Telegram Web Link
80 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+7 ' ማንችስተር ሲቲ 2-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
       ስቶንስ               ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ነጥብ ተጋርተዋል !

በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርሰናልን ግብ ጋብሬል ማግሀሌስ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለማንችስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ጆን ሴቶንስ አስቆጥሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በ 105 ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ፋጣን ተጨዋች በመሆን የክርስቲያኖ ሮናልዶን ሪከርድ መጋራት ችሏል።

ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ አስራ ስድስተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ለአርሰናል አስቆጥሯል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በአራት ጨዋታዎች አስረኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ማንችስተር ሲቲ :- 13 ነጥብ
4️⃣ኛ አርሰናል :- 11 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ኒውካስል ከ ማንችስተር ሲቲ

ቅዳሜ አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አፄዎቹ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአፄዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቢኒያም ላንቃሞ እና ምኞት ደበበ ከመረብ ሲያሳርፉ ፍፁም ጥላሁን በፍፁም ቅጣት ምት ለፈረሰኞቹ አስቆጥ

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ ⏩️  ፋሲል ከነማ ከ መቐለ 70 እንደርታ

አርብ ⏩️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጎሉን በማስቆጠሬ ደስ ብሎኛል “ ጆን ስቶንስ

የማንችስተር ሲቲን የአቻነት ጎል በመጨረሻ ደቂቃ ያስቆጠረው ጆን ስቶንስ “ ደስተኛ ነኝ “ ሲል ከጨዋታው በኃላ ተደምጧል።

በቋሚ አሰላለፍ ጨዋታውን አለመጀመሩ ያላስደሰተው ስቶንስ “ ተቀይሬ ወደ ሜዳ የገባሁት ብልጫ እንድንወስድ ነው ፣ ያገኘሁትን አንድ እድል ወደ ግብነት ቀይሬያለሁ “ ብሏል።

ፔፕ ጋርድዮላ ያለውን መተግበሩን የተናገረው ስቶንስ “ ፔፕ ከሀላንድ ጋር በቅርበት እንድጫወት እና የአየር ላይ ኳሶችን እንድጠቀም ነግሮኛል “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በተጫዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባሳየው ብቃት “ ኮርቻለሁ “ ሲሉ ተጫዋቾቻውን አወድሰዋል።

“ በተጫዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ያሉት ሚኬል አርቴታ “ ከአለማችን ምርጡ ክለብ ጋር የተደረገ መርሐ ግብር ነበር “ በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ በዕለቱ ስለነበረው የዳኝነት ሁኔታ ሲጠየቁም “ ስለ ዳኝነቱ ማውራት ጥቅም የለውም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ቡድናችን በአስር ተጫዋቾች ለብዙ ደቂቃ መምራታችን ተአምር ነው “ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከቪያሪያል ጋር አድርጎ 5ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ 2x ፣ ፓብሎ ቶሬ እና ራፊንሀ 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለቪያሪያል ፔሬዝ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና በመጀመሪያ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ ሀያ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ ሁሉንም ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 18 ነጥብ
5️⃣ኛ ቪያሪያል :- 11 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሮብ ባርሴሎና ከ ሄታፌ

ሐሙስ እስፓኞል ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቀጣይ ተጨዋቾቼ ዳኛው ሲጠራቸው እንዳይሄዱ እነግራቸዋለሁ “ ጋርዲዮ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አርሰናሎች በመከላከል ላሳያችሁት ጥንካሬ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ተናግረዋል።

ስለ አርሰናል የመጀመሪያ ግብ ያነሱት ፔፕ ጋርዲዮላ “ በቀጣይ ለተጨዋቾቼ ዳኛው ጠርቶ ኑና አናግሩኝ ሲላችሁ መሄድ የለባችሁም እነሱ ይምጡና ያናግሯችሁ ብዬ እነግራቸዋለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቀጥለውም “ ቡድናችን አሁንም ለሊጉ ዋንጫ ለመፎካከር ፍቅሩ አለው “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዳኛው ስራ የጨዋታውን ውበት መጠበቅ ነው “

በአርሰናል መለያ በሊጉ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከጨዋታው በኃላ በዕለቱ ዳኛ ላይ ትችቱን ገልፆል።

“ የዳኛው ስራ የጨዋታውን ውበት መጠበቅ እና ሁለቱን ቡድኖች እኩል መርዳት ነው ፣ ይህ ግን በዛሬው ጨዋታ አልሆነም “ ሲል ካላፊዮሪ ተናግሯል።

ካላፊዮሪ በቀይ ካርድ የወጣው የቡድን አጋሩ ትሮሳርድ “ የዳኛውን ፊሽካ አልሰማም ነበር “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያን ፑልሲች እና ማቲኦ ጋብያ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢንተር ሚላን ፌዴሪኮ ዲማርኮ አስቆጥሯል።

ኤሲ ሚላን ከሁለት አመታት በኋላ ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረገውን የዴላ ማዶኒና ደርቢን ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ?

6️⃣ኛ ኢንተር ሚላን :- 8 ነጥብ
7️⃣ኛ ኤሲ ሚላን :- 8 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ኤሲ ሚላን ከ ሊቼ

ቅዳሜ ዩዲኔዜ ከ ኢንተር ሚላን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🥁 እነሆ አሸናፊ 🥁🥁

🌟 የዴሊ ጃክፖት የ 100,000ብር አሸናፊ::

🌟 ቤቲካ ዛሬም ውድ ደንበኞቹን ማንበሽበሹን ቀጥሏል!

🔥 እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ?ቀንዎን ዳጎስ ባለ አሸናፊነት ከመጀመር የተሻለ ምን አለ?

👉🏾 አሁኑኑ የነገውን ያሸንፉ Betika.et !

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
#PremierLeague

የአምስተኛ ሳምንት የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች ሲገባደዱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረክበዋል።

በውድድር አመቱ አራት ቡድኖች በሊጉ ያልተሸነፉ ሲሆን :-

- ማንችስተር ሲቲ
- አርሰናል
- ብራይተን እና
- ኖቲንግሀም ፎረስት በሊጉ ያልተሸነፉ ብቸኞቹ ክለቦች ናቸው።

በተቃራኒው :-

- ሌስተር ሲቲ
- ክሪስታል ፓላስ
- ኢፕስዊች ታውን
- ሳውዝሀምፕተን
- ኤቨርተን እና
- ዎልቭስ በሊጉ የአምስት ሳምንታት ጎዞ ሶስት ነጥብ ማግኘት ያልቻሉ ክለቦች ሆነዋል።

በወራጅ ቀጠናው ሳውዝሀምፕተን ፣ ኤቨርተን እና ዎልቭስ ይገኛሉ።

በቀጣይ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብርም :-

- ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ

- ቼልሲ ከ ብራይተን እና

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም የሚያደርጉት ጨዋታ ከተጠባቂ መርሐ ግብሮች መካከል ይገኙበታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጨዋታ :-

1️⃣@The_endxyz
2️⃣ኛ Yonathan
3️⃣@LEAVETOALLAH

የባርሴሎና እና ቪያሪያል ጨዋታ :-

1️⃣@Gunne_rs
2️⃣ኛ Habtamu
3️⃣@Nalosmigad

የኢንተር ሚላን እና ኤሲ ሚላን ጨዋታ :-

1️⃣@Gd20ya
2️⃣ኛ Freedom Tesema
3️⃣@Abiiti

@tikvahethsport
“ በሜዳችን በደንብ እንጠብቃቸዋለን “ ጋብሬል

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የኋላ መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ቡድናቸው ማንችስተር ሲቲን በሜዳው ሲገጥም ለማሸነፍ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ ነጥብ ከጣሉበት ከምሽት ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ጋብሬል ማግሀሌስ “ አሁን እነሱን በሜዳችን በጥሩ ሁኔታ እንጠብቃቸዋለን “ ሲል ተናግሯል።

ጋብሬል ማግሀሌስ አርሰናል ከተቀላቀለ ወዲህ ከየትኛውም የፕርሚየር ሊግ ተከላካይ በበለጠ 16 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የሊቨርፑል አምበል መሆን እፈልጋለሁ “ አርኖልድ

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በቀጣይ የሊቨርፑል አምበል የመሆን ህልም እንዳለው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ የሊቨርፑል አምበል መሆን እፈልጋለሁ የሁልጊዜም ህልሜ ይህ ነው ሊሳካም ላይሳካም ይችላል የእኔ ውሳኔ አይደለም የሚሆነው “ ሲል አሌክሳንደር አርኖልድ ተናግሯል።

“ አሁን ሙሉ ትኩረት የማደርገው የውድድር አመቱ ላይ እና ቡድኑ ሊጉን እንዲያሸንፍ ማገዝ ነው ፣ አውሮፓ ላይ ማንም ሊቀርበው የማይፈልገው ተከላካይ መሆን እፈልጋለሁ።"አርኖልድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኒውካስል ካራባኦ ካፕ ጨዋታ ተራዘመ !

ኒውካስል ዩናይትድ ነገ ከዌምብለደን ጋር ሊያደርገው የነበረው የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታው የተራዘመው በዌምብለደን ቼሪ ሬድ ሪኮርድስ ስታዲየም በገጠመ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ስታዲየሙ ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ጨዋታውን አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ሊሰጡ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረዙ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ባርሴሎና ተጨማሪ ተጨዋች ባለማስፈረሙ አመሰገንኩ “ ዣቪየር ቴባስ

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ባርሴሎና በአሁን ሰዓት ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚችል ገልጸዋል።

“ ባርሴሎና ተጨማሪ ተጨዋች ባለማስፈረሙ ፈጣሪን አመሰገንኩ “ ያሉት ፕሬዝዳን ዣቪየር ቴባስ ባይሆን ጨዋታዎችን 10ለ0 ነበር የሚያሸንፉት “ ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚችል ተናግረዋል።

“ እንደ ላሚን ያማል እና ቪንሰስ ጁኒየር ያሉ ተጨዋቾችን ልንከባከባቸው ይገባል።“ ዣቪየር ቴባስ

ባርሴሎና የግብ ጠባቂው ቴር ስቴገንን መጎዳት ተከትሎ ጉዳቱ የረጅም ጊዜ ከሆነ በቀጣይ ግብ ጠባቂ ማስፈረም እንደሚችል ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 17:33:12
Back to Top
HTML Embed Code: