Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን መከፈቱን በይፋ አብስረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#TPLF

ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮች እንዳልተሳተፉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለBBC አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ ህወሓት በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱ ፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን ለBBC ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው፥የፓርላማው የስልጣን ዘመን ማክተሙን በመግለጽ ፣ ከፓርላማው በተጨማሪ ፓርላማው ያቋቋመው መንግሥም ፣ ካቢኔም የተመረጡት ለ5 ዓመት መሆኑን ጠቅሰው የሰልጣን ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዘንድሮ የሚካሄደው ምርጫ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ እና እውነተኛ ዴሞክራሲ በተግባር የሚገለጽበት ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ባለፉት አስር (10) ዓመታት የተካሄዱ ምርጫዎች ከክርክር አንፃር እውነተኛ ፉክክር ያልተካሄደባቸውና ፖለቲካዊ ምህዳሩ ያልተመጣጠነ ነበር ብለዋል።

በዘንድሮው ምርጫ ፓርላማው የተለያዩ ፓርቲዎች ሃሳባቸወና ድምጻቸውን የሚያሰሙበትና እውነተኛ ውክልና የሚያገኙበት እንዲሆን እንደሚሠራ አስረድተዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኮቪድ_19_ወረርሽኝን_ለመከላከልና_ለመቆጣጣር_በወጣ_መመሪያ_1.pdf
108 KB
#SHARE #ሼር

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ አውጥተዋል፡፡

ያወጡት መመሪያ ስሙ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ፤ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ሲሆን 10 ክፍሎች እና 31 አንቀፆች አሉት።

#ይነበብ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ጤና ሚኒስቴር እና EPHI ፦

"ለልደት ፣ ለምረቃ ፣ ለማህበር ፣ ሀዘንን መሰረት የሚያደርጉ ዝግጅቶች (ከቀብርና ከቀብር መልስ ያሉ ስነስርዓቶች ውጭ) እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበሪዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆነ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለ ነው።

ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ የሰርግ ስነስርዓት በተመለከተ ማንኛውም ሰው ከ50 በላይ የማይበልጡ ሰዎች በመሆን እና ሁለት ሜትር ተራርቆ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የሰርግ ስነስርዑት ማካሄድ ይችላል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በኦሮሚያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ከ100 አለፉ!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አንድ መቶ አንድ (101) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት መመዝገቡን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 12,647 ደርሰዋል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ከ 512 የላብራቶሪ ምርመራ 120 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

ጥንቃቄ አይለየን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የጤና ሚኒስቴር እና EPHI ፦

"እንደ ካፌዎች ፣ ካፌ እና ሬስቶራንቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ ይገባል።

አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

የሚስተናገዱ ሰዎች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጭ የአፍ እና አፍንጫ መሽፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ህወሓት ከዛሬ ጀምሮ በፌዴራል ደረጃ ኃላፊነቶች እና ውክልና የነበራቸው የድርጅቱ አመራር እና የፌደራል ፓርላማ አባላት ሀላፊነታቸው በማስቆም ወደ ድርጅታቸው (ህወሓት) ሪፖርት እንዲያደርጉ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ያላቸውን ኃላፊነት በማስቆም ሪፖርት እንዲያደርጉ የተባሉት በፌዴራል ደረጃ ህወሓትን ወክለው ሲሰሩ የነበሩ አመራሮችና የፓርላማ አባላት ስም ዝርዝር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አውጥቷል፤ ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

በነገራችን ላይ የፌዴራል ኃላፊነታቸውን በማስቆም ወደ ድርጅቱ (ህወሓት) ሪፖርት እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ካስተላለፈላቸው አመራሮች መካከል ዶ/ር አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።

ዶ/ር አርከበ እቁባይ የህወሓት ነባር ታጋይ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አማካሪ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,062 የላብራቶሪ ምርመራ 618 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 956 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 79,437 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,230 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 34,016 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ በዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ !

ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ብቸኛዋ ትግራይ ክልል ተወካይ ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ ተገኝተው ነበር።

ትግራይ ክልል በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት ሰላሳ ስምንት (38) ተወካዮች መካከል ሰላሳ ሰባቱ (37) ሳይገኙ ቀርተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ጌታ በ102 ዓመታቸው አረፉ!

በወሎ እና አካባቢው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ጌታ በ102 ዓመታቸው አርፈዋል።

ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ከሃይማኖት አባትነታቸው ባሻገር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ሕሙማን በሚሰጡት የባህል ሕክምና ታዋቂ ነበሩ፡፡

መስጅዶችን ማስገንባታቸው ፣ የተቸገሩ መርዳታቸው ፣ በተለይ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር እንዲኖር ያለመሰልቸት መሥራታቸው በጉልህ ይጠቀስላቸዋል፡፡

ሀጅ ሙሀመድ ጌታ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የፌዴራልና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን ከአብመድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስክሬን ሽኝት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ እንደሚገኝ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ በሚገኘው ልደታ አዳራሽ ሽኝት ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የልደታ አዳራሽ ሥነ-ስርዓቱ እንደተጠናቀቀ የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አስክሬን ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚያመራና ከቀኑ 6 ሠዓት እስከ 7 ሠዓት በካቴድራሉ በሚካሄድ ሥነ-ስርዓት ቀብራቸው ይፈፀማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ ከሆስፒተል ወጥተዋል!

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ህክምናቸውን በቤተ መንግሥታቸው ፣ ዋይት ሃውስ ለመቀጠል ከሆስፒታል መውጣታቸውን BBC አስነብቧል።

ዶናልድ ትራምፕ ፥ " በጣም በጥሩ ስሜት ላይ ነኝ። ኮቪድን አትፍሩት። ህይወታችሁን እንዲቆጣጠረው አትፍቀዱለት " በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ባስተላለፉት የትዊተር መልዕክታቸው ፥ "በአሁኑ ወቅት ከሃያ አመታት በፊት ከነበረው ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፤ በቅርቡ ወደ ምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻዬ እመለሳለሁ" ብለዋል ።

እንደ BBC መረጃ በኮቪድ-19 ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ 7.4 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ፣ 210 ሺህ ዜጎቿም ህይወታቸውን አጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ክፍት የስራ ቦታ በአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ !

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ 2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክፍት የስራ መደቦች ላይ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ዝርዝር መረጃው ከላይ ባሉት ፎቶዎች ተመልከቱ።

ማሳሰቢያ ፦

• ማስታወቂያው የሚቆይበት ጊዜ - ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት

• ምዝገባው የሚካሄደው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ድረስ ከጥዋቱ 2:30 - 11:30 ሰዓት

• የትምህርት ማስረጃ እና የስራ ልምድ ዋናውና የማይመለስ ኮፒ

• የግል፣ የቤተክህነት እና የሚሲዮን ትምህርት ቤቶች የስራ ልምድ ተቀባይነት አይኖረም

• ከግል የትምህርት ተቋም የሚቀርብ የትምህርት ማስረጃ ቀድሞ በወጣው የሰራተኞች የቅጥር መመሪያ መሰረት ይሆናል

• የስራ ቦታው አዲስ አበባ (10ሩም ክፍለ ከተሞች)

ለተጨማሪ መረጃ : 011-869-83-76

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 08:46:19
Back to Top
HTML Embed Code: