Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Switzerland-Germany
Scotland-Hungary
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ሁሉም ተጨዋቾች ድንቅ ነበሩ " ዶሜኒኮ ታዴስኮ

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ ትላንት ምሽት ሮማንያን ባሸነፉበት ጨዋታ ሁሉም ተጨዋቾች ያደረጉትን እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየትም " የተጫወትነው እንደ መጀመሪያው ጨዋታ በተመሳሳይ ቅርፅ ነው ፣ ቴሌማንስ ጥሩ ነበር ሁሉም ተጨዋቾች ያደረጉት ድንቅ ነገር ነው።

ሮማንያ ቀላል ቡድን አልነበረም ሶስት ነጥቡን ይዘን በመውጣታችን ደስተኞች ነን አሁን ስለቀጣዩ ጨዋታ ማሰብ አለብን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ነው ! ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል ንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። ሪያል ማድሪድን በዚህ ክረምት እንደሚለቅ የሚጠበቀው ናቾ ዝውውሩን ባያጠናቀቅም ከአል ኢትሀድ ጋር እያደረገ የሚገኘው ንግግር በጥሩ ሁኔታ መቀጠሉ ተዘግቧል። የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ለናቾ 40 ሚልዮን…
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማምራት ተስማማ !

ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ናቾ ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ በመልቀቅ ለሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ የሁለት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተነግሯል።

ናቾ ከዚህ በፊት አል ኢትሀድን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሌላኛውን የሳውዲ አረቢያ ክለብ አል ካድስያ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ በወዳጅነት ጨዋታ ተሳትፏል !

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ አፍንጫው ላይ ጉዳት ካጋጠመው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፎ መጫወቱ ተገልጿል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ትላንት በዝግ ከፓደርቦርን ወጣት ቡድን ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ ተሰልፎ ሲጫወት ሁለት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ ማቀበሉ ተዘግቧል።

ከጨዋታው በፊት የፓደርቦርን ወጣት ተጨዋቾች ከኪሊያን ምባፔ ጋር በሚገናኙበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ከፍተኛ ሀይል እንዳይጠቀሙ እንደተነገራቸው ተገልጿል።

በጨዋታው ኪሊያን ምባፔ ጥቁር የፊት ጭምብል ለብሶ ጨዋታውን ማድረጉ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፖግባ አይመለስም አብቅቶለታል " ፖግባ

ፈረንሳዊው የአንድ ጊዜ አለም ዋንጫ አሸናፊ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከዚህ በፊት በነበረው የእግርኳስ ህይወቱ የስፖርት ማህበረሰቡን ቀልብ የገዛበት የእግርኳስ ችሎታው በድጋሜ እንደማይመለስ ገልጿል።

የቀድሞ የጁቬንቱስ እና ማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ በቅርቡ በአበረታች ንጥረ ነገር ጋር በተያያዘ ለአራት አመታት ከእግር ኳስ መታገዱ አይዘነጋም።

ቀጣይ ስለሚኖረው የእግርኳስ ህይወቱ አስተያየት የሰጠው ፖል ፖግባ " ከዚህ በፊት የነበሩኝ ነገሮች ሁሉ አብቅተዋል ፣ አሁን አብቅቶልኛል የድሮው ፖግባ በድጋሜ እያንሰራራም " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #የዋናውን አዲስ ምርት እናስታውስዎ

👉🏾 ከነፃ ዴሊቨሪ ጋር በ1399 ብር ብቻ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportswear
🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ!
የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!
እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።
አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው - 👉ln.run/k_QQW
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
ዩኤፋ የፀጥታ አካላትን እንደሚያጠናክር ገለጸ !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በቀጣይ በሚደረጉ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታዎች ላይ የፀጥታ ሁኔታውን ሊያጠናክር መሆኑን አስታውቋል።

እግርኳስ ማህበሩ የፀጥታ ሁኔታውን ለማጠናከር እና የፀጥታ አካላትን ቁጥር ለመጨመር የወሰነው ሜዳ ውስጥ ፎቶ ለመነሳት ጥሰው የሚገቡ ተመልካቾችን ለመቆጣጠር መሆኑን ገልጿል።

ዩኤፋ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በትላንቱ የፖርቹጋል እና ቱርክ ጨዋታ ወቅት ሰባት ደጋፊዎች ክርስትያኖ ሮናልዶን ኢላማ በማድረግ ሜዳውን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

" ዩኤፋ የስታዲየም እና ሜዳ እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው " ያለው ዩኤፋ በመግለጫው ሜዳን ጥሶ መግባት የስታዲየም እገዳ እንዲሁም የወንጀል ክስ እንደሚያስከትል አስታውሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሩድ ቫን ኔስትሮይ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ?

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ እንዲካተት ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል።

ኔዘርላንዳዊ የቀድሞ የፊት መስመር ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች አድርጎ አንድ መቶ ሀምሳ ግቦች አስቆጥሯል።

ሩድ ቫን ኔስትሮይ በተጨማሪም ከቪንሴንት ኮምፓኒ ጋር የተለያየውን በርንሌይ በሀላፊነት ለመረከብ በእጩነት ከቀረቡ አሰልጣኞች መካከል አንዱ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች በኮፓ አሜሪካ !

በአሜሪካ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ 2024
ኮፓ አሜሪካ ውድድር በርካታ አርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖችን ይመራሉ።

በኮፓ አሜሪካ ውድድር ከሚሳተፉ አስራ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ሰባት ብሔራዊ ቡድኖች የሚመሩት በአርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች መሆኑ ተገልጿል።

አርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች ከሚመሯቸው ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አርጀንቲናን ጨምሮ ፣ በአሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ የምትሰለጥነው ዩራጓይ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

በተጨማሪም ኮሎምቢያ ( ኔስትሮ ሎሬንዞ ) ፣  ቬንዙዌላ ( ፈርናንዶ ባቲስታ ) ፣ ቺሊ ( ሪካርዶ ጋሬካ ) ፣ ፓራጓይ ( ዳንኤል ጋርኔሮ ) እና ኮስታሪካ ( ጉስታቮ አልፋሮ ) በአርጀንቲና አሰልጣኝ ይመራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከንግድ ባንክ ነጥብ ተጋርተዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የፈረሰኞቹን ግብ ኤፍሬም ታምራት በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥር ባሲሩ ዑመር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 58 ነጥብ

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ  :- 44 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና

እሁድ - ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሀምበሪቾ ዱራሜ ሁለት ጨዋታ እየቀራቸው ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መውረዳቸው ተረጋግጧል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 33 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 9 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ

አርብ - ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ወልቂጤ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኛን ማሸነፍ ከባድ ነው " ጋክፖ

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ ቡድናቸው በአውሮፓ ዋንጫው ለማሸነፍ ጠንካራ ስብስብ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ኮዲ ጋክፖ በንግግሩም " እኛ በስብስባችን ውስጥ የተለያዩ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾችን ይዘናል ፣ እኛን ማሸነፍ ከባድ ይመስለኛል " በማለት ተናግሯል።

ምድቡን በአራት ነጥብ እየመራ የሚገኘው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን የፊታችን ማክሰኞ ከኦስትሪያ ጋር ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 ስዊዘርላንድ ከ ጀርመን

4:00 ስኮትላንድ ከ ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በምሽቱ የስዊዘርላንድ ጨዋታ በመጀመሪያ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች የተጠቀሙትን የቡድን ስብስብ ይዘው ይገባሉ።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑዌር በአስራ ስምንት ጨዋታዎች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጨዋታዎች ያደረገ ግብ ጠባቂ ይሆናል።

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ተመሳሳይ አማካይ ፣ ተከላካዮች እና ግብ ጠባቂ ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

በምሽቱ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ሁለት የፊት መስመር ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ሲገቡ ጆርዳን ሻኪሪ ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2 '

ስዊዘርላንድ 0-0 ጀርመን

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 '

ስዊዘርላንድ 0-0 ጀርመን

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/28 11:33:46
Back to Top
HTML Embed Code: