Telegram Web Link
‹‹ሄይ…አልተኛሽም አይደል…?››
---------------------------------------
ከበፊት ጀምሮ የዚህ የመብራት ፈረቃ ነገር ሊያሳስበው የሚገባው መብራት
ሃይልን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብ መምሪያም ነው ስንል በነሲብ ሳይሆን ምክንያት
ነው፡፡እንዲሁ በወሬ በወሬ መብራት በብዛት ሲጠፋ ብዙ ህፃናት ይፈጠራሉ የሚል ነገር አውቅ ነበር፡፡ የመብራት ፈረቃ ዳግም ሲጀመር ግን ሆነ ብዬ ጨለማ እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ቁርኝት ካላቸው ብዬ ትንሽ ዳሰሳ አደረግኩ፡፡ አላቸው! ብዙ ምሳሌ አገኘሁ፡፡….ለምሳሌ የዛሬ 11 አመት ዛንዚባር ለአንድ ወር መብራት ድርግም አድርጋ ከርማ በአስረኛው ወር ላይ የሚወልዱ እናቶች ቁጥር በሃያ በመቶ እንደጨመረ አነበብኩ፡፡ስለዚህ….ያው… ሌላ ጊዜ ቲቪ የሚያዩ ባልና ሚስት መብራት ከሌለ እርስ በርስ ስለሚተያዩ…ሌላ ጊዜ ራዲዮ የሚያደምጡ ባልና ሚስት መብራት ከሌለ ስሜታቸውን ስለሚያዳምጡ…ሌላ የሚያዝናና ነገር ስለማይኖር በ‹‹እንትን›› ብቻ ስለሚዝናኑ…እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸው ሲገላበጡ ቆይተው ‹‹እ…አልተኛህም እንዴ?›› …‹‹ሄይ…አልተኛሽም አይደል…?›› በሚል ለፍቅር ድግስ ስለሚዘጋጁ….የመብራት ሃይልን ብስጭት ለመወጣት አንዳቸው ላንዳቸው ብቸኛ የደስታ ምንጭ ስለሚሆኑ….ሁለት ሆነው ተኝተው ሶስት ሆነው ስለሚነሱ…..….የካቲት 2012 ላይ ወላ ጋንዲ፣ ወላ ጤና ጣቢያ፣ ወላ በፀጋህ….፣ በየመብራት ፈረቃ ልጆች ምጥ ተይዘው በሚመጡ ነፍሰጡር እናቶች ባይጣበቡ
ምን አለች በሉኝ!ለሁሉም፣ የዚህ የመብራት ፈረቃ ነገር ሊያሳስበው የሚገባው መብራት 😄

@wegoch
@wegoch
@paappii

#by_hiwot_emishaw
ሰላም ጤና ይስጥልኝ. አርቲስት #በረከት_ግርማ (አቢቹ) እባላለው የአዲስ አበባ ነዋሪ ስሆን የተለያዩ የኪነ #ቅርፅ እና ኪነ #ቅብ ስራዎችን እሰራለው። ስራዎቼን @artbekiyechalal ገፅ ውስጥ በመቀላቀል እንድትጎበኙልኝ በ አክብሮት ጠይቃለው።.................

@artbekiyechalal @artbekiyechalal

አመሰግናለው!!

@seiloch @seiloch
እንኳን ለ 1440 ኛው የ #ኢድ_አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን!

መልካም በዓል

@seiloch
@getem
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
Eid-Mubarak
@Mykeyliyew
ሰዶማዊነት፤
።።።።።።።።።። ።።።።።።።።።።
(ቡርሐን አዲስ)
በአጭሩ ከነብዩ ሎጥ (ዐ›ሰ) ጋር አያይዘን ከኃይማኖታዊ አንድምታው መነሳት ይቻላል፤
ሰዶማዊነት በዋናነት የቁሳዊነት ስልጣኔ አንዱ ጀብድ ነው፤ ከጥንት እስከዛሬ ሰዶማዊያንን
የምናገኘው… ከተነሱ ስልጣኔዎች አኳያ ነው፤ የአንድ ስልጣኔ ህልፈት መዳረሻም ምልክት
ነው፤ ታላቁ የስነ-መንግስት ምሁር ጀነራል ሰር ጆን ግለብ ፌት ኦፍ ኢምፓየርስ በተሰኘ
ጥናቱ ስድስት የአንድ ስልጣኔ ኡደቶችን አቅርቧል፡፡ የትኛውም ስልጣኔ እነዚህን ኡደቶች
ያልፋል፤ ስድስተኛው ኡደት ላይ ከደረሰ የዚያ ስልጣኔ ህልፈት ጫፍ መሆኑን ያስረግጣሉ፤
ከጥንት ግሪክ እስከአሁን የተነሱ ስልጣኔዎችን በዚህ ቅኝት መዳሰስ ይቻላል፡፡ በአማካይ
እስከ 250 አመታት እድሜ ይቆያሉ ስልጣኔዎች፡፡ ከዚያ ሌላ መልክ ለሚኖረው ስልጣኔ
ተሸናፊ ይሆናሉ፤ ግሪኮ ሮማን የስልጣኔያቸው መጨረሻ ሰሞን ሴሰኝነትን አቅፈው
እናገኛለን፤ ሴተኛ አዳሪዎች የነገስታት አማካሪ እስከመሆን ደርሰው ነበር፡፡
ታላቁ የኦቶማን ሱልጣኔት … ሀረም የሚሉት ባዕደ-ልማድ ማጓን ሲጀምሩ ስልጣኔው
መዉደቂያው ላይ ነበር፤ ይኼው አንግሎ አሜሪካን የሚቃኘው የዘመናችን ስልጣኔም
ያለበትን እውነት ማየት ቀላል ነው፤ ከተሞች አደጉ ስንል የነሱን መልክ ይይዛሉ፤ ወዲያው
ሞራል መክሳት ይጀምራል፤ ሴሰኝነት፣ ስርቆት፣ ዘረፋ፣ ግድያና መሰል ኢ-ፍትሃዊ፣ ኢ,-
ሰብዓዊ ክዋኔያት በዝተው ይጎርፋሉ፤
አዲስ አበባ ከአስርና ሀያ አመት በፊት ከነበራት የዋልጌነት ጠባይ አሁን በብዙ እጥፍ ብዙ
ዋልግነቶች አልበዙባትም? ሴሰኝነቱ፣ ዝርፊያው፣ ቀማኛው፣ ወሲብ ለባሹ፣ ሱሰኛው ደባሉ
ወዘተ… እየጋተን ያለውን የሞራል ዉርደት ማሰብ አይከብድም፡፡
ስለሰዶማዊነት፤
በሞራል የታነጸ ህዝብ ከሚገለፅባቸው መለያዎች አንዱ ሰዶማዊነትን መቃወሙ ነው፤
ከለመደው ቤተሰባዊ ባህሉ መዉጣት አለመፈለጉ ነው፡፡ ይህን ስርዓት ለማፍረስ
ከሚያስችሉ የቁስ አምልኮ ስልጣኔዎች አንዱ ሰዶማዊነት ነው፤ የሎጥ ህዝቦች እኮ
በጊዜው ንቃት ነበራቸው፤ ሰዶማዊ ሆነው ከሰሙ እንጂ፤ በ14ኛው ክፍለ ዘመን በጣሊያን
ፖምፔ ተመሳሳይ ሰዶማዊያን በዝተው እንደነበር ይታወሳል፤ ዛሬ ከባድ ዝማሬ የተነገበለት
አንዱ አጀንዳ ይኼው ሆኗል፡፡
በነገራችን ላይ ባዮሎጂካዊ እንደሆነ ጭምር የሚቀርቡ ጥናቶች አሉ፤ ፍጹም የተጋነና
የሳይንስን ክብር ያጎደፈ ነው፤ ራሳቸው ሰዶማዊ የሖኑ ሳይንቲስቶችና ከፍተኛ ክፍያን ድጋፍ
ያደረጉ የሙያ ሙሰኞች ጎባጣ ሳይንሳዊነት እንጂ እውነተኛ ሳይንስ ሆኖ አይደለም፡፡ ሌላ
ጊዜ አስፈላጊ ሲሆን የምለው ይኖር ይሆናል፡፡
….
ሰዶማዊነት አንዱ የቤተሰብ ዋጋን ማርከሻ አብዮት ነው፤ ሰዎች ቤተሰብ ሆነው እንዳይኖሩ
የማስቻል ነውጥም ነው፤ ወሲብን የማጮህና በሴስ የተቋጠረ ልቅ ስርዓትን የማንሰራፋት
የማህበረሰብ ጅምላ መቆጣጠሪያ እንከን ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በርካታ እውነቶችን
ማውሳት ይቻላል፡፡
ሶስተኛው ሞገድ የሚባለውን የአክራሪ ፌሚኒስቶች እንቅስቃሴ ካየን እንዲሁ ቤተሰብን
ማፍረስ የሴቶችን መብት በህያውነት ለማስከበር ይረዳናል የሚሉ፡፡ ይህም ሌዚቢያንነትን
እስከማስፋት መድረሱን ይታዘቧል፡፡ ብዙ ጉዳዮችን በድፍረትና ባልታዩበት አዉድ መታዘብና
ማጥናት ካልቻልን ከባድ ፈተና ውስጥ ነን፡፡
“ጋብቻ ወንድን ለማገለግል የሚጠቅም መሳሪያ ነው፤ ስለዚህ ጥረታችን ሁሉ ጋብቻን
ማፍረስ ላይ ይሁን ሴቶችን ነጻ ለማዉጣት አይነተኛ መሳሪያችን ጋብቻን ማፍረስ ነውና
ሴቶች ባላቸውን እንዲተው ማድረግ አለብን”
ዲክለሬሽን ኦፍ ፌሚኒዝም 1971
የተከበረ ጋብቻን ማፍረስ ለምን አስፈለገ? ሰዶማዊነትን መዝመርስ ጠቀሜታው ምን
ይሆን? እንቀጥለው ይሆናል፤ ግን ሁላችንም በየራሳችን መንገድ መፈተሸ ብንችልስ?

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ዘረኝነት ራሱ ግብረ-ሰዶምነት ነው!!
የራሱን አይነት ብቻ የሚያስከጅል። ሁለቱም ጥንቦች ናቸውና አንፈልጋቸውም!!"
----
ደግ ደጉን
((ጀማል አማን ዘወሎ ))

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚
ነፃነትህም የተፈጥሮ ለመሆኑ ተንታኝ እስኪነግርህ አትጠብቅ፡፡
መመሪያህ ፍቅር እንጂ ጥላቻ አይሁን፤ ፍቅር ከጥላቻ ጋር ህብረት የለውም፤ ባለሰይፍን
በሰይፍ መቀየሩም፣ ጉልቻ ቢለዋወጥ… ነውና
መንገድህ ሁሉ ፍፁም ሰላማዊ ይሁን!
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ነፃነትን የሰወረ መቃብር የሚፈነቀለው በፍቅር ብቻ ነው፤ ዘላቂ
ለውጥም ከምህረት እንጂ ከበቀል አይሰርፅም።


ሸጋ ቀን !!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
የምንችለውን ወይስ የሚገባንን?
(ዲ.ዳንኤል ክብረት)

ይነበብ
፨፨፨

የሚቻለውን መሥራት የዐቅም ጉዳይ ነው፡፡ የሚገባውን መሥራት ግን የሕግና የሞራል ጉዳይ ነው፡፡ ኃይልን ለመጠቀም የሚያስችል ትምህርት ለሚማሩ ሰዎች በጥብቅ የሚነገራቸው ነገር ቢኖር የተገቢነት ጉዳይ ነው፡፡ ካራቴ፣ ጂዶ፣ ቦክስ፣ ውትድርና፣ ፖሊስነት የተማሩ ሰዎች ኃይልን ለመጠቀም ቅርብ ናቸው፡፡ በእጃቸው ማጠናፈር፣ በእግራቸው መዘረር፣ በጉልበታቸው ማርገፍ፣ በመሣሪያቸው ማንጠፍ፣ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በባረቀባቸው፣ በፈላባቸውና በነደዳቸው ቁጥር ኃይል እንዳይጠቀሙ የተገቢነትን ጉዳይ እንዲያስቡበት ይመከራሉ፤ ይሠለጥናሉ፡፡ ይቻላል ሳይሆን ይገባል ወይ? ብለው እንዲጠይቁ፡፡

አሁን ባለቺው ኢትዮጵያ ‹ይቻላል› እንጂ ‹ይገባል› ተገቢውን ቦታ አላገኘም፡፡ ሁሉም የሚችለውን ለማድረግ ነው የተነሣው፡፡ ‹ይህንን ማድረግኮ ይቻላል፤ እነ እንትናን መቀስቀስኮ ይቻላል፤ እንዲህ አድርገን ልናሳያቸውኮ እንችላለን፤ እንዲህ ብሎ መከራከርኮ ይቻላል፤ እንዲህ አድርጎ ምላሽ መስጠት ይቻላል፤ እንዲህ ሠርቶ መበሻሸቅ ይቻላል› የሚሉ ነገሮችን ነው የምንሰማው፡፡ ባለ ሥልጣኑም፣ ፖለቲከኛውም፣ አክቲቪስቱም፣ ጸሐፊውም፣ ጋዜጠኛውም ምን ማድረግ እንደሚችል እየነገረን ነው፡፡ ሁሉም የጉልበቱን ልክ እያሳየን ነው፡፡ ‹ይህንን ማድረግ ተገቢ ነው?› ብሎ የሚጠይቅ ግን ብዙም የለም፡፡



ሁላችንም የምንችለውን ብቻ ካደረግን የሚተርፍ አይኖርም፡፡ የሚያኗኑረን ተገቢውን ብቻ ለማድረግ ያለን የአእምሮ መለኪያ ነው፡፡ ኃይልንና ጉልበትን ከማን አለብኝነት የማቀቢያው መንገድ ‹ተገቢነት› ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከሕግና ከሞራል አንፃር የሚታይ ነው፡፡ ለጊዜው ዐቅም ወይም ሥልጣን ወይም ዕድል የላቸውም ብለን በምናስባቸው ወገኖች ላይ ‹እንችላለን› በሚል ስሜት ብቻ የምናከናውነው ተግባር ሌላ ‹እችላለሁ ባይ› ይፈጥራል፡፡ የማሸነፊያው ኃይል ሐሳብ መሆኑ ይቀርና ጉልበት ይሆናል፡፡ ጉልበት ማጠራቀም ደግሞ ሐሳብን ከማጠራቀም ይልቅ ቀላል ነው፡፡ ሂደታችንም ያረጀን ጉልበታም በአፍለኛ ጉልበታም የመተካት ሂደት ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ዛሬ ዛሬ ዛፎችን የማይቆርጠው፣ እንስሳትን የማያድነው፣ በካይ ጋዝ ወደ አየር የማይለቀው ዐቅም አንሶት አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡ ግን አይገባውም፡፡

ማኅበረሰብን በሰላምና በጤና የሚያኑዋኑረው ‹ተገቢነት› ነው፡፡ ይህን ነገር መናገር፣ መጻፍ፣ ማሠር፣ መግደል፣ መከልከል፣ መውሰድ፣ መስጠት፣ ተገቢ ነው ወይ? የሚያስገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ያኗኑራል ወይ? በዜጎች ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ምንድን ነው? የሚሉት ጉዳዮች መታየት አለባቸው፡፡ ማድረግ የምችለውን ሁሉ ማድረግ፣ መናገር የምንችለውን ሁሉ መናገር፣ መጻፍ የምንችለውን ሁሉ መጻፍ፣ ማባረር የምንለውን ሁሉ ማባረር፣ ማፍረስ የምንችለውን ሁሉ ማፍረስ፣ መገንባት የምንችለውን ሁሉ መገንባት አለብን? ተገቢ ነው?



የሰው ልጅ አካላት በሦስት መልክ ይገለጣሉ፡፡ በአንድ በኩል ለሕዝብ ሁሉ የሚገለጡ የአካል ክፍሎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚገለጡ የአካል ክፍሎች አሉ፡፡ ሦስተኛዎቹ ደግሞ ለማንም የማይገለጡ የአካል ክፍሎች ናቸው፡፡ በፎቶ ግራፎቻችን ላይ በብዛት የምናገኛቸው ለሕዝብ ሁሉ የሚገለጡትን የአካል ክፍሎቻችንን ነው፡፡ እነዚህ የአካል ክፍሎች ብዙ ጊዜ ልብስ አይለብሱም፡፡ ቢለብሱም በአደባባይ ልብሳቸው ሊወልቅ የሚችል ነው፡፡ ለቅርብ ሰዎቻችን ብቻ የምናሳያቸው የአካል ክፍሎችም አሉን፡፡ እነዚህ ብዙ ጊዜ በልብስ ተሸፍነው የሚውሉ ናቸው፡፡ እነዚህን ለሰው ሁሉ መግለጥ የጤናም፣ የሞራልም፣ የባሕልም፣ የሥነ ምግባርም ቀውስ ያመጣል፡፡ ሦስተኛዎቹ በቆዳችን ተሸፍነው የሚኖሩ የሰውነት ክፍሎች ናቸው፡፡ እነዚህን ለማየት የውስጥ አካልን የሚያሳዩ መሣሪያዎች ያስፈልጋሉ፡፡ በቀዶ ጥገና ለማየትም የተለየ ሞያና ሥነ ምግባር ይጠይቃሉ፡፡ እነዚህ በቆዳ ተሸፍነው የሚኖሩ የሰውነት ክፍሎቻችንን ከፍተን ብንተዋቸው በሰውዬው ላይ አደጋ ይከሠታል፡፡ መጨረሻውም ሞት ነው፡፡

የሰው ልጅ ጉዳዮችም እንዲሁ ናቸው፡፡ ለሁሉም የሚገለጡ አሉ፡፡ ለተመረጡ ብቻ የሚገለጡ አሉ፡፡ ለማንም የማይገለጡም አሉ፡፡ አሁን በሀገራችን እያየን ያለነው ግን ከዚህ በተለየ ነው፡፡ ሁሉንም በአደባባይ የመዘርገፍ አባዜ ውስጥ ወድቀናል፡፡ ይህንን የምናደርገው ደግሞ ‹ማድረግ እንችላለን› በሚል ጉልበተኛ ስሜት ነው፡፡ ‹ማድረግ ተገቢ ነውን?› በሚል የጠቢብነት መንፈስ አይደለም፡፡ ከሕዝብ ሁሉ ጋር የምናደርጋቸው ነገሮች አሉ፤ ከተመረጡ ወገኖች ጋር መነጋገር፣ መከራከር መወያት ያለብን ነገሮችም አሉ፡፡ አንዳንድ ነገሮች ግን ስሜታችንን ቢገፋፉትም፣ ውስጣችንን በል በል ቢለንም፣ ጉልበታችን ቢሞግተንም፣ እንኳን ይዘን መኖር ያሉብንም ነገሮች አሉ፡፡ ይገለጡ ቢባሉ እንኳን በተገቢው መንገድ ለመያዝ የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ ተገቢነት ይህን ይጠይቃልና፡፡
እስኪ የሀገራችን ኃያላን - የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ ተውና የሚገባችሁን ብቻ አድርጉ፡፡

ምንጭ ፦ የዳንኤል ክብረት የጡመራ ገጽ / Daniel Kibret Blog /

#ንባብ_ለሕይወት

@Wegoch
@wegoch
ጣታቸው ከሙስበሃው ተፋትቶ፣ ዚክርን ትቶ በእንቅልፍ ብዛት ደልቦ ከመሞት በላይ
አፈሙዝ አያስፈራቸውም።
------
እነዚህን ልቦች የቱንም ያክል ብትታጠቅ አታሸብራቸውም፣ መዝከሪያ ሙስበሃቸውን
አታስጥላቸውም!!

መልካም ጁምኣ!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከቀናቶች በአንዱ
(ቡሩክ ካሳሁን)

‹አንዳንዴ በመናገርና ባለመናገር መካከል ያለው ልዩነት አስገራሚ ነው› ዱባለ ነው፡፡
‹እንዴት› አልኩት
‹ስለ አንድ ነገር ወይም ስለ አንድ ሰው፤ ስለተደረገ ነገር እራስ ላይም ሊሆን ይችላል፤ ሲደረግ እያየክ እንዳላየ ሆነክ ዝም ስትል፤ አንድ የራሽያዎች ተረት አለ፤ እዛጋ የተሰቀለው የበሬ ፎቶ ይታይሀል?› አለኝ የስጋ ቤት ታፔላ ላይ ወደተሰቀለው እያሳየኝ፡፡
‹አዎን› ብዬ መለስኩለት
‹እንግዲያውስ እያየክ ዝም ካልክ ከሱ አትሻልም ምክንያቱም ይሄ በሬ በጣም ብዙ በሬ ወገኖቹ እዚ እየገቡ ስጋቸው ሲቆረጥ አጥንታቸው ሲፈለጥ አይቷል ነገር ግን ምንም አይናገርም፡፡ አንተም ዝም ካልክ ከሱ አትሻልም ማለት ነው፡፡› አለኝ
.
ወዲያው ሁለት ጠብደል ሌቦች አንዲት ልጅን ሀብል ነጥቀዋት ሲሮጡ ባቅራቢያዋ የነበረ ‹ፋኖ› ማለት ይቀለኛል (ወዶ ሟች ማለቴ ዘማች ለማለት ነው) ሁለቱን ሌቦች ሊያሯሩጥ ሲከተላቸው አንዴ ቆሙና ፍሬውን ከገለባው ለዩት (መቼም ደበደቡት ብዬ ስራቸውን አላጣጥልባቸውም)፡፡ እንደዛ ሲመክረኝ የነበረው ዱባለን ዞር ብዬ ‹ኸረ ሊገሉት ነው ሄደን እንገላግል› ስለው ‹ለዛሬ የበሬውን ፎቶ ነኝ፡፡ ይልቅ ለምስክርነት ምናምን ብለው አፋፍሰው ሳይወስዱን ቶሎ ስልታዊ ማፈግፈግ እናድርግ አለበለዚያ እስኪጣራ ብለው አስገብተው መንግስት ካልተገለበጠ አያስወጡንም፤ ቴክኒካሊ ስፒኪንግ መቼም ማለት ነው› ብሎኝ አረፈው፡፡
ጥቂት ሶምሶማ ከሮጥን በኋላ መራቃችንን ስናረጋግጥ ረጋ ብለን መሄድ ጀመርን፡፡ የት እንዳለን ጠየቅኩት፡፡ ‹ምን አውቃለው እኔ ጂ.ፒ.ኤስ እንጠቀማ› አለኝና ዞር ዞር ብሎ ንግድ ባንክ ከፈለገ በኋላ ‹ይኸው ቄራ ደርሰናል › አለኝ፡፡ ተአምር ነው ፒያሳ ለተነሳ ጠብ በሶምሶማ ቄራ ከደረስን ብንሮጥ ኖሮ ከኦሮሞና ከሱማሌ ወገኖቻችን ጋር ሶስተኛ ቦታ ተካፋይ ሆነን ጦር መማዘዛችን አይቀሬ ነበር፡፡ ዱባለ የነፍስ አባቱን ስላገኘ ሁለታችንም ከተሳለምን በኋላ በግራ እጃቸው እሱን ያዝ አድርገው አስቀሩት ጎንበስ ብሎ አሜን አሜን ሲል ይታየኛል፡፡ ተመልሶ ሲመጣ ምነው ምን ብለውህ ነው እንዲ ‹አሜን አሜን ስትል የነበረው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡
እርሱም ‹አይ ጥቂት አወሩኝና ሊሄዱ ሲሉ መስቀል ተሳልሜ ይፍቱኝ አባቴ ብላቸው ‹ሀጢያትህን እንደ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት አሁንም አሁንም ይሰርዘው፤ ምቀኞችህን መተንፈሻ ፍቃድ ይከልክልልህ› አይሉኝም መሰለህ› አለኝ፡፡
‹ዉዉዉ በቃ በዚ አቋማቸው ለመጨረሻ ጊዜ ነዋ ዛሬ የተሳለምናቸው› አልኩት ፡፡
‹እቺ ሌባ› አለ ዱባለ ቀና ብዬ ሳይ የቀበሌያችን ሊቀመንበር የነበረችዋ ሴትዮ ናት፡፡
‹ምነው ምን አደረገችህ› ጠየቅሁት
‹ምን ማታረገው ነገር አለ እቺ፤ ባለፈው 1 ማህተም ለማስመታት እሷ ምድር ላይ ተንቀባራ ‹‹ወረቀቱን ከ4ኛ ፎቅ አምጣ›› አለቺኝ እሺ ብዬ አመጣሁ፤ 3ኛ ፎቅ ውሰደውና አስፈርም አለችኝ ሄጄ አስፈረምኩ፤ ያን ሁሉ ደረጃ እንደ ኮትኳች አጎንብሼ ወጥቼ ወርጄ ሳበቃ ‹‹የማህተም መምቻ ቀለም አልቋል ሰሞኑን ና›› አትለኝም መሰለህ፤ ድሮም ኢትዮጵያና ቢሮክራሲ› አለኝ እልህ በያዘው ድምፅ
‹ቅጠል ጨፍጭፈህ ለቀለምነት አምጣ ካልተባልክም ከፍታ ነው › አልኩት እየሳኩኝ
በመራመድ ላይ እያለን ገጀራው የሰፈራችን ግዙፉ ከፊታችን ድቅን አለ፡፡ ‹እንዴ ደሞ እዚ ምን ትሰራለህ? ሰፈር ደረስን እንዴ?› አለ ዱባለ ድንግጥ ብሎ
ገጀራውም ‹ አሁን ምንም ወሬ አልፈልግም ባለፈው ያበደርኩህን 5 ብሬን አምጣ› ብሎ ሳይጨርስ ዱባለ ሩጫ ሲጀምር ገጀራው ለ5 ብር ብሎ 5ሺ ገደማ የገዛውን ስልክ ወርውሮ ዱባለ አናት ላይ እንደ እንቁጣጣሽ ርችት በተነው፡፡ ዱባለ ጭንቅላቱን እንኳን አላሻሸም ቦልትን በሚያስንቅ ሁኔታ ገሰገሰ፤ ገጀራው ስልኩ መበተኑን ሲያይ ‹ወይኔ ስልኬን› ብሎ ከበፊቱ የበለጠ ንዴቱ ጨምሮ ተከትሎት መሮጥ ጀመረ፡፡ ገጀራው ዛፍ በመቁረጥ ሚተዳደር ፀረ ልማት ወጣት ነው፡፡ መጥረቢያ ይዞ ቢሆን ኖሮ ብዬ አሰብኩትና ስለዘገነነኝ ቶሎ ቶሎ ወደቤት አቀናሁ፡፡
2010 ዓ.ም

@burukassahunc

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from SPACE COMPUTER
🇪🇹🇪🇹🇪🇹አምስተኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነው። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን ዕንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው #ገነት_መናፈሻ ሠኔ 4/2011

እማይቀርበት!


@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ለቅዳሜያችን
💚
ሲታሰብ ከባድ ቢመስልም በአንድ ወቅት ውስጥህን ያቆሰሉትን ያቆሸሹትን የጎዱህን
የጣሉህን ሁሉ ተዋቸው።
አንተ ደስታህን ሊሰጥህ ስለሚችል ነገር ብቻ ላይ ትኩረትህን አድርግ።
ባሳዘኑህ ነገሮች ላይ ባተኮርክ ቁጥር አሁን ያለህን የደስታህን ጊዜ ታጣዋለህ። በቻልከው
መጠን አስተሳሰብህን ቋጥሮ ከያዘክ የሀሳብ እስር ቤት ራስህን በራስህ አውጣ።
ስለ ህመምህ ብቻ ካሰብክ ከፊትለፊትህ ያለውንንና እንዳትንቀሳቀስ ያደረገህን ግርግዳ
ራስህ በራስህ ታጠነክረዋለህ።
ከፊትህ ያለውን ግርግዳ ናቀውና እለፈው ትልቅነቱን ሳይሆን
የአንተን የአሁን የደስታህን ትልቅነት ብቻ አስብ።
ስላለፈው ሳይሆን ስለአሁኑ ስለቀረው ሳይሆን ስለመጪው የምታስብ ሁንና ደስታህን
በእጅህ አድርግ።

ፍልቅልቅ ያለች ፣ ድምቅምቅ፣ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ ትሁንልን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
እንደምን አመሻችሁ ወዳጆቸ፡፡

ሁሌም የሚቆጨኝ በጣምም የሚያሸማቅቀኝ የዚህ ትዉልድ አካል መሆኔ ነዉ::
ምናለ በዛን በደጋግ አባቶቸ ዘመን ፈጥረህኝ ላይሆን ያስብለኛል፤ከእወቀትም ባዶ ከጥበብም አላዋቂ ከሀይማኖት ና ምግባረም ዜሮ ከሆነ የትዉልድ አካል አንዱ መሆኔ እናቴ ማርያምን ይቆጨኛል፡፡
በተለይ በተለይ የዘመናት የአበዉ የትንቢት መፈፀሚያ የሰቆቃዉ ዘመን በደረሰበት በዚህ የሺወች አመታት መቋጫዉ እረጉም ዘመን መፈጠሬ ያሳፈረኛል፡፡
የትንቢቱ ቃል ሲፈፀም በአይን ማየት በጀሮስ መስማቱ ምን ያክል ያስፈራል በእዉነት ሳስበዉ ልቦናየ እራደብኝ፡፡
ይህ የተንኮላዉያን ዘመን ዘመናችን ሊያሳጣን ነዉ ይህ የእርኩሳን ዘመን ሊያራክስን ነዉ፡፡
ሰሞኑን የሚሰማዉ ጉድ ደግሞ ያስፈራል እኒህ የኢሉሚናቲ ቡድን የሰይጣን ጋሻጃግሬ የረከሱ ርኩሳን ግብረሰዶማውያን የቅድስት ሀገራችንን ቅድስና ሊያሳጡ ሊመጡ ነዉ አሉን፡፡
ወገኖቸ የሚገርምዉ እኮ የሚመጡት የኛቱን የኦረቶዶክስን ቤተክረስቲያን ሊጎበኙ ነዉ፡፡ ያዉም ፃድቅም ነጉስም ካህንም የሆነዉን የላሊበላን ቤተ መቅደሶች ሊጓበኙ፡፡ ይህ አያስለቅስም? ይህ አያስቆጫችሁም? የአባቶቻችንን አደራ እንብላ? ዝም እነበላቸዉ?
አላማዉ ግልፅ ነዉ፡፡ ለምን ይመጣሉ?
ብዙ ጊዜ በዚሁ ፔጅ ላይ በተደጋጋሚ ገለጨዋለሁ የአለሙ የፖለቲካ አላም የምእራባዉያን ክፋት ዋናዉ አላማቸዉ የመጀመሪያዉ እቅዳቸዉ ኦረቶዶክስን ከአለም የእምነት ተቋማት ዝርዝር ዉስጥ ማዉጣት ነዉ፡፡ ኦረቶዶክስ የሚባል ሀይማኖትን ከምድረ ገፅ ላይ ማጥፋት ነዉ፡፡ ለምን? የአንድ ጻድቅ ፀሎት ብቻ የሉስፈር ድልዳል መቀመጫዉን ያሳጣዋል፡፡ እንደ ጦረም ይወጋዋል የጻድቅ ሰዉ ጸሎት ሀይል አላት ና! ስለዚህ የአለሙን አስተሳሰብ ግሎባላይዜሽን በተባለ ቁማር ጠፍንጎ በአንድ መንደር አስተሳሰብ ዉስጥ በማስገባት የሉሲፈር ወንበረ በማይነቅንቅ በሰወች የልብ ዙፋን ዉስጥ ፀንቶ እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰወች የቃልኪዳን ንፃህናቸዉን ማሳጣት ና ማጉደፍ ነዉ፡፡
እኔ እኮ የሚገረመኝ እንዴት ማስተዋል አቃተን፡፡
ለምንስ አላማ ለምንስ ጉዳይ እንደሚመጡ ነገሪ እኮ አያስፈልግም ለምን ቢሉ፡፡
ለመዘናናት እማ ፖሪስ አትመረጥም? የዉብ ህንፃወች ባለቤት ዱባይስ ከኢትዮጵያ ድንኮነች እጅጉንስ አትስብም? የቱርክ አረቲፊሻል ተፈጥሮስ ከኢትዮጵያዉያን ኮረብታወች ለመዝናናት አትመረጥም፡፡
ወዳጀ ወዲህ ነዉ አላማዉ ....
ይህንን የረከሰ የእረኩሳን ማህበር ሀገራችን እኒዲረግጣት አንፈቅድለትም፡፡
ስለዚህስ ብንሞትም አይቆጨን ከሀጣን ጋ ተባብረን በሂወት ከምንኖር ይልቅ ሙተን ከፃድቃን ጋ ህያዉ ብንሆን ይሻለናል፡፡
ሁሉም ሰዉ ይህንን መልክት ለሚችለዉ ሰዉ ሸር ያድረግ ማንም ግብረሰዶም ሀገራችን እንዳይገባ በእያለንበት ሀሳቡን ለማህበረሰባችን እናሳወቀዉ ከ መንግስትም ሆነ ከሚመለከታቸዉ አካላት ደረሶ ቶሎ እልባት እንዲያገኝ፡፡
ሁላችንም ና ቡ ቴ እንበል የአባቶቻችን እርስት አሳልፈን አንሰጥም!
ይህ ፈለገ ጥበባት ነዉ ፡፡

ሀሳብ አስተያየት @paulos3 ላይ አድረሱኝ
26/9/7511

@wegoch
@wegoch
ባቲ!!
----------
ለባቲ የተዘፈነው ሁሉ ደሳሳ ጎጆዎቿ በሆዳቸው አቅፈው ከያዙት ፍቅርና ውበት፡ አንድነትና
ደግነት ሊስተካከል ከቶ አይችልም!! ባቲ ገለል ያለች፣ መንግስትም ሰይጣንም "እጃቸውን"
ብዙም ያላስገቡባት፣ በነበረ ልማዷና ወጓ ያለች የወሎ ሆድ፡ የወሎ ኗሪ ምስክር ነች!!
ባቲ እንደ ቦሌ የሰውን ደም ድንገት አፍልታ ድንገት የምታቀዘቅዝ
ብርቅርቅ፣ሽብርቅርቅ፣ስሜትና ጥድፊያ ከቶ አይደለችም። ባቲ ቀስ ብላ የምትገባህ፣ እንደ
ውሃ እያሳሳቀች የምትወስድህ፣ የረጋች፣ ለብ ያለች፣ ያልተንቀለቀለች አርምሞዋ የበዛ
"አስማጭ" ከተማ ናት!! ይሄ ሁሉ እንዲገባህ ወደ ውስጥ ግባ!!

መልካም አዳር !!!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለሰንበቲታችን
💚
ዘርአ ያዕቆብ ለኔ ኢትዮጵያዊ ነውና ሲመክረኝ እንዲህ ይላል፦
ልጄ ሆይ በምር እንዳትፀፀትና በቁጣህም ላይ ፀሐይ እንዳትጠልቅብህ ከቶ ቁጡ አትሁን።
ባልንጀራህን ብታሳዝነውም ለእሱ ያደረግህበትን ተሎ ተነስተህ ስለክፉ መልካም መልስለት
እንጂ አትዘግይ።
ከስህተትም ለመመለስ ትጋ። አምላክ እንዲባርክህና ሰላም እንዲሆንላችሁ ከእርሱ
ከባለእንጀራህ ጋር ሰላማዊ ሰው ሁን
ከችግረኞችና ከሃዘንተኞች ጋር አፅናኝና ርሕሩሕ ሁን። እግዚአብሔር ዋጋህን ይከፍልሀልና
ምፅዋት ማድረግን አትርሳ
እግዚአብሔር በመልካም ነገር ሁሉ እንዲያጠግብህ እንጀራ ቢኖርህ ከተራቡት
ወንድሞችህ ጋር ተካፈለው።
ያስጥልሃል እንጂ እግዚአብሔር የሓጥአንን በትር ባንተ ላይ አያሳርፈውምና ኅይል ቢኖርህ
የእሚባረሩ ወንድሞችህን አስጥላቸው።
እግዚአብሔር የተሰወረውን ምስጢር እንዲያሳይህና እንዲያስታውቅህ ጥበብ ካለህ
ዕውቀት ለሌላቸው አስተምራቸው ።

መልካም የረፍት ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/28 05:17:24
Back to Top
HTML Embed Code: