Telegram Web Link
“ቴዲ አፍሮ ትናንት ለምን አልዘፈነም ጠቅላያችንን
እና ህዝብን ንቆ ነው!" ሲል አንዱ ቀበል አረገና ምን
ቢል ጥሩ ነው" አንተ እኮ ዝም ካሉህ ጥሩነሽ
ዲባባም ነበረች ለምን አልሮጠችም ትላለህ!"

@Wegoch
@wegoch
(ዘውድአለም ታደሰ)

እቺን ሁለት ቀን ነገር ተምታቶብኛል ... ጠኋት ከእንቅልፌ ተጣድፌ ተነስቼ ለባብሼ ምናምን
.... ተመልሼ እተኛለሁ። ካፌ ገብቼ “ጠቆር ያለ ስፕራይት” ብዬ አዛለሁ። ሰው ጋር ደውዬ
“ሃሎ” ሲሉኝ “ማን ልበል?” እላለሁ። ቴሌ ቴክስት ሲልክል “አመሰግናለሁ” ምናምን ብዬ
እመልሳለሁ። የልጅ ኢያሱን ታሪክ ለማንበብ አስቤ የልጅ ሚካኤልን ዘፈን አዳምጣለሁ።
ኤክስ ገርልፍሬንዴን አግኝቼ እየተጨዋወትን “ትዝ ይልሃል? እንዳገባህ ጠይቀኸኝ ነበርኮ”
ስትለኝ «እና አገባሁሽ?» ብዬ ግራ አጋብቻታለሁ። ጓደኛዬን ከሶስት አመት ልጁና ከሚስቱ
ጋር አግኝቸው ሚስቱን አገላብጬ ስሜ ልጁን በሁለት እጄ ጨብጬ አወዛግቤያቸዋለሁ።
ሱማሊኛ ዜና አንገቴን እየነቀነቅኩ አዳምጣለሁ። ባቶቢስ እየሄድኩ ፌርማታ ላይ ሳልደርስ
“ወራጅ አለ” እያልኩ እጮሃለሁ። ብቻ ግራ ገብቶኛል!! ልክ እንደህውሃት መግለጫ!!

@wegoch
@wegoch
ይህች ሀገር አሁን በ (ታ) ላይ ነች ...በይቅርታ .....በቅሬታ....በኮሽታ


የጎደለ ካለ ሙሉበት!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሙስና መቼ ይቆማል ያልሽኝ ልጅ በቪያግራም አይቆምም
እልሻለሁ አከተመ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የኢትዮጱያ አየር መንገድ ከዛሬ ሐምሌ ፲፩ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ መደበኛ በረራ መጀመሩን ሰምተናል።
🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷
ለሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ አያልን
መልካም ቀን እንመኛለን።

@getem
@Wegoch
@Mykeypictures
ይቅር ብያለሁ!
ይህ ቅንጭብ መጣጥፍ ‹ደቦ› ውስጥ የተካተተ ነው፡፡
ስመኝ ግዛው ናት የጻፈችው፡፡ የዘረኝነት መንፈስ ከልባችን
ከቤታችንና ከሀገራችን ልናስወግደው የሚገባ የእቡያን
እኩይ ፈረስ እንደሆነ እድናስተውል ያደርገናል፡፡ ልብ
ይነካል፤ከሌላው ብቻ ሳይሆን ከራስም ያስታርቃል፡፡
መቼም የትም ሊነበብ የሚገባው ነው፡፡ እያንዳንዱን
አርፍተነገር ስናነብ ራሳችንን ፣ሀገራችንን፣ዙርያችን
እንድናስተውል ያደርገናል የሚል እምነት አለኝ፤
እንደምትወዱትም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ተጋበዙልኝ!
….
ይቅር ብያለሁ
…..
ሲምፑቱ ታዋቂ የሩዋንዳ የሙዚቃ አቀንቃኝ ነው፣
ከአፍሪካ ምድር እስከ አሜሪካ ድረስ ዕረፍት የለሽ በሆነ
የሙዚቃ ኮንሰርቶች የተጠመደ፡፡ በዚህም ያልተሰጠው
ሽልማት ክብርና ሞገስ የለም ማለቱ ይቀላል፡፡ ሽልማቱም
እስከ ታላቁ የአፍሪካ የሙዚቃ ኮራ አዋርድ ተሸላሚነት
አድርሶታል፡፡
“እኔን የሳበኝ” ይላሉ ጆሀንስ ክሪስቶፈር፣ “እኔን የሳበኝ
ይህ ሁሉ የሱ ገድል አይደለም፡፡ ይልቅስ የቁጣ፣ የእልህ፣
የንዴት፣ የቂምና የጥላቻ ኋላም የይቅርታና የሰላም ጉዞው
እንጂ!”
እስኪ አስቡት! አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በ19 ቀናት ውስጥ!
ሩዋንዳውያን…ጓደኞች ጓደኞቻቸውን ገድለዋል፡፡
ወንድሞች ወንድሞቻቸውን፣ እህቶች እህቶቻቸውን፣ ልጆች
ወላጆቻቸውን፣ ወላጆች ልጆቻቸውን፣ ባሎችም
ሚስቶቻቸውን፣ ሚስቶችም ባሎቻቸውን…ጐረቤቶች
ጐረቤቶቻቸውን …
“በዚያን ጊዜ እኔ፣ ወደ ብሩንዲና ዑጋንዳ እየተጓዝኩ
ነበር፡፡ ያኔ አባቴ ክፉው ሁሉ ታይቶት ከነገሮች እንዳመልጥ
መክሮኝ ነበር፡፡ ይሁንና በጁላይ 1994 (እ.ኤ.አ.) ልክ
የዘር ጭፍጨፋው እንዳበቃ ወደ ሀገሬ መመለሴ ግድ
ነበር… ”
“በእርግጥ” ይላል ሲምፑቱ፣ “ቤተሰቦቼ ሁሉ ማለቃቸውን
ደመነፍሴ ነግሮኛል፡፡በእርግጥም ቤተሰቦቼ ሁሉ
በጭፍጨፋው አልቀዋል፡፡ መኖሪያችን ከዋና ከተማዋ
በስተደቡብ ነበር፡፡ ሦስቱ ወንድሞቼ ተገድለዋል፡፡ ታላቅ
እህቴም! 34 ዓመቷ ነበር…ምን ያህል ሰቅጣጭና ምን
ያህል ለአዕምሮ የሚከብድ መሆኑን ልብ በሉ!”
“እኛ ቱትሲዎች ነን!...በቤተሰባችን ላይ ጭፍጨፋውን
ያካሄደው ከሩቅ የመጣ ጠላት አልነበረም፡፡ የቅርብ
ጐረቤቶቻችን ነበር ይህን የሠሩት፡፡ የሚገርም ነገር
ልንገራችሁ! እህቴ በአንፃሩ ያገባችው የሁቱ ጐሣን ነበር፡፡
በዚህች አጋጣሚም እሷ የመትረፍ ዕድል አላት ብሎ ልቤ
አስቦ ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡ ሁሉንም ጨርሰዋቸዋል፡፡
መቼም የሰው ልጅ ያጋጠመውን ሊተርክ ይችላል -
ማንኛውንም ጉዳይ! እኔ ግን ጉዳዩን መተረክና መናገር
የማልችለው እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡”
ሲምፑቱ ወደ ሩዋንዳ ምድር እንደተመለሰ በቀጥታ ቡተሬ
ወደተሰኘው መንደሩ ነበር ያመራው፡፡ በእንባ ታጥቧል!
ይንዘፈዘፋል! ይንቀጠቀጣል! በንዴት በእልህ
የሚያደርገውን አያውቅም ነበር፡፡
“ወደ አባቴ ቤት ገባሁ- ኦና ባዶ! ጎረቤቶቻችንን ቃኘሁ፡፡
ማንም የለ! እዚያም እዚህ ብቻ የወደቀ በድን፡፡ መንደሩ
ሁሉ ይጠነባል፤ አስከሬን እዚያም እዚህ…በዓለም ብቻዬን
የቀረሁ እስኪመስለኝ ድረስ ጮህኩ፡፡ እንደ አጋጣሚ ግን
ከጭፍጨፋው በተዓምር የተረፉትን ማግኘቴ አልቀረም፡፡
“ቤተሰቦቼን ማን ነው የገደላቸው?” ስል ጠየቅሁ፡፡ ምላሹ
አስደንጋጭ ነበር፡፡ የልጅነት አብሮ አደጌ ጓደኛዬ ቪንሰንት!
“ምን እናገራለሁ? ከቪንሰንት ጋር አብረን አድገናል፤
አብረን ኳስ ተጫውተናል፡፡ እናም የሰማሁትን ለማመን
አልቻልኩም፡፡ እጅግ አስደንጋጭ መርዶ ነበር፡፡ ሙሉ
ለሙሉ ማንነቴን ያጠፋው አብሮ አደጌ ቪንሰንት!”
ሲምፑቱ በሁኔታው ራሱን ሳተ፡፡
ከዚያ በኋላ ሕይወት መልኳን ቀየረች፡፡ ሲምፑቱ
ያለመጠጥ፣ ያለ አደንዛዥ ዕፅ መንቀሳቀስ እስከማይችል
ድረስ ተለወጠ፡፡ ደረቁን የአፍሪካውያን ጂን ካልተጎነጨ
መዋል ማደር የማይችል እስከመሆን ድረሰ፡፡ በዚህም፣
“ለምን እንደማልሞት ይደንቀኝ ነበር” ሲል ተናግሯል፡፡
“ከዚያች ቀን በኋላ ያሉትን ዘጠኝ ዓመታት የኖርኩት
ምንም ሳልተነፍስና ሳልናገር በድንጋጤ ውስጥ
እንደተዋጥኩ ነበር፡፡
“በውስጤ የሚንቀለቀል ቁጣ፣ ውስጣዊ ሕመም፣ ንዴትና
ምሬት ሁለመናዬን ሙሉ በሙሉ አውድመውት ነበር ማለት
ይቻላል፡፡ በውስጤ ከፍተኛና የማያባራ ጦርነት ይካሄዳል፤
ውስጤ ያለቅሳል፤ልቤ ይደማል፡፡
“ሙዚቃውንም ሙሉ በሙሉ ተውኩት፡፡ ምክንያቱም
ሁሌም እጠጣለሁ፡፡ ተመልሼ መድረክ ላይ የመውጣት
ፍላጎቱም ሕልሙም በጭራሽ ከውስጤ ጠፍቷል፡፡”
ሲምፑቱ በጓደኞቹ ጉትጎታ ወደ ዑጋንዳ ቢሄድም
የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ እዚያ የሚያውቁት ጓደኞቹ
ሊረዱት ሞከሩ፡፡ የሕክምና ዶክተሮች እንዲያነጋግሩት
አደረጉ፡፡ የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ ሲምፑቱ ውስጡ
በቁጣ ይነዳል፡፡
“በራሴና በአምላኬም ላይ ተቆጣሁ፤ ደጋግሜ ጮህኩ፡፡
‹ለመሆኑ አምላክ የት ነህ?› እያልኩ ሚሊዮን ጊዜ ደግሜ
ደጋግሜ እጠይቃለሁ፡፡ ‹አምላክ ሆይ ይህ ሁሉ እንዲሆን
ለምንና እንዴት ነው የፈቀድከው?›እላለሁ፡፡
ሲምፑቱ የደረሰበት እንዳለ ሆኖ በውጭ ሀገር የምትኖረው
ባለቤቱ የአዲስ ሕፃን ልጅ እናት ሆና ነበር፡፡ እጅግ
የሚያሳዝነው የተወለደችው ልጅ አካል ጉዳተኛ መሆኗ!
እሱ ባለበት ብስጭትና ምስቅልቅል መንፈስ ላይ ይህን
መስማት መኖርን የሚፈታተን ነበር፡፡ “ሁኔታው የውስጥ
ብስጭቱን ጣራ አስነካው፡፡ ፈጣሪን ወቀስኩ፡፡ ለዚህ ሁሉ
ነገር ተጠያቂም አደረግሁት…”
……….
ይህ ከሆነ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሲምፑቱ ወደ ካናዳ
አመራ፡፡ በሞንትሪያል ለሩዋንዳ በተሰጠው የስደተኞች
ካምፕም መኖር ጀመረ፡፡ ይሁንና እዚያ ብዙ አልቆየም፡፡
ከባለቤቱ ጋር ባለመስማማቱ ሲምፑቱ ዳግም ወደ አፍሪካ
ተመለሰ፡፡
“በዚህ ወቅት በተወሰነ ደረጃ ስሜቱ ረገብ ማለት ችሎ
ነበር፡፡ በእርግጥ አዎ! ታዋቂ የሙዚቃ ሰው ነኝ፡፡ ኮንሰርት
አዘጋጀሁ፡፡ ዳግመኛም ገንዘብ የማገኝበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡
ይሁንና በመጠጡና በአደንዛዥ ዕጽ የተነሳ በተደጋጋሚ
ወደ እሥር ቤት እወረወር ጀመር፡፡ እታሰራለሁ፤
እወጣለሁ፡፡ እታሰራለሁ፤ እፈታለሁ፡፡ እዚያ ዑጋንዳ ያሉ
እሥር ቤቶችን ሁሉ አዳረስኩ፡፡
“በመጨረሻም ከማውቃቸው ጓደኞቼ አንዱ ከፍተኛ ገንዘብ
ከፍሎ አስፈታኝና ይዞኝ ወደሚኖርበት ኬንያ አመራ፡፡ እዚያ
ከቤተሰቦቹና ከሌሎች ሰዎች ጋር ተዋወቅሁ፡፡ ሁኔታዬን
ያዩ ሁሉ እንድረጋጋና እንድፀልይ ይመክሩኝ ነበር፡፡ ይሁንና
ፈጽሞ የሚሉትን አልሰማቸውም ነበር፡፡ በአንድ ጆሮዬ
አዳምጬ በሌላኛው ጆሮዬ አፈሰው ነበር፡፡
“ይሁንና ተግሳጽና የሰዎች ምክር እየተደገመ ሲሄድ እኔም
ወደ ውስጤ መመልከት ጀመርኩ፡፡ እናም ከምወስደው
መጠጥና አደንዛዥ ዕጽ ለመቀነስ ጥረት አደርግ ጀመረ፡፡
እያደር ሕይወቴንም የመለወጤን ጥረት ቀጠልኩ፡፡ በሦስት
ወራት ውስጥም ለውጥ ማሳየት ጀመርኩ፡፡ በኋላም ወደ
ዑጋንዳ ስመለስ የኔ ሕይወት መለወጥ ትልቅ የመነጋገሪያ
አጀንዳ ሆነ፡፡ የሲምፑቱ ሕይወት ተቀየረ በሚል ዜናዎች
ሳይቀር በጋዜጣና መጽሔቶች ወጡ፡፡
“ሆኖም ግን መጠጡንና አደንዛዥ ዕጽ መጠቀምን
ብተውም ውስጤ ያለው እልህ ቁጣና ምሬት ግን ቅንጣት
ታክል አልተቀነሰም፡፡ ቪንሰንት ደግሞ ደጋግሞ በኅሊናዬ
ይመጣል፡፡ ብቀላም በልቤ ይመላለሳል፡፡ ሁኔታዎችን ሁሉ
ተረድቼ ለመተው የሚያስችል አንዳችም አቅም
አልነበረኝም፡፡”
በዚህ መካከል ነበር ሲምፑቱ ከአንድ የሃይማኖትና
የሥነልቦና ባለሙያ ጋር የተዋወቀው፡፡ እሳቸውም፣
“ካለህበት የምሬት መንፈስ የሚያወጣህ አንድ ነገር ብቻ
ነው - ይቅር ባይ መሆን!” ሲሉ ደጋግመው ነገሩት፡፡
ይህ ግን ፈጽሞ የሚዋጥለት አልነበረም፡፡ ቤተሰቦቹን ሁሉ
አጥፍቶ ብቻውን ያስቀረውን አብሮ አደጉን ቪንሰንት
እንዴት ብሎ ይቅር ሊለው ይችላል?
ይህ ከሆነ ከዓመት በኋላ…ሲምፑቱን የይቅርታን መንፈሰ
ወደ ልቡ ለማስገባት በርካታ ወራትን ጠይቆታል፡፡ ከራሱ
ጋር ይሄ ነው የማይባል ጦርነት ውስጥም ገብቷል፡፡
በስተመጨረሻም ነገሮችን ሁሉ ለመተው ለቪንሰንትም
ይቅርታ ለማድረግ ወሰነ፡፡
“በቃ አሁን ቪንሰትን ይቅር ለማለት ዝግጁ ሆኛለሁ፤
‹ቪንሰንት ይቅር ብዬሃለሁ› ስል ጮህኩ!” ይላል
ሲምፑቱ፡፡ “በዚህም ካሳለፍኩት ሕይወቴ ነጻ የመውጣት
ስሜት ተሰማኝ- ልክ ከእሥር እንደተለቀቀ ዓይነት ሰው…
ለመጀመሪያ ጊዜም ለልቤ ሰላም ተሰማኝ …በመጀመሪያ
ያደረግሁት ነገር ቢኖር ለተለየኋት ባለቤቴ ስልክ መደወል
ነበር፡፡ ከዚያም ለቪንሰንት ባለቤት ደወልኩና ቪንሰንትን
ይቅር ልለው እፈልጋለሁ አልኳት፡፡ ይህን አብሮ አደጌን
ፈጽሞ አይቼው አላውቅም- እሥር ቤት በመሆኑ፡፡ በቀጥታ
ባገኘው እንደምገድለው ነበር የማስበው፡፡ ባለቤቱ
ለቪንሰንት መልእክቴን ካደረሰች በኋላ ምላሽ ይዛልኝ
መጣኝ፡፡ ‹ይሄ በምድር ላይ እንዴት ይቻላል ይህን ሁሉ
ይቅር ባይነት ባትቀበል ያንተ ችግር ነው፣እንዳለችውም
አጫወተችኝ፡፡ በመጨረሻም ቪንሰንት የሆነውን ማመን
እያቃተው የቀረበለትን ይቅርታ ተቀበለ፤ራሱንም ይቅር
እንዳለው ለባለቤቱ እንዳጫወታት ሰማሁ፡፡ ከእሥር
ከተለቀቀ በኋላም ሕይወት ፍጹም በሚገርም ሁኔታ
መልኳን ለወጠች፡፡ አሁን ቪንሰንት ከባለቤቱ ጋር ይኖራል፤
ቤታቸው እሄዳለሁ፡፡ አብሬያቸው እመገባለሁ፡፡ ይህ ሁሉ
የይቅርታ ኃይል ያደረገው መሆኑን ሳስብ ግርም ይለኛል …
ያልፋል የማይባለው ጊዜም በይቅርታ ኃይል ማለፉ
ይደንቀኛል…”


@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሚዛን!!!!


ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ታከለ ኡማን የአዲስ አበባ ከተማ
ከንቲባ አድርገው ስለሾሙ ተሳስተዋልና እስከዛሬ የሰሩትን
ስራ ሁሉ ርሱትና ሻሩት ብሎ መስበክ ጭፍን ድምዳሜ
ሳይሆን አይቀርም ። ስህተት ሰርተዋል አልሰሩም የሚለው
ሙግት እንደተጠበቀ ሆኖ ስህተት እንኳን ቢሰሩ ይህ
ስህተት እስከዛሬ ከሰሩት መልካም ስራ አንጻር ሲታይ
ከዚህ ግባ የሚባል አይደለም ። ወፍ በባህርሩ ላይ
ሽንቷን ብትሸና ባህሩ እንደማይደፈርስ ሁሉ ይህ ስህተት
ጠሚው የሰሯቸውን አስደናቂ ተግባራት የማደፍረስ
አቅምና ቅዋ አለው የሚያስብል አይመስለኝም ((ስህተት
ነው የሚያሰኝ ከሆነ ) ። ይህንን ጉዳይ ወደ ተራራነት
በማግዘፍ ባንዲት ጀምበር የእስከዛሬውን ልፍትና መልካም
ስራ ለማደፍረስ መሞከርና የሰውየውን ኢትዩጲያዊ
መንፈስ ወደ ጎጥ ቁመና ለማውረድ መታተር የመስፈሪያ
ሚዛናችንን የሚያዛንፍና የወፏ ሽንት የግድ ባህሩን
አደፍርሷል ብላችሁ ግግም በሉ ወደሚል የአይናችሁን
ጨፍኑ ፍርድ ይመራልና የተከሰተውን ስህተት ብቻ ነጥሎ
በስህተቱ ወርድና ቁመና ልክ ከመተቸት አልፎ ወደ
ሁለንተናዊ ድምዳሜ በመዝለቅ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራ
አበቃለት ፤ ዋጋም የለው እያሉ ሙሾ እንቀመጥ ብሎ
መገምደል ያስተዛዝበናል ።


ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንላቹ !!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ይድረስ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች

#ክፍል2

🔍🔍ስራ ስትፈልጉ

📒📒የቃል ፈተና(Interview) ስታደርጉ ማስተዋል ያለባችሁ ቁምነገሮች!

አሁን ባለንበት በዚህ በሰለጠነ ዘመን በ21ኛው ክ/ዘ እኛ ሀገር መረጃ ማግኘት ውቅያኖስ ውስጥ መርፌ እንደመፈለግ ያህል ከባድ ነው።አድካሚ ነው።እናም በዚህ ምክንያት በስራ ፍለጋ ላይ እና Interview ሲደረግ ያስተዋልኳቸው ከራሴም፣ከብዙ ሰዎችም በተደጋጋሚ ያስተዋልኳቸውን መሰረታዊ ስህተቶች እንደተሞክሮ ላካፍላችሁ ወደድኩ።ሁለቱ ጉዳዮች ሁላችንም ት/ት አጠናቀን ከተመረቅን በኋላ የምንጋፈጣቸው አይቀሬ ፈተናዎች ናቸው።እኔም እስኪበቃኝ ታሽቼባቸዋለሁ።ከተራ መኪና ማጠቢያ ድርጅት እስከ ትላልቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች Interview ተደርጌአለሁ።
አንዳንዴ ተስፋ ሰጪ ይሆናል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚፈትን ይሆናል።ያም ሆነ ይህ መገንዘብ ያለብን ነገር "There is no such a thing as a free lunch" እንደሚሉት ነጮቹ ወይም የእኛ አባቶች "እንበለ ሕማም ወጻም ኢይትረከብ ጸጋ" እንደሚሉት ሳይደከም እና ሳይፈተን የሚወጣልን እንጀራ የለም።ትንሽ መታሸትን (ups and downs) ይጠይቃል።(ይህ ግን የተደላደለ እና ባለሀብት የሚባል ቤተሰብ ያላቸውን ምሩቃን አይወክልም።) የህዝብ ብዛት በፍጥነት እየጨመረ ሰለሆነ የስራ እና ስራ ፈላጊው (supply and demand) አልተመጣጠነም።ይህም የሰው ኃይል ገበያው ላይ ብዙ ፉክክር እንዲኖር እያደረገ ነው።
ባጭሩ ካስተዋልኳቸው በጣም common እና ብዙዎቻችን የምንሸወዳቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።

🔍🔍ስራ ስትፈልጉ
CV is mandatory!! ፦መጀመሪያ መደረግ ያለበት ነገር cv ማዘጋጀት ነው።CV( curriculum vitae) ማለት ራሳችሁን እና የትምህርት ደረጃችሁን የምተገልጹበት ከ2 ገጽ ያለበለጠ info ነው።ለዚህ google ላይ ከsample ጋር ማግኘት ትችላላችሁ።የሚቀጥራችሁ ድርጅት መጀመሪያ የሚያየው cv ስለሆነ ያልተጋነነ፣ያልበዛ፣ትክክለኛ info የያዘ መሆን አለበት።

አካላዊም ስነ ልቦናዊም ቅድመ ዝግጅት፦ስራ መፈለግ ራሱ ስራ እየሆነ ሰለሆነ ለነገሮች መዘጀት ይገባል።በነገሮች ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ወይም ብዙ expect ማድረግ አግባብ አደለም።ሁሉንም እንደአመጣጡ ማስተናገድ ይገባል።ወጣም ወረደ የፈለገ ቢያታግላችሁ ዘግይቶም ቢሆን የምትፈልጉት ነገር እጃችሁ መግባቱ አይቀርም። It's a matter of #Effort & #Time.

የህትመት ውጤቶችን፦
ጋዜጣ፣መጽሔት፣ብሮሸር
+የሀገር ውስጥ ድረገጾች
+የሀገር ውስጥ ስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች
+የድርጅቶች የግል ድረገጾች
+የራድዮ ፕሮግራሞች
+የሰሌዳ ማስታወቂያዎች....እነዚህ በብዛት ስራ የምታገኙባቸው አድራሻዎች ናቸው።በጣም በንቃት እነዚህን መከታተል ይጠቅማል።ጊዜአችሁን የምታሳልፉበትን ቦታ ና ጉዳይ በማስተዋል ለዩ።በረሃብ ሰአት በግ ስጋ ቤት በር ላይ፣ ውሻስ ግጦሽ ምስክ ላይ ምን ይሰራሉ🤔???ለማለት የፈለኩት አሁን ኃላፊነት የምትሸከሙበት ጊዜ ነው፤እናም ብዙ ጊዜአችሁን ስራ ጋር ከተያያዙ ነገሮች ጋር ማዋል ይግባል።ፓርቲ፣ክለብ፣መዝናናት፣ከሰፈር ልጆች ጋር ቁጭ ብሎ ሙድ መያዝ...ሁሉም ይደረስበታል።

የስራ ማስታወቂያአንዳንድ ድርጅት cv አትስጡ። ብዙ ሰዎች 100 ኮፒ cv አድርገው የከተማዋን ድርጅት ሁሉ ያድሉታል። It won't work that way!!! Dust bin ውስጥ ነው የሚጨመረው።የስራ ማስታወቂያ ላወጣ ድርጅት ብቻ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቀን submit ማድረግ።

ያገኛችሁት ስራ የሰለጠናችሁበት እንኳን ባይሆን ሞክሩት።አንዳንድ ድርጅቶች ማንኛውንም አይነት ወይም ተዛማች ምሩቃንን ይቀበላሉ።ከዚህ በፊት እንዳልኩት ያገኛችሁትን ስራ አትግፉ።አንዳንዴም ባንዴ ብዙ ቦታዎች ተቀባይነት ታገኙ ይሆናል።በዚህ ጊዜ ወደተሻለው መሄድ ነው።መረጃ ለሌሎች ማካፈልም መልካም ነው።እናንተ ካልተሳካላችሁ ለሌላው አሳውቁ፤ይሞክሩት።


📒📒፦Interviw (የቃል ፈተና)
Interview ያላችሁ ቀን(ብዙ ጊዜ ጠዋት ነው) በቀዝቃዛ ውሃ ሻወር መውሰድ፤ምግብ በደንብ መመገብ(ተፈጥሯዊ የሆነ መደናገጥ ስለሚኖር ሰውነታችሁ ዝለት እንዳይሰማው ምግብ ወሳኝ ነው)፤ ንጹህ ልብስ መልበስ።ምንም አይነት መደናገጥ እና ስጋት አያስፈልግም።

Protocol/አለባበስ ይታያል።ሊቀጥራችሁ ቃለመጠይቅ የሚያደርጋችሁ አካል ብዙ ሀብቱን ፈሰስ ያደረገበትን፣የደከመበትን ድርጅት እንድትሰሩበት፣ትርፋማ እንድታደርጉት ስለሆነ የሚፈልጋችሁ ለዛ ኃላፊነት ከወዲሁ ነው የሚገመግማችሁ።"አንድ በአለባበስ፣ በንጽህና ራሱን ያልጠበቀ ሰው እንዴት ድርጅቴን በአግባቡ ይመራልኛል?!" የሚል ትርጉም ይሰጠዋል።አስታውሳለሁ...ለinterview ተጠርቼ ጫማዬን በቫዝሊን ጠርጌ የሄድኩበትን😊።በጣምም ደሞ ለፋሽን ሾው የምትሄዱ እስክትመስሉ መጋነን የለበትም። Just be gentle።ማካፕም በልኩ፤ሽቶም በልኩ።እነዚህ ሲበዙ የምትጠየቁበትን ክፍል ይንጠውና እናንተን ለመገላገል ጠያቂ ቶሎ ያሰናብታችኋል።

በራስ መተማመን ያለው አነጋገር(confidence)። Interview ስትደረጉ እናንተ ስራውን እንደምትፈልጉት ሳይሆን ስራው እናንተን በጽኑ እንደሚፈልጋችሁ አስቡት። Interview ላይ ከሚታዩት ዋና ነገሮች አንዱ ይሄ ነው። ጥያቄ ስትጠየቁ ሳትርበተበቱ በነጻነት የመሰላችሁን መልስ መስጠት ነው።ከናንተ የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። confidence ሲበዛ ደሞ ትእቢትም ስለሚመስል ሁሉንም በልኩ ማድረግ።

የምትመልሰውን መልስ አስተውል!!! የቃል ፈተና ላይ ብዙ ሰው የሚሳሳተው ነገር ለተጠየቀው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ትክክለኛ የራሱን ማንነት የሚገልጽ ሳይሆን "ጠያቂው ይወደዋል? Impress ያደርገዋል? ብሎ ያሰበውን ነው።በዚህ ዙርያ " #ጠብታ_ማር "የምትል መጽሐፍ ላይ አንድ ከ20 አመት በላይ በHR (ሰው ኃይል አስተዳደር) የሰራ ሰው ልምዱን ሲያካፍል ይሄንኑ ጉዳይ እንደተቸገረበት ይገልጻል።እኔም በቅርቡ የታዘብኩት "" ልጁ ስለ marine engineering ሰው ሲያወራ ይሰማል።አዲስ ምሩቅ ነው።እናም ስራ በጣም ስለፈለገ ብቻ አመልክቶ ለቃልሀገሪቱ ይጠሩታል።ስለስራው ምንም ስለማያውቅና ስላልተዘጋጀ አብዛኛውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸገረ። በመጨረሻ ጠያቂው "እሺ ለምን ይህን ስራ ፈለክ?ለምን ከእኛ ድርጅት ጋር ለመስራት ፈለክ?" ሲለው ልጁም " because it's my dream job from childhood" አለው። marine engineering ኢትዮጵያ ውስጥ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን ከትንሽ አመታት ወዲህ ነው የተጀመረው።ሀገሪቱ ውስጥ ብዙም አልታወቀም።እንዴት የልጅነት ህልም ሊሆን ይችላል? በልጅነት ዶክተር ኢንጅነር ነበር የምንለው።በዚህ ምክንያት reject ተደረገ።
እናም ለምትጠየቋቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ እና ጤነኛ መልስ መስጠት ዋጋችሁን ከፍ ያደርገዋል።

ጸሎት፦እንደዚህ አይነት ለህይወታችሁ በጣም አስፈላጊ ሁነቶች ላይ እና በጽኑ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሲኖሩ በየእምነታችሁ መጸለይ ያግዛችኋል።ያ የምትፈልጉት ነገር ወደ እናንተ ቢመጣ አመስግናችሁ በአግባቡ ልትይዙት፣ እንደፈለጋችሁት ሳይሆን ቢቀርም ወይም ባይመጣም ወትሮም የማይጠቅማችሁ መሆኑን መለያ ነው።እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን ለኛ
የሚያስፈልገንን


ንዲሰጠን በትሁት ልቦና ፈጣሪን መጠየቅ ጥሩ ነው።ምክንያቱም የእኛ ፍላጎት በስሜት የተነዳ እና አመክንዮአዊ ያልሆነ ነው።ፈጣሪ ግን መቼ ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል።ስለዚህ በየእምነታችን እንደየአቅማችን መጸለይ ይመከራል። so attach to him and let him do what's best for you:)

ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው።ከዚህ ውጭ የተለያዩ ጽሑፎችን (web publication, how to articles..) ድረ ገጾች ላይ በማንበብ ፣ ሰዎች ጋር መረጃ በመለዋወጥ...ራሳችሁን ለመረጃ ቅርብ አድርጉት። አደራ ታዲያ ስራውን ካገኛችሁ በኋላ የመጀመሪያው ደሞዝ ላይ እንዳትረሱን😊😉

የባለፈውን ጽሑፍ ተከትሎ በጣም ብዙ ምስጋናዎች እና ጥያቄዎች እየመጡ ነበር።ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። በዚች ምድር ላይ ያለን ሰዎች ሁሉ ስለምንዘነጋው ነው እንጂ በ Eco system እርስ በእርሳችን የተደጋገፍን ነን።የአንዳችን መጠቀም ሌላችንን በተዘዋዋሪ ይጠቅማል።የሀገርንም ኢኮኖሚና ገጽታ ያሳድጋል።የአንዳችን ጉዳትም እንዲሁ ጉዳቱ ለሁላችንም ነው።እናም ያለንን፣የምናውቀውን እናካፍል፤ በስራ ፍለጋውም በቃለ መጠይቁም መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ።

እነዚህ መጽሐፍት ይረዷችኋል።

How to win friends and influence people (Dale Carnegie)
በራስ መተማመን በሚል ተተርጉሟል።

Pursuit of happyness (Chris Gardner)
በፊልም ተሰርቷል።

@Fafi_G21
@Wegoch
@wegoch
ነፃነትን የማያውቅ ነፃ ወጪ
( ናትናኤል ጌቱ )
.....
የሆነ ጊዜ ላይ The Shawnshank Redemption የተሰኘ ቆየት ያለ ፊልም ተመልክቼ ነበር ። ፊልሙ አንዲ የተባለ ወጣት ባንከር በግድያ ወንጀል ተወንጅሎ ወህኒ ቤት ውስጥ የሚያሳልፈውን ውጣ ውረድ ይተርካል ።
ታድያ በጣም የማረከኝ የታሪኩ ክፍል ይህ ነው ። ወህኒ ቤቱ ውስጥ አንዲን ጨምሮ በርካታ የእድሜ ልክ እስረኞች
ይኖራሉ ፤ ከእነዚህም ውስጥ ሀምሳ አመታትን በዚሁ ወህኒ ቤት ያሳለፈው ሽማግሌው ብሩክስ አንዱ ነው ። ሽማግሌው ብሩክስ ህይወትን የሚያውቃት በወህኒ ውስጥ ባለው የጭቆና አኗኗር ነው ። በ1954 ዓ.ም ታድያ ብሩክስ ከጓደኞቹ ውስጥ ባንዱ ላይ አንገቱ ስር ቢለዋ ደቅኖ "አርደዋለሁ!" ሲል ማስፈራራት ጀመረ ። አንዲ የፀቡ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያደርጋል ። ፀብ አልነበረም ። ሽማግሌው ብሩክስ ከ50 አመታት የእስር ህይወት በኋላ ከእስር
ሊለቀቅ መሆኑ ተነግሮት ነው። ብሩክስን ያበሳጨው እንግዲህ ይህ ነበር ።
ምክንያቱም ለብሩክስ ህይወት ማለት ነፃነትን ከተነፈጉ እስረኞች ጋር ቁርኝት መፍጠርና ቤተ መፅሀፍቱ ውስጥ የተሰጠውን ስራ መስራት ነው። ለብሩክስ የህይወት ትርጉሟ ነፃነት ሳይሆን በእስር መኖርና ነፃነትን ተነፍጎ መንገላታት ነው። እናም ከእስር ላለመውጣት ድጋሚ ወንጀል ለመስራት ሞከረ ።

ታሪኩ ሲቀጠጥል… ሰው የመግደል ፍላጎት የሌለው ብሩክስ እስር ቤቱን ለቆ ወደ ተዘጋጀለት መኖርያ አመራ ። ኑሮን በነፃነት በኩል ለመቅመስ ሞከረ ። ጠዋት ተነስቶ ወደ ስራ ይሄዳል ፣ ሲጨርስ ይመለሳል ከዛ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል። ብሩክስ አልቻለም
። ይህን ህይወት አለመደውም ብሩክስ! ቀጥታ የወሰነውን ነገር ፈፀመው ። ራሱን በገመድ አንቆ ሞተ! ! ነፃነት ያለበት ህይወት ምኑ ህይወት ነውና ?

ታድያ… ሬድ የተባለው የአንዲ ጓደኛም ከእስር ተፈታ ። ብሩክስ ሲኖርበት ወደነበረው ጊዜያዊ መኖርያ አቀና ። ልክ እንደ ብሩክስ ሁሉ ሬድም ህይወት ታከተችው ። ሬድ ብሩክስ ራሱን ያንጠለጠለበትን ብረት ቀና ብሎ ማየት ጀመረ ። ሁኖም ግን የሆነ ነገር ትዝ አለው ። አንዲ የተወለት ወረቀት ። አንዲ የተወለተ ተስፋ ። ሬድ አንዲን ለመፈለግና ከተስፋው ለመቋደስ ሲል ( ለማወቅ ባለው ጉጉት ምክንያት ) ከሞት ተረፈ !!!
...
ይህ እንግዲህ የኛኑ ታሪክ የሚያንፀባርቅ ይመስለኛል ።ባንድ ወቅት ደርግ ሀገሪቱን መቆምያ መቀመጫ ሲያሳጣት ህዝቡ "ተጨቆንኩ" ብሎ በረሀ ገባ ። አስራ ሰባት አመታትን ታግሎ ደርግን የጣለው ድርጅት ስልጣኑን በእጁ አደረገ ። ግን ነፃነት መጣ? አልመጣም ። የደርግ
ስህተት ተደገመ ። ነፃነትን የማያውቀው ነፃ አውጪ ህዝቡን ጨቆነ ። ዶ/ር አብይ ከመጣ በኋላ ደግሞ ጥቂት መረጋጋትና ነገሮች ፈር መያዝ ጀመሩ ። ሀገራዊ አንድነት ተሰበከ ። ስለ ብሔር ግጭት አላስፈላጊነትና ስለመደመር ብዙ ተባለ ። ግን ይቺን ጥቂት የነፃነት ብርሀን መቅመስ ያልለመደው ህዝብ ወደ ግጭቱ መመለስ ጀመረ ። ነፃነትን የማያውቅ ነፃ ወጪ ማለት ይህ ነው ። ሀያ ሰባት አመታት ስንጮህ የነበረው
መንግስትን መቃወም ወንጀል አይደለም ብለን ነው ። ዛሬ አንድ ሰው የአብይ አመራር ላይ ጥያቄ ቢያነሳ ስድብና ዛቻ እንደ ጎርፍ ይሄድበታል ፣ አብይን ከተቃወምክ "ሌባ ነህ! " ትባላለህ ።
ረጅም አመታትን "ፍቅር ያሸንፋል" ሲል የኖረ የቴዲ አፍሮ ተከታይ በቴዲ ተከፍቻለሁ ብትለው ከነዘርማንዘርህ ይሞልጭሀል ። ፍቅር ያሸንፋል ብሎ መጮህ እንጂ በፍቅር ማሸነፍ ምን እንደሆነ አያውቅማ ! ቴዲን ያለመውደድ ሌላ ሙዚቀኛ የማድነቅ መብትህን እንደ ሽንኩርት ትገፈፋለህ ። ታድያ ኦሾ "እስረኛ የሆናችሁት ነፃ ስለሆናችሁ ነው ፣ በነፃነታችሁ ምክንያት እስርን መረጣችሁ" ያለው ትክክል አይደለም ?
ነፃነትን የማናውቅ ነፃ ወጪዎች… ነፍፍፍፍፍፍ … ነን! !!

መልካም ቀን !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አንድ ቀን ለገጣሚው ( ለባለቅኔ ) << እስከምትሞት ድረስ የአንተን ዋጋ አናውቅም >> አልኩት።

እሱም :- << ልክ ነህ ፣ ሞት ሁልጊዜም ሁሉን ገላጭ ነው። በእርግጥ ጥቅሜን የምታውቁት ከሆነ ልቤ ውስጥ ያለው ፣ ምላሴ ላይ ካለው እንደሚበልጥና የምፈልገውም እጄ ላይ ካለው የበለጠ መሆኑን ትረዳላችሁ >> በማለት መለሰልኝ።


(( ካህሊል ጅብራን ))

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
ማንበብ ሙሉ ሠው ያረጋል..??

ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም የተሻለ ሰዉ እንጂ!!!!

ለማንኛውም ምን ለማለት ነው አበቦቼ...ንባብ ለህይወት በሚል ከሀምሌ 26,27,28,29,30 በኤግዚቢሽን ማዕከል ታላቅ የመፅሐፍ ቡፌ አለ!!.

መግቢያ በነፃ !!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ታክሲዎቻችን ጥቅሶቻቸውን ይቀይሩ ... !

© ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜፀሃዲዛ)

፩. የቀን ጅቦችን አንጭንም !
፪. መደመር ያዋጣልና ጠጋ ጠጋ በሉ !
፫. ስንጀምር ወያላ ስንጨርስ ሹፌር ነን !
፬. ጥያቄዎቻችንን አብይ መልሷልና መልስ አጠይቁን !
፭. ሴቶች ሆይ በፍቅር እና በመደመር ሰአት ሹፌሩን መጥበስ ይቻላል
... መጀመሪያ ግን ሂሳብ ክፈሉ።
፮. ቦንብን እንደ ማስታወሻዎ ደብተር ኪሳቸው ውስጥ ይዘው ለሚሄዱ
ሰዎች እንፀልያለቸው እና ይታሰሩ።
፯. አብያችን ሆይ የመደመር መንታ ወንድም "መቀነስን" በአግባቡ
ይጠቀሙበት።
፰. ወያላውን መደመር ይቻላል ... "መልስ ስጠኝ" እያሉ መነዝመዝ
ግን የቀን ጅብነት ነው።
፱. ታክሲ ውስጥ ሰልፍ ማካሄድ ይቻላል።
፲. ታክሲ ውስጥ ስለ ዘር የሚያወሩ ሰዎችን ወፍጮ ቤት እናደርሳለን።
፲፩. ሚስት ሆይ በመደመር ሰአት ባልሽን አትቀንሺ።
፲፪. ባል ሆይ የአለም ዋንጫ ትዳር አይሆንም።
፲፫. ጠጋ ጠጋ በሉ ... ETV ልንከፍት ነው።
፲፬. ETV ለሚያይ ተሳፋሪ ESAT'ን እንጨምራለን።
፲፭. እስከ አስመራ መንገድ በነፃ እናሳፍራለን።
፲፮. አባዱላዊ ሂሳብ እየመቱ ወያላን በታሪፍ መጨቅጨቅ የቀን
ጅብነት ነው።
፲፯. ስንኖር ወያላ እና ሹፌር ... ስንሞት ታክሲ ነን !
፲፰. የ27 አመት ዱንዙዝ ታሪክ ያላቸውን ሰዎች መምህር ግርማ ጋር
እንወስዳለን።
፲፱. በመደመር አስታኮ ታክሲ ውስጥ መጀንጀን ሂሳብ ያስጨምራል።
፳. ታክሲ ውስጥ አለመቆም ክልክል ነው።
፳፩. ታክሲ ውስጥ ስለ አስመራ ለሚያወሩ ሰዎች ባድመን
እንመርቃለን !
፳፪. እንደምራችሁ ብለን ነው እንጂ መቀነስ አያቅተንም !
፳፫. ETV'ን ያደሰ አብይ ... እግርኳሳችንንም ያድሰው!
፳፬. የሸገር ሴት አግብቶ ... የአስመራ ሴትን መናፈቅ መልካም
አይደለምና "ሞኖፖላዊ አስተሳብ" ይቅር ...
፳፭. የአስመራዋን ቆንጆ ላላገቡት ሸገሮች ይልቀቁ እንጂ "ሹገር ዳዲ"
እየሆኑ እንደ እነንትና አያስቸግሩ።
፳፮. EBS ሆይ የት ነህ ? ...
፳፯. ኬምስትሪን ለዘር መጠቀም ባይሎጂካዊ እብደት ነው።
፳፰. ኤፈርት እና ኢትፍሩት የሃገር ንብረት ናቸው ...
፳፱. ባለ ራዕይ መሪዎችን ራዕይ እናስተምራለን !
፴. ማሽላ ከጤፍ ማህፀን ዱቄት የሚወጣ አይመስላትምና ትንቃታለች
... የቀን ጅቦቹም እንደዛው !
፴፩. የሃገር እዳችንን ሳይመልሱ አንደመርም !
፴፪. ተራራን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ለምን ይንቀጠቀጣል ?
፴፫. ወያላን ከፖለቲካ ጨዋታ ማግለል የቀን ጅብነት ነው።
፴፬. ላወቀበት እና የግራ ጎኑን ላጣ ሰው ታክሲ ጥሩ ካፌ ነው ...
ሰልፍም ጥሩ መናፈሻ !
.
.
.
© ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜፀሃዲዛ)
.


@wegoch
@wegoch
ኮብላዩ አናሲሞስ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባል የማንችስተርን ጨዋታ አየና ሞቅ እንዳለው አምሽቶ ቤቱ ገባ። ሳሎን ሆኖ በንዴት እያወራ ነው። ሚስት ሆዬ ከጓዳ ውስጥ ሆና ለሚያወራው ትመልስለታለች …

ባል:- "ሞሪንሆ ምንም ቡድኑን መስራት አልቻለም …

ሚስት:- ኡኡቴ ወግ ወጉ ተይዟል… እረ ባክህ አንተስ መች እኔን መስራት ትችልና ነው።

ባል:- ዝም ብለው እኮ ነው ሜዳ ላይ የሚገቡት።

ሚስት:- ዝም ብለህ እኮ ነው አንተም ወደ መኝታ ቤት የምትገባው ደሞ አንተም ታወራለህ… ?

ባል:- ደሞ ምንም መለከክ የማይችል ሰው ሉካኩ ይላሉ።

ሚስት:- ምንም ሳትችል አይደል እንዴ 'አይችሉህም' ብለው ስም ያወጡልህ።

ባል:- ይሄ ፌላኒ ደግሞ ያንን ጎል ይስታል…ፀጉር ብቻ!!

ሚስት:-ያንተም ስንቴ እንደሳተ መደሰቺያዬ ይቁጠረው ባክህ …ፀጉር
ብቻ!!

ባል:- የሰው ሜዳ ላይ ማሸነፍ ባይችሉ አቻ መውጣት ያቅታቸዋል…? ዝም ብለው ብቻ መጨረሻ ላይ ይንደፋደፋሉ።

ሚስት:- እነሱ እንኳን በሰው ሜዳ ነው። አንተ በሜዳህ መቼ አቻ ወጥተህ ታውቃለህ… መጨረሻዋ ላይ መንደፋደፍ ብቻ…ኤድያልኝ እቴ!!

ባል:-ነያ እንደ ተጫዋች ቀይሪኝ… ወያላ!

ሚስት:- እረ ቅያሪው ቀርቶ የሚቀበለኝ አግኝቼ በውሰት በሰጠሁህ። 😜

@wegoch
@paappii
የቁርጥ ቀን እንዲሁም የጥብስና የቅቅል ቀን መግለጫ!!!

(በላይ በቀለ ወያ)
"
"
* "yetebaberut የሚለውን የተባረሩት ብለህ ያነበብከው ልጅ ግን
እስካሁን አልተባረርክም?" TOTAL የሚለውን ተትቷል * * * ብለሽ
ያነበብሽው ልጅ ግን ባልሽ አልተወሽም?" ምንትስ ቅብርጥስ እያላችሁ
በዛገ ቀልድ ሲያዝጉኝ የነበሩትን
* የዘረኝትና የሰውን ሀይማኖት የሚያንቋሽሽ ፖስት የተገኘባቸውን
* የሰው ኑሮ ላይ ጣልቃ ገብተው ሲፈተፍቱ የተገኙትን
* ከኔ ጋር ሲጀናጀኑ ቆይተው ሌላ ያገቡትን
* ብድር አበድረውኝ አልረሳ ብለው የሚጨቀጭቁኝን
* እኔ ፖስት ላይ ተሳትፎ የማያደርጉትን
* ቴክስት ጵፌላቸው ያልመለሱልኝን ፣ በሰው ሀዘን ደስታ ለማግኘት
የሚርመሰመሱትን
* ዶላር ሲያሸሹ አግኝቻቸው "አላሸሸንም አፈገፈግን እንጂ " ያሉኝን
* ፅፈውልኝ ስመልስላቸው እንደትልቅ ነገር "በላይኮ ያወራኛል" እያሉ
ያወራነውን ለሌሎች የሚያሳዩትን(ጌታ ቢያወራቸው ምን ሊሆኑ ነው
ሆ?"
*,የአላህ ባሪያ ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ በሚል ስም አካውንት
ከፍተው ሰይጣናዊ ፖስት የሚፖስቱትን
* ፅሁፌን ከኔነቴ ጋር እያያዙ ያስቸገሩ ፣ ሲቸግረኝ የማያበድሩ
፣የገንዘብና የግንዛቤ ችግር ያገኘሁባቸውን
* እኔ የተሰደብኩበትን ፖስት እየተከታተሉ በስቲከር ጥርሳቸው
ሲገለፍጡ የተገኙትን
* ኢሉሚናቲ ነው ብለው የሚያስወሩብኝን ፣ ጌታን ተቀበሉ ስል ዜንደርና
ብሉቱዝ ከፍተው ላክልን የሚሉኝን
* ጥፍር አለን ብለው ያልበላቸውን የሚያኩትን
* ለእድገቴ ሳይሆን ለውድቀቴ ሚተጉትን
*ዝሞ ስላቸው ጢባራም ፣ ሳወራቸው ቅሌታም የሚሉኝን
* ተሳዳቢዎችን ፣ እንደኔ አስብ ባዮችን ፣ ምንም አይነት ፕሮፋይል
የሌላቸውን
* ታይምላይናቸው ላይ ወርክ የሚለው ቦታ ዲሲ ሆም ታውን የሚለው
ላይ አርሲ በማለት የሞሉትን(በማን ገንዘብ ነው ከአርሲ ዲሲ
እየተወላለሱ የሚሰሩት?" በአጠቃላይ አልደመር ብለው ያስቸገሩ አንድ
ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሶስት ሰዎችን ዛሬ በብሎክ አፈናቅያቸዋለሁ።
በስህተት ያፈናቀልኩት ካለ ቅሬታውን በውስጥ መስመር ቢነግረኝ
ይቅርታ ጠይቄ አስገባለሁ። በተረፈ ማፈናቀሌን በርትቼ እገፋበታለሁ!!!!

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
ተወዳጁ ደራሲ፣ጸጋዬ ገብረመድኅን (ሎሬት)፣ ከ45
ዓመታት በፊት ‹እናት ዓለም ጠኑ› በተሰኘ ተውኔቱ እንዲህ
ብሎልን/ብሎን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ቀጥየ ምገልጸውን
ከፊል ሃሳብ ተሾመ ምትኩና ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ
አፍሮ)ማባባት በሚችልና ሙሾ በተቀላቀለበት ውብ ዜማ
አንጎራጉረውት በአልበማቸው ውስጥ አካትተውታል፡፡ ቃለ
ተውኔቱን ዛሬ ደግመን ስናነበው ለእኛ የተባለ ያህል
ይሰማናል፤ አንገት ያስደፋናል፤ያሳፍረናልም፡፡ እንዲህ
ይላል - የ‹እናት ዓለም ጠኑ›ው ዳምበል የተባለው
ገጸባሕርይ፡፡(ከገጽ 134-139 የተቀነጨበ)

…‹‹አንዲት የዱር አውሬ፣በምትወልድበት ሰሞን ፣ ልጅዋን
ትበላለች አሉ ምጥ የጠናባት እንደሆን››…ልጄን በላሁ፡፡
ልጆቻችንን በላን፡፡…ትላንት የነጻነትን ምጥ ከአፋፍ
መንግለን፣የጥላቻ ውርስ አቆይተን፣ አፍአዊ ነጻነት
አውርሰን፣ ምነው ቢሉ ልጆቻችንን ገፍተን፣ አፍአዊ
እኩልነት፣ አፍአዊ ክትባት ከትበን፣ፍርሃት ወርሰን ፍርሃት
አውርሰን፣ሕያው ሳንሆን አፍአዊ፣ ቃለ-ህይወት ሳንሆን
ብኩን ቃለ-አፍ…እንጂ ቤታችን አንድ ነው፡፡…

…ቤታችንስ አንድ ነው፤ ላሳበድናቸውም፣
ላወናበድናቸውም፣ ለሳቁብንም ለተሳለቁብንም፣ለገፉንም
ለተቀበሉንም፣ ላጭበረበርናቸውም፣ ለፈነገልናቸውም፣
ያወረስናቸው ቤታችን ፍቅር የሞተበት ቤታችን ያው አንድ
ነው፡፡…

…ድሮ ሰው በሰው ነው አሉ ራሱን ፈልጎ እሚያገኝ፡፡
የራሱን ጉድለት፣ የራሱን ማንነትና ምንነት
እሚረዳው፣የሌላውን ቀርቦ፣መርምሮ አጥንቶ ነው
ይባላል፡፡ እኛ ግን በተቀራረብን ቁጥር እንተጣጣለን፡፡
እንጠፋፋለን፡፡ አንገናኝም፡፡ በተጠጋጋን ቁጥር
እንራራቃለን፡፡…

…የሰው ጣር-እንባ መሻት፣የሰው ሰቀቀን ማነፍነፍ፤ ውሎ
አድሮ ባህላችን ሆነ፡፡ ሌላው ካላደፈ የኛ ንጽህና፣ሌላው
ካልተጎሳቆለ የኛ ጥጋብ፣ጎልቶ አከልታየን አለ፡፡…

….ፈራን፡፡ የነፍሳችንን አንደበት ዘጋን፡፡ሰብዓዊነታችንን
ራሳችን ከውስጣችን ነድፈን አክስመን፤ሰው የምንለው
ሰብዓዊ ፍጡር ብጤአችን እያደር ከቶም አልገባን አለ፡፡
በዘልማድ ብቻ ሰውን ሰው፣ውሻን ውሻ ብለን፣ ዓሜን
ብለን መቀበል እንጂ፣ ሰው የሚባል ረቂቅ ፍጡር፣ሰው
የሚባል የእግዚአብሄር ተፈጥሮ ተአምር፣ከቶም አልገባን
አለ፤ ከብጤአችን ተጣጣን፡፡ንፍገታችን ከሰብዓዊነታችን
ገነጠለን፡፡..ፈራን፡፡…

((( እንዳለጌታ ከበደ )))

@balmbaras
@wegoch
@Wegoch
2024/11/05 19:01:13
Back to Top
HTML Embed Code: