Telegram Web Link
ይቀጥላል

እኛ ኢትዮጵያንኮ በአንድ አቅማዳ ውስጥ የተከተትን የተለያየን ዘሮች ድምር ነን፡፡ ከሚያጣላን ይልቅ የሚያፍቅረን፣ ከሚያለያየን ይልቅ አንድ የሚያደርገን ብዙ ነገር አለን፡፡ እኛኮ በአንድ ክረምት፣ በአንድ በጋ፣ በአንድእለት፣ በአንድ የጊዜ ቀመር የምንኖር ልዮ ሕዝቦች ነን፡፡ ማጉ ቢለያይ፣ ድሩ ቢለያይ፣ ሸማኔው ቢለያይ፣ ቋጪው ቢለያይ ሁላችንም የምንለብሰው ልብስ ግን አንድ ነው፡፡ ....አዋ አንድነው እዉነት እላቹሃለው የምንረግጠው አፈር፣ ቀና ብለን ስናይ በቀሰተ ደመናው የፈካው ሰንደቅ አላማችን፣ በብዙ ሕዝቦች አንደበት የተቀመረው ቋንቋችን፣ በሰለጠነ ትምህርት ሳይሆን በበሰለ አይምሮ ፣በበለፀገ ቴክኖሎጂ ሳይሆን በጠንካራ እጆች አሻራ የተነደፈበት የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቻችን፣ የሰው ልጅ እኔማንነኝ፡? ከየትስ መጣው? ብሎ ሲጠይቅ የማንነቱን ጥያቄ የሚያገኝበት ሀገር <ኢትዮጽያ>ናት፡፡እኛ ኢትዮጽዊያን ትናንት ለአለም ሁሉ መነሻ ነበርን .......

ዛሬም ነገም....


ይቀጥላል



ከ አሸናፈፍቃዱ/1050/

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
አራተኛ ዙር መሠናዶ ሲሆን ወግ ፣መነባነብ፣ግጥም፣ተውኔት እና ሌሎችም በዋሽንት፣ ክራር ፣መሠንቆ እና ኪቦርድ ጋር ተዋዝቶ የፊታችን እሁድ ምሽት12:00 በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ

@getem
@wegoch
የጥበብ ምሽት ከአንጋፋ አርቲስቶች ጋር
🔰ዕንቁላል ፋብሪካ
ከእምቢልታ ሆቴል ከፍ ብሎ በሚገኘው ገነት መናፈሻ እንድቅትዮን
(የብርሃን ዕለት) በወሩ የመጨረሻ ማክሰኞ መጋቢት ፳፬-፳፻፲፩
ዓ.ም. የጥበብ ድግሱን አሰናድቶ ይጠብቆታል.

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
@getem
በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር።

ይህ ሰው ውሀ ከወንዝ እየቀዳ ቤተ-መንግስት ዘወትር ያመላልስ ነበር። ውሀ
የሚያመላልስባቸው ሁለት እንስራዎችም ነበሩት በነዚህ እንስራዎች
ውሀ እየሞላ ወደ ቤተመንግስት ይውስድባቸው ነበር። ከሁለቱ እንስራዎች አንዱ
ግን ቀዳዳ ነበረው፤ እና ምንም እንኳን ከወንዙ ሁለቱንም እኩል
ውሀ ሞልቷቸው ቢሄድም ቤተመንግስት ሲደርስ ግን አንደኛው እንስራ ሙሉ፤
ቀዳዳ ያለበት እንስራ ደግሞ ጎዶሎ ይሆን ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰውዬው
በሁለቱ እንስራዎች አንድ ሙሉ እንስራ ውሀ፤ በሌላኛው ደግሞ ጎዶሎ ውሀ
እያመላለሰ ለረጅም ጊዚያት ቆየ።
ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ቀዳዳ ያለበት እና ዘወትር እያንጠባጠበ የሚሄደው
እንስራ እንዲህ ሲል ለሰውዬው አቤቱታ አቀረበ፡፡
እንስራው፦ "እኔን እና ጓደኛዬን እየተሸከምክ ውሀ ማመላለስ ከጀመርክ እንሆ
ቆየህ።
ሰባራ ሆኜም እንኳን ስታመላልስብኝ ሰነበትክ አሁን ግን ዘወትር ከጌታዬ ፊት
ጎዶሎ ውሀ እየያዝኩኝ መቅረብ አሳፈረኝ። ጓደኛዬ ዘወትር ሙሉ ውሀ ሲወስድ
እኔ ግን ሁሌ ጎዶሎ ማቅረቡ አንገቴን አስደፈኝ። እናም በኔ ውሀ ማመላለሱ
ቢበቃህ ይሻላል።" አለው። ይህን የእንስራውን አሳዛኝ ንግግር የሰማው ሰውዬ
በማስተዋል ቀዳዳውን
እንስራ እየተመለከተ፡-
ሰውዬው፦ "ዛሬ ውሀ ቀድተን ስንመለስ አንድ ነገር አሳይሀልሁ" ሲል ነገረው።
ውሀ ቀድተው ሲመለሱ ሰውዬው የሚያንጠባጥበውን እንስራ ወደ መሬት
እያስተዋለ እንዲሄድ ነገረው። እንስራውም እንደተባለው አደረገ።
በእሱ በኩል እጽዋቶችን ተመለከተ ፍሬ ያፈሩ አትክልቶችን አስተዋለ
የሚያማምሩ አበባዎችን አየ። በዛኛው እንስራ በኩል ግን ምንም አልነበረም።
ምንም እንኳን ዘወትር በተመሳሳይ መንገድ ቢሄዱም እንደዛሬው አስተውሎ
አያውቅም ነበር።
ሰውዬው፦ "አየህ ወደጄ አንተ እንደምታንጠባጥብ ሳውቅ ባንተ በኩል ዘሮችን
ዘራሁ፤ ዘወትር ካንተ በሚንጠባጠበው ውሀ ጥማታቸውን አራሱ፣ ፍሬ አፈሩ፣
አበቡም። ይህ የምትመለከተው አትክልት ሁላ ባንተ በኩል ብቻ ነው ያለው
ሌላኛውን
እንስራ በምሸከምበት በኩል ምንም ነገር የለም እናም ጥቅም የለኝም አትበል።
ሌላው ቢቀር ደካማ ጎንህ እንኳን ለሌሎች ጥቅም አለው" ሲል አስረዳው።
አንዳንዴ ልዩነታችንን አይተን፤ በንጽጽር ብቻ ጥቅም የለኝም እርባና ቢስ ነኝ
ብለን እናስብ ይሆናል። ሌላው ሰው የቻለውን እኛ ባለመቻላችን ብቻ ጎዶሎ
እንደሆንን እናስባለን።
የሌሎች ብርሀን እንጂ የኛ ስለማይታየን ከጨለማ መውጣት ያቅተናል።
ሰባራው እንስራ ሌላኛው እንስራ ሙሉ ውሀ መውሰዱን ተመለከተ እንጂ
በሱ ውሀ ስንት የእጽዋት ነፍስ እንደበቀለ አላስተዋለም።
እኛም እንዲህ ነን የየራሳችን ብርሀን አለን ነገር ግን የሌላው ሰው
ጭላንጭል ያስቀናናል።
ሌሎች ሙሉ ውሀ መሸከም ቢችሉ እንዳንተ ነፍስ መዝራት አይችሉም።
አንተ
እንደነሱ ሙሉ ውሀ መሸከም ቢያቅትህ ጉድለትህ ሌሎች እንዲያብቡ ያደርጋል።
@wegoch
@teku_melanin
********
This is a story about a lonely, lonely man
He lived in a lonely house
On a lonely street
In a lonely part of the world
But, of course, he had the internet
The internet, as you know, was his friend
You could say, his best friend
They would play with each other every day
Watching videos of humans doing all sorts of things
Having sex with each other
Informing people on what was wrong with them and their life
Playing games with young children at home with their parents

The internet looked at him and said, "Yes, I love you very, very, very, very, very, very much. I am your best friend. In fact, I love you so much that I never, ever want us to be apart ever again ever"
"I would like that," said the man
And so they embarked on a life together
Wherever the man went, he took his friend
The man and the internet went everywhere together, except of course the places where the internet could not go
They went to the countryside
They went to birthday parties of the children of some of his less important friends
Different countries
Even the moon
When the man got sad, his friend had so many clever ways to make him feel better
He would get him cooked animals, and show him the people having sex again, and he would always, always agree with him
This one was the man's favourite, and it made him very happy
The man trusted his friend so much
"I feel like I could tell you anything," he said, on a particularly lonely day
"You can. You can tell me anything. I'm your best friend. Anything you say to me will stay strictly between you and the internet"

And so he did
The man shared everything with his friend
All of his fears and desires
All of his loves – past and present
All of the places he had been and was going, and pictures of his penis
He would tell himself, "Man does not live by bread alone"

And then he died
In his lonely house
On the lonely street
In that lonely part of the world 🖤

@wegoch
@teku_melanin
'ተ'ነ'ፋ'ፍ'ቀ'ው'
.
( ዴቭ)
.
ናፈቃት እሷም ናፈቀችው
ፈለጋት እሷም ፈለገችው
በናፈቀው አይኗ የናፈቃት ፊቱን ልታየው ወደደች…በናፈቀው ጆሮዋ
ያን ስርቅርቅ ድምጹን ልትሰማው ከጀለች…በናፈቀው አፍንጫዋ
ወንድነቱን ልታሸት ናፈቀች…በናፈቀው ከንፈሯ ከንፈሩን ልትስም
ናፈቀች…በእጆቹ ሲዳስሳት በሃሳብ ተሰማት፡፡
.
.
እሱም ፈለጋት በናፈቁት አይኖቹ ዳሌዋን ሊያማትር ፈለገ…በናፈቃት
ጆሮው ትንፋሿን መስማት ናፈቀ…በናፈቁት እጆቹ ጡቶቿን ሊዳስስ
አማረው…ሰውነቱን ከሰውነቷ አጣብቆ ሲይዛት ተሰማው…በጀርባው
በኩል ጥብቅ አድርጋ ስታቅፈው በሃሳቡ ውል አለበት፡፡
.
.
ልክ እንደለመደው በግርግዳ ስልክ አልፎ ሂያጇን ጠርቶ
እንድታወራለት አስማምቶ ደውሎ አስጠራት ያ ቁጠኛ አባቷ ቢያገኙት
ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ አላሰበም አሁን
ማሰቢያው እሷ ጋር ነው፡፡
.
.
እንገናኝ ሲላት በደስታ ልቧ ደለቀ የናፍቆቷን ረሃብ እስከሚተርፋት
ልታጣጥም ሞልቶ እስከሚተርፋት ስንቅ አድርጋ ልትወስደው
ቋመጠች፡፡ የለበሰችውን ቢጃማ አወላልቃ የሚወደውን ሮዝ አጭር
ጉርድ ከሚወደው ጠቆር ያለ ኮት ጋር አመሳስላ ለበሰች፡፡ ሁሌ ልበሽ
የሚላትን ፍላት ትንሽየ ጫማ አጠለቀች የገዛላትን ሮዝ ሊፕስቲክ
በስሱ ተቀባች ጸጉሯን እሱ እንደሚወደው አስተካከለች፡፡ከፊቷ
በቆመው መስታወት ራሷን ተመለከተች እሱ የሚወዳትን መሰለች
እሱን እሱን እንድትሆን ትሻለች እና፡፡
.
.
የወዳደቁት የቆሸሹ እና ያልቆሸሹ ካልሲዎች ሰበሰበ ተጠርጎ
የማያውቀውን አቧራ የሞላውን ቤቱን አፀዳዳ የተመነቀረውን አልጋ
በወጉ በወጉ አስተካከለ ትንሿን ቤቱን በሰንደል ጭስ አመጋት ጥሩ
ሽቶ ጨመረባት እሷን ይፈልጋል እና የቀጠሮውን ሰአት አየ መምጫዋ
ሲደርስ ልቡ መምታቷን ጨመረች፡፡
.
.
በትንፋሿ መቆራረጥ በአካሄዷ መሮጥ በናፍቆት መረገጥ ልቧ ክፉኛ
መታ ሰውነቷን የማታውቀው ስሜት ወረራት እሱ ጋር ለመድረስ……
እየደረሰች ናፈቀች……እናፈቀች ተጓዘች……እየተጓዘች ደረሰች፡፡
ስትደርስለት ደስ አለው ተቃቀፉ አንገቱ ስር ሽጉጥ አለች አይኖቿን
ጨፍና በባቢሎን ግንብ እንደታጠረች በሽህ ሰራዊት እንደተከበበች
ቆጠረች ምንም መቶ ከዛ ግንብ ሊያስወጣት እንደማይችል
ደመደመች፡፡
.
.
እንዳቀፋት ሰውነቱ ሞቀ ከፀጉር እስከጥፍሩ በማያውቀው ስሜት
ሰውነቶቹ ቆሙ…እንዳቀፋት አልጋ ላይ ወደቁ…እንደ እንዝርት
አሾራት……እንደ ዳርት ወረወራት……እንደ እንዝርት ሾረች እንደዳርት
ተወረወረች እሳት ሆነ ክሰል ሆነች……ክብሪት ሆነ ጭድ ሆነች ……
አራገባት ነደደች በነደደው ገላዋ መልሳ አቃጠለችው……እንደፈለገው
ሆነችለት አመማት ደስ አለው አቃሰተች ጨመረ ክብሯን ሰጠችው
ክብሯን ወሰደ፡፡
.
.
ደስ የሚል ስቃይ አመማት እሱ ግን ከፋው መውደዷ ጨመረ ሌላ
ሴት አሰበ አብራው መኖር ፈለገች ከቤቱ ሊያስወጣት ወሰነ በፍቅሩ
ተጎዳች ያደረገውን ጀብዱ ለጓደኞቹ ነገረ እነሱም አደነቁት ከዛን ግዜ
በኋላ የማታውቀው የሴት ድምጽ አልሰማችም ቀጠሮም አልያዘችም
ቤት ውስጥ ዘግታ ተቀመጠች ወንዶች እንደዚህ ናቸው አለች
መቅረብ አልፈልግም ብላ ሁሉንም ኮነነች ሴትነቷን የሚፈልግ ወንድ
አግኝቷት ወንዶችን ሁሉ ጠላች እሱም ስራውን
ተያይዞታል እሷም ወንዶችን መውቀስ መጥላት ቀጥላለች፡፡
.
.
ወሰነች ማድረግ አለብኝ አለች የአባቷን ሽጉጥ ሰረቀች ወደ ቤቱ
ሄደች የዛን ግዜ የነበረው ሽታ አሁንም አለ የዛን ግዜው ሰንደል
ከውጭ ይሸታል ልክ የዛን ግዜ እንደነበረው የሲቃ ድምጽ……
ከፍታው ገባች ራቁቱን አየችው…እንደገና ሌላ ራቁት አየች
አላመነታችም ሽጉጧን አወጣች አቀባበለችው……
.
.
ከነመለመሉ ስለወንድ ልጅ ብሎ ለመነ እሷ ግን
አልሰማችውምየጥይት ጩኸት አካባውን ረበሸው ወፎች በድምጹ
ደንግጠው በረሩ……
አቅፏት አለቀሰ ባደረገው ነገር ፀፀት ውስጡን ተቆጣጠረው ልጅቷ
ራሷን አጠፋች
ለወደደችው ፍቅር ልታስፈራራው ይዛው የመጣችውን ማስፈራሪያ
ራሷን ገደለችበት፡፡
እስር ቤት እራሱን ዘጋ ከህይወት ገጽም እስኪሰረዝ መጠበቅ
አልፈለገም ሞትን በሞቷ አብሯት ሊሞት በቁሙ ሞተ ………
ህይወት ግን አታቆምም አሁንም የሚሸኙትን ትሸኛለች የሚተኩትን
ትተካለች ፡፡

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 4.pdf
4.5 MB
📠 Melkam74 ቅፅ 1 ቁጥር 4

💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.27 ብቻ 💰
Fight autism home teacher for autistic children በኦቲዝም ለታመሙ ልጆች ብቻ:

በኦቲዝም ለተጠቃ/ች ልጅ ድጋፍ፣ ክትትል እና የቤት ዉስጥ ትምህርት ይፈልጋሉ?
ኦቲዝም ምንድን ነው?
ኦቲዝም በህፃናት/ልጆች የነርቭና የእድገት ሂደት ላይ ውስንነትን በማስከተል ልጆቹ ከሰዉ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነትና የመግባባት ክህሎት እንዲሁም የመረዳት ችሎታ የሚጎዳ/የሚቀንስ ህመም ነዉ።
ኦቲዝም ለሁለንተናዊ የህፃናት/የልጆች እድገት አስፈላጊ የሆኑ ማህበራዊ ግንኙነቶችን እንዲሁም የልጆቹን ግለሰባዊ ባህሪያቶች ይጎዳል።
መፍትሄው ምንድን ነው?

ምንም እንኳ እስከ አሁን ድረስ ኦቲዝምን ፈፅሞ ሊያድን የሚችል ህክምና ባይኖርም ልጅዎ ላይ የሚታዩትን የህመም ምልክቶች በመቀነስ የልጅዎን እድገትና የትምህርት አቀባበል ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል።
ይህንንም የልጁ/ቷን ማህበረዊ፣ የመግባባት ክህሎትና ባህሪ ላይ አትኩረው በሚሰሩ ባለሙያዎች በሚተገበሩ ተከታታይ እና የተዋጣላቸዉ መርሃግብሮች ማሳካት ይቻላል።
ከምንሰጣቸው ድጋፍ፣ ክትትል እና ትምህርት መካከል፦
የመግባባት ክህሎት፦ የኦቲዝም ተጠቂ ልጅን የማህበራዊ እና የቋንቋ ችግሮች ላይ በመሥራት የመግባባት ክህሎትን ማጎልበት።
የባህሪ ለዉጥ፡- የኦቲዝም ተጠቂ ልጅ ሊኖሩት/ዋት የሚችሉትን አስቸጋሪ ባህሪያትን በመቀነስ እና መልካም ሥነምግባርን በማስረፅ ተፈላጊ የባህሪ ለዉጥ ማምጣት።

ትምህርት፡- ኦቲዝም ላለባቸዉ ህፃናት በጥናት በተቀረፀ የትምህርት መርኃግብር እና ለዚሁ አላማ በተዘጋጁ የትምህርት መርጃ መሳርያዎች በመታገዝ የቤት ውስጥ ተጨማሪ ትምህርት በመስጠት የልጆቹን የትምህርት አቀባበል ማሳደግ።

ቤተሰብ ተኮር ድጋፍ፡- ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የኦቲዝም ተጠቂ ልጅን የመግባባት ክህሎት እና ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር በምን መልኩ መቅረብ እና አብረዉ መጫወት እንዳላባቸው ማስተማር።

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ይደውሉ፦
0913011134
0910916602

@wegoch
@gebriel_19
*********
ህይወት ተከታትለው የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ድንገተኛ ለውጦች ድምር ናት፡፡
ለውጦችን ለመታገል እና ለቋቋም አትጣሩ፡፡በራሳችሁ ላይ ሀዘን ከመጥራት በቀር የምታተርፉት ነገር የለም እውነታ እውነታ ይሆን ዘንድ ተውት
ነገሮች ሁሉ ተፈጥሮአዊ መንገዳቸውን ተከትለው
እንደፈቀዱት እንዲፈሱ እድል ስጡዋቸው ሁሉም ነገር ባለበት ሁኔታ ደስ
ይበላችሁ፡፡
ይህን ስትረዱ መኖር ይቀላችኋል፡፡

🖋በሄደው አትናደድ፤ በመጣውም አይግረምህ፤
ዛሬ የመጣውም ነገ ይሄዳል።
ትላንት የሄደውም ነገ ይመጣል።
ሁሉም እንደ ሰአቱ ይለዋወጣል።
አንተ ግን ቅንነትህን አትጣል!"😊

🖍 ከታዋቂነት ከዝና ይልቅ ልትጨነቅ የሚገባህ ለባህርይህ ነው
ምክንያቱም ዝና ሌሎች አንተ ነህ ብለው የሚያስቡት ነገር ሲሆን ባህሪ ግን አንተ በትክክል የሆንከው ነገር ነው ።

🖌ከእርቃን ሰውነት ይልቅ እርቃን ነብስ ታሳዝነኛለች!
ገላን በብጣሽ ጨርቅ መሸፈን ይቻላል
ባዶ ነብስ መሸፈን መሙላት ግን ከባድ ነው።

@wegoch
@words19 💖
የሚስቴ ሰርግ ማስታወሻ(ልዑል ሀይሌ)
......................................................
ውዴ! ምንም እንኳ ቁመቴ አጥሮ ለሌላ ሲድሩሽ አማትሬ ማየትቢሳነኝም
በቤታችሁ አጥር ተንጠላጥዬ ናፍቆቴን ልገልፅልሽ እንደምንም የደረሰውን እጄን
አወዛውዤ ነበር።ነገር ግን የአባትሽ ከዘራ ከአንቺ የናፍቆት ምላሽ ቀድሞ እጄን
ስለሰበረኝ ካንቺ በፊት ስለ አባትሽ ከዘራ ልፅፍ ቀሪዋን ግራ እጄን
አለማምጃለሁ!(ለካ አሁን ሲገባኝ የቀኝ እጅ የቀለም ቀንድ የግራ እጅ መሃይም ኖሪያለሁ)...እውነት ውዴ!..አባትሽ አባትሽ ባይሆኑ እንዲህ እላቸው ነበር። "ምነው እጄን ነሱኝ ልጆን ሰላም ልላት አንድ እጄን ሳነሳ፤ ከዘራዎት ነው ወይ
ለልጆ የተዳረ ያ ጎበዝ ጎልማሳ።"
.
እውነት ውዴ አባትሽ አባትሽ ባይሆኑ እንዲህ እላቸው ነበር
"ይኸው ዕድሜ ለእርሶ
ዱላዎት ሰብሮኛል፤
ለድብደባ ሱሶ ነገ ልምጣሎት ወይ አንድ እግሬ ቀርቶኛል።"
ነገር ግን የአባትሽን አባት መሆን ልሽር አይቻለኝምና።ወደ ከዘራው
ተሸጋግሬ
ልወቅሰው ተነሳሁ። ውዴ! ያ ከዘራ የአባትሽ ሆነ እንጂ ሌላ ከዘራ ቢሆን
እንዲህ
ብዬ ቅስሙን ልሰብረው ተነስቼ ነበር(አ
ይጣል የከዘራ ቅስም!)
"ምን አይተህ ነው ከ`ጄ
አጥንት የሰበርከው
ሲቀር ተከፋህ ወይ
አምና የለመድከው"
ዳሩ ምን ያደርጋል ከዘራው የአባትሽ ስለሆነ ትቼዋለሁ...ለነገሩ ምን
አለፋኝ
አጥር ዘልዬ እጄን እንዳነሳ፤ አባትሽም ከዘራቸውን እንዲያነሱ ምክንያት
የሆንሺው አንቺ አለሽ አይደል?! ብዬ ወዳንቺ ልዞር አሰብኩኝ። እውነት
ውዴ!...አንቺ አንቺን ባትሆኚ እንዲህ ብዬ ባለማመድኳት ግራ እጄ
ልፅፍልሽ
አስቤ ነበር
"ናፍቆት አንገብግቦኝ እጄን ባነሳልሽ፤
የአምናው ክህደት ዳዴ
በአባትሽ ከዘራ እግ፡ር አወጣልሽ፤
ክህደትሽስ ይሁን ይቁም እግር ያውጣ፤
ልብ ይሰበራል ወይ
ፍቅሩን ሊገልፅልሽ ለሰርግሽ ለመጣ።"
ምን ዋጋ አለው?! አንቺ አንቺ ሆነሻል...
ምን ያደርጋል!?..ከዘራውን መንካት አባትሽን፤ አባትሽን መንካት አንቺን፤
አንቺን
መንካት የገዛ ራሴን ህመም መቀስቀስ ስለሚሆንብኝ ልተወው
ተገድጄአለሁ! ...ምክንያቱም አፈቅርሻለሁ!!..የፍቅሬ ልክ ክደሽኝ ሄደሽ
እንኳ
በሰርግሽ ዕለት በአጥራችሁ ተንጠልጥዬ የአባትሽ ከዘራ ሲሳይ ሆኜ
በመመለስ
ገልጫለሁ። ያወዛወዝኩትን እጄን በቅፅበት አይተሽው ከሆነ ለስንብት
እንዳነሳሁት ታውቂልኝ ዘንድ አሳውቅሻለሁ...(የሚቀጥል...)


፲፰-፩-፳፻፲፩
ከለሊቱ ፭ ሰዓት ከ ፲፭

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
ሲገባኝ ከታች ያሉት ጥያቄዎች ነጋችንን ያሳያሉ!
ከማን ጋር ነው የምትውሉት?
የት ነው ምትውሉት?
ምን እያወራችሁ ነው የምትውሉት?
እሱ ነገር ሊያሳስበን ይገባል!

@hanahailu
@wegoch
🔝


"ኢትዮጵያን አናውቃትም"

**** **** ****
*ኢትዮጵያን አናውቃትም! አውቃታለሁ የሚል ደፋር ነው። ከምናስባት ሁሉ በላይ የማትገመት ሀገር ናት።
እኛኮ ያልሞከርነው ክፋት የለም። እንደ ሂትለር ዘር ተኮር ስብከትን አስፋፍተናል። እንደ አይሁድ ሰውን እርቃኑን ሰቅለናል፤ በድንጋይ ወግረን ገድለናል። እንደ ስታሊን ቁልቁል ሰቅለን ገርፈናል፤ አሰቃይተናል።
*እኛ ኢትዮጵያውያን ሩዋንዳን ከበተነው የዘር ተኮር ጥላቻ ስብከት በላይ ተሰብከናል፤ ሶማሊያን መንግሥት አልባ ካደረገው በላይ ችግር ተፈጽሞብናል፤ ሶሪያን ካፈራረሰው በላይ ሴራና ግጭት ተከናውኖብናል። ተከፋፍለንና ተበታትነን እንድንጠፋ እስከመገንጠል መብት ተሰጥቶናል። ይህ ሁሉ ተሞክሮም ግን አለን። ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ልዩ ምሥጢር ካልሆነ በቀር ማነው የሚያኖራት?
*ሳስበው ክፋትን ሁሉ ሞክረን ስለጨረስን አሁን መልካም ነገር የሚሞከርበት ጊዜ ላይ ነው። ካሁን በኋላ በዚህች ሀገር ላይ ያልተሞከረ አዲስ ክፋት ፈልጎ ሊያገኝ የሚችል ስለማይኖር ሁሉም በጎ በጎውን ማሰብና መሥራት መጀመሩ አይቀርም። ለኢትዮጵያ የተሻለ ጊዜ እየመጣ ነው።
*"ኢትዮጵያን አውቃታለሁ" የሚል ሰው ድፍረቱ ይገርመኛል። እኔ እንደማላውቃት ነው ማውቀው። ኢትዮጵያን አናውቃትም። ፈጽሞ አላስተዋልናትም። ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት ሀገር ስለሆነች ከሌላ ሀገር በተቀዳ ሐሳብ ልትመራ አትችልም። ማንም ሀገር የሌለው የራሷ የሆነ ጥበብና እውቀት አላት። በድህነት መነፅር ስለምናያት ነው እንጅ... ልዩና ማንም የሚመኛት ሀገር ናት።
*አንዳንዱ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀኛል፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የምታገለው፣ ሕዝቡ ከእኔ ጋር ነው..." ሲል ይሰማል። ምን ማለቱ ነው? የትኛው ሕዝብ? ፌስቡክ ላይ ያለው? ሚዲያ ያለው? ፖለቲከኛው? ሃይማኖተኛው? ወይስ የቱ? መለየት አለበት። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀውም የሚሰማውም ሰው ያለ አይመስለኝም። እያስተዋልን እንናገር።"

# ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ
የእመጓ ዝጎራ እና መርበብት ደራሲ
ኅዳር 5/2011 ዓ/ም በራስ ሆቴል አዳራሽ ከተናገሩት የተወሰደ

@wegoch
"አዲስ ባሬስታ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ!" [Arts Tv World] 16k
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ #92-02 | በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
"አዲስ ባሬስታ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ!" (Arts Tv World)
👤 ጦቢያ ግጥምን በጃዝ #92-02 | በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር

🕜 11:50
💾 10.97 MB

ግጥም ብቻ

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
👆👆👆👆


አድምጧት አጭር፣አስተማሪና አዝናኝ ወግ!!

ምንጭ
ደራሲ :-አሌክስ አብርሀም
ከ "ዙቤይዳ" መጽሐፍ
ገጽ 201 የተወሰደ
ርዕስ:- "እግር በእግር"
ተራኪ :- ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
ሚያዚያ 2011 WOLDIYA UNIVERSTY

@wegoch
@wegoch
ሦስት ሙሉ ጥሪ ጨርሶ በአራተኛው በሰላም ሊሆን እንደማይችል ገምቼ ነበር
ስልኩን ያነሳሁት። 'ስልኬንም ማንሳት ደበረሽ?' ሲለኝ ተናደድኩበት። ደብሮኝ ሳይሆን ፡ ልትደውል የሚያስችልህ ፡ የቀረህ ነገር እንደሌለ ስለማውቅ ነው ማንሳቱን ያልመረጥኩት። አሁንም ተደጋጋሚ ሲሆንብኝ የሰላም ስላልመሰለኝ ነው። መጀመርያ ግን ሰላምታ አይቀድምም? ። ገርሞኛል ድፍን 60 ቀናት ተቆጥረዋል ሳንደዋወልም ላንገናኝ ከተስማማንም። "በዚህ ፍጥነት እንዲህ ትረሺኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም" አለኝ። ድፍረቱ! 'ተውኩህ እንጂ አልረሳውህም'
"ያው ነው ፣ ጭራሽ ነው ያቆምሽው፣ መደወሉንም ፣ መልዕክት መላኩንም።
ጉድሽን ልየው ብዬ ነበር ዝም ያልኩሽ" አለኝ። ስልክ ማውራት የማይመች ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩኝ ፡ ይቅርታ ጠይቄው መልሼ እንደምደውልለት ነግሬው ስልኩን ዘጋሁት። ገርሞኛል ፣ ምን ነበር የጠበቀው? ተስማምተን አልነበር እንዴ የተለያየነው? ሀሳቡ ከርሱ አልነበር የመጣው? ከሁለት ወራት በፊት የሆነው እንዲህ ነበር ... ሰሞኑን እየሆንን ያለነው ነገር ምንድነው? ብዬ ጠየኩት። መክሰስ በልተን አስተናጋጁ እቃዎቹን ካነሳልን በኋላ "እንዳትለምጂኝ እያደረኩ ነው " ሲለኝ ለአፉ እንኳን አልከበደውም! በሰዓቱ ድንጋጤ ብቻ አልነበርም የተሰማኝ ፣ በተቀመጠበት ትቼው መሄድ
ፈልጌኣለሁ ፣ ግን ደሞ ፈራሁ ። መለየትን እፈራለሁ ፣ ተላምዶ መለያየትን ፣ ጨለማን በህይወቴ በጣም ከምፈራቸው ነገሮች ቁጥሩ አንድ ነው። ማጣትን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ፡ ለዓይን ምንም እንደማይታይ ዓይነት እፈራዋለሁ።
ዓይኔን እያየ "እንዳትለምጂኝ" ሲለኝ በፈጠረብኝ የመደናገር ስሜት ብድግ ብዬ ብሄድ ተመኝቼ ሁላ ነበር። ግን ድጋሚ ባላገኘውስ ብዬ ፈራሁ ፣ አጎንብሶ ስልኩ ላይ አፍጥጧል። አየዋለሁ ፡ በየመሃሉ ከስልኩ በሚያየው ነገር ይመስላል ፈገግ ይላል መች ነው እንደዚህ የሆነው? ሴትነቴ እሱን አለማስደሰት የጀመረው መች ነበር? ከሁለት ሳምንት በፊት "ካንቺ ጋር ስሆን የማገኘውን ደስታ እስከዛሬ የትም
አግኝቼው አላውቅም" አላለኝም ነበር? ጆሮዬ ነው የፈጠረው፡ ወይስ ብሎኝ
ነበር? ድንገት መደንገጤንም ፡ ንዴቴንም ዋጥ አደረኩና 'ዎክ እናድርግ የኔ ፍቅር ?' አልኩት ልምምጥ በሚመስል ቅላፄ "ውይ ደክሞኛል ዛሬ ፣ ታክሲ ያዥና ሂጂ" ሲለኝ በድንገት እምባዬ ከየት መጣ? ጉንጮቼን አልፎ በአንገቴ በኩል አድርጎ እየወረደ መሆኑን እንዴት አላስተዋልኩትም? አሁንም ስልኩ ላይ እንዳቀረቀረ ነው። ፍቅሬን ምን ነካው? ባለፈው ፡ የጥር ሚካኤል ዕለት አልነበር ፡ ከጥምቀት መልስ ቤታቸው ሄደን እናቱን እየተፍለቀለቀ '' ወደፊት የማገባት ሚስቴ እሷ ናት'' ብሎ ያስተዋወቀኝ? እናቱ ከግንባሬ እስከ አንገቴ አገላብጠው ስመውኝ አልነበር? እሺ በጣም በቅርብ አልነበር እንዴ ከውጭ ከመጣው ወንድሙ ጋር ለ 3 ቀናት ደብረዘይት ሄደን አሪፍ ጊዜ አሳልፈን የመጣነው? ፍቅሬ የት ሄደ? ሰሞኑን በስልክ ጭቅጭቅ ስላበዛን ነበር ዛሬ የተገናኘነው። መታገስ አለብኝ ፣ ንዴቴን መቆጣጠር ፣ ተረጋግቼ ማዋራት አለብኝ። ውሃ ልጠጣ? ወይስ አየር በደንብ እየሳብኩ ላስወጣና ራሴን ላረጋጋ? ምን ነበር ራስን ለማረጋጋት የሚደረገው? ብድግ አልኩና መታጠብያ ቤት ሄጄ ራሴን አረጋግቼ ተመለስኩ። የሰሞኑ ሁኔታህ ምንም አላማረኝም የኔ ፍቅር ፣ ምንድነው የሆንከው? ልታሳውቀኝ የምትፈልገው ነገር እንዳለ ስለነገርከኝ ነበር የመጣሁት። ግን ደሞ
ለማውራት ፈቃደኛም አይደለህም ፡ ምንድነው የሆንከው? ብዬ ጠየኩት።
ምን ሆኜ ነው የምለማመጠው? ትዕግስት ነው ወይስ ፍራቻ እንዲህ
የሚያደርገኝ? ቀና አለና ከአንገቱ ተመለከተኝ። ዓይኔን ግን ይሸሻል "ይሄን ስልሽ አዝናለሁ ምንም የምነግርሽ ምክንያት የለኝም ። ግን ግንኙነታችን እዚሁ ላይ ቢያበቃ ደስተኛ ነው ምሆነው" አለኝ። ሆዴን ለምን ቆረጠኝ? ምንድነው የተበጠሰው ከውስጤ? ለደቂቃዎች ያህል ምንም አልመለስኩለትም : ዝምታዬ ያስፈራው ይመስል በየመሀሉ እየሰረቀ ያየኛል።
ከብዙ ዝምታ በኋላ፡ አንተን የሚያስደስትህን ነገር እኔም አደርጋለሁ።
ምክንያትህን እንድትነግረኝም አላስጨንቅህም። ሀሳብህን አከብራለሁ። በነበረን ጊዜም በጣም ደስተኛ ነበርኩ ፡አመሰግናለሁ የኔ ፍቅር። ብዬ ከንፈሩን በስሱ ስሜው ደህና እንዲያድር ተመኝቼለት ነበር በተቀመጠበት ትቼው ወደ ቤቴ የገባሁት። መሰናበቻ ነበር!
ረጅም መንገድ በእግሬ ተጉዣለሁ ፣ ካለፈው ህይወቴ እንደተማርኩ የገባኝ የዛን ምሽት ነበር። በማግስቱ ጧት ለአለቃዬ እንዳመመኝ እና ስራ እንደማልገባ መልዕክት በስልኩ ትቼለት ስልኬን አጠፋሁና ለሁለት ቀናት ከቤቴ ሳልወጣ ከራሴ ጋር ሆንኩኝ። በ 3ኛ ቀኔ በጧት ተነስቼ ቁርሴን በአግባቡ ተመግቤ ቆንጆ ሆኜ ወደ ስራ ገባሁ። ብርታት አገኘሁ፣ ነገ የተሻለ አዲስ ቀን እንደሆነ አምኜ ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ። ፍፁም ሰላማዊ ሆኜ መኖር ጀምሬአለሁ። እና ዛሬ በምን ትዝ ብዬው ምን ፈልጎ ነበር የደወለው? እኛ እንደዚህ ነን። በቃ የምንሸዋወድ ሰዎች ነን። የውስጣችንን ስሜት ፣ ዕውነት የሆነውን ስሜታችንን ማዳመጥና መኖር የምንሸሽ ፣ በትንሽ ክፍተት ደስታችንን የምናጣ . . . ስንቶቻችን ተላልፈናል? እኔ ግን...መልሼም አልደውልለትም።ቢደውልም የሚቀየር ነገር አይኖርም። እኔና እሱ የአብሮነትን መንገዳችንን ስተናል። ምናልባትም የፍቅሬን መጠን መፈተኛ መንገድ መስሎት ይሆን? ቢሆንም ግን ስህተት ሰርተናል፡ በቃ ተላልፈናል ...


@wegoch
@wegoch
@paappii

By ጠርሲዳ ከበደ
በአንድ ዘመን ላይ ኖረውልን ቢሆን ኖሮ ማንም አይደርስብን!

👉 መከላከያ ሚኒስቴር
አሉላ አባ ነጋ 👊

👉 የቴክኒዮሎጂ ሚኒስቴር
አፄ ምንይልክ 👌

👉 የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
አፄ ሐይለስላሴ 🙏

👉 አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን
ዋና -አቶ መለስ ዜናዊ
ምክትል -ታማኝ

👉 የመንግስት ቃልአቀባይ
ዶር ብርሃኑ ነጋ

👉 የፌዴራል ፖሊስ ዋና አዛዥ
ኦቦ አብዲሳ አጋ

👉 የሁሉም ልዮ ሃይሎች ዋና አዛዥ
በላይ ዘለቀ
ምክትል -ዋለልኝ

👉 ትምህርት ሚኒስቴር
ሼኽ በክሪ ሰበሎ
ምክትል - ነጋድራስ እሸቴ

👉 ኤኮኖሚ ምኒስቴር
አትሌት ሃይሌገብረስላሴ
ሼኽ አሊ አል አሙዲን

👉 ውሃ እና ፍሳሽ የበላይ ሃላፊ
ጌታቸው አሰፋ 😊

👉 ማዕድን ሚኒስቴር
መለስ ዜናዊ

👉 የሰላም ሚኒስትር
ሃይለማርያም ደስ አለኝ 😃

👉 ሕዝብ ግንኙነት ሚኒስቴር
ዋና - ለማ መገርሳ
ራስ አሊ (ወሎ )
ምክትል -(የጅማው) አባጅፋር

👉 ሰብሳቢ- ክቡር ነጋሶ ጊዳዳ

👉 ፀሃፊ-አይተ እቁባይ በርሄ

👉 ማስታወቂያ ሚኒስቴር
ጃዋር መሃመድ
ደሳለኝ ጫኔ

👉 የሶማሊያ እና ጎረቤት ሃገሮች ጉዳይ አማካሪ
ኦቦ ዳውድ ኢብሳ

👉 የከተማ ፕላን
አፄ ፋሲል

👉 የየሰሜን ዋልታ ጫፍ አምባሳደር
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

👉 ጠቅላይ ሚኒስቴር
አብይ አህመድ

👉 ፕሬዝደንት
መንግስቱ ሃይለማርያም 💪

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Abeba birhanu
"አንድ ግጥም አንድ ወግ" በልዑል ሀይሌ እና አዱኛ አስራት

አይጠራጠሩ ይወዱታል!!

https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
#የድሮ_ጓዴ
አቅራቢ :ትንቢት ዳንኤል
ደርሰት ፦ትንቢት ዳንኤል

@wegoch
@wegoch
ግጥም ብቻ
ሰልችቶናል! (ከአጠገቤ ለተቀመጠችዋ የተፃፈ)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከአሰልቺው መንገድ... እንደ ቢንቢ ጆሮህ ስር እየተከተለ ጥዝዝዝዝዝዝዝዝዝ እያለ የሚመታህ የሰሞኑ ፀሀይ... እረፍት ቢስ ሀሳብ እና ረጅም የህይወት ጉዞ ለመገላገል ወደ ቤት እየሮጥኩ ነው፡፡ ግድግዳ እና ጣራ ከሚባል ከሀሳቤ ጭንቀት ሊያድነኝ ወደማይችል ውሸት እሮጣለሁ፡፡ ጭንቅላቴ አካባቢ የሆነ ጭምቅ የሚያደርግ ስሜት ይሰማኛል... ህመም ብርቅ ባልሆነበት አለም ውስጥ ቢጨምቀኝ ቢጠምቀኝ ለዚህች አለም ህመም ጩኸት አላዋጣም! የሆነ ራሴንም እያመመኝ ነው... እኔንጃ አልገረመኝም! ይመመኛ! አስራ ስንት ሺህ ግዜኛ ነው ራሴን ያመመኝ? ሌሎቹን ምን ሆንኩ? ምንም! ለዚህች አለም ጩኸት እና 'እህህህህ' የሚል የህመም ድምፅ አላዋጣም! ሰልችቶኛል!

አንዳች ከባድ ሸክም ከጀርባዬ አዝያለሁ... ለሰው ይታያል ወይስ እኔ እየመሰለኝ ነው? ምን እንደሆነ እንጃ... ልነካው እጄን ወደ ጀርባዬ ስሰድ ጣቶቼ ምንም አይነኩም... በቃ ተሸክሜው ዞራለሁ... ስተኛ ተሸክሜ ፣ ስቀመጥ ተሸክሜ ፣ ቸርች ስሄድ ተሸክሜ ፣ ስመለስ ተሸክሜ ፣ በመሰላቸት የሆነ ሌላ ሰው የፈነቀለውን ክብ ድንጋይ ጠልዛለሁ፡፡ ምን ሆናለሁ?
ወደ ቤቴ የሚወስደኝ ታክሲ ጋር ስደርስ ሰልፍ አለ፡፡ ስሰለፍ ተሸክሜ... ሰልፍ ሰልችቶኛል... ምንም ሰልችቶኛል፡፡ ጩህ ጩህ አለኝ! አይይይ! ለዚህች ብጥብጥ አለም ጩኸት አላዋጣም፡፡ ሰልፉ ረጅም ነው... ሄጄ ከሰልፉ ፊት ለፊት ቆምኩ (ከሰው ጋር መጨቃጨቅ አልሰለቸኝ ይሆን?) ዝም ብዬ ቆምኩ! መኪና መጣ... እንደ መብቴ ገባሁ፡፡ ማሸነፌ ይሆን? ሳሸንፍ ተሸክሜ ይሆን?

አንድ ወጣት መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች፡፡ አላየሁዋትም... መቁለጭለጭ ሰልችቶኛል... የማያውቁትን ለማወቅ መጣር ሰልችቶኛል፡፡
መሄድ ጀመርን... በመስኮቱ ልታምር ስንዝር የሚቀራትን ጨረቃ እያየሁ ነው፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ ዞሬ ሳያት እያለቀሰች ነው... ቆንጆ ናት... ሳያት አፈረች... ማፈሯ እንባዋን አልያዘውም ከደገፈችበት እጇ ስር አንድ ዘለላ እንባ መስመር እየሳለ ወረደ፡፡ ዞርኩ... በአይኔ ሽንፈቷን ልሰብካት አልፈለኩም... ከማልቀስ በላይ ሲያለቅሱ መታየት ያስለቅሳል፡፡ መስኮቱን ከፈትኩላት... ንፋሱ እንባዋን እንዲያደርቀው አስቤ ነው? ማልቀሷ በምን ይታወቃል? እንባዋን ካደረቅኩባት... ሀዘኑን በእንባው መጠን በሚለካ ህዝብ እና ባህል መሀል እየኖሩ የሰው እንባ ማድረቄ ያስጠይቀኝ ይሆን? ምናልባት ለዚህች ስግብግብ አለም እንባ እያዋጣች ይሆን?
እኔንጃ! አለማወቄን ይሆን የተሸከምኩት?

ምን ሆና ይሆን? ምን ልበላት ብዬ አሰብኩ...ምናልባት ከእጮኛዋ ጋር ተጣልታ? በዚህ ፀብ ዘመን አለመጣላት እኮ ነው የሚከብደው፡፡ ወይ ዘመድ ሞቶባት? ወይ የአክስቷ ልጅ ሰድባት... ወይ አክስቷ? ጓደኛዋን ከሌላ ሴት ጋር አይታው? ምናልባት እሷ ያላወቀቻቸው አራት ሌሎች ሴቶች ይኖሩታል... እሱን ብታውቅ የበለጠ ታለቅሳለች? ነው ወይስ እንደ እኔ ሁሉ ስልችት ብሏት ነው?
እንደ ፈላስፋው ኒቼ ከእግዜር ትግል ገጥማ ደክሟት ነው?
"a peace is a buffer zone between two wars" እንዳለው ሆና ይሆን? ከሆነችስ ጦርነቷ ወይስ ሰላሟ የሚያስለቅሳት?
እንጃ! አለማወቅን ብቻ ነው ለአለም የማዋጣው፡፡ መውረጃዬ ደረሰ... እጇን ያዝኳት... በዚህ በሀዘኗ ሰዓት ባለ ውለታዋ ለመሆን እየሞከርኩ ነው? እኔንጃ! ሰልችቷታል ከተደገፈችበት ቀስስ ብላ ዞረች፡፡
አፌ ላይ ያለውን አወራሁ "ምን እንደሆንሽ አላውቅም! ሰው እያየሽ አታልቅሺ፡፡ አይዞሽ!" በሆነ አይነት አስተያየት እያየችኝ ነው... ሸክሜ ታይቷት ይሆን እንደዚህ ምታየኝ?

"ወራጅ" አልኩ ክንዷን ለቅቄ... ሰው ፊት ስለ እምባዋ አውርቼ አሳፈርኳት? እንጃ!
ወረድኩ... ከኀላዬ ወረደች... ቀስስ ብላ መራመድ ጀመረች... ቆሜ አየሁዋት፡፡ ተሻገረች... ውስጤ ሂድ አፅናናት ይለኛል... ነው ወይስ ሌላ ፍላጎት አለኝ? አየኀት... ቀስስ ብላ ትሄዳለች፡፡ እሷም ሸክሟ ከብዷት ይሆን?
ለዚህች ልጅ የኔ ቃል ምኗ ነው? ዞሬ ሄድኩ...
አሰብኳት... አሳዘነችኝ... ከእህት የቀረበች መሰለችኝ... የሴት እምባ ይከብደኛል የሚፈስ የሀዘን አሎሎ...
ሄድኩ... ራቅሁ.... ቀስ ብሎ ከአንዱ አይኔ ስስ እምባ ተንከባለለ
ለዚህች ልጅ የኔ የምፅዋት እምባ ምኗ ነው?
ሰልችቶኛል...
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
2024/09/28 15:27:32
Back to Top
HTML Embed Code: