Telegram Web Link
የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የአትሌቲክ ቢልባኦው ዋና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የስፔን ላሊጋ የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ አትሌቲክ ቢልባኦን እየመሩ በወሩ ካደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

አትሌቲክ ቢልባኦ በሊጉ በአስራ አራት ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፍራንክ ዲ ዮንግ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በማገገም ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ባርሴሎና ዛሬ ከያንግ ቦይስ ጋር ለሚያደርገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ፍራንክ ዲ ዮንግን በስብስቡ ማካተቱ ይፋ ተደርጓል።

ኔዘርላንዳዊው አማካይ ፍራንክ ዲ ዮንግ ለመጨረሻ ጊዜ ለባርሴሎና የተጫወተው ከአምስት ወራት በፊት እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ተጨዋቾቹ ልምምድ አልሰሩም !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ በዛሬው ዕለት የቡድን ልምምድ አለመስራቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም ጣልያናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ በቡድኑ ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ህመም አጋጥሞት የነበረው ዳርዊን ኑኔዝ እና አንዲ ሮበርትሰን በክለቡ መደበኛ ልምምድ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሊቨርፑል በነገው እለት በአንፊልድ ስታዲየም ከቦሎኛ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከ 100 ሚልዮን ዩሮ በላይ ይገባኛል “ ኦሲሜን

ናይጄሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን ለእሱ እየተጠየቀ የሚገኘው የዝውውር ሒሳብ የሚገባው መሆኑን ገልጿል።

በራሱ ብቃት እና ችሎታ እንደሚተማመን የሚገልጸው ቪክቶር ኦሲሜን “ ከ 100 ሚልዮን ዩሮ በላይ የዝውውር ሒሳብ ቢወጣብኝ ይገባኛል “ ብሏል።

በዘመናዊ እግርኳስ ውስጥ እንደ እሱ አይነት የአጨዋወት ባህሪ እና ስኬት ያላቸው ተጨዋቾች ጥቂት ብቻ መሆናቸውን ኦሲሜን አክሎ ገልጿል።

ስሙ በታላላቅ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ቪክቶር ኦሲሜን በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት መጨረሻ ቀን በውሰት ጋላታሳራይን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቴንሀግ ሁልጊዜም ሊባረር ሲል ያሸንፋል “ ኤቭራ

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ፓትሪስ ኤቭራ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የመሰናበት አደጋ አላቸው የሚባሉ ጨዋታዎችን የማሸነፍ ልምድ እንዳላቸው ተናግሯል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ ከፖርቶ እና አስቶን ቪላ ጋር የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የወደፊት ቆይታቸውን ሊወስኑ እንደሚችሉ እየተነገረ ይገኛል።

“ ሁልጊዜም ኤሪክ ቴንሀግ እነዚህን ጨዋታዎች ካላሸነፈ ይሰናበታል ብለን ስናስብ ሁሉንም ያሸንፋቸዋል በዚህ ፍራቻ የለኝም “ ሲል ኤቭራ ተናግሯል።

ፓትሪስ ኤቭራ አያይዞም አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የክለቡ ባለቤቶች " INEOS " ድጋፍ አላቸው ብሎ እንደሚያስብ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀሪ ኬን ልምምድ ሰርቷል !

እንግሊዛዊው የባየር ሙኒክ የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በቡድኑ መደበኛ ልምምድ መሳተፉ ተገልጿል።

ሀሪ ኬን ከቀናት በፊት ባየር ሙኒክ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር አቻ በተለያዩበት የሊግ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት አስተናግዶ ነበር።

ይህንንም ተከትሎ ባየር ሙኒክ ነገ ምሽት ቪላ ፓርክ ላይ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው የሻምፒየንስ ላግ ጨዋታ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ተጨዋቾቹ ልምምድ አልሰሩም ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ በዛሬው ዕለት የቡድን ልምምድ አለመስራቱ ተገልጿል። በተጨማሪም ጣልያናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ በቡድኑ ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተዘግቧል። በሌላ በኩል ህመም አጋጥሞት የነበረው ዳርዊን ኑኔዝ እና አንዲ ሮበርትሰን በክለቡ መደበኛ ልምምድ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል። ሊቨርፑል…
ሊቨርፑል የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ሊቨርፑል ነገ ከቦሎኛ ከሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

ፌዴሪኮ ኬሳ ሊቨርፑል ቅዳሜ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ በበኩሉ ለነገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከስሑል ሽረ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ስሑል ሽረ :- 5 ነጥብ

3️⃣ ፋሲል ከነማ :- 5 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ⏩️  ድሬዳዋ ከተማ ከ ስሑል ሽረ

ሰኞ ፋሲል ከነማ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
⚡️ #ከዋናው ይዘዙ፣ በስጦታ ይንበሽበሹ! ⚡️

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ8289 ወይም በስልክ ቁጥሮቻችን በመደወል፤ እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

ክርስቲያን ኤሪክሰን

አሌሀንድሮ ጋርናቾ

አንድሬ ኦናና የመስከረም ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያናዊው ዳኛ ከስራቸው ታገዱ !

ጣልያናዊው ዳኛ ፋቢዮ ማሬስካ የጣሊያን ሴርያ ጨዋታዎችን ለአንድ ወር እንዳይዳኙ መታገዳቸው ተገልጿል።

ዋና ዳኛው በቅርቡ የኩዌት ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ በመሩበት ወቅት ተጨዋች አስፈራርተዋል በሚል ቅሬታ እንደቀረበባቸው ተገልጿል።

ቅሬታ አቅራቢው ተጨዋች ዋና ዳኛው " በቀጣይ ስንገናኝ እገልሀለሁ " ብሎ አስፈራርቶኛል በሚል ቅሬታ ማቅረቡ ተነግሯል።

የ 43ዓመቱ ዳኛ ፋቢዮ ማሬስካ በተጨማሪም ዛሬ ምሽት አራተኛ ዳኛ ሆነው ሊመሩ ከነበረው የፒኤስቪ እና ስፖርቲንግ ሊስበን ጨዋታ በሌላ ዳኛ መተካታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ከጉዳቱ አገግሟል !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ካጋጠመው ጉዳት ማገገሙን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አረጋግጠዋል።

ከተጠበቀው ጊዜ ቀደም ብሎ ከጉዳቱ ያገገመው ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ልምምዱን እንደሚሰራ አሰልጣኙ ገልጸዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ነገ ከሊል ጋር በሚያደርጉት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ መሰለፉን አይተው እንደሚወስኑ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከአርሰናል ጋር ሻምፒየንስ ሊግ ካሸነፍኩ ለእኔ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል “ ካይ ሀቨርትዝ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ከአርሰናል ጋር የሚያሸንፍ ከሆነ የበለጠ እንደሚያስደስተው ገልጿል።

“ ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ በጣም አስደሳች ነው ነገርግን ከአርሰናል ጋር ማሸነፍ ከቻልኩ የበለጠ አስደሳች ይሆናል ለእኔ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል “ ሲል ካይ ሀቨርትዝ ተናግሯል።

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ ከዚህ በፊት ከቼልሲ ጋር የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማሳካቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ተሻረ !

ፖርቹጋላዊው የቀያይ ሴጣኖቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከቀናት በፊት በቶተንሀም ጨዋታ የተመለከተው ቀይ ካርድ እንደተሻረለት ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቹ የተመለከተውን ቀይ ካርድ በመቃወም ይግባኝ ጠይቀው እንደነበር ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በቀጣይ የሊግ መርሐ ግብሮች ለማንችስተር ዩናይትድ ግልጋሎት መስጠት እንደሚችል ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጣና ሞገዶቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የጣና ሞገዶቹን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም አለሙ እና መሳይ አገኘሁ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ?

2️⃣ኛ ባሕር ዳር ከተማ :- 6 ነጥብ

1️⃣2️⃣ኛ ሀድያ ሆሳዕና :- 3 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ

ማክሰኞ ⏩️ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ባሕር ዳር ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 አርሰናል ከ ፒኤስጂ

4:00 ስሎቫን ብራቲስላቫ ከ ማንችስተር ሲቲ

4:00 ባርሴሎና ከ ያንግ ቦይስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለማድረግ የምንፈልገው ጨዋታ ነው “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ከደቂቃዎች በኋላ ከፒኤስጂ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ መጓጓቱን ገልጸዋል።

“ ጨዋታውን ለማድረግ ጓጉተናል ጨዋታው ልናደርገው የምንፈልገው ትልቅ ጨዋታ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ፒኤስጂ ኳስ ተቆጣጥሮ የሚጫወት ቡድን መሆኑን ያነሱት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ኳስ ሲቀሙ በፍጥነት ለመቀበል ጥረት የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 08:22:43
Back to Top
HTML Embed Code: