Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
'የብሮድካስት ባለስልጣን ማስተባበያ'

ትላንትና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወንድወሰን አንዱአለም ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ፦

- ለዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC ፣ ሮይተርስ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው፤

- የሮይተርስ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ሙሉ በሙሉ እንደታገደች፤

በራሳቸው አንደበት ተናግረው ነበር።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ደግሞ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ተከታዩን ሲሉ ተደምጠዋል (በቅድሚያ ያነሱት ታገደች ስለተባለችው የ "ሮይተርስ" ዘጋቢ ነው) ፦

"..የሀገሩን ህግ አክብረሽ በትህትና መረጃዎችሽን ለማግኘት ጥረት የማታደርጊ ከሆነ ፤ እዚህ እንድትሰሪ የምንፈቅደው በሀገሪቱ ህግ ስለሆነ ናይሮቢ ከሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ጋር ተነጋግረን አንቺ እንድትተኪ እናደርጋለን ፤ ይሄንን ደግሞ ላንቺ በግልፅ እንነግርሻለን፣ ምክንያቱ ደግሞ ይሄ ይሄ ነው ብለን አስረድተናት ፤ ተቀብላ ነው የወጣችው።

ምንም ያገድነው ነገር የለም። እኛ ለሮይተርስ ነው ውሳኔውን የተውነው ፤ ሮይተርስ እኛ ባቀረብነው ቅሬታ ላይ ተመስርቶ አቤቱታችንን ተቀብሎ ካነሳት ሴትዮዋን #የሮይተርስ ነው ውሰኔው የሚሆነው እንጂ አሁንም የፕሬስ ፍቃዷ በእጇ ነው እኛ ያገድናት ነገር የለም።

ለሌሎቹም ሚዲያዎች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ የሚባለው ነገር ማስጠንቀቂያ ሳይሆን በሪፖርቶቻቸው ላይ ውይይትና ምክክር ነው። ለምን ማድረግ የሚገባቸውን ነገር ሳያደርጉ እንደቀሩ አንድም ለማገዝ ፤ አለበለዛም ሞያዊ ግዴታቸውን በአግባቢ እንዲወጡ ለመሞገት የተደረገ ጥረት ነው ፤ እንጂ ሌላ ነገር የለውም።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ጥዋት አዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ተገልጿል።

ሰራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቐለ እያመራ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Youtube

ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር እና ለሁሉም ማስታወቂያ ግን ክፍያ ላይፈጽም እንደሚችል አስታውቋል።

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የማስታወቂያ ገቢውን በሽርክና መርሃ ግብሩ ላይ ከተመዘገቡ ቪዲዮ ሠሪዎች ጋር ይጋራል።

ከዚህ በኋላ ግን ዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆኑ በአንዳንድ ቪዲዮዎች ላይም ማስታወቂያዎችን ማስገባት እጀምራለሁ ብሏል።

በአገልግሎት ውሉ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ዩቲዩብ ከማስታወቂያዎቹ የሚገኘውን ገቢ ለቪዲዮ ሠሪዎች ላያጋራ ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ተመልካቾች ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያላቸውን ማስታወቂያዎችን እንዲያዩ ሊገደዱ ይችላሉ መባሉን BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የንፁሃን_ዜጎቻችን_ስደት

ከUNHCR ባገኘነው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎቻችን ቁጥር ከ33 ሺ አልፏል።

አሁንም በየዕለቱ 'ሰላምን ፍለጋ' በሺዎች ዜጎቻችን ወደ ሱዳን እየተሰደዱ መሆናቸው UNHCR ገልጿል።

ዜጎቻችን በተሰደዱበት ቦታ ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው።

የተሰደዱት ዜጎቻችን ምግብ ፣ ንፁህ ውሃ ፣ መጠለያ ፣ የጤና እገዛ ያስፈልጋቸዋል። UNHCR እና አጋሮቹ ከለጋሾች እጅግ አስቸኳይ እገዛ እንደሚያስፈልገው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,589
• በበሽታው የተያዙ - 473
• ህይወታቸው ያለፈ - 16
• ከበሽታው ያገገሙ - 209

አጠቃላይ 105,352 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,636 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 65,534 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

319 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6_284
• በበሽታው የተያዙ - 544
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,108

አጠቃላይ 119,025 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,843 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 100,859 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

261 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት !

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

• ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

• ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

• ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

• 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

• በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

• ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NዋM_ኦሪጅናል_ማሊያ_አስመጪ !

NዋM አዳዲስ እና ኦሪጅናል ማሊያዎችን እያስመጣ ይገኛል።

የሁሉም ክለብ ኦርጂናል ማሊያዎች ፣ ቱታዎች ፣ የትሬኒግ ልብሶች ፣ የሻምፒዬንስ ሊግ እና ሊግ ኳሶች ፣ ታኬታዎችን...ያስመጣል።

ለተጨማሪ መረጃ : @NwaMsport 0911912441 or 0911535658 ለማዘዝ : @bilu14 @Order_NwaM



#ሻሎም_ሪፍሌክሴሎጂ_የእግር_ማሳጅ

ሪፍሌክሶሎጂ በውስጥ እግር ላይ የሚገኙ በርካታ የነርቭ ጫፎችን በማነቃቃት የተፈጥሮ ጤና የሚጠብቅ ጥበብ ነው፡፡

ድካምን ይቀንሳል ፣ ነርቮችን ያነቃቃል ፣ የደም ዝውውርን ያሻሽላል ፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያዋች ጤናን ይጠብቃል፣ የእንቅልፍ ችግርን ያስተካከላል ፣...

አድራሻ:- ቁጥር 1 መገናኛ ሴንቸሪ ሞል 2ኛ ፎቅ/ ቁጥር 2 ሚኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ ሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊትለፊት 0983414141 or 0952957575
ተጨማሪ : @shalomreflexology
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Metekel

ሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን አስታውቀዋል።

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፣ የንጹሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሌፍተናንት ጄኔራሉ ተናግረዋል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በአ/አ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ 2013 ዓ/ም በ156 መፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወራቸውን የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልላዊ ፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች ዛሬ ተሰራጭቷል።

ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,171
• በበሽታው የተያዙ - 281
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 553

አጠቃላይ 123,145 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,912 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 109,846 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

231 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#TikvahFamilyMekelle

ዛሬ ከሰዓት የባንክ አገልግሎት መጀመሩን የመቐለ ቲክቫህ አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

የንግድ ባንክ ቅርጫፎች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

እጅግ በርካታ ሰዎችም ገንዘብ ለማውጣት ረጅም ሰልፍ ተሰልፈው ነበር።

በተለይ በዋናው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የነበረው ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የመቐለ ቲክቫህ አባላት በስልክ ገልፀዋል።

ከኢፕድ ድረገፅ እንደተመለከትነው ደግሞ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ የግል ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቀዋል።

የቲክቫህ አባላት በከተማቸው የባንክ አገልግሎት አለመኖር ነዋሪውን ክፉኛ ችግር ላይ ጥሎት እንደነበር ነግረውናል። አሁን ባንክ መከፈቱ መልካም ቢሆንም ጫናው እንዲቃለል ሁሉም ባንኮች በፍጥነት ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ በከተማው ያለው የዋጋ ንረት ለነዋሪዎች ከፍተኛ ፈተና ሆኗል፤ይህም በፍጥነት እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

በፀጥታ በኩል አሁንም የሚታዩ ዘረፋዎች መኖራቸውን በመጠቆም ለህዝቡ በሰላም መንቀሳቀስ የደህንነት ስራው እንዲጠናከር አደራ ብለዋል።

በሌላ በኩል፦

የመቐለ ቲክቫህ አባላት ኔትዎክ በሌለባቸው የትግራይ ከተሞች የዘመድ አዝማዶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ እንደተቸገሩ ገልፀዋል።

አንዳንዶችም በሰዎች ደብዳቤ በመላክ የእናት እና አባቶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል።

ኔትዎርክ በሌለባቸው አካባቢዎች ኔትዎርክ ሲከፈት የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በዝርዝር ለቲክቫህ አባላት እንደሚያጋሩ አሳውቀዋል።

በትግራይ የሚኖሩ እና በተለያዩ የሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ሄደው የሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ MoSE ለተማሪዎቹ ሊደረግ ስለታሰበው ነገር በሚዲያ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Tikvah)
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,547
• በበሽታው የተያዙ - 408
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 226

አጠቃላይ 124,164 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,923 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 112,096 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

234 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Tikvah)
#Egypt #Ethiopia

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ፥ “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ” ማለታቸውን ተከትሎ ግብጽ በኩል ቅሬታዎች እየመጡ ነው፡፡

“የሱዳንን ሰፊ መሬትን የያዙ አሉ፤ ግን ለሱዳን ተቆርቋሪ እየመሰሉ ይረብሻሉ” ያሉት አምባሳደር ዲና “ስማቸውን መናገር ግን አልፈልግም ፤ እናንተው ታውቋቸዋላችሁ” ሲሉ ማንነታቸውን በግልጽ ሳይጠቅሱ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠታቸው ተገቢ አይደለም” ብሏል፡፡

“አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግብጽን በተመለከተ ኃላፊነት የጎደለው አስተያየት ሰጥተዋል” ያሉት የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር አሕመድ ሀፊዝ “ግብፅ የግድቡን ግንባታ የምትቃወመው በሀገሪቱ ያለባትን ቀውስ ለማቀዝቀዝ ነው ማለታቸው ተገቢ አስተያየት አይደለም” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡ 

አምባሳደር ዲና “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ ነው ያልነው ፣ ነገር ግን ሌባ እናት ልጇን ስለማታምን ይህንን የምናደርገው እኛ ነን ካሉ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#FireAlert #DebreMarkos

ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኘው ጉልት ገበያ ሱቆች ላይ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሱቆች ተቃጥለዋል።

የከተማው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
2024/09/21 03:05:17
Back to Top
HTML Embed Code: