Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በኢትዮጵያ የሶስት ቀን የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ልዑካቸው ዛሬ ወደ ኤርትራ ተመልሰዋል።

ከፕሬዜዳንቱ እና ልዑካቸው ጋር በልዩ ልዩ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ካተኮረ ውይይት መደረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሕዳሴው ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ ቦታ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

- የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ ያስመረተውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተረከቧል።

- የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተረክበው ለየክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ተወካዮች አስረክበዋል።

- በወረዳና ከዚያ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት እንዲጀምሩ ይደረጋል። በቦታዎች ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዳይጀምሩ ማሰስቢያ ተሰጥቷል።

- እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቀመጡት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የማስክ አቅርቦት ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ነው።

- በሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመረተው ማስክም ወደየትምህርት ቤቶች የማድረስ ስራ እየተሰራ ነው።

#MoE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

ዛሬ ረፋድ በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው ተሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝ ተመልክቷል።

በትዕዛዙ የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ተቀይሯል መባሉን ተከትሎ ተወካይ ወይም የክፍል ሃላፊ ለምን እንዳልቀረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርበው እንዲያብራሩም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ በተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትና መሰረት ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤቱ አዟል። (ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በጋምቤላ ክልል ሰኞ ትምህርት ይጀምራል !

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በስተቀር 257 ትምህርት ቤቶች የፊታችን ሰኞ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራቸው እንደሚጀምሩ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

አቶ ሙሴ ጋጄት (የቢሮው ኃላፊ) ለኢዜአ ከተናገሩት ፦

- ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንዲጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

- የመማር ማስተማር ሥራው በ257 ትምህርት ቤቶች ይጀምራል።

- በክልሉ በኑዌር እና በአኝዋክ ዞኖችና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው 86 ትምህርት ቤቶች ግን ትምህርት መስጠት የሚጀምሩት በሂደት ነው።

- ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በተቻለ ፍጥነት ተስተካክላው ሥራ እንዲጀምሩ እተሠራ ነው።

- በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የማስክ ድጋፍ እንዳለ ሆኖ የውኃና ሌሎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት እየተሰራ ይገኛል።

- በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ጨምሮ ከ173,000 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቢሮው እየሠራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በሰሜን ወሎ ዞን ከ286 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል!

ከነሐሴ 28/2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ውሎ ዞን የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ፣ በእንስሳት መኖ እና በቁጥቋጦ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

እስከ መስከረም 27 ቀን 2013 ድረስ በተመዘገበው የጉዳት መጠን 286 ሺህ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አብመድ የዞኑን አስተዳደሪ ወልደትንሳኤ መኮንንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ሥርጭቱን በፍጥነት መከላከል ካልተቻለም ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ይጨምራል ተብሏል፡፡

የአንበጣ መንጋው በዞኑ ከተከሰበት ጊዜ አንስቶ አርሶ አደሩ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እየተከላከለ መሆኑን ተገልጿል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሥርጭት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን እየከበደ መጥቷል።

ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው። (AMMA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በዛሬው ዕለት 357 የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከዛሬዎቹ ተመላሾች መካከል 262 ሴቶች ሲሆኑ 95ቱ ህጻናት ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል እና የተቋረጠውን ትምህርት በጥንቃቄ ለማስቀጠል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዛሬ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስላደረገው ዝግጅት እንደሚከተለው አሳውቆናል ፦

- ከወዲሁ የተመራቂ ተማሪዎች የዶርም ድልድል ተጠናቋል ፣ የተመደቡበት የመኝታ ቁጥር በቴሌግራም በኩል እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በአንድ ዶርም 2 ተማሪ ብቻ ይኖራል።

- በዋናው ጊቢ ዛሬ ተማሪዎች በሚመላለሱባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ተካሂዷል።

- በቀጣይ የፀረ ተዋህስ ኬሚካል ርጭት በተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሾች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ቢሮዎች ይካሄዳል።

- ግቢ ውስጥ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ በየቦታው እንዲቀመጥ ተደርጓል።

- በ1 ክፍል ውስጥ ከ25 ያልበለጠ ተማሪ ይማራል፣ በእያንዳንዱ ወንበር ላይ የተማሪዎች ስም ይፃፋል ፣ ተማሪዎች ስማቸው ከተፃፈበት ወንበር ሌላ መቀመጥ አይችሉም።

ቲክቫህ ላለፉት አመታት ሲያደርግ እንደቆየው የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀናትን እና አሁን ደግሞ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ ዝግጅቶቻቸውን እየተከታተለ ለወላጆች እና ለተማሪዎች ያሳውቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ህንጣሎ ወረዳ አንበጣ መንጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ሁለት ዘመናዊ ማሽኖች የኬሚካል ርጭት እያከናወኑ ነው።

"ካኖን ስፕሬየር" የሚባሉት እነዚህ ዘመናዊ ማሽኖች በግል ድርጅት አማካኝነት ከቻይና በአውሮፕላን እንዲመጡ የተደረጉ ናቸው።

በአሁን ሰዓት በስራ ላይ የዋሉት 2ቱ ማሽኖች አመርቂ የሆነ ስራ እንደሚሰራባቸው የሚጠበቅ ሲሆን ሌሎች ማሽኖችም በመምጣት ላይ እንደሚገኙ ከድምፂ ወያነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እየተሰሩ የሚገኙ ህዝብን ያሳተፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል።

የተለያዩ ድርጅቶች ፣ በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ፣ የመንግስት ተቋማት፣ ባለሃብቶች በቁሳቁስና በገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አትሌቶቻችን በሰላም ገብተዋል !

የ24 ኛው የአለም ግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ ልዑክ ፖላንድ ግዲኒያ በሰለም የደረሰ ሲሆን ሁሉም አትሌቶቻችን የኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል" - ዶ/ር ይናገር ደሴ (የብሄራዊ ባንክ ገዥ)

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካሉት ሶስት የቢሮ ህንፃዎች መካከል በአንደኛው ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር አሳውቀዋል።

ዶክተር ይናገር ደሴ የእሳት አደጋው በፍጥነት መቆጣጠር በመቻሉ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ለetv ተናግረዋል።

የእሳት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

አንበጣ መንጋው ዛሬ በጉባ ቆርቻ ወረዳ ያሉትን 22 ቀበሌዎች እና ሁለት ከተሞችን በሙሉ አዳርሷል።

የማሽላ እና ቦቆሎውን ጨርሶ ወደ ቦሎቄ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ እና ባቄላ ተላልፏል።

የወረዳው አመራሮች ሁኔታው ከአቅማችን በላይ ሆኗል እያሉ ነው።

አውሮፕላንም ይሁን ድሮን ተልኮ ለአካባቢው ህዝብ ሊደረስለት እንደሚገባ የቲክቫህ አባላት መልዕክት አስተለፈዋል።

የአንበጣ መንጋው ጫትንም ወደ መብላት ዞሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣

ምዕራብ ሀረርጌ ጭሮ ከተማ አንበጣ መንጋው ከቁጥጥር ውጪ እየሆነብን ነው ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ !

(አስከፊ ደረጃ ላይ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ)

- የኮንሶ ዞን እና አዋሳኝ አካባቢዎች
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የምዕራብ ወለጋና የቄለም ወለጋ አካባቢዎች
- የጋዜጠኞች እስር

ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም

* ይህ መግለጫ የወጣው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከእስር ከመፈታቱ ቀደም ብሎ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲያበቃ እና ችግሩ በድርድር እንዲፈታ በርካቶች ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ህወሓትም ጦርነቱ ቆሞ ችግሩ በውይይት ይፈታ ዘንድ ለAU እና ለሌሎችም ጥሪ ሲያቀርብ ነበር።

ድርድርን በሚመለከት የፌዴራል መንግስቱ በፍፁም ህወሓት ውስጥ ካሉት 'ወንጀለኛ' ቡድን ጋር ቁጭ ብዬ #አልደራደርም ብሎ አሳውቋል።

ይህ 'ህወሓት' ውስጥ ያለው ቡድን ታሪክ ይቅር የማይለውን ጥፋት አጥፍቷል፣ የሀገር መከታ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት አጥቅቷል ፣ ይህን ጉዳይ አምኗል ፤ አሁን እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር እና የሀገርን ህልውና እና ክብር የማስጠበቅ ዘመቻ የሚጠናቀቀው ወንጀለኞቹ ህግ ፊት ሲቀርቡ ብቻ ነው ሲል ከዚህ ቀደም አቋሙን ገልጿል።

ትላንት ምሽት ድርድርን በሚመለከት በተለያዩ መገናኛ ብዙን አንድ መረጃ ሲሰራጭ ነበር። ይህ የተሰራጨው መረጃው ግን ሀሰተኛ ነው ተብሏል።

ጉዳዩን በሚመለከት ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተሰጠው አጭር ምላሽ ይኸው ነው ፦

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀ መንበር የሆኑትን የሲሪል ራማፎሳን ልዑካን ተቀብለው በግል ይወያያሉ።

ሆኖም ግን ፣ የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና #ሀሰት መሆኑን እናረጋግጣለን።

#ድርድርን አስመልክቶ የፌደራል መንግሥት ያለው አቋም ፈጽሞ ያልተለወጠ ነው።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
2024/09/21 09:34:31
Back to Top
HTML Embed Code: