Telegram Web Link
እኔ ዘረኛ ነኝ! ለጳጉሜ ፍሬዎች! ቅድሚያ ጳጉሜ!

በሀገራችን ላይ ትኩረት ተነፍገን ለ 27 አመታት ያለምንም ቅሬታ ብንኖርም አሁን ለውጡን ተመልክቶ ጭራሽ አናሳ ብሄሮች በማለት እና በማንጓጠጥ እየደረሰብን ያለው ጫና እና ጭቆና ሰልችቶናል።
በተለይ ከ 12 ትላልቅ ብሔረሰቦች ሁለቱ የሚያዋስኑን ከላይ #ነሃሴ ከታች #መስከረም የሚባሉት በርካታ የማህረሰብ እንዳላቸው በማመን በግድ ተቀራምተው ወደ ራሳቸው ብሄር ሊጠቀልሉን እየተነኮሱን ነው። እኛ የጳጉሜ ብሔረሰብ ተወላጆች ቁጥራችን ይነስ እንጂ ለማንም ብሔር የማያንስ ጉልበት እና ልብ እንዳለን ማሳየት አያቅተንም ። የሀገሪቱን ለውጥ ተከትሎ ለውጡ የጋራ ተጠቃሚ ካላደረገን ግን እኛም የራሳችንን እርምጃ መውሰድ እንደምንችል እያስጠነቀቅን ነው።
ብሄራችን የራሱ የሆነ አደረጃጀት ሲኖረው ዲሞክራሲን ላለም ያስተዋወቀ የመመሪያ ስርአት አለው ። መሪያችን የጳጉሜ 6 ተወላች ሲሆን ባራት አመት አንዴ የስልጣን ሽግግር እናደርጋለን። በብሄራችን እምነት በ 600 አመት አንዴ ሚወለደው የጳጉሜ 7 የኛ ነብይ ሲሆን ከአምላክ ጋር የሚያስታርቀን እና አለምን በበላይነት እንድንገዛ የሚመራን ቅዱስ መሪያችን ነው።

እናም አቋማችን :_
ሁላችሁም የጳጉሜ ብሄር ተወላጆች በይበልጥ ከነሃሴ እና ከመስከረም የሚሰነዘርብንን ግዛት የማስፋት ሙከራ ለመመከት ባላችሁበት ተዘጋጁ። ለምንወስደው እርምጃ ሀላፊነቱን መንግስት ይውሰድ።

ጳጉሜ ዘላለም ትለምልም። ቅድሚያ ጳጉሜ! '
ለጠቅላይ ሃገር እምዬ ኢትዮጵያ።


meleyawi

@wegoch
@wegoch
86ኛው ግጥም በጃዝ የፊታችን
ረቡዕ ይካሄዳል


ዕለቱ ለአንጋፋዋ ከያኒ አለምፀሀይ ወዳጆ ተበርክቷል
86ኛው ጦቢያ ግጥም በጃዝ የፊታችን ረቡዕ መስከረም 2 ቀን 2011
ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
ዕለቱ ለአንጋፋዋ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ የተበረከተ ሲሆን፤ ደበበ እሸቱ፣
አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ነብይ መኮንን፣ ጌትነት እንየው፣ ሰርፀፍሬ ስብሃት፣ ተፈሪ
አለሙ፣ የህናት አምባ ኳየር እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤
“ኮሚቴው” የተሰኘ አጭር ተውነት በአርቲሰት ፍቃዱ ከበደ እንደሚቀርብ
ታውቋል፡፡ በምሽቱ የዘመኑ ወጣት ገጣሚያን በጋራ የሰሩትን ልዩ የዘመን
መለወጫ ግጥም ለአንጋፋዋ አርቲስት ለተበረከተው 86ኛው ምሽት
እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

እዚህ ፕሮግራም ላይ መቅረት አይታሰብ.....!!!!!!💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ዘሀራን ቡዳ በላት…
(ናትናኤል ጌቱ)

የመጨረሻ ክፍል

ነገ መስከረም 1, 2011
ከ ቀኑ 7 ሰአት ላይ

@wegoch
@wegoch
ለውድ ቤተሰቦቼ፣ ወዳጅ ዘመዶቼና ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ መልካም
አዲስ ዓመት!!! መጪው ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከትና የመተሳሰብ እንዲሆንልን
አብዝቼ እመኛለሁ!
በዚህ መንደር በነገሮች ሁሉ ሳትታክቱ ላስተማራችሁኝ፣ ሃሳባችሁን ላካፈላችሁኝ፣
ላዝናናችሁኝ፣ ላሳቃችሁኝ፣ ላሳዘናችሁኝ... በሙሉ በዚህ ሁሉ መውጣትና መግባት
ውስጥ አብዝቼ አትርፌ ተምሬበታለሁና አመሰግናችኃለሁ!
መልካም አዲስ ዓመት!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️


እኔ ምፈልገው!!!!!


በወየበ ምድር፤ ሃሩር ባደረቀው፤
በጣመነ ሰማይ፤ ደመና በራቀው፤
አንዳንድ ቀን አለ፤
ክፋት በማረሻው፤ የሚሰነጥቀው፤
አንዳንድ ቀን አለ፤
ደግነት እንደቆጥ፤ ተሰቅሎ ሚርቀው፤
ግን እንዲህም ሆኖ፤
በተጠማው ምድር፤ ሀሩር በጠበሰው፤
በበነነው አለም፤
በክፋት መዶሻ፤ በተፈረከሰው፤
በጨለመው ጉያ፤ ክፋት ባዳፈነው፤
ይህ ተስፈኛው ልቤ፤ አጀብ ነው አጀብ ነው ፤
እሱ ሚፈልገው፤
እንደ ጥቅምት አደይ፤
አበባ መሆን ነው፤አበባ መሆን ነው።


((( ጃ ኖ )))

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ለሁላችሁም ኢትዮጵያዉያን የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳቸሁ መልካም በአል እያልኩኝ
**** በ2011***
ያለንን 💚💛❤️
ክፋትን 👎👎
ይቅረታን🙏✖️✖️✖️ 🙏
በፍቅር ❤️❤️
የምናሳልፈው አመት ያድርግልን።።።
🙏ልዑል🙏

@lula_al_greeko
@wegoch
@seiloch
@getem
Zewdalem Tadesse

ኢትዮጵያዊቷ በግ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
ኮንዶሚኒየም መኖር ችግር ነው! ሁሉም ዶሮና በጉን በሩ ላይ አስሮ ብሎካችንን ኤልፎራ አስመስሏታል። እኔም ሚስቴ በግ ካልገዛህ እያለች ስትነተርከኝ ጥቂት ብር ይዤ በግ ልገዛ ብወጣ አንድ ቀውላላ በግ ነጋዴ ሁለት ፊታቸው ላይ ከባድ ድብርት የሚታይ ከሲታ በጎች ይዞ ቆሞ አገኘሁና ጠጋ ብዬ
 «ልትሸጣቸው ነው?» አልኩት
«እና ሐገር ላስጎበኛቸው ነው ካገሬ ይዣቸው የወጣሁት?» አለኝ
«እንደው ኩነኔ አይሆንም እነዚህን መግደል?» ስለው ፈጠን ብሎ
«አንቀህ ነው እንዴ ምትገድላቸው?» አለኝ
«አይ ያው በቢላም ቢሆን ...» ብዬ ሳልጨርስ
«ወንድሜ ካሳዘኑህ ውሰድና በጉዲፈቻ አሳድጋቸው» አለኝ
«እሺ ስንት ነች እቺ?» አልኩት ወደአንዷ እየጠቆምኩ
«በግ ታውቃለህ ማለት ነው። በጣም አስተዋይ በግ ነች እሷ» ብሎ ጀርባዋን መታ መታ ሲያደርጋት ወደጎን ፍንግል አለችና አቧራዋን አራግፋ ተነሳች። 
«እኔ አስተውሎቷ ምን ይሰራልኛል ላስተምራት አይደለም እኮ ምወስዳት» ስለው 
«ሁለት ሺ ብር ክፈል» አለኝ 
«ሁለት ሺ ብርማ አታወጣም» 
«በርግጥ ላታወጣ ትችላለች ነገር ግን እኔ ሁለት ሺ ብር ነው የሚያስፈልገኝ»
«ቀንስና ልውሰድልህ» አልኩት
«አይ ወዳጄ በጓን ግን አይተሃታል? ውስጠ ወይራ እኮ ነች። መፍዘዟን አትይ። በዚያ ላይ በእንክብካቤ ነው ያደለብኳት» 
«ጭራሽ ደልባ ነው እንዲህ የከሳችው?»
«አዎና! በርግጥ እኔ ስብእናዋ ላይ ነው የሰራሁት። በጥሩ ስነምግባር ነው ያሳደግኋት» አለኝ ቆፍጠን ብሎ። ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ 
«አንድ ሺ ብር ትሸጥልኛለ ...?» ብዬ ሳልጨርስ 
«ውሰዳት!» አለኝ በደስታ ተሞልቶ። 
ምነው ዝም ባልኩ ብዬ በይሉኝታ አንድ ሺ ብር ሰጥቼው በጓን ይዤ ልሄድ ስል መራመድ አቅቷት በቀስታ ስታዘግም
«ቃሬዛ ቢኖርኮ ደግ ነበር» አለኝ ሰውዬው በጉን በሃዘን እየሸኘ።
ተበሳጭቼ ዝም ብዬው ስሄድ 
«ወንድሜ እንደው ለነፍስ ትሆንሃለች መጀመሪያ የህክምና እርዳታ አርግላት» አለኝ
መንገድ ላይ በጓን ያየ ሁሉ ከንፈሩን እየመጠጠ ያልፋል። አንዳንዱ እኔን እያየ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። በግ ላርድ ሳይሆን እንደአብርሃም ልጄን ልሰዋ ይዤ እየሄድኩ ነው ያስመሰሉት። ሽምቅቅ እንዳልኩ ቤት ደረስኩ። ሚስቴ በጓን እንዳየቻት
«ምንድነው ይዘህብኝ የመጣኸው?» ብላ ጮኸች። በጩኸቷ ከኔ ይልቅ የደነገጠችው በጓ ነች። አይኗን አስለምልማ መሬት ወደቀች! የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ላደርግላት ሞከርኩ። አልነቃ ስትለኝ በአፌ ትንፋሽ ልሰጣት ሳጎነብስ ሚስቴ
«በዚህ አፍህ እኔ ከንፈር ጋር ድርሽ እንደማትል እወቀው!» ስትለኝ ቀና ብዬ መጨረሻዋን ማየት ጀመርኩ ... ለብዙ ደቂቃዎች ስታጣጥር ቆይታ ኢትዮጵያዊ የነበረችው በግ በስተመጨረሻ ኢትዮጵያ ሆነች!
ነፍስ ይማር ... ብላችሁ ደሜን እንዳታፈሉት! 😂
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ዘሀራን ቡዳ በላት… የመጨረሻ ክፍል
( ናትናኤል ጌቱ )


መኮንን ወደ ግራ ሲታጠፍ እንዳየሁት ፈጠን ብዬ ተከተልኩት ። በቀጥታ ወደ ቤቱ ነው ያመራው ። ሰው ግን እንዴት
ነው ክፉ አጋጣሚዎችን ለግል ጥቅሙ የሚያውለው? መኮንን ሌባው ያ ሁሉ
ሰው በተሰበሰበት የዘሀራን ሀብል ሰረቀ ! ለካ እንዳንዘረፍ እያልን ጠባቂ እናበዛለን እንጂ ጠባቂ ሲበዛ ነው ለሌባ የሚመቸው ። ለካ የዘበኞች ብዛት ነው ለሌቦች ከለላ የሚሰጣቸው! ! በዚህ አይነት እንደ ህዝብ ምን ያህል ተሰርቀን ይሆን ? ለምንም አይነት ጭቅጭቅ ጊዜና ትዕግስት ስላልነበረኝ ከቤቱ እንደገባሁ ሀብሉን ተቀብየው ወጣሁ ። መንገድ ላይ ሁኜ ዘሀራ በአይነ ህሊናዬ ድቅን አለችብኝ! ዘሀራ ምስኪኗ ለማመን የሚከብድ ህመም ታማለች ። ሰው በልቷታል ነው የተባለው። ሰው እንዴት ሰውን ይበላዋል? ግራኮ ነው የሚያጋባው ። ቤቷ በዚህ ሰአት ዝግ እንደሚሆን ስለማውቅ ባሻጋሪ ደጃፉን እያየሁ
ወደ ቤቴ አመራሁ ። ቤቴ ከገባሁ በኋላ እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም! ብዙ ጥያቄዎች ወደ አይምሮዬ ተመላለሱ
ለመሆኑ የበላትን ሰው ባገኘው ምንድን ነው የምለው? "እባክህን ምስኪን ልጅ ናት ተዋት" ነው የምለው? ወይስ ልዝትበት ነው? እኔ እንዴትም ላናግረው ብቻ ይኸ በላት የተባለው መምህር ከዚህ
በኋላ ሌላ ሴት የሚበላ አይመስለኝም! ዘሀራኮ የውበት ጥግ ናት! እሷን በበላበት አይንማ ሌላ ሴት ልብላ ቢል አይሆንለትም ። እንዲህ እንዲያ እያሰብኩ ድንገት ሀብሏ ላይ ያለው ልብ ቅርፅ መከፈት የሚችል መሆኑን ተመለከትኩ ። ቀስ አድርጌ ከፈትኩት…በልብ ቅርፁ lልክ የተቀመጠ የደበዘዘ ፎቶ አለ ። ፎቶውን ከዚህ ቀደም ከዘሀራ ቤት አይቼው ነበር? አንዳች ሚስጥር እንዳለው ሀብሉን አገላበጥኩት ። ከዛ በኋላ ምን ያህል እንደቆየሁ አላውቅም… ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ! !

ጠዋት የተነሳሁት አረፋፍጄ ነው። ልክ እንደተነሳሁ ምሽት ያየሁትን ሀብል ደግሜ አስተዋልኩ ደግሜ ፎቶውን ተመለከትኩ! ፎቶው በሀብሏ
ልብ ቅርፅ መጠን ስለሆነ ፎቶው ላይ ያለው ወንድ የለበሰው ነጭ ልብስ በደንብ አያስታውቅም ። ግን ድንገት የሆነ ነገር ቅፍፍ አለኝ ። ከሀብሉና ፎቶው ጋር ተያይዞ የሆነ ነገር ልክ አልመሰለኝም ። ወደ ሰርቢሷ ልሄድ አሰብኩና መልሼ ተውኩት ። በሁለተኛውም ቀን እንዲሁ እየቀፈፈኝ አመንትቼ ተውኩት ። እንደውም ለጥቂት ጊዜ ያህል ከአካባቢው ገለል ለማለት ወሰንኩ ። ለአንድ ሳምንት ከአንድ ጓደኛዬ ቤት አሳለፍኩ ። ሳምንቱ ሲያልፍ እየቀፈፈኝም ቢሆን መመለስ ግድ ሆነብኝ ። ወደ ቤቴ በሚወስደኝ ጠባብ መንገድ የዘሀራን ሰርቢስ ዞር ብየ ለማየት ሳልደፍር
አለፍኩ ። ከሰአት በኋላ ግን ቢያንስ ሀብሉን መመለስ እንዳለብኝ ስለተሰማኝ
በቀጥታ ወደ ዘሀራ ሰርቢስ ገሰገስኩ ። የዘሀራ ሰርቢስ እንደ ያኔው ምሽት አልተጨናነቀም ። ጭር ብሏል ። እትዬ አሰለፈች ከዘሀራ ሰርቢስ ሲወጡ እኔ ደግሞ ልገባ ስል ተገጣጠምን ። ሰላምታ ሰጥተውኝ ፈገግ ብለው አለፉ። ፈገግታቸው የዘሀራን ደህንነት አበሰረኝ ። በደንብ ተሽሏታል ማለት ነው! እፎይ!
ገብቼ ሰላምታ ተለዋወጥንና ስለ ደህንነቷ አጥብቄ ጠየኳት ። ክብ ፊቷን እያሸከረከረች ሰላም መሆኗን ነገረችኝ ።
ሳምንት ስለተፈጠረው ነገር ጠየኳት ። ምን እንደተፈጠረ በውል እንደማታስታውስ ነገረችኝ ። አብራርተው እንዳልነገሯት ገመትኩ ። ምን እንደለፈለፈች ሁሉ ረስታዋለች ። ቢሆንም ዘሀራ ተሽሏታል ። እንደውም ያለ ወትሮዋ ዘሀራ ተጫዋች ሁና አገኘኋት ። ዝምተኝነቷ የተገፈፈ መሰለኝ ። ከፊት ለፊቷ አንዲት አነስ ያለች ጠረጴዛ አለች ። ስታነበው የነበረው ቅዱስ ቁርአን ከላይ ተቀምጧል ። "እባክህ ሻይ ጠጣ " ብላ ለመነችኝ ። እንዲሁ ናት ዘሀራ ። በሆነ
አጋጣሚ ከሷ ሰርቢስ የገባ ሰው ሻይ ሳይጠጣ መውጣት አይችልም! " በቃ ተማሪና ሻይ ግን አይነጣጠሉም አይደል? " አልኳትና ተሳሳቅን ። ዘሀራ ሻይ እስክታቀራርብ ድረስ ሰርቢሷን ቃኘሁ ።
በአረብኛና በአማርኛ የተፃፉ ጥቅሶች ከዛም ከዚም ተለጥፈዋል ። ከጥግ ያለችው ሳጥን ላይ ደግሞ አነስ ያለ ፎቶ መያዣ ተቀምጧል ። ይህን የፎቶ አልበም ከዚህ በፊትም ቃኝቼዋለሁ ።
አንድ ጊዜ በሆነ አጋጣሚ ቤቷ ገብቼ ሻይ ጋብዛኛለች ። ተንጠራርቼ አነሳሁትና ማገላበጥ ጀመርኩ ። ፎቶ 1: ቁርጥ እሷን የሚመስሉ ትልቅ ሴትዮ (እናቷ መሰሉኝ ) … ፎቶ 2 : እሷን የሚመስል ወንድ ( ወንድሟ!) … ፎቶ 3: ስብስብ ያሉ መመህራንና ተማሪዎች ። ዘሀራ የምትማርበት ኮሌጅ ውስጥ መሆኑን አላጣሁትም ። ፎቶ 4: የሆነ ደደብዘዝ ብሎ የሚታይ ወንድ ፊት ። አዎ ! ከሀብሏ ላይ ያየሁት ሰው ራሱ ነው ። ፎቶው ቅድም ካየሁት ሰብሰብ ብለው ከተነሱት ውስጥ ያንዱ ወጣት ምስል Zoom ተደርጎና ተቆርጦ እንደሆነ ገባኝ ። ዘሀራ ሻዬን ስታስጠጋልኝ ፉት እያልኩ
"የቤተሰቦችሽ ፎቶ ያምራል " አልኳት ዘሀራ ፈገግ ስትል… እንደ ብርቱካን ክብ የሆነው ፊቷ ክፍል አለ! "ይሄኛው ግን አንቺን አይመስልም" አልኳት ። ትንሽ እንደመደንገጥ ስትል አየኋት ።
ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል በመሀላችን ፀጥታ ነገሰ ። ትንሽ ቆይቶ ዘሀራ
ስትፈራ ስትቸር " መምህሬ ነው … ! " አለችኝ! እንደፈራሁት! !
"ትንሽ ስኳር ጨምሪልኝ" አልኳት ። ሻዩ አልያም የሰጠችኝ ምላሽ ከሁለት አንዱ አፌን መሮታል ። በመጨረሻም ሀብሏን አስረከቢያት ስወጣ ከልብ እያዘንኩላት ነበር ።ምን ያህል ብታፈቅረው ነው ሰብሰብ ብለው ከተነሱት ፎቶ ቆርጣ በሀብሏ የያዘችው ። እሱስ ያውቅ ይሆን? አያውቅም! አያውቅም! ቢያውቅ ኑሮማ እንዲህ ባልተጨነቀች ፣ ራሱ ተጨንቆ ፎቶ በሰጣትና … የማህበር ፎቶ ዙም አድርጋ ባልያዘች ነበር። እንዲህ ውስጥ ለውስጥ በልቧ አፍቅራው እስከመቼ? እስከመቼ ከጭንቀት ብዛት መምህሬ በላኝ እያለች ትለፍልፍ? አሳዘነችኝ የእውነት ዘሀራ አሳዘነችኝ! !!


ተፈፀመ።

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
• ሁለቱ ገጣሚን/ካህሊልጅብራል/
ከብዙ ክ/ዘመናት በፊት ነበር፡፡ ሁለት ታዋቂ የግሪክ ገጣሚያን ወደ አቴንስ ሲጓዙ መንገድ
ላይ ተገናኙ፡፡ ከሰላምታ በኋላ ስለሥራቸው ተጫወቱ፡፡
‹‹በቅርቡ ምን ዐይነ ት ግጥም ጻፍክ?›› በማለት አንዱ ጠየቀው፡፡
ሌላኛው እጅግ ተኩራርቶ ‹‹እስከዛሬ ድረስ በግሪክ ምድር ያልተፃፈ ድንቅ ግጥም ጽፌ
መጨረሴ ነው፡፡ ግጥሙ ስለ ታላቁ ዜውስ መውድስ ነው›› በማለት ከብብቱ ስር ብራናውን
አውጥ አነበበለት›› ግጥሙ እጅግ በጣም ረጅም ነበር፡፡
‹‹በጣም ጥሩ ግጥም ፅፈኋል፡፡ ከዘመናት በኋላም እንደሚታወስ እርግጠኛ ነኝ›› በማለት
ሌላኛው ገጣሚ አደነቀው፡፡
በመቀጠል የእርሱን ሥራ ሲጠይቀው ‹‹የእኔ እንኳን አጭር ናት 8 መስመር ብቻ!›› ብሎ
ስለ ልጅነት ወራት ትዝታ የፃፋትን አጭር ግጥም አነበበለት፡፡
የረጅሙ ግጥም ጸሐፊም ‹‹መጥፎ አይደለም›› ሲል አስተያየት ሰጥቶት ሁለቱ ተለያዩ፡፡
አሁን ታዲያ ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ ባለ 8 መስመሯ በብዙዎች ዘንድ የምትወደድና
በቃላቸው የተያዘች ናት፡፡ ረጅሙ ግጥም በቤተ መጽሐፍት ለዘመናት ተቀምጦ ቢገኝም
ቅሉ መኖሩ ይታወቃል እንጂ ያነበበውም ሆነ ስለርሱ የሚናገር ሰው የለም፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
86ኛው ግጥም በጃዝ የፊታችን
ረቡዕ ይካሄዳል


ዕለቱ ለአንጋፋዋ ከያኒ አለምፀሀይ ወዳጆ ተበርክቷል
86ኛው ጦቢያ ግጥም በጃዝ የፊታችን ረቡዕ መስከረም 2 ቀን 2011
ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
ዕለቱ ለአንጋፋዋ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ የተበረከተ ሲሆን፤ ደበበ እሸቱ፣
አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ነብይ መኮንን፣ ጌትነት እንየው፣ ሰርፀፍሬ ስብሃት፣ ተፈሪ
አለሙ፣ የህናት አምባ ኳየር እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤
“ኮሚቴው” የተሰኘ አጭር ተውነት በአርቲሰት ፍቃዱ ከበደ እንደሚቀርብ
ታውቋል፡፡ በምሽቱ የዘመኑ ወጣት ገጣሚያን በጋራ የሰሩትን ልዩ የዘመን
መለወጫ ግጥም ለአንጋፋዋ አርቲስት ለተበረከተው 86ኛው ምሽት
እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

እዚህ ፕሮግራም ላይ መቅረት አይታሰብ.....!!!!!!💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እውነት በግ ገዛሁ ወይ??
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ዘመዴ አንዳንድ ጊዜ አኪር ከበረገደልህ በረገደልህ ነው።
እንደምታውቀው ቀኑን ሙሉ ስባሪ ሳንቲም ኪሴ ውስጥ ያልነበረኝ ሰውዬ ከየት መጣ ባላልኩት የገንዘብ ማዕበል ተመታሁልህ
ወዲያው ያገኘሁትን ገንዘብ ሰሞኑን ሙሉ ወጥሮ ሲያስጨንቀኝ ለነበረው የበግ ግዢ ለማዋል ወደ ገበያ ስሄድ ደቂቃዎች አልፈጁብኝም። የዛች ነጭናጫ ሚስቴንና የዛ ቀውላላ ልጄን አምሮት ለመቁረጥ ስል የማልገባበት ጉድጓድ የማልወርድበት ቁልቁለት ሊኖር አይችልም።
በገበያው ውስጥ ትንሽ ስንጎራደድ አንድ ከሚንጎማለል የበግ ሙክት ላይ አይኔ ስላረፈ ሻጩን ሰውዬ ቀረብ ብዬ "ስንት ትለዋለህ?" ስል ጠየቅሁት።
"25 ነው " አለኝ ረጋ ብሎ
"ሀያ አምስት...ሀያ አምስት?" መልሼ ጠየቅሁት
"እኛ ሳናስበው ሀይለ ስላሴ ተመልሰው ስልጣን ያዙ እንዴ?"
ሻጩ ሰውዬ አፉን ከወለጋ እስከ ቦንጋ ድረስ አንጋዶ ገላመጠኝ(ነገሩን ገነን ሳደርገው ማለት ነው )
"ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነው" ልልህ የፈለግሁት ሲለኝ ገና እንደ ሎጥ ሚስት ላልተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል የጨው ሀውልት የሆንኩ ይመስል ድርቅ ብዬ ቀረሁ።
ይሁንና ግን እጄን ወደ ኪሴ ስሰድ ሳላስበው የወረደልኝ የገንዘብ መና እንኳን አንድ በግ አይደለም የአባይን ቀሪ ግድብ የማስጨረስ አቅም ያለው ስለሆነ መዥረጥ አድርጌ ብሩን ከፈልሁት።
በነገራችን ላይ ያን የመሰለ ሙክት ይዤ ወደ ሰፈሬ ስመለስ "ጌታዬ አንተን አይንህን ከሚያሳየኝ ገሀነም እሳት ውስጥ ቢከተኝ ይቀለኛል" የሚሉት እትዬ አበራሽ ሁሉ ሳይቀሩ ለንቦጫቸው መሬቱን እስኪነካ ድረስ አጎንብሰው ሰላምታ ሰጡኝ።
"ብዙ ድሀ አውቃለሁ የሚካኤል አስጨናቃን አይነት ድህነት ግን መንግስት በሌለባት ሱማሊያ ሀገር እንኳ አይቼ አላውቅም።" ብለው ሲተርቱብኝ የነበሩት አስር አለቃ ሁንዴ ደግሞ የሚያዩትን ባለማመን ያን ጨንቧሳ አይናቸውን በቡልኮ ጋቢያቸው ጫፍ ደጋግመው ጠራረጉት ።
ሴትየዋን ናቅ አድርጌያቸው አለፍሁና ከቤቴ በራፍ ልደርስ አካባቢ
"ሚኪዬ...ሚኩዬ" እያለ ያ ጦልጧላ ልጄ ሊጠመጠብኝ ተንደረደረ...
"ሚኩ...አባባ...አባዬ ተነሳና በግ ግዛልና በዓሉ እኮ ነገ ነው።" የሚለው ጥሪ ግን ከምናባዊው የህልም ጉዞዬ አናጥቦኝ ወዲያው ከመኝታ ቤቴ ኮርኒስ ላይ አይኔ ተተክሎ ቀረ።
ከምን አይነት ህልም ነው የቀሰቀሰኝ ግን
"አባዬ.. .."
"አቦይ ፀሀዬ መዓት ያውርዱብህ!"
ልጄን ማየት ጠላሁ

@wegoch
@wegoch
የኢሠፓ ምስረታ በዓል እና ሀገር አቀፉ ረሃብ (መስከረም 2/ 1977)
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
-----
ልክ የዛሬ ሰላሣ አራት ዓመት ነው!! በዚያች ዕለት (መስከረም 2/1977) ደርግ ከአጼ
ኃይለሥላሤ መንግሥት ስልጣን የተረከበበት 10ኛው የአብዮት በዓል ይከበር ነበር፡፡ ያ
በዓል ከቀደሙት በዓላት ለየት የሚልበት አንድ ነገር ታይቶበታል፡፡ ይህም የስመገናናው
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ምስረታ በይፋ መታወጅ ነው፡፡ ይህንን ድርብ ደስታ
ለማድመቅ ተብሎ የተዘጋጀው ክብረ በዓል በሀገራችን ታሪክ በድጋሚ አልታየም፡፡ ለዚህ
በዓል ማክበሪያ በትንሹ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል (ያ ገንዘብ በአሁኑ ስሌት
ሁለት ቢሊዮን ብር ሊሆን ይችላል)፡፡
በዚያን ጊዜ ነው በአስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር የተሰራው ታላቁ የኢሠፓ የጉባኤ አዳራሽ
ተመርቆ የተከፈተው፡፡ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት ያለው የ“ትግላችን” ሀውልትም
በዚህ በዓል ወቅት ነው የተመረቀው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለበዓሉ የታጨችው አዲስ አበባ
በደማቅ መብራቶችና በልዩ ልዩ መፈክሮች ተጥለቅልቃ ነበር፡፡ እንግዶች
በሚንቀሳቀሱባቸው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ያሉ አሮጌ ቤቶች በግንብ አጥርና በትላልቅ
የጨርቅ ሽፋኖች እንዲከለሉ ተደርገዋል፡፡ የክፍለ ሀገር ዋና ከተሞችና የአውራጃ
ከተሞችም በመፈክሮችና በማጭድና መዶሻ ምስሎች አሸብርቀዋል፡፡ በዋና ዋና
መንገዶች ላይ ያሉ የንግድ ድርጅቶችና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሶስት ቀለማት
(አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ) የተዘጋጁ አምፖሎችን እንዲያበሩ ታዘዋል፡፡ በየቀበሌው የተቋቋሙ
የኪነት ቡድኖችም ኢሠፓን የሚያወድሱ መዝሙሮችን አፍልቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
የነጭና ጥቁር ስርጭቱን ትቶ ወደ ሙሉ ቀለም ስርጭት የተሸጋገረው በዚያች ታሪካዊ
ዕለት ነው፡፡
በዚያ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ የምስራቅ ጀርመን ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሀገሪቱ መሪ
የነበሩትን ጓድ ኤሪኽ ሆኔከርንና የየመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ደቡብ የመን) መሪ ጓድ
ዓሊ ናስር አል-ሐሰንን ጨምሮ በርካታ የሶሻሊስት ሀገራት ልዑካን ተገኝተዋል፡፡ ከአፍሪቃም
የዛምቢያው ኬኔት ካውንዳ፤ የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤና የሞዛምቢኩ ጓድ ሳሞራ
ማሼል የበዓሉ ታዳሚ ነበሩ፡፡ ዋናው የበዓሉ አከባበር ስነ-ስርዓት በኢሠፓ ጉባኤ አዳራሽና
በአብዮት አደባባይ የተካሄደ ሲሆን በተለይም በአብዮት አደባባይ የተካሄደው ልዩ ትርዒትና
ወታደራዊ ሰልፍ በሀገሪቱ ታሪክ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡
*
“ኢሠፓ” የሚባለው ዝነኛ ፓርቲ የተመሰረተው ለአምስት ዓመታት የዘለቀ መጠነ ሰፊ
ዝግጅት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ ለፓርቲው ምስረታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን
እንዲያቀላጥፍና ህዝቡን በሶሻሊስታዊ ስርዓት እንዲያደራጅ በሚል “የኢትዮጵያ ሰርቶ
አደሮች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን” (ኢሠፓአኮ) የተባለ ከፍተኛ የአስፈጻሚ አካል በመስከረም
1972 ተመስርቶ ነበር፡፡ ይህንን ኮሚሽን ማቋቋሙ ያስፈለገው “የሰርቶ አደሩን ፓርቲ
ለመመስረት የሚቻለው ህዝቡን በማንቃትና በማደራጀት በአንድ ማዕከል ዙሪያ ካሰባሰቡ
በኋላ ነው ” በሚለው የኮሚኒስቶች ርዕዮተ-ዓለማዊ መርህ መሰረት ነው፡፡ የዚህ ኮሚሽን
ተጠሪ በመሆን በየክፍለ ሀገሩ የተመደቡ ወኪሎች የየአካባቢው የበላይ ውሳኔ ሰጪዎች
ነበሩ፡፡ የኮሚሽኑን ዓላማ የሚገልጸው “የኢሠፓአኮ ተልዕኮ ይሳካል” የተሰኘ መፈክር
በመላው ኢትዮጵያ ተደጋግሞ ይሰማ ነበር፡፡
ኢሠፓ የተመሰረተው ለአምስት ቀናት በተካሄደ መስራች ጉባዔ ነው፡፡ በጉባኤው ማጠቃለያ
ላይ በድርጅታዊ አሰራር የተዘጋጀ ምርጫ ተደረገ፡፡ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም የፓርቲው
ዋና ጸሐፊ ሆነው መመረጣቸውም ተነገረ፡፡ ከርሳቸው ጋርም መቶ ሰማኒያ ሶስት
የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተመረጡ፡፡
*
የኢሠፓ አወቃቀርና አሠራር በሌሎች የሶሻሊስት ሀገራት ከታዩት ኮሚኒስት ፓርቲዎች ጋር
ተመሳሳይ ነው፡፡ ፓርቲው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የበላይ ነው፡፡ የፓርቲውና
የአስፈጻሚ አካላቱ ግንኙነት የጎንዮሽ ሳይሆን ከላይ ወደታች የተዘረጋ መዋቅራዊ መልክ
ነበረው፡፡ በመሆኑም ኢሠፓ በየትኛውም እርከን ላይ ላሉት አስፈጻሚ አካላት የበላይና
አመራር ሰጪ ነው፡፡ ይህ አወቃቀር በሀገር አቀፍ፣ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ የተዘረጋ
ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራር የሚቀበሉት ከኢሠፓ
ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ነው፡፡ በክፍለ ሀገርና በአውራጃ ደረጃ ያሉ መስሪያ ቤቶችም
ከኢሠፓ ጽ/ቤት ነው አመራር የሚሰጣቸው፡፡ በመሆኑም የአውራጃና የክፍለ ሀገር የኢሠፓ
ኮሚቴ አንደኛ ፀሐፊ ሆኖ የተመደበ ሰው በፕሮቶኮልም ሆነ በስልጣኑ ከሌሎች ተሿሚዎች
ሁሉ ይበልጣል፡፡
የኢሠፓ መዋቅር በኢ-መደበኛ ሁኔታ ሁሉንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አዳርሷል፡፡
በያንዳንዱ የመንግሥት መስሪያ ቤት፣ በማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅቶችና በከፍተኛ
የትምህርት ተቋማት ውስጥ “የኢሠፓ መሰረታዊ ድርጅት ጽ/ቤት” የሚባል መምሪያ ነበረ፡፡
የዚህ መሰረታዊ ድርጅት ዓላማ የኢሠፓን ርዕዮተ ዓለም ማስተማርና ከበላይ አካል የመጡ
መመሪያዎች ተፈጻሚ መሆናቸውን መቆጣጠር ነው፡፡ ለፓርቲ አባልነት ብቁ የሆኑ ጓዶችን
መልምሎ የአባልነት መታወቂያ የሚሰጠውም እርሱ ነው፡፡
ኢሠፓ በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር፡፡ የፓርቲው ልሳን “ሠርቶ
አደር” የሚባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡ መስከረም ደግሞ የፓርቲው የርዕዮተ ዓለም
መጽሔት ነው፡፡ የፓርቲው አባላት በሁለቱ ህትመቶች በወጡ ጽሑፎች ላይ የመወያየት
ግዴታ አለባቸው፡፡
ኢሠፓ የደርግ መንግሥት ከስልጣን እስከተወገደበት ጊዜ ድረስ ቆይቷል፡፡ በስልጣን ላይ
በነበረባቸው ሰባት ዓመታት በጠቅላላው ከ100, 000 ያላነሱ አባላትን አፍርቷል፡፡ አባላቱ
ከሲቪልም ሆነ ከጦር ሀይሉ ክፍል የተመለመሉ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የፓርቲ አባል በስራ
ቀናት ከካኪ የተሰፋ ሱሪና ኮት የመልበስ ግዴታ አለበት (ይህ መመሪያ የወጣው “የሀገር
ውስጥ ምርቶችን ማበረታታት አለብን” በሚል መነሻ ነው፤ ካኪው በቃሊቲ ጨርቃጨርቅ
ፋብሪካ ነው የሚመረተው)፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት የኢሠፓ ዋና ፀሐፊ ጓድ መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ነበሩ፡፡ ፓርቲው
ምክትል ዋና ፀሐፊ በይፋ ባይሰይምም የጓድ መንግሥቱ ተከታይ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ጓድ
ፍቅረ ሥላሤ ወግደረስ ናቸው፡፡ የርዕዮተ-ዓለም መምሪያ ሃላፊው ጓድ ሽመልስ ማዘንጊያ
ሲሆኑ ጓድ ብርሃኑ ባይህ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ነበሩ፡፡ ጓድ ሸዋንዳኝ በለጠ
የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ፤ ጓድ ተካ ቱሉ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሃላፊ፣ ጓድ
ደበላ ዲንሳ የማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ፣ ጓድ ሜጀር ጄኔራል ገብረየስ ወልደሃና
የወታደራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ነበሩ፡፡ ከሁሉም በላይ ስልጣናቸው ገንኖ የነበረው ግን
የድርጅት መምሪያ ሃላፊው ጓድ ለገሠ አስፋው ናቸው፡፡
*
ኢሠፓ የምስረታ ጉባኤውን በሚያካሄድበት ወቅት (ጳጉሜ1-ጳጉሜ 5/1976) ሀገሪቱ
በከፍተኛ ድርቅ ተጠቅታ ነበር፡፡ ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎች በትግራይ፣ በወሎ፣
በጎንደር፣ በኤርትራ፣ በሀረርጌና በባሌ ክፍላተ ሀገር በቸነፈር ተጠብሰው በሞት አፋፍ ላይ
ነበሩ፡፡ አንዳንድ የሀገር ተቆርቋሪዎች መንግሥት የፓርቲ ምስረታ ጉባኤውን ለሌላ ጊዜ
እንዲያስተላልፍና የ10ኛ አብዮት በዓልን እንዲያስቀር ቢወተውቱም ሰሚ አላገኙም፡፡
የወቅቱ መንግሥት የድርቁ መኖር ከታወቀ በአብዮት በዓል አከባበሩ ላይ ጥላውን ያጠላል
በማለት የምዕራብ ሀገራት የዜና አውታሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከልክሎአቸው
ነበር፡፡ ይሁንና አንዳንድ ሚዲያዎች የዜና ዘጋቢዎቻቸውንና የቪዲዮ ሪፖርተሮቻቸውን
በድብቅ ወደ ሀገር ውስጥ በማስረግ የዓለም ህዝብ አስከፊውን ድርቅ እንዲያየው
አድርገዋል፡፡ በነዚያ ሪፖርተሮች የተቀረጹ ምስሎችን የተመለከቱ የዓለም ህዝቦች ለድርቅ
የተጋለጠውን ኢትዮጵያዊ ረሀብተኛ ለመታደግ በተንቀሳቅሰዋል (በሰር ቦብ ጊልዶፍ
አስተባባሪነት የተሰባሰቡ የዓለማችን እውቅ አርቲስቶች Live Aid የተባለውን የሙዚቃ
ዝግጅት ያቀረቡት ያኔ ነው፡፡ አርቲስቶቹ በዝግጅቱ ላይ በጋራ ያዜሙት We are the
world የተሰኘው ዜማ ከምንጊዜም ምርጥ ዜማዎች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል)፡፡
የደርግ መንግሥት በህጋዊ መንገድ ፈቅዶላቸው የመጡ ጥቂት የሶሻሊስት ሀገራት
ዘጋቢዎች ደግሞ “ድርቅ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ እየቀጠፈ ለዚህ በዓል ከፍተኛ
በጀት መመደብ አግባብ ነውን?” የሚል ጥያቄ በይፋ በማቅረብ የሀገሪቱን ከፍተኛ
ባለስልጣናት አጨናንቀዋል፡፡ በመሆኑም የአብዮት በዓሉ ሲፈጸም መንግሥት በድርቅ
የተጎዳውን ህዝብ ለመታደግ መንቀሳቀሱ ግድ ሆኖበታል፡፡ ሆኖም የመንግሥት እርምጃ
በጣም የዘገየ በመሆኑ አምስት መቶ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዚያ አስከፊ ድርቅ
አልቀዋል፡፡
-----
አፈንዲ ሙተቂ
መስከረም 2/2007

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
"መብቶቻችን ከግዴታዎቻችን አይበልጡም፡፡ መብቶቻችን ሊጠበቁ የሚችሉት፤
ግዴታዎቻችንን ለማሟላት በሚኖረን ብቃት ላይ ተመርኩዘው ነው፡፡" (ጆን. ኤፍ. ኬኔዲ)
ከወደ አዲስ አበባ እየተሰማ ያለው ጉዳይ አጃኢብ ያሰኛል፡፡ እኔ ያልኩት ካልሆነ፣ የኔ
ብቻ... እያልን ስለምንስ የንትርክ አጀንዳ እየፈለግን እንነታረክ? የሌላውን ሳይነኩ የራስን
ማድረግ አይቻልምን??? ይሄስ ምን ያህል መንገድ ያስኬደናል??? በዚህ መንገድ
የሄዱትስ ምን አትርፈው አየናቸው???
ይሄ የእልህና ድራ መንገድ ወደየት ይዞን ሊሄድ እንደሚችል ቆም ብሎ አስቦ
በሚያሰባስበንና አንድ በሚያደርገን ነገር ላይ ትኩረት ብናደርግና ብንሰራ አይበጀንም???
ይሄ ዓይነቱ "የፉክክር በራፍ ሳይዘጋ ያድራል" የሚለው አካሄድስ መቼ ይሆን የሚቆመው?
ኧረ እየተስተዋለ!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ይሄ ቀን የብዙ ደም ውጤት ነው!!
የብዙ መገፋትና የጭካኔ ዶፍ ውርጅብኝ!!
ይሄ ግፍና መከራ ያመጣውን ለውጥ ወደ ውጤት መቀየር የሰፊው ህዝብ ስራ ይሆናል።
ትግሉን ማንም ይታገለው፣ አምባገነኑን ማንም ይገርሥሰው፥ የትግሉ ውጤት ፍሬ
እንዲያፈራ ማድረግም ትሩፋቱ ለመጪው ትውልድ ከደም ማፍሰስ በላይ ነው።
የታገልንለት ለውጥ ከታገልንው አምባገነን ስርኣት በላይ ተገዳዳሪ ነው።
አሁን ትግሉ ከራስ ጋር ነው!!!!!!!!
-------

ትልቁ ጀሃድ (ትግል ) ከራስህ ጋር ምታደርገው ነው!! ነብዩ መሀመድ


ጀምኣው!!!!!! ራስህን ሁን ነብስያህን አድምጥ!!!!!!!!!!

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወይን እና እምባ
በ 9 ሲኒማ
📔የ ግጥም አልበም ምርቃት
በእለቱ
#ግጥም በጃዝ
#Standup comedy
#አውዳዊተውኔት
#መነባነብፕሮግራሙን ያደምቁታል


አሁድ መስከረም 06/2011
ከ 8:00 ጀምሮ
በ ሻሸመኔ 9 ሲኒማ

@Tebeb_mereja
@tebeb_mereja @gebriel_19
2024/09/30 05:16:30
Back to Top
HTML Embed Code: