Telegram Web Link
እቴጌ ለምኒሊክ እንዲህ አሏቸው
"እኔ ሴት ነኝ፤ ጦርነት አልወድም፡፡ ግን እንደዚህ ዓይነት ውል ከምቀበል ሞትን (ጦርነትን)እመርጣለሁ”
ለእኛለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነው አድዋን ድል በጥቂቱ በወፍ በረር ቅኝት.....

"ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሀበሻ"



ሃያዘጠኝሺህፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳተራራ)፤ማርያምሸዊቶ፤አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃርአሳየኝ)…በመሠኘትየሚታወቁትእነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች የጣልያንን ጦር ድል አደረገው ፡፡

የደረሰው ጉዳት
በኢትዮጵያ በኩል

የሞቱ፦፡ከ፬ እስከ ፭ ሺህ
የቆሰሉ፦
፰ ሺህ

በጥልያን በኩል
የሞቱ፦ ፯ ሺህ
የቆሰሉ፦ ፩ ሺህ ፭፻
የተያዙ፦፫ ሺህ
በጦርነቱ ወቅት ከተፈፀሙ እጅግ ከሚያስገርሙ ታሪኮች መካከል.......
“ጣሊያኖችእንዳስላሴወጥተው‘የእየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ልቀቁ፤ ጦርነቱ ሲያልቅ በትልቅ ህንጻ እንሰራላችኋለን።’ አሏቸውና አንድ ሺህ ብር ሰጧቸው። ሁሉም ቤተክርስቲያኑን ሲልለቁ አንድ የሃምሳ አመት ቄስ ግን እምቢ አሉና ወዲያውኑ ተገደሉ። ከዚያም ቤተ ክርስቲያኑንና ቦታውን ጣልያኖች ተቆጣጠሩት። ሆኖም ክርስቲያን የሆኑ የጣሊያን ወታደሮች ‘ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አንዋጋም’ በማለታቸው ክርስቲያን ያልሆኑ ወታደሮች እዚያ ገብተው ጦርነቱ ቀጠለ… በጣሊያኖቹ ወገን ከእንዳስላሴ የሚተኮሰው መድፍ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ጨረሰ።
ይሄን ጊዜ ነበር እንግዲህ እንዲህ ተብሎ የተገጠመላቸው
"የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው"

““ ፊትአውራሪ ገበየሁ ደረታቸውን ሰጥተው የጠላትን ጦር መግቢያ መውጪያ በማሳጣት ሲተገትጉ፣ በጥይት ተመትተው ሞቱና እዚያው ምንድብዳብ ተቀበሩ፡፡

ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው በጦርነቱ ላይ ሲሰዉ አጼ ምኒልክን ጨምሮ ብዙዎች አዘኑ። በዚህን ጊዜ ምኒልክንም ሆነ ህዝቡን ለማጽናናት፤ “ገበየሁ ቢሞትም ባልቻ አለልዎ” ለማለት ጭምር እንዲህ ተባለ።
"ገበየሁ ቢሞት፣ ተተካ ባልቻ፤
መድፍ አገላባጭ፣ ብቻ ለብቻ" ተብሎ ተፈከረ
በደጃዝማች ጦር ስር የነበሩትና ታላቅ ጀብድ የፈፀሙት ሌላኛው ጀግና ሊቀ መኳስ አባተ ቧያለው ናቸው፡፡
አንደኛዉ የጣልያን መድፍ አፈሙዝ ላይ አነጣጥረዉ ሲተኩሱ፣ መድፉ ለቅርስ እንኳ ሳይተርፍ እንክትክቱ ወጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት፣
‹‹አባተ አባ ይትረፍ-ነገረኛ ሰዉ
ይህን መድፍ ከዚያ መድፍ አቆራረጠዉ
አበሻ ጉድ አለ-ጣሊያን ወተወተ
ዓይነ-ጥሩ ተኳሽ!ቧያለዉአባተ፡፡›› ተብሎ ተገጠመላቸዉ፡
የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅትጥቅመድሃኒት)አቅምሳይዳከምበፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤ ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡
ባሻ አውአሎም በኤርትራና በትግራይ የሚመላለሱ ነጋዴ ነበሩ፡፡ ቀደም ሲል ራስ አሉላ ኢጣሊያኖችን እየሰለሉ እንዲግሯቸው፣ የኢትዮጵያን ጦር ምስጢር ደግሞ አሳስተው እንዲጠቁሟቸው ከባሻ አውአሎም ጋር ተስማምተው ነበር፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች)ጋርወደባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡
ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡ የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ምሌሊቱንሙሉሲጓዝ አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ምአድዋጦርግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡- አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡
ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ እነ ራስ አሉላ በጀርባው ቆርጠው ገብተው መድፍ ሲተኩሱ ከአድዋ 10 ኪ.ሜወደኋላመሆኑን አርሞንዲ አያውቅም ነበር፡፡ ስለዚህ፣ ለተቀረው ጦር “ገብቻለሁ” ሲል በተመሳሳይ ሰዓት ከሦስቱም አቅጣጫ ተኩስ ተከፈተበት፡፡
የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው ፡፡
የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡ ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን "ግብር አብልታ "አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ አገራቸው ሰደደች፡፡

በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት23ቀን)እንዳማርያምላይተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን)ለሰጠውአምላክምሥጋና አቅርቧል፡፡
"
አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድልእንድናደርግ)ስለረዳኸንእናመሰግንሃለን..."
በጥቂቱየአድዋድልይህን ይመስላል፡፡
ክብር ክብር ክብር ክብር
ደም ከፍለው አጥንት ከስክሰው ሀገር እና ሀይማኖታቸውን ጠብቀው ቅድስቲቱን ሀገር ኢትዮጵያን ላወረሱን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ይሁን፡፡

ዩርዳን

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
ሙሉ ንቃት



ሕልሞችሽ ላይ መንቃት ፥ በመካከላቸው መመላለስ ፥ በውስጣቸው መኖር እፈልጋለሁ፡፡
ድንቅ ሕልሞችሽ ላይ፡፡
እውንሽ ላይ ብቻ መኖሬ አይበቃኝም፡፡ያንሰኛል፡፡እውን ነጠላ ነው፡፡ሌጣ ኑረት፡፡ብዙ
አለመቻሎች ፥ በርካታ ጉድለቶች ፥ አያሌ እንከኖች አሉበት፡፡
በእውን እግር ተራማጅ እንጂ በራሪ አይደለም፡፡እግር ክንፍ አይደለም፡፡በእውን አይን
ከግድግዳ አልፎ ፥ ከመጋረጃ ጀርባ ፥ ከአድማስ ባሻገር ተሻግሮ አያይም፡፡የተከደነን ፥
የተዘጋን ፥ የታሸገን አልፎ በውስጥ ምን እንደሚገኝ አያይም፡፡ፊት ለፊቱ የተደቀነን ፥
የተገሰጠበትን ፥ ያልራቀውን ብቻ ነው የሚያየው፡፡
በእውን ጆሮ የራቀን አይሰማም፡፡ከትየለሌ የሚዜምን ጣፋጭ ማኅሌት አያደምጥም፡፡
ከሰባተኛው ሰማይ የሚመጣ የሚያድነው ቃል የእውን ጆሮ ጋር አይደርስም፡፡ያልተወራን
አይሰማም፡፡የእውን ጆሮ ከአጠገቡ የራቀን ድምፅ አይሰማ አይለማ፡፡
በእውን ልብ አይጨበጥም፡፡ከነአስደናቂ ፍቅሩና መሰጠቱ ፥ በእውን ልብ በመዳፍ
መካከል አይያዝም፡፡
በእውን አካል ከገለባ የቀለለ ፥ ከላባ የሳሳና የለሰለሰ አይሆንም፡፡አካል ጠጣርና ግዙፍ ነው
በእውን፡፡አካል ሲጠበድል ቋጥኝ ፥ ሲኮሰምን ጠጠር ነው በእውን፡፡ሲመቸው ትንቡክ ፥
ድሎት ሲርቀው ጋጥ ባይ ነው አካል በእውን፡፡
አየሽ.....
ለምን ሕልምሽ ላይ መንቃት እንደምፈልግ!?
ሕልም ብዙ የማይቻሉ ነገሮች የሚቻሉበት ነው፡፡በተለይ የእንዳንቺ አይነቷ ቆንጆ ሕልም
ሲሆን፡፡ራሱ ሕልሙ ይዋባል፡፡
< የቆንጆ ሕልም የተዋበ ነው፡፡ከቁንጅናዋ ወዘና ሩሑን ይጠነስሳል፡፡ከውበቷ ናሙና
ነፍስያውን ይቀምራል....> ይለኝ ነበረ ያ ቆንጆ አፍቃሪ ወዳጄ፡፡
የማፍቀር ቂልነቱ እንዲህ የሚያስብለውና የሚያሳስበው እየመሰለኝ እስቅበት ነበረ፡፡እሱ
አይስቅም፡፡ስለቆንጆው ሕልም ውብ መሆን ከልቡ ያወራል፡፡ቁም ነገር ብሎ ደጋግሞ
ስለውበታም ሕልም ደጋግሞ ይተርክልኝ ነበረ፡፡
እኔ እስቅበት ነበረ፡፡
ፍቅር እንዳጃጃለው አምን ነበረ፡፡
ጅል መሆኑን ደጋግሜ እነግረው ነበረ፡፡
አንድ ቀን እንዲህ አለኝ....
"እኩለ ቀንና እኩለ ለሊት ተጋቡ፡፡
እንደፋኖስና ብርጭቆ የድርሻ ፥ የድርሻ ጥምረት ፥ የኔ ይበልጥ ፥ ያንተ ያንስ አልነበረም
ውሕደቱ...
"ቀኑ እኩል...ለሊቱ እኩል...እኩል በእኩል ሲሆኑ ነው የተጋቡት፡፡
"እኩለ ቀን...እኩል ብርሃን ፥ እኩል ጨለማ አዛይ ነው፡፡
"እኩለ ለሊት....እኩል ጨለማ ፥ እኩል ቀን አቃፊ ነው፡፡
"እኩል በእኩል ነው ጋብቻው፡፡
"ሰምረት!!!
"አየህ....ይሔ ውብ ሕልም ነው፡፡ቆንጆ ያልሆነች አታየውም፡፡ይሔ ውብ ሕልም ፥ የቆንጆ
ሕልም ነው" አለኝ፡፡
በሕልሙ ሳኩኝ፡፡
በጅልነቱ አፌዝኩኝ፡፡
በነገረ ስራው ስላቄን ጠነሰስኩ፡፡
ዛሬ ግን ገባኝ፡፡ቆንጆ ሳፈቅር፡፡ነጠላ እውኗ ላይ ብቻ መገኘት እንደማይበቃኝ፡፡ውብ ሕልሟ
ላይ መንቃት እንዳለብኝ ገባኝ፡፡
ማነው ባለተራ!?
በኔ ማፍቀር የሚስቅ!?
ማነው ባለሳምንት!?
በኔ ጅልነት የሚንከተከት!?
የቆንጆ ሕልም ውብ ነው፡፡
እሱ ላይ መንቃትና መገኘትም ሙሉ ንቃት ነው፡፡ሙሉ ንቃት ሁሉን ቻይ መሆን ነው፡፡
ተአምርን እንደአክርማ መሰንጠቅ ነው፡፡መቻልን እንደጣሳ ውሃ በአንድ ትንፋሽ መጨለጥ
ነው፡፡
ይሄን ሁሉ ድንቅ ስጦታ ፍቅር ያመጣዋል፡፡በሙሉ ልቡ አፍቅሮ ፥ በፍቅሩ ምሕዋር የለቀቀ
ጅል የሆነ ሰው የሚሰጠው ስጦታ ነው ሙሉ ንቃ

((( ጆ ኒ ሀብቴ )))

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
#1
በአፄ ምኒልክ ጊዜ ምረቴ የሚባል አልቃሽ ነበር። አንድ አውዳመት ላይ ሰዎች ዳቦ
ይሰጡታል። ይሁንና ሌቦች ካስቀመጠበት ቦታ ወስደው በሉበት ። በዚህ ጊዜ ሁኔታውን
የሰሙ መጥተው “እከሌ ቤት ብታስቀምጠው ኖሮ አትሰረቅም ነበር።” እያሉ ይመክሩት
ጀመረ። በዚህን ጊዜ ምረቴ እንዲህ አለ፦
ከመከራ ኋላ ምክር መገኘቱ
ዳቦዬ ተበላ አበላለ ከንቱ!😢
#2
በአንድ ወቅት ደብረሊባኖስ ሁለት መነኮሳት ወደሴት ሄዳችኋል ተብለው ተከሰው ቀረቡ።
ይሁንና ከተከሳሾቹ አንዱ ሕጹብ (ስልብ) ነበሩና ወደተከሳሽ ጓደኛው እየተመለከቱ፦
“እርሳቸውስ እሺ፣ እኔ ምን አድርገሃል ተብዬ ነው የተከሰስኩት?” አሉ።
በዚህን ጊዜ ጉዳዩን ሲከታተሉ ከነበሩ አባቶች አንዱ እንዲህ ተናገሩ፦
“ይተዉ እባክዎ፤ እርስዎም አፍዎ አያርፍም” ( )😜😜

#3
ጥያቄ፦ ከዚህ በላይ ያሉት ሁለት ታሪኮችን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው?
መልስ፦ ዳቦ😊

ሸጋ ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
የካራ_ማራ_ጦርነት ( ኢትዮ - ሶማሌ ጦርነት )

የካቲት 26 / 1970 ዓ.ም
" የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የኦጋዴን ጦርነት ከሶማሌ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጋር በ1969 ዓ.ም ተጀምሮ የካቲት 26/1970 ዓ.ም የተጠናቀቀው ጦርነት ነው፡፡

መጀመሪያ.በሶቪዬት ህብረት ቀጥሎም በ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኢትዮጵያን የወረረው የሰይድ ባሬ (ዚያድባሬ) ጦር ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› እያለ ከመላው የኢትዮጵያ ምድር በተሰባበሰበ
ጀግናው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድባቅ ተመታ፡፡

ዚያድ ባሬ የካቲት 26፣ 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያን ምድር ዘልቆ በመውረሩ፣
የኢትዮጵያ ጦር በመልሶ ማጥቃት በአየርና በምድር # ካራማራ ተራራ ላይ ከባድ ውጊያ አካሄደ፡፡

የሶማሊያን የአየር ክልል ጭምር ዘልቆ በመግባት የኢትዮጵያ የጦር ጀቶች ማሰስና ማደባየት ቻሉ ።

ዓለምም ጭምር ሶማሊያን ማገዝ አይደለም ስለ ሶማሊያ ነጋሪ እስኪጠፋው ወደመች ።

የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አደጋ ውስጥ ወደቀ ተራራዎቹ ሁሉ በምድር በካርቤል እና እና ቢየም ሮኬቶችና መካከለኛ
ርቀት ተተኳሽ ሚሳዮሎች ከሰማይ ደግሞ የአውሮፕላን ሮኬቶችና ቦንቦች ካራማራ ተራራ ላይ ዶፍ ወረደባት ፤ ከምድር እሳተገሞራ የፈነዳባት መሰለች ።

ከዚያም የኢትዮጵያ ጦር ጅግጅጋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ ከ አራት ቀናት በኋላ ሁኔታው ያስፈራው ሰይድ ባሬ ፣ የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን
ምድር ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ አስተላለፈ፡፡

ኢትዮጵያውያንም በድል ተመለሱ፡፡ በጦርነቱ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንን የመሳሰሉ አገሮች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ድጋፍ አድርገዋል፤ ከ 16,000 በላይ የኩባ ወታደሮችም የታሪኩ ተካፋይ ናቸው፡፡ " ታላቋ ሶማሊያም" ፈራረሰች፡፡

የዚያድባሬ የመጨረሻ ቃልም ‹‹ Nothing is permanent on this
world’’ በሚል ተቋጨ፡፡ "

" ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ደማቸውን ላፈሰሱ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰራዊት አባላት ። "

ምንጭ ፦
Office of the Prime Minister-Ethiopia /Abiy Ahmed's Speech

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

ምንጭ:-....የታሪክ-ድርሳናት...የቴሌግራም ቻናል የተወሰደ


ከሶማሌ ወረራ ነፃ ለማውጣት 150 ሺህ የኢትዮጵያ ወጣቶች አልቀዋል።

ክብር ለጀግኖቹ ሰማዕታት!!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ተቃርኖ



ወጥቷል፡፡
ወደዓለም፡፡ለዓለም፡፡
ሊኖር ነው፡፡
ከዓለመኞች ጋር፡፡
ዓለመኞች ቆንጆ መሳይ ናቸው፡፡ተጣዳፊዎች፡፡ለሁሉ የሚሮጡ፡፡የሞላላቸው መሳዮች ግን
በማብቂያው ፥ ምንም ያልያዙ መናጢዎች፡፡
ያፈቅራሉ፡፡
ቸኩለው ልብ ይሰጣሉ፡፡ተጣድፈው ሁሉን ተሰጣጥተው ይጨርሳሉ፡፡በንጥቀት ይሰለቻቻሉ፡፡
ደሞ ወደሌላ ይሮጣሉ፡፡መሬት ላይ ይሮጣሉ፡፡አልጋ ላይ ይሮጣሉ፡፡አየር ላይ ይሮጣሉ፡፡ፍቅር
ላይ ፥ ጥላቻ ላይ ይሮጣሉ፡፡ሳቅ እንባ ላይ ይሮጣሉ፡፡
ሁሉ ላይ ይሮጣሉ፡፡ረግተው ካየሀቸው ለሌላ እሩጫ እያደቡ እንጂ እርጋታን አውቀውት
አይደለም፡፡በዚህ ሁሉ ጥድፈታቸው ውሸታሞች ፥ ቀጣፊዎች ፥ አጭበርባሪዎች ሆነው
ይታዩታል፡፡
"አትሩጥ፡፡ለምንም ነገር አትፍጠን፡፡ያንተ ያንተ ነው፡፡ላንተ ያለው እንጀራ ሻግቶ ይወድቃል
እንጂ ማንም አይበላው" ይለው ነበረ እረኛ እያለ የሚያግደው በጉ፡፡
የታደለ ረኛ ነበረ፡፡የሚያወራ በግ የነበረው፡፡ይሄ ከሚሊዮን እረኛ አንዱ ብቻ የሚያገኘው
እጣ ነው፡፡ወርቅ እንቁላል እንደምትጥለው ዶሮ ነው ይሄ በግ፡፡አይገኝም፡፡ሲገኝም በዘመን
አንዴ ነው፡፡
አዋቂ ነው፡፡ልሳን አለው፡፡የጣፈጠ አንደበቱ እውቀቱን አሳምሮ ይናገራል፡፡
" ዛሬ ዛሬ ሁሉ ይሮጣል፡፡አንተ ግን ዝግ በል፡፡የሮጠውን ያህል ማንም አያገኝም፡፡
በማብቂያው ሁሉ በሮጠው መጠን እርካታ የለውም....." ይለዋል ተናጋሪ በጉ፡፡
" እኔና አንተ ያለነው እልም ያለ ገጠር ፥ ለምን ስለከተሜው ታወራኛለህ?የት
ታውቀዋለህ?"
ሳቅ ይልና " ዝም ብዬ የምታረድ በግ አልምሰልህ፡፡እሱ የአብርሐም በግ ነው፡፡እኔ
ብታረድም አዋቂ በግ ነኝ " ይለዋል፡፡
" እሺ ይሄ ወሬ ለኔ ምን ይረባኛል!?"
"ቀንህ ሲደርስ ከተሜ ነህ፡፡በጊዜህ ከተሜኛ ነህ፡፡ለዛ ጊዜ የሚሆንህን ነው ዛሬ
የምነግርህ፡፡"
ወጥቷል፡፡
ያየው ደነቀው፡፡ግራ ገባው፡፡
ይሄ ሕይወት እንቀልፍ አልባ ነው፡፡ንቃት ግን የለውም፡፡ረፍት አልባ ነው፡፡ስራው ግን
አጥጋቢ አይደለም፡፡ይኳኳላል፡፡ግን ውብ አይደለም፡፡ያነጣጥራል፡፡ኢላማ ግን ይስታል፡፡
ደስተኛ ነኝ ይላል፡፡ግን ብስክስክ ብሶቱን ታቅፎ ነዋሪ ነው፡፡ይብለጨለጫል፡፡ግን
አያበራም፡፡
መጥታ ያቀፈችው ማን ነበረች!?
አዎ!!
ሔርሜላ ነች፡፡
ብዙ ሳቅ ያላት ሔርሜላ፡፡ብዙ ድምፅ ፥ ምንም ዝምታ የሌላት ሔርሜላ፡፡እየሳቀች እዛው
የምታለቅስ፡፡እኩል በእኩል ሳቋም እንባዋም የበዙ፡፡
እንዴት ወደሱ መጣች!?
ከየት ወደሱ መጣች!?
ለምን እሱን አቀፈችው!?
ሁሉ ተሳከረበት፡፡ብብብብብብብብዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥ ያለ ሆነበት፡፡አልጠራ
ያለ መደፍረስ፡፡አያጥቡት ግን የሁሌ ጭቃ፡፡ተወቅጦ የላመ ፥ የደቀቀ ውሃ፡፡
" የኔ ፍቅር !?" አለች ሔርሜላ፡፡
እ!?
" ወይዬ " አለ እሱም፡፡
እ!?
" ልሄድ ነው በቃ፡፡ "
ከአይኑ የእንባ ኳሶች አንከባለለ፡፡ጉንጩን አብዶ ሰርቶ ፥ አፍንጫውን በሎጬ አታልሎ ፥
ሪዙን አብዶ ሰርቶ የእንባ ኳሶቹን ቁልቁል ወደመሬት ጎሉ በሹት ጠለዘው፡፡
" እሺ በቃ ሂጂ " አለ እንደምንም ብሎ፡፡
መቼ መጥታ!?
መቼ ልትሄድ!?
አሁን አቀፈችው አልተባለም እንዴ!?
አሁን ሳቀች ሲባል አልነበረ እንዴ!?
ምን ጉድ ነው ይሄ!?
እያለቀሰ ፥ እያለቀሰች ተቋጨች፡፡አከተመች፡፡ተቋጩ፡፡አከተሙ፡፡
" አለህልኝ የኔ ፍቅር!?" እያለች ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ አተመች፡፡
" የኔ ኮኪዬ " አለ ከንፈሯን እያጣጣመ፡፡
ኮኪ ማን ነች ደሞ!?
የኔ የኔ ከተባባሉ የእነሱ የራሳቸው ናቸው፡፡እሱ የእሷ ፥ እሷ የእሱ፡፡
ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡
ሽቅርቅር ያለች፡፡የሽቅርቅሯ መርቀቅ ከአጠገቧ ያለን ሁሉ አፈር ድሜ አስበልቶ የሚያስረሳ፡፡
ሁሉ ነገሯ አይን ይጠራል፡፡አይን ማራኪ ጀግና መሽቀርቅር ፥ አይን ጎታች ማግኔት
መሽቀርቀር ፥ አይን ጋባዥ ለጋስ መሽቀርቀር ነው ያላት፡፡
ያያት ሁሉ ይስቃል፡፡እሷን እያየ አብሯት ያለን ይረሳል፡፡ሲያያት ይደሰታል፡፡ከተሜ ቅብ ደስታ፡፡
ጥድፊያ ውስዋስ ደስታ፡፡
" በጣም ነው የማዝነው የኔ ፍቅር፡፡"
" ይገባኛል፡፡"
" ግዴታ ስለሆነብኝ ነው፡፡መሄድ አለብኝ፡፡"
የእንባ ኳሱ.....የለቅሶ ግጥሚያው....የእንባ ሊጉ.....የዚህ ዘመኑ ውድድር ኮኪ ነበረች፡፡
የመለየት ዋንጫውን አብልታውና ሸልማው ሄደች፡፡
ያ በጉ ታውሰው፡፡ሊያወራው ፈለገ፡፡
እንዲህ አይነት ወሬ....
"የማዝነው...
ክፉዎች ባሸነፉበት ዓለም ላይ በመኖሬ አይደለም!!!
"ቅዱሳኖቹ ተለይተው ስላልታወቁ እንጂ!!!
የሚከፋኝ...
"ዋናው እርኩስ ታውቆ ፥ ታላቁ ቅዱስ በማይታወቅበት ዓለም ላይ ስላለሁ ነው
የሚያስጠላኝ...
"እኔ ለማን ፥ ማን ለኔ እንደቆምን አለማወቃችን ነው...." ሊለው ፈለገ፡፡
ግን አይለውም፡፡ሊለው አይችልም፡፡ሰንቆታላ፡፡ከገጠር ወደከተማ ሲገባ፡፡
" እረደኝ፡፡ግን ፈጥነህ አትግፈፈኝ፡፡ቃሌን ለማቋረጥ በጥድፊያ ካራ አትሳል...." እያለው
ከሚሊዮን አንድ እጣውን በፈጥነት ፈጣጥሞት ከተማ መግቢያ ስንቁ አድርጎታል፡፡
ምን አይነት ዓለም ላይ ነው የወጣው!?
ሰውዬው ከእንስሳው የሚያንስበት ፥ እረኛውን ከብቱ በሚያግድበት ፥ ጠባቂውን
ተጠባቂው ተግቶ ዘብ የሚቆምለት ዓለም ላይ ነው የወጣው፡፡

((( ጆ ኒ )))💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
"ዛሬ ዛሬ ሙሉ በሙሉ የተረዳሁት የሐበሾች ስር ነቀልነት መሠረቱ ስሜት መሆኑ ነው፡፡
ከዐሥረኛ ፎቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሆሆሆ ብለው እርስ በርስ ተነዳድተው ይወድቃሉ፡፡
ለነሱ ዋናው ጉዳይ መውደቁ ሳይሆን ከፋም ለማም እጅ ለእጅ መያያዙ ነው፡፡ በሰው
የደረሰው ቢደርስባቸው ስህተት አይደለም።
ማሰብ የሚጀምሩት በመዋግደ ሕሊና ግፊት በመውደቅ ጎዳና ላይ ስምንተኛ ፎቅ ሲደርሱ
ነው፡፡ ወዴት እየሄድን ነው? ፓራሹት ይዘሀል ወይ? ይባባላሉ፡፡
ከአምስተኛ ፎቅ ጀምሮ ወሬያቸው ጭቅጭቅና ፀፀት ነው፡፡ እስከ ዜሮ ፎቅ ያለው ጉዞ
በጸሎት የታጠረ ምሬት ነው፡፡ በየደጀሰላሙ መንበርከክ ነው፤ ነጫጭ ለብሶ በኪራላይሶ
መንደድ ነው፤ ለ'ተለመነኝ' በሚያጤሱት ዕጣን መታፈን ነው፤ እዝጌር በምሬት
ይገጠምበታል፤ የሚረገም ይረገማል፤ ስለት ይገባል፤ ጥንቆላ ይጠነቆላል፤ የሚታማ ማሰስ
ነው። እጃቸውን የያዘውን ደባል ዘላያቸውን መርገም ነው፡፡ ወደ ኋላ እየተመለሱ
በአጀማመራቸው ማሳበብ ነው፡፡ መሬት ወድቀው በትዕንግርት ከመሰባበርና ከመሞት ቢድኑ
፤ የአወዳደቃቸውን ዚቅ ሊያርሙ እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ተያይዘው ወደ ፎቁ ይወጣሉ፡፡
ስህተቱ መውደቁ ሳይሆን አወዳደቃቸው ይመስላቸዋል፡፡"

አዳም ረታ
# የስንብት_ቀለማት

ሸጋው ቀን!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ፈላስፈው እና ደራሲው ካህሊል ጅብራን:-"አንዱ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል" አለ። በዛሬዋ ኢትዮጵያ የብዙዎች ማንነት እንዲሁ መስሏል።😊😊

@wegoch
@wegoch
በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ ለህዝቡ የሚጠቅም ህግ ማውጣትን አሰበና ከ'የ ግዛቱ ጠቢባን የተባሉ አንድ ሺህ ሰዎች በቤተ መንግስቱ ሰበሰበ።እያንዳዳቸውንም ለሀገር ይጠቅማል የሚሉትን ህግ አርቅቀው እንዲያቀርቡለት አዘዘ። የጠቢባኑ ህግ ተረቅቆ በንጉሱ ፊት ሲቀርብ ግን፣እጅግ አዘነ፤አምርሮ አለቀሰ።በተረቀቀው ህግ አዝኖ መስሏቸውም ሊያፅናኑት ሲጠጉት:-"የለም፣እኔ ያሳዘነኝ ያረቀቃቹት አንድ ሺህ ህግ ሳይሆን፣በሀገሬ አንድ ሺህ ዓይነት ወንጀል መኖሩን እስከዛሬ አለማወቄ ነው:" አላቸው።

ንጉሱ በመቀጠል የጠቢባኑን አንድ ሺህ ህግ ከፊቱ አስነሳ በምትኩምእሱ ያዘጋጃቸው ሰባት ህጎች ለሕዝቡ በቂ ናቸው አለ። በዚህ ጊዜ ጠቢባኑ ተቆጡ:-"እኛን ያደከመን በከንቱ ነውን?!" አሉ። ወደ ግዛታቸው ተመልሰው የእነሱን ህግ ሕዝቡ እንዲከተል አሳመኑ። በዚያች ታላቅ ሀገር ዛሬ አንድ ሺህ ህጎችን የጣሱ ወንዶች እና ሴቶች የሞሉባቸው አንድ ሺህ አስር ቤቶች ይገኛሉ።

እርግጥ ነው ሀገሪቱ ዛሬም ታላቅ ነች፤ነገር ግን፣ህዝቡ የአንድ ሺህ ህግ አውጪዎች እና የአንድ ንጉስ ተከታይ ሆኖ ቀርቷል።

የእኛ እምነት "ሰው" አያውቅም። ዛሬ በኢትዮጵያ የአማኝ እንጂ የእምነት ተቋማት ችግር የለም። የእኛ አማኝ በጥላቻ፣በነቀፌታ፣እና በራስ ፍቅር የተጠመደ ነው። ለእኛ ሀገር አማኝ "ሰው" መሆንህን ብቻ አይበቃውም። እሱ የሚያምነውን ማመን፣እሱ የሚከተለውን መከተል፣የእሱን ቋንቋ መናገር ካልቻልክ፣"ሰው"ብቻ ብትሆን፣ምን ያደርግለታል?የቱንም ያህል ጥሩ እና በጎ አድራጊ ሰው ልትሆን ትችላለህ፤እንደ'ምትከተለው ሃይማኖት የሰማይ ዋጋህን በ'የ ጓዳቸው ይወስኑልሃል፣እንጂ፣በአንተ አይቀኑም። በአደባባይ ደግሞ "ተቻችሎ የመኖር ባህል"ይሉታል። ሰውን እንደ "ሰው"በእኩልነት የሚመለከት እምነት ቢኖረንማ፣ተቻችሎ መኖር ቀድሞውንም ባልተደሰኮረ ነበር።

በመጨረሻም እንዲህ እላለሁ:-"ማንም ሰው ጌታው እንዲሆን የማይፈቅድ እና እሱም የማንም ሰው ጌታ መሆን የማይሻ በእርግጥ እሱ ታላቅ ሰው ነው!"

👆👆👆👆👆በተለይ ይችን ነገር በደንብ ያዙልኝ....
💚❤️💛💚❤️💛💚💛❤️💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚💚💚💚
ከሱፊዝም የእምነትና የሕይወት ፍልስፍናና ስንጨልፍ ለጁመዐችን አል-ጋኽዛሊ ስለ ፍቅር
የተናገሩትን እናገኛለን፦
የፍቅር መኖሪያው ልባችን ነው። ፍቅር ልዩና የሚያስደስት ስቃይ የተሞላ የፈጣሪ ስጦታ
ነው። ፍቅርን በልቡ ተሸክሞ የሚዞር እሱ ሚስጥሩን ለማወቅም የሚቸግረው አይሆንም።
ፍቅርን ስትሸከም ነገር ሁሉ ለአንተ እዉነትና ወደእውነት ብቻ የሚወስድ ይሆናል።
በፍቅር ውስጥ ከእውነት በቀር ሌላ ነገር የለም። ለዚህም ነው አፍቃሪዎች በእውነት ባህር
እየተሸነፉ ሲሰምጡ የምናየው።


ሸጋ ጁመኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbars
??????????
--------
ጦርነትን ለመጥላት በጦርነት ጠፍቶ ማወቅን አይሻም። ጦርነት ጦር የመስበቅን ያክል
ቀላል አደይደለም። ሰላም፣ እኩልነትና ፍትህን እንደ ህዝብ እርስ በእርስ በመጫረስ አንተ
ብቻ አታገኛቸውም።
-----
ዛሬ ትግሉን ያሸነፈ የሚመስለው ጦረኛ ሁሉ በእውነት በትልቅ የውድቀት መንገድ ላይ
ነው። አዎ፣ የነጻነት ብርሃኑ ልክ ነበር!! ላየንው፣ ለሰማንውና ለኖርንው አንጻራዊ ነጻነት
እውቅና እንሰጣለን። ግን ደግሞ ለአቅመ- ዲሞክራሲ ያልደረሰ ሰፊ ቀለም ጨላጭ
ተማርኩ ባይ ማይም በዚህች አገር አእላፍ መሆኑንም በውል ተገንዝበናል።
አዎ በህዝባዊ የፖለቲካ ትግል ወድቆ የመቅረት እንጂ ወድቆ የመነሳትና የማሸነፍ የስኬት
ታሪክ አልነበረንምና ዳግም ልንገነደስ አፋፍ ላይ ነን።
--------
ተስፋ አደርጋለሁ፥ ደም ያላጠባት፣ የከረፋ የመጠፋፋት ታሪክ የማይጣፍባት የልጆቼ አገር
ኢትዮጵያ ከህመሟ ትፈወስ ይሆናል። ለምን ቢባል፣ ምንም ስለማያውቀው መልካም
ህዝብ፣ ስለሚያሳሱ እንቡጥ ህጻናትና እናቶች ሰላምና ጸሎት ሲባል ባቻ። አዎ፣ የክፉዎች
መንገድና የሻጥረኞች ሴራ ይከስማል!!
----------
# የተደመርኩት ስላየሁት መልካም ብርሃንና የሰውነት መንገድ ነው፥ አልተሳሳትኩምም!!
ያሸነፉ የሚመስላቸው ደቂቃን-ኦነጎች፣ የጦርነት ነጋሪት ጎሳሚ እፍኝቶች፥ ቧልትንና
ፖለቲካን ቀላቅለው የሚያኝኩ የዋሆች ህልማቸው ቅዥት ነው!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ነብስያህን አድምጥ! ራስህን ሁን!!

ብትወዱኝም ብትጠሉኝም ሁለቱም ይመቸኛል። ብትወዱኝ ልባችሁ ውስጥ ነኝ ብትጠሉኝ
ደግሞ ጭንቅላታችሁ ውስጥ ነኝ..!
እኔ አይደለሁም ያልኩት፤ ዊልያም ሼክስፒር ነው የተናገረው ሀሳቡ ግን ፈገግ ያደርጋል።😊😊😊


ሽቶን ስጦታ ብለህ ስትሰጠው ...!!! ሸተሃል ለማለት ፈልገህ ነው....ከሚል ሰው ጋ እንዴት ነው የምንግባባው ጃል??....!!..!!ደግሞም አንዳንድ ሰው አለ ጨረቃን በጣትህ እያሳየሀው ከጨረቃ ይልቅ ጣትህን የሚያይ..!!!


ከራስ ጋር!!!

ፊት ለፊት ስንገናኝ መተቃቀፍ ወደየቤታችን ስንሄድ እንደ kappa ማስታወቂያ ጀርባ ለጀርባ
መሆን ምንም አያዋጣንም. ..ጠራቢዬ ሆይ ወዴት አለህ /ሽ?ሁሉንም ፅሁፎቼን ስጽፍ የነበረው
ፈገግ እያልኩ ነው ይሄንን ግን ኮስተር ብዬ ነው።እዚህ ውስጥ እኮ አስተማሪዎቼ ትንሽ
ናቸው ተማሪዎች ግን የሉኝም...የማትረዳኝ/ ሆይ ይሄንን በማምበብ ጊዜህን አታጥፋ/ፊ !!!


ይቅርታ ለማድረግ አሰቀድሞ መቁሰል ግድ፣ይላል፣ቆስሎ ይቅርታ ለማድረግም ደግሞ ኩራትን በውስጥ መሸከም ግድ ነው።ከልብ የሆነ ልግስና ለመፈፀም አስቀድሞ "እኔ" የሚለውን ወይም "የእኔነት" አስተሳሰብ አውጥቶ መጣል ብቸኛው መፍትሔ ነው!!....ስለ እኛ እያወራህ ስለ ራስህ ራስህን ነፃ ለማውጣት ነው ከተባልክ ምን ታረገዋለህ......የምትናገረው ነገር ልክ መሆን ወይም አለመሆንህ ሚረጋገጠው....እንደሰውየው አረዳድ ነው......ያ ማለት ግን አንተ ልክ አይደለህም ወይም እሱ ልክ አይደለም ማለት ላይሆን ይችላል...😊

ካህሊል ጅብራል የልቧ ሰው ምን ይላል....."ከጥንቸሎች የበለጠ ኤሊዎች መንገድ ያውቃሉ"....

ቴድ አፍሮ..የልቧ ሰው ምን ይላል......ተመልከትልኝ



ቀላል ይሆናል
.......
ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ
የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት እርስቴ
ቀላል ይሆናል ቀና አርገኝ ፅናቴ
ቀላል ይሆናል(4)
ቀላል ይሆናል
ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ
አለ ቂል ሰው ሁሉም አከተመ
ደቂቃ ተስፋን ካየናት አርቀን
ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን
ቀላል ይሆናል (8)
ቀላል ይሆናል
ፈራን
ፍቅርን ፈራን
ልጅነት የለገሰንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ በረቂቅ ያለበሰንን
በመለኮት የቀባንን
እውነት ፈራን...ፍቅር ፈራን
አሄ አሄሄሄሄ (8)
ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ ይላል.......ዳገቱ አንድም የህይወት መስመራችን ኑሯችንን ነው..ውጣውረዱን እንቅፋቱን ፈርተን ዳገት ላይ እንዳንቀር ...ስልቹ ሆነን ተስፋ አጥተን ለዳገቱና ለፈተናው ተሸንፈን እንዳንቀር ሲል አትዛል ጉልበቴ በማለት የሚመክር ዜማ ነው...። መጽሐፍ ቅዱሱም ቢሆን ፈተና በበዛባት አለም ላይ እንደምንኖር ያትታል...የየእለት ፀሎታችንም ቢሆን ...ወደፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጅ የሚል ነው....ስለዚህ ይሄ ሁሉ የሚያመላክተን ምንኛ የዚህ አለም ኑሮ ፈታኝ እንደሆነ ነው.....ይሄን ፈተና ደግሞ በፅናት መወጣት ያስፈልጋል....ዳገቱን መፍራት የለብንም ሲል ነው አትዛል ጉልበቴ ያለው ይመስለኛል። ብሎም የህይወትን የዳገት አለም ፅናት እስካለን ድረስ እናልፈዋለን ሲል ቀላል ይሆናል ቀና አርገኝ ፅናቴ በማለት ከገዛ ፅናቱ ጋር ይነጋገራል። ይሄ በጣም ግልፅ እና ፊትለፊት የምናኘው መልዕክቱ ነው ወይንም ሰሙ ነው....ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ ጀርባ ያለው ወርቁ ይመስለኛል።
ከዚህ ከምናየው ከተረዳነው ጀርባ ያለ ሌላ ሃሳብ ያለ ይመስለኛል። የአለምን ዳገቱን ካለፍን ውጣ ውረዱን ከሸኘን በስቲያ ያለ እጣፈንታን የሚያስቃኝ ቅኔ ነው። የተራራው ጫፍ ርስታችን ፍቅር ነው ሲል ይተርካል....የተራራው ጫፍ የሚለው ክርስቶስን ወይንም አላህን ወይንም በአጠቃላይ ፈጣሪን ይመስለኛል። ፍቅር እንደ ርስት...ፍቅር እንደ ቡራኬ ፅድቅ....ፍቅር እንደ ትልቅ የህይወት ግብ የሚሰበከውና የሚሰጠው በፈጣሪ ዘንድ ብቻ ነው ብል አላጋነንኩም.....ፈጣሪ ደግሞ ያለው ከውጣውረዱ ከዳገቱ በላይ ነው....በተራራው አናት ላይ ነው ክርስቶስ ያለው...እናም የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴ ይለናል ብላቴናው።
ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ
አለ ቂል ሰው ሁሉም አከተመ
....ትንሿን የፈጣሪ ፈተና አይቶ ሁሉም የሚጋረድበትና በቃ ሁሉም ነገር አከተመለት ብሎ ተስፋ ስለሚቆርጥ ቂል ሰውም ያትታል። በተለይ የአምላክን ድርጊትና የመለኮትን ህልውና ለማወቅ ዘለግ ያለ ጠለቅ ያለ እይታና ጥበብን ያሻል ለዛም ነው ይህን በቀላሉ ተስፋ ቆራጩን ሰው ቂል ነው ያለው። እዚህ ላይ ድንቁ ሎሬት በእሳት ወይ አበባው መግቢያ ላይ ካላት ጋር ትመሳሰልብኛለች።
"እና እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑን የታወረ
እግረ ሕሊናው የከረረ
ባሕረ-ሃሳቡን ያልታደለ
የውበት ዓይኑ የሰለለ
ሰማይ ጨለማ ነው እንጅ አበባ እኮ አደለም አለ
ያልታደለ።" ይለናል ሎሬቱ.....እዚህ ላይ በትርጉም ቀጥታ ካነሳነው ሃሳብ ጋር ባይሄድም ቴዲ ቂል ሰው ያለበትና ጋሽ ፀግሽ እግረ ሕሊናው የከረረ ያለበት መስመር ይገናኛል...ሁለቱም ለተለያየ ጉዳይ ይበሉት እንጅ ጭብጡ ግን በምናብ ርቀን መጥቀን...በተመስጦ ከአምላክ ጋር ካልተገናኘን ...በጥበብና በከፍታ አይን መመስጠር ካልቻልን ቴዲ እንዳለው ቂል በቀላሉ ሁሉም አከተመ እንላለን ማለት ነው...ለዚያም ነው እኮ ገና ትንሿን ደመና ሲያይ...ደመና መና መሆኑን...ደመና የእርገት መሰላል መሆኑን....ደመና መገለጫ መሆኑን ሳያመሰጥር ቂሉ የጨለመ የመሰለው።
....ደቂቃ ተስፋን ካየናት አርቀን
ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን
ደቂቀ ተስፋ ያላት የሚመስለኝ ....እምነትን ነው...የሰናፍጭ ታክል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ማንቀሳቀስ ትችላላችሁ.. .የሚል በቀጥታም ባይሆን የመፅሐፍ ቅዱስ አባባል አለ። እንግዲህ ትንሿ ደቃቃዋ የተባለችው የሰናፍጭ ታክሏ እምነት ናት....እምነት ደግሞ በራሱ በፈጣሪ ላይ ያለን ተስፋ ማለት ነው አይደል....? ስለዚህ እምነት ካለ ነገ ሌላ ቀን ነው ይለናል.....አሁንም እኛ ካሻን በአለማዊም መጠቀም እንችላለን ምክንያቱም ለሁለቱም እንዲያስኬድ ተደርጎ የተሰነደ ቅኔ ነውና...ነገር ግን ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን ያለው....ቅድም እንዳልነው ከላይ የተራራው ጫፍ ክርስቶስ ነው ፍቅር የተባለው ካልን...ደቂቀ ተስፋው እምነት ነው ካልን በእምነታችን ጉልበት የተራራውን ጫፍ ፍቅር ማግኘት የምንችለው በሌላኛው አለም....ስጋ ሞትን ከሞትን በስቲያ ይመስለኛል ። ስለዚህ ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን የተባለው ጥሩ ቀኑ ያኛው አለም መንግስተ ሰማያት ይመስለኛል። አይ በፈጣሪ ከታመንን የነገ አለማዊ ቀናችንን ያሳምርልናል ማለቱ ነው ብላችሁ መረዳትም መብታችሁ ነው ይቻላል።
ከዚያ ዝቅ ይልና ብላቴናው ማንን ወዲህ ተውሶ አመጣ ሃሳቡን ደህና አርጎ የሚያስተሳስርለትን ሎሬቱን.....
ፈራን
ፍቅርን ፈራን
ልጅነት የለገሰንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ በረቂቅ ያለበሰንን
በመለኮት የቀባንን
እውነት ፈራን...ፍቅርን ፈራን
ሲል የህልውናችንን መናጋት...የነፍሳችንን ፈተና...የስጋችንን ብክነት ያትታል።
ፈጣሪ ፍቅርን በረቂቅ አልብሶናል...ለዚያም በልጅነት ጊዜ የኖርነው ኑሮ ምሳሌ ነው..ህፃንነት እኮ ውበት ነው የዋህነት ነው...አሁን ተጣልተን አሁን እንታረቃለን.....


ቅዱስ ቁርአን ምን ይላል መሰለህ......."ከችግር ቦኃላ ምቾት አለ ""



በብቻነት ኑሮ ብቻ ይወደዳል በብቻነት ኑሮ ብቻ የሚለው ቃል...ብቻ ይወደዳል ...

የፀጥታ ዜማ ቅኝት ይወለዳል!!!

ሁላችሁንም ለነበረኝ ግዜ በጣም አመሰግናለሁ...
Forwarded from Natnael Fikru (Natnael Fikru)
እንግዲህ ለዚች ወተን ስለመመለሳችን እርግጠኛ ላልሆንበት ህይወት ነው ክልሌ ....... እንትን የኔ ናት እንትን የኔ ነው ...... የእንትን ብሔር ይውጣ እያልን የምንባለው እርስበእርስ የምንገዳደለው የምንከፋፋው ........ ቢገባን ዛሬ የሆነው ሁሉ ፈጣሪ ሊያስተምርን ያረገው ነው .........
ፓለቲከኛ አደለውም ! ስለፓለቲካ መፃፍም አልፈልግም (አለወድም) !!! አሳቤን ለማካፈል ነው ፡፡
ህይወታቸውን ላጡት መላው ተሳፋሪ ቤተሰብ እና ወገኖች መፅናናትን እመኛለው ! 🙏😞
ፖለቲካ አስጠላኝ ፍቅር ናፈቀኝ😢😢
@wegoch
Barcho ባርቾ Ethiopian Fiction Narration By Samrawit Kebede 2019
netb tube ነጥብ ቲዩብ
Watch "‹‹ደብዳቤው›› DEBDABEW by samrawit kebede 2019" on YouTube
https://youtu.be/-JXPNUQg9PE

@wegoch
@wegoch
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል Digital Magazine(1).pdf
4.9 MB
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት

ቅፅ 1- ቁጥር2

💰ፓኬጅ ከገዙ 0.60 ሳንቲም ብቻ💰

@kendilM
@kendilM
ዳቦ ቤት በራፍ ላይ በራብ የሞተው ሰው😔😔😔
ከደምሰው መርሻ በሶፊ
Worth to share
👉👂👏
@wegoch
@wegoch
@bestletters
2024/09/28 17:29:21
Back to Top
HTML Embed Code: