Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
🌼 እስከ ጥቅምት 15 #ከዋናው ይዘዙ! 🌼

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ቴር ስቴገን ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል !

ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ቴር ስቴገን ትላንት ምሽት ክለቡ ቪያሪያልን ባሸነፈበት ጨዋታ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

ግብ ጠባቂው በቀኝ ጉልበቱ ላይ የመሰበር አደጋ እንዳጋጠመው ባርሴሎና ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ቴር ስቴገን ዛሬ ከሰዓት በኋላ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያደርግ ባርሴሎና አያይዞ ይፋ አድርጓል።

ይህንንም ተከትሎ ቴር ስቴገን በጉዳቱ ምክንያት እስከ ስምንት ወራት ጊዜ ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው ! ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የግራ መስመር ተጨዋች ፌርላንድ ሜንዲ ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ አዲስ የሶስት አመት ውል ለመፈረም መስማማቱ ተነግሯል። ሎስ ብላንኮዎቹ ካናዳዊውን የባየር ሙኒክ የመስመር ተጨዋች አልፎንሶ ዴቪስ የሚያስፈርሙ ከሆነ ፌርላንድ ሜንዲ…
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የግራ መስመር ተጨዋች ፌርላንድ ሜንዲ ኮንትራት ማራዘሙን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በይፋ አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ አዲስ የሶስት አመት ውል መፈረሙ ተነግሯል።

“ ፌርላንድ ሜንዲ አዲስ ውል ፈርሟል በእሱ በጣም ደስተኞች ነን “ ሲሉ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ምንም ቢያደርግ መጨረሻ ላይ ዋንጫው የኛ ነው “ አካንጂ

የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ማኑኤል አካንጂ ሁልጊዜም ከአርሰናል ጋር ስንጫወት ድራማ መስራት ነው የሚፈልጉት በማለት ተናግሯል።

“ በምሽቱ ጨዋታ እንዳደረጉት ከእነሱ የተሻለ ይኖራል ብዬ አላስብም “ ያለው ማኑኤል አካንጂ ነገርግን በዚህ አመትም የተለየ አይሆንም በመጨረሻ ዋንጫው የኛ ነው ሊጉን በድጋሜ እናሸንፋለን “ ብሏል።

“ እነሱ ሁልጊዜ የሚፈልጉት ድራማ ነው ፣ በአንድ ነጥብ ከተደሰቱ ለእነሱ ሰርቷል እኛ ግን ደስተኛ አይደለንም ቢሆንም አሁንም የሊጉ መሪ ነን “ ሲል ማኑኤል አካንጂ ተናግሯል።

“ ለማሸነፍ ሞክረን ነበር በተለይ የአንድ ተጨዋች ብልጫ በወሰድንበት ከእረፍት በኋላ ነገርግን በአስር ተጨዋች በፍፁም ቅጣት ምት ክልላቸው ውስጥ ሲከላከሉ ነበር ከባድ ነበር “ ማኑኤል አካንጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን አዲስ ባለቤት ማግኘቱ ይፋ ሆነ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ባለቤት ፋርሀድ ሞሽሪ በክለቡ ያላቸውን ድርሻ ለፍሬድኪን ግሩፕ ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል።

ይህንንም ተከትሎ ፍሬድኪን ግሩፕ ፋርሀድ ሞሽሪ በመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የነበራቸውን 94.1% ድርሻ በመግዛት ክለቡን በበላይነት እንደሚቆጣጠረው ተነግሯል።

ፍሬድኪን ግሩፕ የክለቡን ድርሻ በመቆጣጠር የተወሰነውን እዳም ለመክፈል ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል።

አሜሪካዊው ፍሬድኪን በተጨማሪ የጣልያኑ ክለብ ሮማ ባለቤት እና ፕሬዝዳንት መሆናቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ባለፉት ሁለት አመታት ትልቁ ተፎካካሪያችን ነው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ባለፉት ሁለት አመታት አርሰናልን በዋንጫ ፉክክሩ በመርታታቸው “ እድለኛ ነበርኩ “ ብለዋል።

“ አርሰናል ባለፉት ሁለት አመታት ትልቁ ተፎካካሪያችን ነው ፤ እነሱን በመርታታችን እድለኞች ነን ነገርግን ፍልሚያውን እናውቀዋለን ፈተናውን መቀበል አለብን “ ሲሉ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ኬቨን ዴብሮይን ያጋጠመው ጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘው ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም ዴብሮይን ቡድናቸው በቀጣይ ከዋትፎርድ እና ኒውካስል ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ መድረሱን እርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስሑል ሽረ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ስሑል ሽረ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የስሑል ሽረን የማሸነፊያ ግቦች አሌክስ ኪታታ ፣ አላዛር አድማሱ እና አሊያስ አህመድ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ነቢል ኑሪ እና ቢኒያም አይተን በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️  ሀዋሳ ከተማ ከ ስሑል ሽረ

አርብ ⏩️ ባሕር ዳር ከተማ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬይለር ናቫስ ወደ ባርሴሎና ?

ኮስታሪካዊው ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሊያስፈርመው የሚፈልግ ከሆነ ቡድኑን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል።

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂው ቴር ስቴገን ለረጅም ጊዜ መጎዳቱን ተከትሎ አዲስ ግብ ጠባቂ ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ በቅርቡ ከፒኤስጂ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮድሪ ጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ?

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ በትላንቱ የአርሰናል ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

ስፔናዊው አማካይ ሮድሪ በቀኝ ጉልበቱ ላይ ያጋጠመው ጉዳት የ " ACL " ጉዳት ሳይሆን እንዳልቀረ በመዘገብ ላይ ይገኛል።

ይህ ከሆነ ሮድሪ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ በርካታ ወራት እንደሚያስፈልገው እና ምናልባትም በዚህ የውድድር አመት ላንመለከተው እንደምንችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሮድሪ ጉዳት ሁኔታ ምን ይመስላል ? የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ በትላንቱ የአርሰናል ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። ስፔናዊው አማካይ ሮድሪ በቀኝ ጉልበቱ ላይ ያጋጠመው ጉዳት የ " ACL " ጉዳት ሳይሆን እንዳልቀረ በመዘገብ ላይ ይገኛል። ይህ ከሆነ ሮድሪ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ በርካታ ወራት እንደሚያስፈልገው እና ምናልባትም በዚህ የውድድር አመት…
ሮድሪ ከውድድር አመቱ ውጪ ሊሆን ይችላል !

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪ በትላንቱ የአርሰናል ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።

ይህንንም ተከትሎ የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ሮድሪ በጉዳቱ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

ማንችስተር ሲቲዎች ተጨዋቹ በጉዳት ከውድድር አመቱ ውጪ ይሆናል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው ተነግሯል።

ሮድሪ በእግርኳስ ህይወቱ ከዚህ በፊት በጉዳት ምክንያት ለሀገሩ እና ክለቡ ያመለጡት ጨዋታዎች ስምንት ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ኪንግስ ካፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ አል ነስር ከ አል ሀዜም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ሳዲዮ ማኔ እና አል ቡሻይል ማስቆጠር ችለዋል።

አል ነስር ማሸነፉን ተከትሎ የሰዑዲ ዓረቢያ ኪንግስ ካፕ አስራ ስድስት ውስጥ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️  ሀዋሳ ከተማ ከ ስሑል ሽረ

ቅዳሜ ⏩️ መቻል ከ ሲዳማ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውን የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከጊኒ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል።

ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሁለቱንም ጨዋታ በ ኮትዲቯር ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት ፌዴሬሽኖች በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍን መስፈርት የሚያሟላ ስታዲየም ስለሌለው ለማጣርያ ጨዋታዎች ኮትዲቯርን ምርጫው አድርጎ ቆይቷል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ 20,000 ተመልካችን በሚይዘው በያሙሶኩሮ ቻርለስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የደርሶ መልስ መርሐ ግብሩ መስከረም 30 እና ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ለማድረግ መታሰቡም ታውቋል።

ዋልያዎቹ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው በምድባቸው ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የፓርቲዛን ደጋፊዎች አሰልጣኛቸውን ደብድበዋል !

በሰርቢያ ሊግ የሚጠበቀው የቤልግሬድ ኢተርናል ደርቢ ጨዋታ ትላንት ምሽት ሲካሄድ ሬድ ስታር ቤልግሬድ ፓርቲዛንን በሜዳው 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በገጠማቸው ከባድ ሽንፈት የተበሳጩት የፓርቲዛን ደጋፊዎች የክለባችን መልበሻ ቤት ሰብረው መግባታቸው ተገልጿል።

ደጋፊዎቹ የክለቡ አሰልጣኝ አሌክሳንደር ስታኖጄቪች  እና ተጨዋቾች ላይ ስብርባሪዎችን በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸው ተነግሯል።

ፓርቲዛን መሸነፉን ተከትሎ ሊጉን ከሚመራው ታሪካዊ ተቀናቃኙ ሬድ ስታር ቤልግሬድ በአስር ነጥብ ርቆ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤን ቺልዌል ወደ ስብስብ ይመለሳል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ቤን ቺልዌል ወደ ቡድኑ ስብስብ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ቤን ቺልዌል ዛሬ ሰማያዊዎቹ ከባሮው ጋር በሚያደርጉት የሊግ ካፕ ጨዋታ ሜዳ ላይ ልንመለከተው እንደምንችል ተገልጿል።

ተጨዋቹ በቅርቡ በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ እንደማይፈልግ ተነግሮት ቼልሲን ለመልቀቅ ተቃርቦ እንደነበር አይዘነጋም።

አሰልጣኙ ስለ ስብሰባቸው ሲናገሩም ቀላል ነው በእኔ የአጨዋወት እሳቤ ውጪ የተገዙ ተጨዋቾች አይጫወቱም በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የአሊሰንን ግልጋሎት አያገኝም !

ሊቨርፑል ነገ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ የግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከርን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል ቅዳሜ ከዎልቭስ ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የአሊሰንን ግልጋሎት ላያገኝ እንደሚችል አሰልጣኙ ተናግረዋል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር በኤሲ ሚላን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወቅት የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 15:49:23
Back to Top
HTML Embed Code: