Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ደብረማርቆስ
የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ።
በአደጋው ለጊዜው ቁጥሩ ባይታወቅም በርካታ ንብረት ወድሟል።
እሳቱ ቅርብ ስለሆነ ወደ ሆስፒታሉ የመዛመት እድሉም ሰፊ ነበር ነገር ግን ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተረባርቦ አጥፍቶታል።
ዘግይቶም ቢሆን አንድ የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና ፤ አንድ የውሀ ቦቲ እና ሌላ የውሀ ታንከር የጫነ ሲኖ ትራክ መኪና ደርሰው እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
እሳቱ የተነሳው ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር 4:10 ላይ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል !
በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።
በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።
በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።
በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።
ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀዋል።
በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።
በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።
በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
Via EPA
@tikvahethiopia

"... የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ ከሆነ አሜሪካ ኤርትራን በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ተቀባይነት የሌላት ሀገር አድርጋ ልትቆጥራት ትችላለች" - ዴቪድ ሺን
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትና አሁን ላይ በአሜሪከ ጆርጅ ዋሽንግተን ዩንቨርስቲ የውጭ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ዴቪድ ሺን ከአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
በቃለ ምልልሳቸው ከነሷቸው ሀሳቦች :
- አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያስቆምና ክልሉን መልሶ ለመገንባት እንዲችል እየጣረች መሆኑንና ያንን ለማድረግ የሚያስችል የማማከርና የሰብዓዊ ርዳታ እየሰጠች ነው ብለዋል።
- አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ አትፈልግም ብለዋል።
- የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ህዝብ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መኖራቸውን ይቀበላሉ ብለው እንደማያስቡ ገልፀዋል።
- የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መኖራቸው ሉዓላዊነትን የሚፈታተን መሆኑን ገልፀው ወታደሮቹ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ መመለሳቸው የኢትዮጵያም፣ የአሜሪካም፣ የኤርትራም ፍላጎት እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
- የኤርትራ ወታደሮች የማይመለሱ ከሆነ አሜሪካ ኤርትራን በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ተቀባይነት የሌላት ሀገር አርጋ ልትቆጥራት ትችላለች ብለዋል።
ሙሉውን ያንብቡ : telegra.ph/USA-ETHIOPIA-05-05
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

Telegraph
USA ETHIOPIA
ዴቪድ ሺን ከቪኦኤ ጋር : ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያና በቡርኪናፋሶ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትና አሁን ላይ በአሜሪካን ሀገር ጆርጅ ዋሽንግተን ዩንቨርስቲ የውጭ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሺን ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለምልልስ አድርገዋል። ዴቪድ ሺን ፥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጋር ባላት ግንኙነትና በተለይ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭት…