Telegram Web Link
ቪኒሰስ ምንም ፍፁም ቅጣት ምት አልሳተም !

ከሶስቱ የሪያል ማድሪድ የፍፁም ቅጣት ምት መቺዎች መካከል በዚህ አመት ቪኒሰስ ጁኒየር ምንም የፍፁም ቅጣት ምት ያልሳተ ተጨዋች መሆኑ ተገልጿል።

ቪኒሰስ ጁኒየር በዚህ አመት በሪያል ማድሪድ ያገኛቸውን 7️⃣ የፍፁም ቅጣት ምቶች በሙሉ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል።

ኪሊያን ምባፔ በበኩሉ ካገኛቸው የፍፁም ቅጣት ምት እድሎች ስልሳ በመቶውን ወደ ግብነት መቀየሩ ተነግሯል።

ሌላኛው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በዚህ አመት በክለቡ ካገኛቸው ፍፁም ቅጣት ምቶች ሀምሳ በመቶውን ወደ ግብነት ቀይሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የአንሄ ፖስቴኮግሉ የቶተንሀም ቆይታ ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በክለቡ ያላቸው ሀላፊነት የሚያሰጋቸው አለመሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ከቶተንሀም ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ሲዘገብ ነበር።

አሁን ላይ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በቶተንሀም ቤት ያላቸው ሀላፊነት መቶ በመቶ የሚያሰጋቸው አለመሆኑን ዴቪድ ኦርንስቴን ዘግቧል።

የቶተንሀም ሀላፊዎች አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ የጀመሩትን እቅድ ከግብ እንዲያደርሱ ከጎናቸው እንደሚሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
መሐመድ ሳላህ ስንት ክፍያ ጠየቀ ?

ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ውሉን ለማራዘም እስካሁን መስማማት ባለመቻሉ በክለቡ የመጨረሻ አመቱ እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል።

መሐመድ ሳላህ ሊቨርፑል በሳምንት 400,000 ፓውንድ የደሞዝ ክፍያ እንዲያቀርቡለት መጠየቁን የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ተናግሯል።

ሳላህ ሊቨርፑል አጠቃላይ 60 ሚልዮን ዩሮ የሚያስገኝለት የሶስት አመት ኮንትራት እንዲቀርብለት መጠየቁ ተገልጿል።

ጋሪ ኔቭል በሰጠው አስተያየትም " ሳላህ ሳምንታዊ 400,000 ይገባዋል እሱን የሚተካ ተጨዋች ለማስፈረም እስከ 70 ሚልዮን ዝውውር እና ደሞዝ ያስፈልግሀል “ ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፌዴሪኮ ኬሳ በሊቨርፑል ይቀጥላል !

ጣልያናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ በቀሪው የውድድር ዘመን በሊቨርፑል ቤት እንደሚቀጥል ወኪሉ አረጋግጧል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ወደ ናፖሊ ያመራል ቢባልም “ ከናፖሊ ጋር ያደረግነው ንግግር የለም ሊቨርፑል የመሸጥ ሀሳብ የለውም “ ሲል ወክሉ ተናግሯል።

ባለፈው ክረምት ሊቨርፑል የተቀላቀለው ፌዴሪኮ ኬሳ በክለቡ ብዙም የመሰለፍ እድል አለማግኘቱን ተከትሎ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲዘገብ ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ፓትሪክ ክላይቨርት በሀላፊነት ሊሾም ነው !

የቀድሞ የባርሴሎና እና ኒውካስል ታሪካዊ ተጨዋች ፓትሪክ ክላይቨርት የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ ቡድንን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

የ 48ዓመቱ ፓትሪክ ክላይቨርት ለኢንዶኔዥያ ብሔራዊ ቡድንን ለሁለት አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ ተነግሯል።

ኢንዶኔዥያ አሰልጣኝ ፓትሪክ ክላይቨርትን የሾመችው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር ለመሳተፍ በማለም መሆኑ ተገልጿል።

በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ 127ኛ ላይ የምትገኘው ኢንዶኔዥያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ጥሩ አጀማመር ያደረገች ሲሆን በምድቡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን ከስሑል ሽረ ጋር  ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግብ መሐመድ አበራ ፣ ረመዳን የሱፍ እና መስፍን ዋሼ ሲያስቆጥሩ ለስሑል ሽረ አሌክስ ኪታታ ከመረብ አሳርፈዋል።

ኢትዮጵያ መድን ያለፉትን ሰባት ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 17 ነጥብ
1️⃣4️⃣ ስሑል ሽረ :- 11 ነጥብ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዎልቭስ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ዎልቭስ የሬምሱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኢማኑኤል አግባዶ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ዎልቭስ ተጫዋቹን በ 18 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና ተጨማሪ ታይቶ የሚጨምር 2 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

የ 27አመቱ ኮትዲቯራዊ ተከላካይ ኢማኑኤል አግባዶ ዎልቭስን በአራት አመት ኮንትራት ለመቀላቀል የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ዚርኪዜን ለማስፈረም እየጣረ ነው !

የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርኪዜን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጁቬንቱስ የተጫዋቹን ወኪል ማነጋገር መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን በውሰት ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ጣልያናዊው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ተጫዋቹን ያለክፍያ በውሰት መስጠት እንደማይፈልጉ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሀሜስ ሮድሪጌዝ ከራዮ ቫዬካኖ ጋር ተለያየ !

ኮሎምቢያዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ ከስፔን ላሊጋው ክለብ ራዮ ቫዬካኖ ያለውን ውል በስምምነት ለማቋረጥ መወሰናቸው ተገልጿል።

የ 33ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ ከአምስት ወራት በፊት ራዮ ቫዬካኖን በአንድ አመት ውል መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።

ክለቡ ከተጨዋቹ ጋር ለመለያየት የወሰነው በስፖርታዊ እና ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።

ሀሜስ ሮድሪጌዝ በራዮ ቫዬካኖ ቤት በሁሉም ውድድሮች ተሰልፎ መጫወት የቻለው በሰባት ጨዋታዎች ነው።

አሁን ላይ ኮሎምቢያዊውን ተጨዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ በነፃ ዝውውር ለማስፈረም በርካታ ክለቦች መጠየቃቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተከላካይ ማስፈረም ይፈልጋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በተከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የኋላ መስመሩን ማጠናከር እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሰማያዊዎቹ በዚህ ወር ተከላካይ ለማስፈረም እያሰቡ እንደሚገኙ የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።

ቼልሲ ለማስፈረም ከተመለከቷቸው ተከላካዮች መካከል የክሪስታል ፓላሱ ማርክ ጉሂ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ ተነግሯል።

ቼልሲ በተጨማሪም ትሬቮህ ቻሎባህን ወደ ቡድን ለመመለስ ሊያስቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢታን ንዋኔሪ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ከቀናት በፊት አርሰናል ከ ብራይተን አቻ በወጣበት ጨዋታ በጉዳት በእረፍት ሰዓት ተቀይሮ መውጣቱ የሚታወስ ነው።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም " እንዳለመታደል ንዋኔሪ ተጎድቷል በጡንቻ ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ካይ ሀቨርትዝ ለኒውካስል ጨዋታ ይደርሳል ?

ጀርመናዊው የአርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ ለነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ሊደርስ እንደሚችል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ “ ሀቨርትዝ ለጨዋታው እንደሚደርስ ተስፋ አደርጋለሁ “ ያሉ ሲሆን ይደርሳል ብዬ መናገር ግን አልችልም በማለት ተናግረዋል።

ሀቨርትዝ ወደ ሜዳ የማይመለስ ከሆነ መድፈኞቹ ነገ በኒውካስል ጨዋታ የቀኝ ክንፍ አማራጭ ተጨዋቾቻቸው ቡካዩ ሳካ ፣ ንዋኔሪ እና ሀቨርትዝን የሚያጡ ይሆናል።

የአርሰናል ጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ?

መድፈኞቹ በነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ

- ቡካዩ ሳካን
- ራሂም ስተርሊንግ
- ኢታን ንዋኔሪ
- ቶሚያሱ እና
- ቤን ወይትን በጉዳት ሲያጡ የካይ ሀቨርትዝ መድረስ አጠራጣሪ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዲያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ተረከበ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ሀዲያ ሆሳዕና ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀዲያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግብ ጫላ ተሺታ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ተሸንፏል።

ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ሰባተኛ ተከታታይ ድላቸውን አሳክተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሀዲያ ሆሳዕና :- 22 ነጥብ
2️⃣ መቻል :- 21 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ስሑል ሽረ ከ መቻል

ቅዳሜ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፒኤስጂ ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው ! የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ከፈረንሳዊው ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ጋር በጥር የዝውውር መስኮት መለያየቱ አይቀሬ መሆኑን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒን በቡድናቸው እንደማይፈልጉት ተገልጿል። ተጨዋቹ ባለፉት ጨዋታዎች ከፒኤስጂ ስብስብ ውጪ እንደነበር የሚታወስ ነው። ራንዳል ኮሎ…
ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ፒኤስጂን ይለቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ መዘገቡ ይታወሳል።

አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በውሰት ውል ለማስፈረም በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

በተጨማሪም ቶተንሀም እና ጁቬንቱስ ራንዳል ኮሎ ሙኣኒን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ክለቦች መሆናቸው ተዘግቧል።

የ 26ዓመቱ ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ከሁለት አመት በፊት በ 90 ሚልዮን ዩሮ ፒኤስጂን ቢቀላቀልም ብዙም የመሰለፍ እድል እየተሰጠው አይገኝም።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ እድልም የምትጎበኘው ጠንካራ ሰራተኞችን ነው “ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ

ፖርቹጋላዊው የኤሲ ሚላን አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ በጁቬንቱስ ጨዋታ ቡድናቸው እድለኛ ነበር ስለመባሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ እድልም ብትሆን የምትጎበኘው ጠንካራ ሰራተኞችን ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ ነገርግን በህይወት ውስጥ ትንሽ እድል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

" እድል የሚባለውን ነገር የማትወዱ ከሆነ ምናልባት የጁቬንቱስ ደጋፊ ከሆናችሁ ነው “ ሲሉ አሰልጣኙ ጨምረው ተናግረዋል።

ኤሲ ሚላን ከደቂቃዎች በኋላ ከኢንተር ሚላን ጋር የሱፐር ኮፓ ኢጣልያ የፍፃሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ትልቅ ሥራ ነው የሰራችሁት ” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ አይሽሬ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የክለቡን ተጨዋቾች አድንቀዋል።

በዛሬው ዕለት በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የማንችስተር ዩናይትድ የረጅም ጊዜ የልምምድ ማዕከሉ እንግዳ ተቀባይ ካት ፊብስ ቀብር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በቀብር ስነስርዓቱ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና አምበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ መሪነት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና የክለቡ የቀድሞ ተጨዋቾች ተግኝተው ነበር።

በስፍራው ንግግር ያደረጉት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የክለቡ ተጨዋቾች ትላንት በሊቨርፑል ጨዋታ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል ብለዋል።

“ በጣም ጥሩ ውጤት ነው ያስመዘገባችሁት ትልቅ ስራ ሰርታችኋል “ ሲሉ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማድሪድ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !

በስፔን ኮፓ ዴላሬ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከዲፖርቲቫ ሚኔራ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግብ አርዳ ጉለር 2x ፣ ካማቪንጋ ፣ ሉካ ሞድሪች እና ቫልቬርዴ አስቆጥረዋል።

ሪያል ማድሪድ ማሸነፉን ተከትሎ የኮፓ ዴላሬ አስራ ስድስት ወስጥ መቀላቀል ችለዋል።

ሉካ ሞድሪች በ 1️⃣3️⃣ አመታት የሪያል ማድሪድ ቆይታው የመጀመሪያውን የኮፓ ዴላሬ ግብ አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ሻምፒዮን ሆኗል !

ሳውዲ አረብያ ሪያድ በተደረገው የጣሊያን ሱፐር ካፕ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ሄርናንዴዝ ፣ ክርስቲያን ፑልሲች እና ታሚ አብርሃም ከመረብ አሳርፈዋል።

የኢንተር ሚላንን ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ታሬሚ አስቆጥረዋል።

ኤሲ ሚላን ከ 2ለ0 ተመሪነት ተነስቶ ከእረፍት በኋላ ባስቆጠራቸው ሶስት ግቦች ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ኮንሴሳኦ ኤስ ሚላንን እየመሩ ያደረጓቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል።

ኤሲ ሚላን የጣልያን ሱፐር ካፕ ዋንጫን በታሪክ #ለስምንተኛ ጊዜ ማንሳት ችለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/07 00:14:33
Back to Top
HTML Embed Code: