Telegram Web Link
85'

ክሪስታል ፓላስ 1-5 አርሰናል

ሳር                    ጄሱስ
                                ሀቨርትዝ
                                 ማርቲኔሊ
ራይስ

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
መድፈኞቹ ድል አድርገዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ጋብሬል ጄሱስ 2x ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ዴክላን ራይስ እና ማርቲኔሊ አስቆጥረዋል።

የክሪስታል ፓላስን ብቸኛ ግብ እስማኤል ሳር ከመረብ አሳርፏል።

አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ያደረጋቸውን ያለፉት አስር ጨዋታዎች አልተሸነፈም ሰባቱን ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።

ብራዚላዊው ተጨዋች ጋብሬል ጄሱስ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ አርሰናል :- 33 ነጥብ
1️⃣5️⃣ ክሪስታል ፓላስ :- 16 ነጥብ

አርብ - አርሰናል ከ ኢፕስዊች ታውን

ሐሙስ - በርንማውዝ ከ ክሪስታል ፓላስ

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
30 '

ባርሴሎና 1-0 አትሌቲኮ ማድሪድ

ፔድሪ

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
የእረፍት ሰአት  !

በስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የባርሴሎናን የመሪነት ግብ ፔድሪ ከመረብ አሳርፏል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመርያው አጋማሽ ባርሴሎና 59% - 41% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
60 '

ባርሴሎና 1-1 አትሌቲኮ ማድሪድ

ፔድሪ ዲ ፓውል

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
90+6 '

ባርሴሎና 1-2 አትሌቲኮ ማድሪድ

ፔድሪ           ዲ ፓውል
ሶርሎት

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
አትሌቲኮ ማድሪድ የሊጉን መሪነት ተረከበ !

በስፔን ላሊጋ አስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አትሌቲኮ ማድሪድ ከባርሴሎና ጋር ያደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የአትሌቲኮ ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ሮድሪጎ ዲ ፓውል እና አሌክሳንደር ሶርሎት ሲያስቆጥሩ የባርሴሎናን ግብ ፔድሪ ከመረብ አሳርፏል።

አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ባርሴሎናን በሜዳው ማሸነፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የሚመራው ባርሴሎና ተከታታይ ሁለተኛ የላሊጋ ጨዋታውን ተሸንፏል።

ባርሴሎና ካለፉት ሰባት የላሊጋ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ጨዋታ ነው።

አትሌቲኮ ማድሪድ በሁሉም ውድድሮች አስራ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ማሳካት ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ አትሌቲኮ ማድሪድ :- 41 ነጥብ
2️⃣ ባርሴሎና :- 38 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ኦሳሱና

ቅዳሜ - ሄታፌ ከ ባርሴሎና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🤩የቤቲካ ምርጥ የቀኑ አሸናፊዎች ! 🤩
🌟ደንበኞቻችን ተወራርደው በትልቁ አሸንፈዋል !
🥁ቀጣዩ የእናንተ ተራ ነው !
🌟አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
🔹Mackbook M2 Air

•02 CC 139,000 Birr
•15 CC 129,000 Birr
•50 CC 119,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

@Heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

11:00 ኢትዮጵያ ከ ሱዳን

11:00 ኤቨርተን ከ ቼልሲ

11:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ በርንማውዝ

12:15 ሪያል ማድሪድ ከ ሲቪያ

1:30 ቶተንሀም ከ ሊቨርፑል

4:45 ሞንዛ ከ ጁቬንቱስ

5:00 ሌንስ ከ ፒኤስጂ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የቡካዩ ሳካ ጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ በትላንቱ የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

ቡካዩ ሳካ ከጨዋታው በኋላ በመራመጃ ታግዞ ስታዲየሙን ለቆ ሲወጣ ተስተውሏል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት የቡካዩ ሳካ ጉዳት እንዳሰጋቸው ገልጸዋል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም “ ቡካዩ ሳካ ጡንቻው ላይ ስሜት ተሰምቶታል በጨዋታው መቀጠል አልቻለም ጉዳቱ አስግቶናል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ቡካዩ ሳካ በቀጣይ ተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንደሚደረግለት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጠቁመዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ነን “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የፕርሚየር ሊጉ ዋንጫ ፉክክር አሁንም ክፍት መሆኑን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሴለ ዋንጫ ፉክክሩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ “ የዋንጫ ፉክክሩ ለእኛ ገና ክፍት ነው “ ቡድናቸው በፉክክሩ መኖሩን ጠቁመዋል።

“ ቡድኑ ሪከርዶችን ማስመዝገቡን መቀጠል አለበት ነገርግን ዋንጫ አይደለም በጣም አስፈላጊ የሆነው ዋንጫ ነው እሱን ማሸነፍ አለብን “ ሲሉ አርቴታ ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዩናይትድ ወደ ማሌዥያ ሊያቀኑ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ በያዝነው የውድድር ዘመን መጨረሻ ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዋ ሀገር ማሌዥያ ለማቅናት ማሰባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በማሌዥያ ከሀገሪቱ ክለብ ኩዋላ ሉምፑር ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ማቀዳቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ማሌዥያ የሚያደርገው ጉዞ 1️⃣0️⃣ ሚልዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝለት ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

በተጨማሪም ቀያዮቹ ሴጣኖች ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ ያመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Ethiopia 🇪🇹 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሳምንት በኋላ ታኅሣሥ 12 እና 13/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። በጉባኤው ለቀጣይ አራት አመታት የሚያገለግል አዲስ ፕሬዝዳንት እንዲሁም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚመረጥ ይጠበቃል። ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የቀረቡ እጩዎች በትላንትናው ዕለት በብሔራዊ ቴሌቪዥን “ አትሌቲክሱ በማን ይመራ ” በሚል…
የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዝዳንት ሾመ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።

በጉባኤው ከሚጠበቁ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀጣዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ አሸንፏል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በምርጫው 1️⃣1️⃣ ድምፆችን በማግኘት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ማሸነፉ ታውቋል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ የወከለኝ ክልል እንኳን አልመረጠኝም “

“ ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም “  የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተወክለው በእጩነት የተወዳደሩት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ “ ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም “ ብለዋል።

“ ምርጫው አልቋል አትሂድ ተብዬ ተነግሮኝ ነበር “ ያሉት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ በጉባኤው ያጋጠመኝም ይሄው ነው በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል።

አቶ ዱቤ ጁሎ ቀጥለውም “ የወከለኝ አዲስ አበባ ከተማ እንኳን እንዴት አንድ ድምፅ ይነፍገኛል “ ያሉ ሲሆን ድምፅ ካልሰጠኝ ታዲያ ለምን ወከለኝ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

“ በሀገር ላይ ደባ እየተሠራ ነው ፤ ምርጫው ፍትሃዊ ነው ብዬ ለመቀበል ይቸግረኛል የቡድንተኝነት ስራ ነው የተሰራው “ ሲሉ የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ ሁኔታውን ገልጸዋል።

ለተመረጡት ሀላፊዎች መልካም እድል እንደሚመኙ የገለፁት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ እንደዚህ አይነት ነገሮች መኖራቸው ለወደፊት ለስፖርቱ “ አደገኛ ነው " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወክሏቸው ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ በምርጫው ምንም ድምፅ አላገኙም።

ምንጭ :- ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የቼልሲ እና ኤቨርተንን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 11:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጨዋታ አሰላለፎች !

11:00 ኤቨርተን ከ ቼልሲ

11:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ በርንማውዝ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2024/12/25 19:42:50
Back to Top
HTML Embed Code: