኛ ለመሆን የወሰነው ።
ስምሽን ማን ልበለው ?
ሊያ !
ሊያ ! እጅግ ደስ የሚል ስም ።
በድጋሚ አጎንብሳ (ይቅርታ መሬት ልሳ 😀) አመሰገነችኝ ። ጀርባዋን ሰጥታኝ ስትሄድ እስከ መታጠፊያው ድረስ በአይኔ ሸኘኋት ።
አመሻሹ ላይ በጠባቧ የቤታችን በር በኩል አንድ ዘግናኝ ሲጃራ የተቀላቀለበት የአንቡላ ሽታ ሰተት ብሎ ገባ !
አቤት ቅርናት ! አቤት ግማት !
እናቴ የዚህ ሽታ ክፉ ትርታ በልቧ አለባት ። ህይወታችንን አመሳቅሎ እናቴን ተስፋ ያስቆረጣት ይህ አይነቱ ግማት ነው ።
ታናሽ ወንድሜ ጥንብዝ ብሎ ሰክሯል ።
አይ ሰይጣን ! ደግሞ ተመልሶ ሰፈረበት ። እናቴ ተስፋዋ ሲጠልም እና በደስታ ሲፍነከነክ የዋለ ፊቷ ክስም ሲል ይታወቀኛል ።
"አንተ ደደብ አህያ ከበሩ ላይ ዞር በልልኝ አለኝ !"
ያ ሁሉ የጠዋት እንክብካቤ አይኔ እያየ ገደል ገባ ። ውሻ አለኝ ቀጥሎ !
እልሄን ውጬ ዝም አልኩት ።
"ሊያ ! እኔ እንደዛ እያፈቀርኩሽ ሌላ ጓደኛ አለኝ ልትይ አይገባም ነበር !" ልትፈርስ አንድ ሀሙስ የቀራት የቤታችን ግድግዳ በወንድሜ ቡጢ ተነረተች ። የእናቴ ልብ ከግድግዳው እኩል ሲወዛወዝ ተሰማኝ ።
ምስኪን እማዬ !!🙂

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚

“ቆመን ጠበቅናቸው፤ ጥለውን
አለፉ”


“ከብረው ይቆዩኝ ከብረው
ባመት ወንድ ልጅ ወልደው!
አምሣ ጥገቶች አሥረው…!”
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አሳማ፤ በጐች በብዛት ወደተሰማሩበት የግጦሽ
መስክ ጐራ ይላል:: እረኛው “ምን ሊያደርግ መጣ” በሚል ጥርጣሬ
ያስተውለዋል፡፡ አሳማው ወደ በጐቹ ለመቀላቀል ይሞክራል፡፡ እረኛው ያደፍጥ
ያደፍጥና ፈጥኖ ተጠግቶ አሳማውን ይይዘዋል፡፡ ከዚያም፤
“ለምን መጣህ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
አሳማውም፤
“ከበጐች ልመሳሰል” ሲል ይመልሳል፡፡
“ተመሳስለህስ?”
“እንደ በጐች ልኖር”
“ኖረህስ?”
“እንደ በጐች እንድታኖረኝ!?”
“አንተን እንኳን ለዚህ አልፈልግህም አያ አሳማ”
“እንግዲያ እንዴት እንድኖር ትፈልጋለህ?”
“አይ፤ ኑሮው ይቅርብህና ወደ ተገቢው ቦታ ብወስድህ ነው የሚሻለው፡፡”
ብሎ፤ እየጐተተ ወደ እንስሳ ማረጃው ቦታ ይዞት ሊሄድ ይጐትተዋል፡፡
አሳማው፤ መወራጨት፣ መንፈራገጥ፣ ማጓራት መጮህ ይጀምራል፡፡
ይሄኔ ከበጐቹ መካከል አንዱ ብቅ ይልና፤
“አያ አሳማ?” አለ በለጋስ ጥያቄ ቅላፄ፡፡
“አቤት” አለ አያ አሳማ፡፡
“ምንድነው እንደዚህ የሚያስጮህህ? እኛ ሁላችንም ’ኮ በጌታችን
እየተጐተትን ወደ ሌላ ቦታ እንወሰዳለን፡፡”
“ነው፡፡ ግን የእኔ ይለያል” አለ አሳማ፡፡
“እንዴት?” አለ በጉ፡፡
“አይ አያ በግ፣ የሁለታችን ለየቅል ነው!”
“እኮ እንዴት?”
“ጌታህ አንተን የሚፈልግህ ከቆዳህ ሱፍ ለመሥራት ነው፡፡ እኔን የሚፈልገኝ
ግን ለሥጋዬ ነው - ጠብሶ ሊበላኝ”
አያ አሳማ፤ እንደፈራው እየተጐተተ ሄደ፡፡
***
በአዲሱ ዓመት ከእንዲህ ያለ ምርጫ ይሰውረን፡፡ ለጥብስ ይሁን ለሱፍ፣ ዞሮ
ዞሮ መታረድ ላይቀር ምርጫውን በቅናት መልክ ከማሰብ ይሰውረን፡፡
አራጁንም መሆን ታራጁንም መሆን በፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ አሰቃቂ ነው፡፡
“አውራ ዶሮ ጮኾ መንጋቱን ነገረኝ
ዛሬ ማታ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ”
እንዳለው አንዱ የእኛ ገጣሚ፤ የታራጅና አራጅ ምፀት የምንነጋገርበት
እንዳይሆን አዲሱ ዓመት ልቡን ይስጠን፡፡ አዲሱን ዓመት የእኩልነት
ያድርግልን!
“ይገብር ካላችሁ ዝንጀሮም ይገብር
የንጉሥ አይደለም ወይ የሚጭረው ምድር” የምንልበት ዘመን ይሁንልን!
“ከብረው ይቆዩኝ ከብረው
ባመት ወንድ ልጅ ወልደው
አምሣ ጥገቶች ወልደው…”
ስንባል ሞቅ የሚለን፣ ከጭንቅ የሚገላግለን የአዎንታዊነት ምርቃት
እንዲሆንልን እንጽና፣ እንጽናና፡፡
የአቦ - ሰጡኝ ሳይሆን የትግል ዓመት እንዲሆንልን ልብና ልቡናውን ይስጠን!
የችግር ማውሪያ ሳይሆን የመፍትሔ መፈለጊያ ዘመን እንዲሆንልን አንጐሉን
ይስጠን!
የመለያያ ሳይሆን የመዋሃጃ፣ የመተሳሰቢያ ዘመን እንዲሆን በጐ አመለካከቱን
አያጨልምብን!
ዕድሜ የጊዜ ሳይሆን፤ የመጠንከር አቅም - የመገንባት፣ እርምጃችንን
የማትባት ይሆንልን ዘንድ እርዳታው አይለየን፡፡
ሽቅብ እየተመነደግን እንጂ ቁልቁል እያደግን እንዳንሄድ፣ ድላችንን
አስተማማኝ ያድርግልን፡፡
ፀሐፊዎቹ እንዳሉን፤
“አንድ ግዙፍ የብርቱካን ዛፍ እናስብ፡፡ በስሎ የተንዠረገገ ብዙ ብርቱካን
አለው፡፡ ወደ ታች፣ በሰው ቁመት ያሉትን ብርቱካኖች በብዛት ለቀምኳቸው፡፡
ከዚያ በላይ ያሉትን ለመቅጠፍ ቁመት አጠረኝ፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ
የብርቱካን እጥረት አለ ልል ነው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን አንድ አዋቂ ሰው
አንድ ቴክኖሎጂ ፈጠረ፤ መሰላል የሚባል፡፡ ወደ ማይደረሱት ብርቱካኖች
መድረሻዬን አበጀልኝ:: ችግሬ ተቃለለ፡፡ ቴክኖሎጂ ወደ ኃይል ምንጭ
መዳረሻ/ ማግኛ ስርዓት ነው፡፡ ያኔ እጥረት ያልነው ነገር፣ አሁን በሽ - በሽ፤
ነው ያሰኘናል፡፡” (“አበንዳንስ”፤ በፒተር ዲያማንዲስ እና ስቲቨን ኮትለር)
ስለ ዕጥረትና ስለ ዕጦት የምናስብበት ዓመት እንዳይሆን መሰላሉን
የሚሰጠን አዋቂ ይዘዝልን፡፡
በሁሉም ዘርፍ ለድል ያብቃን፡፡
የጀመርነው ለውጥም ይቅናን፡፡ ኑሮም ይታደገን!
በጐ እንድንመኝ፣ በጐ እንድናገኝ፤ በጐ እጅ ይስጠን!
“አይቀጭጭ ትልማችን፣ አይራብ ህልማችን!
አይሙት ሐሞታችን፣ አይቃዥ ርዕያችን!
አይንጠፍ ጓዳችን፣ አትምከን ላማችን!
አይክሳ ቀናችን፣ አይላም ጉልበታችን!!
ከሁሉም ከሁሉም አይጥፋ ሻማችን!”
ብለን የምንመኝበትን የህይወት ፀጋ አይንሳን!!
በአንድ ወቅት ታዋቂው የእስፖርት ሰው ይድነቃቸው ተሰማ፣ ሱዳን ከእግር
ኳሱ አምባ ጠፍታ ከርማ ወደ ሜዳ ስትመለስ ያሳየችውን ድንቅ እርምጃ
በተመለከተ የሰጡት አስተያየት፤ ማስገንዘቢያ፣ ማስጠንቀቂያና የእግር ኳሱን
ሂደት ማሳያ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ደግሞ ዋና ማሳሰቢያ ነው!
“ቆመን ጠበቅናቸው ጥለውን አለፉ!” ነበር ያሉት፡፡ ከዚህ ይሰውረን!
እንደ አዲስ ዓመት ምላሽ “ከብረው ይቆዩን ከብረው” የምንባባልበት
እንዲሆን እንመኛለን”
መልካም አዲስ ዓመት!!

#ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ


@wegoch
@wegoch
‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የኪነ
ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

የኢፌዲሪ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ከተስፋ ፊልም
ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በተፈጥሮ፣ በዘመንና የሰው ልጆች
ግንኙነትና መስተጋብር ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ››
የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በብሄራዊ
ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ላይ #ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ሥነ-ጽሑፍና ተፈጥሮ፣
#የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬ ስብሃት ሙዚቃና ተፈጥሮ፣# ሀኪም አበበች
ሽፈራው የባህል ሕክምናና እፅዋት፣ #ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ኢስላምና
ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ሽብሩ ተድላ ደግሞ በእንስሳት ዙሪያ፣ #ደራሲ አለማየሁ ዋሴ
(ዶ/ር) ቤተ ክርስቲያንና ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ታደሰ ደሴ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ
አለማት በእንስሳትና በእጽዋት አያያዝና ተሞክሯቸው ዙሪያ በሚል
ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን #ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ #ደራሲና ጋዜጠኛ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ #ፕ/ር ሰብስቤ ደምሴ፣ በተመሳሳይ ርዕስ ስራዎቻቸውን
ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
#ገጣሚ ረድኤት ተረፈና ገጣሚ #ተዋናይ ተፈሪ አለሙ ግጥሞቻቸውን የሚያነቡ
ሲሆን፣ ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የተሰኘ የ15 ደቂቃ አጭር ተውኔት
እንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ገልጸዋል::

@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚


“ ትዕግሥት ትመስለዋለች። ስታጠና እንደ ነበረችው ረዥም ቀሚሷን ለብሳ፥ በነጠላ
ጫማ አጭር ቁመቷ ይብሱን ተጋልጦ፥ በፈገግታ ጉንጮቿን እያሠረጎደች አቤል መኝታ ቤት
ድረስ በምሽት ከተፍ!
“ምነው አቤል? ሰው ለምን ታስቸግራለህ? እኔንስ ለምን በፍቅር ታሠቃየኛለህ? ለምን
ግልፅ አትሆንልኝም? ማፍቀር'ኮ ነውር አይደለም” ስትለው …
አቤል ግልፅነቷ እየገፋፋውና የተከዘው ገፅታዋ እያሳዘነው፥ “እኔ ምን አደረግኩሽ ታዲያ?
ደግሞ ተበዳይ አንቺ ሆንሽ እንዴ? እኔ ምን ያህል እንደ ተቃጠልኩ ውስጤን ገልጠሽ
ባየሽው!” አላት።
“አትዋሸኝ አቤል! እውነቱን ንገረኝ። ስታየኝ ግንባርህን የምታኮማትርብኝ፥ ዘግተኸኝ
የምታልፈው ለምንድነው? ፍቅር ነው ጥላቻ?”
“የጥላቻ ነገር ለምን ታነሻለሽ? በእኔና በአንቺ መሐል ጥላቻን ምን አመጣው? የማደርገው
ሁሉ የፍቅር ነው።”
“ታዲያ እንዲህ በዕውር ፍቅር እንዴት እንዘልቀዋለን፥ አቤል? ሁለታችንም ውጥረት ላይ
ያለን ተማሪዎች ነን። እኔን የገና ማዕበል እየጠበቀኝ ነው። አንተም መመረቂያ ዓመትህ
ነው። ግልፅ ካልሆንን እኮ ሁኔታችን ለሁለታችንም ግብ መሰናክል ነው።” …
… ከእንቅልፉ ባነነ። እንቅልፍ ዓይን መጨፈን ብቻ በሆነና፥ ከትዕግሥት ጋር ካገናኘው
ሕልሙ ላለመንቃት ዕድሜ ልኩን አይኑን በጨፈነ ምን ነበረበት! …”


ሰመመን | ከሲሳይ ንጉሡ | 1978 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 113-117

ውብ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
"ጤና ይስጥልን" ልዩ እትም ለእናንተ

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 17/01/2013
።።።።። መደረቢያ ።።።።።።።

ከዛ ከኛ ቤት ከባሰ አመዳም ደሃ ጎረቤታችን ቦቸራ ሳረግዝ…… ለአባዬ ውርደቱ ሆንኩ። በየሴሚስተሩ አንደኛ እየወጣች ስሙን የምታስጠራው ልጁ በአንድ ቀን ስህተት አፈር ከድሜ ገባች።
… ወራት ነጎዱ… ትምህርቴን ከ11 ተውኩት። ልጄን ገጠር አክስቴጋ ሄጄ
ወለድኩ።…… የአባዬ ውርደት የነበረው ሌባው ወንድሜ የቤቱ ኩራት ተባለ።……
ሰርቆ እቃ ቢያመጣ እንጂ ልጅ ይዞ አልመጣማ……!!! ከሩቅ ያኔ ቀጥሎ……
እኔ ነኝ ያለ በቅሌቱ መንደር ያወቀው ሀብታም እጄን ለትዳር ጠየቀ። ከነ ልጇ
አንቀባርሬ አገባታለሁ አለ። ደስተኛ እሆን እንደሆነ አይደለም የተጠየቅኩት። ሽማግሌዎቹ ከቤት እንደወጡ ምን ያህል እንዳኮራሁት ነበር አባቴ የነገረኝ። …… ጊዜው ግድ አለው?… ወራት ነጎዱ… ድል ባለ ሰርግ ተዳርኩ።… ልጄን እና የበደነ ልቤን ይዤ ብዙ ቅምጥ ያለው ባሌ ቤት ገባሁ። ገነቴ እኔ ጭኖች መሃል ተለጠፈች እንጂ በእድሜ ቁጥሬ እንደገባኝ የአባዬ መደረቢያ ናት። በሱ ሚዛን የማይሆን ሰው አክሱም ሲጎበኛት " ያለእናት አሳድጌሽ አዋረድሽኝ። የሰፈር መሳለቂያ አደረግሽኝ። ማቅ አለበሽኝ።" እያለ ነጠላ ወጉን የሚለቅባት ፤ በሱ ልኬት ክብሩን የሚመጥን ሰው አክሱም
ሲጎበኛት "አኮራሽኝ ልጄ… ወግ ማዕረግ ክብር አሳየሽኝ።" እያለ ድርብ ወጉን
የሚጠርቅባት…… ክብርም ሆነ ማቅ የትኛው የሰውነት አካል ላይ እንደሚንሳፈፍ ባይገባኝም። የእኔ ገነት ግን የአባዬ አንገት ላይ ጣል እንደሚደረግ መደረቢያ ትመስለኛለች። አንዴ ማቅ ሆና የምታንቀጠቅጠው … ሌላ ጊዜ ክብር ሆና የምታሞቀው…… ቅርብ ያኔ ለታ… ሀብታሙ ባሌ በወንጀል ታስሮ የምኖርበትን ቤት ጨምሮ ንብረቱ በሙሉ ተወርሶ ወደ ቤት ስመለስ። አሁንም አባቴን የሰፈር መጠቋቆሚያ አደረግኩት። ትንሽ ከአሁን ቀድሞ……
ልጄን ጥዬ አረብ አገር ሄጄ ብር መላክ ስጀምር። ድሮምኮ ልጄ መኩሪያዬ ናት
አለኝ አባቴ………… ጊዜው አብሮ ምን እንደሚያንገዋልል መች ቅም ይለዋል?… አመት ነጎደ…… የምሰራበት ቤት ሴትዮ በቃሽኝ ባሌ ዓይኑ አርፎብሻል ብላ
አባረረችኝ።…… ስራ ማግኘት አልቀለለኝም። ውበቴን ያየ ደላላ በሙሉ አረብ ባጫውት ብዙ ብር እንደምሸቅል መከረኝ። አባቴን የምጠላው ጊዜ ይበልጣል።…… ግን መገላገል በማልችለው ዓይነት ልክፍት የሱ ኩራት መሆን እፈልጋለሁ። አሁን ደግሞ ከእርሱ በተጨማሪ የልጄ ኩራት ለመሆን ነፍሴን እሰጣለሁ። አሁን እለት……
አንደኛ ደረጃ ሸርሙጣ ሆንኩ።…ለአባዬና ለልጄ ክብሬን መሰረት ድንጋይ ጥዬ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገነባሁ።…… አባቴ ክብር ደረበ።…… ከአንገቱ ቀና ብሎ
በኩራት ሰፈር ውስጥ ተንቀዋለለ።… "ልጄ ካሰችኝ! ፐ ከወለዱ አይቀር አንድ
የእኔን ልጅ ዓይነት ነው እንጂ… " እያለ የወግ አልበሙን ለቀቀ።……ክብሬን ደጋግሜ መሬት አንጥፌ ለልጄ በቋሚነት ወጪ የሚሸፍንለት ሚኒባስ ገዛሁ።………
በቃኝ አልኩ። ለአባቴ ክብር ልደርብ እኔ ደጋግሜ ተዋረድኩ። የእርሱ ኩራት ለመሆን ደጋግሜ ተናቅኩ።…… በቃኝ አልኩ። ያለኝን ይዤ ሀገሬ እገባለሁ። በቀረኝ ዘመን ራሴን ላክብር…… ደወልኩ።
"አባዬ ልመጣ ነው። ጠቅልዬ ልመጣነው።… ለልጄ እናት ልሁነው።… ባለኝገንዘብ የሆነውን ሰርቼ እንኖራለን።"
"እንድች ብለሽ እግርሽን ወዲህ እንዳታነሺ…… ተዋርደሽ አዋረድሽኝ!! እዛ ምን እንደምትሰሪ ጉድሽን የአይናለም ልጅ መጥታ ነገረችኝ።…ቤት አለኝ ብለሽ
እንድች እንዳትሞክሪያት ነው የምልሽ…… "
……... ጨርሰናል!!………

@wegoch
@wegoch
@paappii
መማር ያሳፍራል ፣ ሀገር ያኮላሻል !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ጋሽ አድማሱ ሁሌ የሚናገሯት ነገር ነበረቻቸው ። "ሰውን ደደብ አትበሉ ... ሰው ደደብ እና ደንቆሮ ብሎ መሳደብ ነውር ነው።" ይላሉ :)
ሰው ደደብ ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ጌቱን ከሆነ ብቻ ነው ብለው ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፉተታ ያክሉባታል :)
በርግጥ ጋሽ አድማሱ ልክ ናቸው ። ሰው ደደብ ተብሎ አይጠራም እንጂ ጌቱ ግን አንድ ክፍል ተማሪ ሙሉ ከመቀመጫው ተነስቶ ያጨበጨበለት ደደብ ነበረ ።
ያኔ ተማሪዎች ሳለን " አበበ በሶ በላ " ተብሎ መነበብ የነበረበትን ዓ.ነገር "አበበ በሶ በዳ" ብሎ በማንበቡ የተነሳ አማርኛ መምህራችን እንዳይሞትም እንዳይድንም አድርገው የደበደቡት ነገር መቼም አይረሳኝም ።
ጌቱ ከዛ ግርፊያ በኋላ ጭራሽ ይባስ ብሎ ድንጉጥና የለየለት ነፈዝ ሆነ ። ወላጅ በየዓመቱ አነሰ ቢባል አስራ አራት ጊዜ ያመጣ ነበር ። በስተ መጨረሻም አባቱ መመላለስ ቢታክታቸው አዲስ ለትምህርት ቤቱ ብዙም የማይርቅ ቤት ተከራይተው እንደነበር ታሪክ ያስታውሰናል (ምን ታሽሟጥጣለህ? ፅሁፌን ለማጣፈጥ የፈጠርኳት ግነት መስሎህ ከሆነ ተፎግረሀል ዝናዬ :) )
እናም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ትምህርት ለሱ እንዳልተፈጠረ መልዐክ ሹክ ያለው ጌቱ ትንሿ ከተማችንን ለቆ በረሀ ለስራ መግባቱን ሰማን። ብዙዎቻችን የክፍሉ ተማሪዎች ገና በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ከገዛው ፓስቲ ላይ አንድ አንድ ጉርሻ የሚለቅብን ጌቱ ከመጥፋቱ በላይ የፓስቲው ትውስታ ብቻ እያናወዘን የመጀመርያ ድግሪ ትምህርታችንን ቋጨን ።
ጋሽ አድማሱ ከዚህ ሁነኛ ክስተት በኋላ ታድያ ዘወትር ከግቢያቸው ፊትለፊት ካለችው ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የጠዋት ጠሀያቸውን እየኮመኮሙ ያገኙትን ፈልፈላ ሁሉ ትምህርት ካልወደዳችሁ እንደዛ የመዝገቡ ልጅ( ጌቱን ማለታቸው ነው 😊!) ...በረሀ ትገቡና አንድ ደም ያቅበዘበዛት ወባ ነድፋ በሽተኛ ሆናችሁ ትቀራላችሁ እያሉ ይመክሩ እንደነበር ትዝ ይለኛል ።
እነሆ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የዓለም ሁኔታ እንደ ቂጣ ተገልብጦ ቁጭ አለ ።
እኛ ብዙዎቻችን ተምረን የመንግስት የወር ጡረተኛ ባርያዎች ስንሆን ጌቱ ግን የራሱን ግዙፍ የንግድ ማዕከል ከፍቶ የናጠጠ ቱጃር መሆኑን ሰማን ።
ለመካሪ ዘካሪያችን ጋሽ አድማሱ የአረቄ ብር ለመስጠት ሶስት ጊዜ ከራሳችን ጋር ረዥም ስብሰባዎችን የምንወስደው ከጌቱ ይልቅ እኛ ኢንጅነርና ዶክተሮቹ ነበርን ።
ከረዥም የመጥፋት ዓመታት በኋላ የተመለሰው ጌቱ ሀገር ቤት በገባን ቁጥር የመንገድ ሊፍት እየሰጠና በየመሸታ ቤቱ ውስኪ በማውረድ ሞራላችን ላይ ዳርት መጫወቱን ቀጠለ ።
ጋሽ አድማሱም አነሰ ቢባል በቀን በትንሹ የሁለት መቶ ብር ድጎማ ከጌቱ ይደረግላቸው ጀመር ።
በዚህ በመስቀል ወቅት ታድያ ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ሀገር ቤት የሄድኩት እኔ ከኋላዬ "አንተ ደደብ ! እዚህ ድረስ መተህ እንኳ እኔን ለመጠየቅ ኮራህ አይደል ?" የሚል ሰቅጣጭ ድምፅ ሰምቼ አንገቴን አሽከርክሬ ዞር ብል ጋሽ አድማሱ ጥርሳቸውን በረዥም ችፍርግ እየፋቁ ሲላላጡብኝ አየኋቸው ።
"ምን እንደ አህያ ወ*ላ ይገትርሀል? ነፈዝ ! ... ድድብናህ አሁንስ ቅጥ አጣ ! ምናለ ከዛ ጎበዝ ጌቱ ሰው መጠየቅን ብትማሩ? "
በድጋሚ የምሰማውን ድምፅ ማመን አልቻልኩም ።
ዘግቻቸው መንገዴን ቀጠልኩ ።
ለመጀመርያ ጊዜ በመማሬ የተፀፀትኩባት ቀን ዛሬ ሆነች :)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
~~ ነዋሪ እና አስነዋሪ ~~

"ዛሬ ጋባዥ እኔ ነኝ! " እላለሁ ሁሌም። እንደተገረፈ ሰው ምን ያስለፈልፈኛል?
"ወየው ሂዊዬ አንቺ ማለትኮ…… " ይሉኛል።…… በቃ ይኸው ነው!!…… ያለኝን እታጠባለሁ። ያቆለጳዽሱኛል። ዘወር ስል ስጋዬን ዘልዝለው እንደሚያሰጡት አውቃለሁ። አንዷ ከመሃከላችን ሳትኖር አብሬያቸው እንደማደርገው። ከአንዱ የቦሌ ውድ ካፌ ወደ ሌላው እየተገላበጥን ራሳችንን መዘረር፤ በማያስቀው ሁሉ ጥርስ ማስቸገር ፤ ባስ ያለ ቀን መቃም ፤ መረር ያለ ቀን ቁርስ ተገባብዞ እየተላዘዙ መለያየት ፤ ልብ የተገዛ ቀን ደግሞ ከአንዱ ሞል ወደአንዱ
እየተንዛለሉ መሸመት…… ስለያቸው ፀጉሬን እየነጨሁ እበሳጫለሁ። ሁለተኛ እላለሁ። ምን ቀን ነው የገጠምኩት…… አማርራለሁ።…… እቤት የዋልኩ ቀን… በእነሱ ሂሳብ ወይ ጠብሾኛል አልያም ዥልጥ እየሆንኩ ነው። ያቺ የፊቷን አመድ በዘመናዊ አመድ የምታብሰው ሀና "ሂዊ እኮ ድሮም ከኛ ጋር ውላ እንጂ ታጥቦ የተቀሸረ እርጥብ ናት… ሃሃሃሃሃ ብር ብቻ!… እስኪ ቤተሰብ እንቀያየር? " ትላለች…… ይኸው ዥልጥ አለመሆኔን ለማስመስከር እዠለጣለሁ። ብሄራዊ ውጪ ላይ ተቀምጬ ያዘዝኩትን ጥብስ ፍርፍር እየበላሁ። " ዛሬ የመጨረሻዬ ነው! ቢቀርስ? ጓደኛ ባይኖረኝስ? እኚህ ምን ጓደኛ ናቸው? እነሱን ለመተው
በሚያስችል መጠንማ ራሴን አከብረዋለሁ።" ሰሃኑ ላይ ግማሽ የጥብስ ፍርፍር እንደቀረ ጠገብኩ። እጄን በሶፍት እየጠረግኩ ሳለ "ልብላው? " የሚል ድምፅ አዞረኝ! ከእድሜያቸው በላይ ችግር ያስረጃቸው ሽማግሌ ናቸው። ያስተረፍኩትን እህል ነው ልብላው ያሉኝ።…እዛ አካባቢ መኪናዬን ሳቆም እየመጡ እንደሚለምኑኝ አዛውንት ናቸው ብዬ አስቤ ብር ልሰጣቸው ቦርሳዬ ውስጥ ገባሁ።"አይ ብር አይደለም የምፈልገው። እህሉን ልብላው ከበቃሽ?" አሉኝ ደግመው። ኩራታቸውን ርሃብ እንደነጠቃቸው በሚያሳብቅ አኳኋን…… ተነሳሁ።……ተቀመጥኩ።… የሆነ ነገር ሆንኩ። "ይቀመጡ አባባ ይቀመጡ አልኳቸው።" "እባክሽ ልጄ ምን ሆነህ ነው? ዓይነት ጥያቄ ከምትጠይቂኝ እህሉ ይቅርብኝ።" አሉኝ። "አልጠይቆትም!! ከእኔ የተረፈውንም አይበሉም። ይኸው አስተናጋጁ የሚፈልጉትን አዘው ይብሉ!" ዓይናቸው ሸሸኝ።…… አዘው መብላት ጀመሩ። ሀና ደወለች። "እ? ዛሬ ምሳ የት ይበላለት? " "ሲኦል ብሉ ስትፈልጉ…… am out! " ኡፈይይይይይይ ስልኩን ስዘጋው ተነፈስኩ። ቦርሳዬ የነበረኝን ብር በሙሉ አውጥቼ ሰጠኋቸው። አላመኑኝም። "እየቀለድሽብኝ ነው ልጄ? ምን አልኩሽ? " "አይደለም አባ…… ምንም አልጠይቆትም! ሊነግሩኝ የሚፈልጉ ቀን ግን በዝህች ስልክ ይደውሉልኝ።" በሶፍት ላይ ፅፌ አቀበልኳቸው። እጄን ተቀብለው አገላብጠው ሲስሙኝ ትኩስ እንባቸው እጄ ላይ ተንጠባጠበ።
…… ጨርሰናል………


@wegoch
@wegoch
@wegoch
የፈጣሪ የመገኛ ስፍራ በእያንዳንዱ የሰው ልብ ውስጥ ነውና


የሰዎችን ቀልብ መስበር የፈጣሪን ክብር እንደ ማጉደል ነው።

ሱፊዎች

ውብ ጁመዐ 💚

@wegoch
@wegoch
ነብስ ይማር

@getem
2024/09/27 11:20:23
Back to Top
HTML Embed Code: