Telegram Web Link
ኢታን ንዋኔሪ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ከቀናት በፊት አርሰናል ከ ብራይተን አቻ በወጣበት ጨዋታ በጉዳት በእረፍት ሰዓት ተቀይሮ መውጣቱ የሚታወስ ነው።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም " እንዳለመታደል ንዋኔሪ ተጎድቷል በጡንቻ ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ካይ ሀቨርትዝ ለኒውካስል ጨዋታ ይደርሳል ?

ጀርመናዊው የአርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ ለነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ሊደርስ እንደሚችል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ “ ሀቨርትዝ ለጨዋታው እንደሚደርስ ተስፋ አደርጋለሁ “ ያሉ ሲሆን ይደርሳል ብዬ መናገር ግን አልችልም በማለት ተናግረዋል።

ሀቨርትዝ ወደ ሜዳ የማይመለስ ከሆነ መድፈኞቹ ነገ በኒውካስል ጨዋታ የቀኝ ክንፍ አማራጭ ተጨዋቾቻቸው ቡካዩ ሳካ ፣ ንዋኔሪ እና ሀቨርትዝን የሚያጡ ይሆናል።

የአርሰናል ጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ?

መድፈኞቹ በነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ

- ቡካዩ ሳካን
- ራሂም ስተርሊንግ
- ኢታን ንዋኔሪ
- ቶሚያሱ እና
- ቤን ወይትን በጉዳት ሲያጡ የካይ ሀቨርትዝ መድረስ አጠራጣሪ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዲያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ተረከበ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ሀዲያ ሆሳዕና ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀዲያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግብ ጫላ ተሺታ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ተሸንፏል።

ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ሰባተኛ ተከታታይ ድላቸውን አሳክተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሀዲያ ሆሳዕና :- 22 ነጥብ
2️⃣ መቻል :- 21 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ስሑል ሽረ ከ መቻል

ቅዳሜ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፒኤስጂ ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው ! የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ከፈረንሳዊው ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ጋር በጥር የዝውውር መስኮት መለያየቱ አይቀሬ መሆኑን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒን በቡድናቸው እንደማይፈልጉት ተገልጿል። ተጨዋቹ ባለፉት ጨዋታዎች ከፒኤስጂ ስብስብ ውጪ እንደነበር የሚታወስ ነው። ራንዳል ኮሎ…
ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ፒኤስጂን ይለቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ መዘገቡ ይታወሳል።

አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በውሰት ውል ለማስፈረም በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

በተጨማሪም ቶተንሀም እና ጁቬንቱስ ራንዳል ኮሎ ሙኣኒን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ክለቦች መሆናቸው ተዘግቧል።

የ 26ዓመቱ ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ከሁለት አመት በፊት በ 90 ሚልዮን ዩሮ ፒኤስጂን ቢቀላቀልም ብዙም የመሰለፍ እድል እየተሰጠው አይገኝም።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ እድልም የምትጎበኘው ጠንካራ ሰራተኞችን ነው “ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ

ፖርቹጋላዊው የኤሲ ሚላን አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ በጁቬንቱስ ጨዋታ ቡድናቸው እድለኛ ነበር ስለመባሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ እድልም ብትሆን የምትጎበኘው ጠንካራ ሰራተኞችን ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ ነገርግን በህይወት ውስጥ ትንሽ እድል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

" እድል የሚባለውን ነገር የማትወዱ ከሆነ ምናልባት የጁቬንቱስ ደጋፊ ከሆናችሁ ነው “ ሲሉ አሰልጣኙ ጨምረው ተናግረዋል።

ኤሲ ሚላን ከደቂቃዎች በኋላ ከኢንተር ሚላን ጋር የሱፐር ኮፓ ኢጣልያ የፍፃሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት ” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ አይሽሬ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የክለቡን ተጨዋቾች አድንቀዋል።

በዛሬው ዕለት በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የማንችስተር ዩናይትድ የረጅም ጊዜ የልምምድ ማዕከሉ እንግዳ ተቀባይ ካት ፊብስ ቀብር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በቀብር ስነስርዓቱ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና አምበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ መሪነት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና የክለቡ የቀድሞ ተጨዋቾች ተግኝተው ነበር።

በስፍራው ንግግር ያደረጉት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የክለቡ ተጨዋቾች ትላንት በሊቨርፑል ጨዋታ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል ብለዋል።

“ በጣም ጥሩ ውጤት ነው ያስመዘገባችሁት ትልቅ ስራ ሰርታችኋል “ ሲሉ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማድሪድ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !

በስፔን ኮፓ ዴላሬ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከዲፖርቲቫ ሚኔራ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግብ አርዳ ጉለር 2x ፣ ካማቪንጋ ፣ ሉካ ሞድሪች እና ቫልቬርዴ አስቆጥረዋል።

ሪያል ማድሪድ ማሸነፉን ተከትሎ የኮፓ ዴላሬ አስራ ስድስት ወስጥ መቀላቀል ችለዋል።

ሉካ ሞድሪች በ 1️⃣3️⃣ አመታት የሪያል ማድሪድ ቆይታው የመጀመሪያውን የኮፓ ዴላሬ ግብ አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ሻምፒዮን ሆኗል !

ሳውዲ አረብያ ሪያድ በተደረገው የጣሊያን ሱፐር ካፕ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ሄርናንዴዝ ፣ ክርስቲያን ፑልሲች እና ታሚ አብርሃም ከመረብ አሳርፈዋል።

የኢንተር ሚላንን ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ታሬሚ አስቆጥረዋል።

ኤሲ ሚላን ከ 2ለ0 ተመሪነት ተነስቶ ከእረፍት በኋላ ባስቆጠራቸው ሶስት ግቦች ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ኮንሴሳኦ ኤስ ሚላንን እየመሩ ያደረጓቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል።

ኤሲ ሚላን የጣልያን ሱፐር ካፕ ዋንጫን በታሪክ #ለስምንተኛ ጊዜ ማንሳት ችለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ታላቅ የገና ስጦታ እስከ ጥር 4 የሚቆይ ቅናሽ

Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ  ጨምረው መቀየር ይችላሉ)

Ps4 Slim NEW
Republish south korea
2 Orginal jestic

5 Game installed
<Fc25
<Batman
<rocket league
<Formula one
<EA football 25 installed
Storage 500gb
Version 12:00
Full accessories
1 years guarantee

ዋጋ=43,000

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ ገና ምንም ነገር አላሳካንም “ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ

ጥሩ የሚባል የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ኖቲንግሀም ፎረስት ትላንት ምሽት በክሪስ ውድ ፣ ጊብስ ዋይት እና አዎኒዪ ግቦች ዎልቭስን 3ለ0 አሸንፏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ “ ትሑት መሆን አለብን ገና ምንም ነገር አላሳካንም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ከአርሰናል እኩል 4️⃣0️⃣ በማድረስ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የሚመራው ኖቲንግሃም ፎረስት ስድስተኛ ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ድሉን አሳክቷል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ከ 5️⃣8️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አሸንፏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ኖቲንግሃም ፎረስት በሜዳው የሊጉን መሪ ሊቨርፑል የሚገጥም ይሆናል።

ኖቲንግሀም ፎረስት በዘንድሮው የውድድር አመት ሊቨርፑልን ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው ቡድን ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ አሁን ላይ ስለ ዋንጫ ለማሰብ ገና ነው “ ክሪስ ውድ

በኖቲንግሀም ጥሩ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው ክሪስ ውድ ቡድናቸው ቀጣይ ትኩረቱ የሊቨርፑል ጨዋታ መሆኑን ገልጿል።

ፕርሚየር ሊጉን ስለ ማሸነፍ እያለሙ ስለመሆኑ የተጠየቀው ክሪስ ውድ “ አሁን ላይ ሆነን በዚህ መልኩ ለማሰብ ጊዜው ገና ነው “ ብሏል።

ተጨዋቹ አክሎም በአሁን ሰዓት ሙሉ ትኩረታችን ቀጣዩን የሊቨርፑል ጨዋታ ማሸነፍ ላይ ነው በማለት ተናግሯል።

ክሪስ ውድ አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድኑን ከተረከቡ በኋላ ሀያ አንድ ግቦችን ያለ ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቪኒሰስ ጁኒየር ወደ ሳውዲ አረቢያ ?

የሳውዲ አረቢያ ሊግ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር ለማስፈረም አሁንም በቅርበት እየተመለከቱ መሆኑ ተገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ ለቪኒሰስ ጁኒየርን ወኪል ስልክ ደውለው በማነጋገር አሁንም ሊያስፈርሙት እንደሚፈልጉ ማሳወቃቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች በሚቀጥለው ክረምት ከፍተኛ የዝውውር ሒሳባቸውን ይዘው ወደ ሪያል ማድሪድ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ቪኒሰስ ጁኒየር በበኩሉ የቀረበለትን ጥያቄ መስማቱ የተገለፀ ሲሆን ነገርግን ትክክለኛው ጊዜ ነው ብሎ እንደማያምን ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ በበኩሉ የተጫዋቹን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ራሽፎርድ ወደ ጣልያን ሊያመራ ይችላል !

እንግሊዛዊው የተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ባለፉት ጨዋታዎች በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አለመመረጡን ተከትሎ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲገለፅ ነበር።

አሁን ላይ ዘ አትሌቲክ ባወጣው ዘገባ ማርከስ ራሽፎርድ በዚህ ወር የጣልያን ሴርያ መዳረሻው ሊሆን እንደሚችል አስነብቧል።

ጆሽዋ ዚርኪዜ በበኩሉ በጁቬንቱስ እየተፈለገ ቢሆንም በጥር ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ እንደማይፈልግ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በበኩላቸው አንቶኒን በውሰት ለመስጠት ማሰባቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማድሪድ አርኖልድን በጥር ለመውሰድ ለምን ፈለገ ?

ሪያል ማድሪድ አሌክሳንደር አርኖልድን ክረምት ላይ በነፃ ከማስፈረም ይልቅ በዚህ ወር በ 20 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ጠይቀዋል።

በጉዳት ምክንያት ተጨዋቾቹን ያጣው ሪያል ማድሪድ በዚህ ወር የቀኝ መስመር ተጨዋች ካላስፈረመ ለሁሉም ዋንጫዎች መፎካከር እንደሚከብደው ማመኑ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የቀኝ ተመላላሽ ተጨዋች ካላስፈረምን በዚህ አመት ሻምፒየንስ ሊጉን ማሸነፍ የማይታሰብ ነው ብለው እንደሚያምኑ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ሪያል ማድሪድ በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት አርኖልድን ለማስፈረም ተጨማሪ ሥራዎችን እንደሚሰራ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አርሰናል ኒኮ ዊሊያምስን በጥር ማስፈረም ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በያዝነው የዝውውር መስኮት ኒኮ ዊሊያምስን ማስፈረም እንደሚፈልግ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ይሁን እንጂ የተጨዋቹ የዝውውር እና የደሞዝ ወጪ ዝውውሩን ከባድ ሊያደርግባቸው እንደሚችል ተነግሯል።

ተጨዋቹ በክለቡ ውል ማፍረሻ 58 ሚልዮን ዩሮ እንዳለው ሲገለፅ የደሞዝ ክፍያው ሲጨመር ዝውውሩን አዳጋች ሊያደርገው እንደሚችል ተጠቁሟል።

ይህንንም ተከትሎ አርሰናል ስፔናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ቀጣይ ክረምት ለመጠበቅ እንደሚገደድ ተዘግቧል።

በሌላ በኩል መድፈኞቹ የፒኤስጂውን የፊት መስመር ተጨዋች ሌ ካንግ ኢን በውሰት ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቶተንሀም የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋቹ ሰን ሁንግ ሚንን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ቶተንሀም ሰን ሁንግ ሚን በኮንትራቱ የነበረውን ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ በመጠቀም ማራዘማቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ደቡብ ኮርያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን በቶተንሀም ቤት እስከ 2026 ሰኔ ወር የሚቆይ ይሆናል።

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe
ደማቁ የካራባው ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል💥

የገና በዓል ምሽት መድፈኞቹ በሜዳቸው ከኒውካስል ጋር የመጀመሪያውን ዙር የካራባው ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ!

👉ይሄንን ፍልሚያ  በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/01/09 12:22:19
Back to Top
HTML Embed Code: