Telegram Web Link
ባየር ሙኒክ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ከወርደር ብሬመን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ኦሊሴ 2x ፣ ሀሪ ኬን ፣ ጀማል ሙሲያላ እና ሰርጅ ግናብሪ አስቆጥረዋል።

ኦሊሴ በመጀመሪያ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ድንቅ ጅማሮ በማድረግ ላይ የሚገኘው ባየር ሙኒክ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ ሀያ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባየር ሙኒክ :- 12 ነጥብ
1️⃣0️⃣ኛ ወርደር ብሬመን :- 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

ቅዳሜ ባየር ሙኒክ ከ ባየር ሌቨርኩሰን

እሁድ ሆፌንሄም ከ ወርደር ብሬመን

የሌሎች የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ውጤት ካላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 '

ሊቨርፑል 3-0 በርንማውዝ

ድያዝ
ኑኔዝ

ቶተንሀም 2-1 ብሬንትፎርድ

ሶላንኬ               ምቤሞ
ጆንሰን

ፉልሀም 2-1 ኒውካስል ዩናይትድ

ሄሚኔዝ              ባርንስ
ስሚዝ ሮው

ሌስተር 0-1 ኤቨርተን
   
               ንድያዬ

አስቶን ቪላ 0-1 ዎልቭስ

               ኩንሀ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
83 '

ሊቨርፑል 3-0 በርንማውዝ

ድያዝ
ኑኔዝ

ቶተንሀም 2-1 ብሬንትፎርድ

ሶላንኬ               ምቤሞ
ጆንሰን

ፉልሀም 2-1 ኒውካስል ዩናይትድ

ሄሚኔዝ              ባርንስ
ስሚዝ ሮው

ሌስተር 1-1 ኤቨርተን
   
ማቪዲዲ               ንድያዬ

አስቶን ቪላ 1-1 ዎልቭስ

ዋትኪንስ               ኩንሀ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ሊቨርፑል 3-0 በርንማውዝ

ድያዝ
ኑኔዝ

ቶተንሀም 3-1 ብሬንትፎርድ

ሶላንኬ               ምቤሞ
ጆንሰን
ማዲሰን

ፉልሀም 3-1 ኒውካስል ዩናይትድ

ሄሚኔዝ              ባርንስ
ስሚዝ ሮው
ኔልሰን

ሌስተር 1-1 ኤቨርተን
   
ማቪዲዲ               ንድያዬ

አስቶን ቪላ 1-1 ዎልቭስ

ዋትኪንስ               ኩንሀ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ፣ በዋናው #ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ፍልሚያ ማን ያሸንፋል?

⚽️ ክሪስታል
ፓላስ ወይስ ማንቺስተር ዩናይትድ ⚽️

💬 ግምትዎን #በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ክለብ እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #3 ተከታታዮቻችን የዋናውን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት ይጠበቅቦታል።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።
👉🏾 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፡፡

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሊቨርፑል ድል አድርጓል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ሉዊስ ዲያዝ 2x እና ዳርዊን ኑኔዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቶተንሀም በዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ጄምስ ማዲሰን እና ጆንሰን ግቦች ብሬንትፎርድን 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

አስቶን ቪላ በበኩሉ ከመመራት ተነስቶ ዎልቭስን በዋትኪንስ ፣ ኮንሳ እና ዱራን ግቦች 3ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ፉልሀም ኒውካስልን 3ለ1 ሲያሸንፍ ኤቨርተን ከሌስተር ሲቲ እንዲሁም ሳውዝሀምፕተን ከኢፕስዊች ታውን በተመሳሳይ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ሊቨርፑል :- 12 ነጥብ
3️⃣ኛ አስቶን ቪላ :- 12 ነጥብ
1️⃣3️⃣ኛ በርንማውዝ :- 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

ቅዳሜ ዎልቭስ ከ ሊቨርፑል

እሁድ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ሰኞ በርንማውዝ ከ ሳውዝሀምፕተን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
1' ክሪስታል ፓላስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ክሪስታል ፓላስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባሕር ዳር ከተማ አመቱን በድል ጀምሯል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ባሕር ዳር ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ ፍፁም አለሙ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ

አርብ ⏩️ ባሕር ዳር ከተማ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የሪያል ማድሪድ እና እስፓኞልን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
#SerieA

በጣሊያን ሴርያ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከጁቬንቱስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ ናፖሊ :- 10 ነጥብ
4️⃣ኛ ጁቬንቱስ :- 9 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ጂኖኣ ከ ጂቬንቱስ

እሁድ ናፖሊ ከ ሞንዛ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ ካደረጋቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣1️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 7 ነጥብ
1️⃣6️⃣ኛ ክሪስታል ፓላስ :- 3 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ቅዳሜ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን “ ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኑን ከዛሬው ድል በኋላ ተናግረዋል።

“ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንገኛለን “ ሲሉ የተደመጡት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የተወሰኑ ነገሮችን ግን ልናሻሽል ይገባል በማለት ገልጸዋል።

ሆኖም ቡድናቸው ሶስት ነጥቡን ማሳካቱ አስፈላጊ መሆኑን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ደረጃቸውን ካሻሻሉበት ድል በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ወደ ማንችስተር መመለስ ከባድ ነው “ ኦናና

የቀያይ ሴጣኖቹ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በምሽቱ ጨዋታ ወሳኝ የግብ እድሎችን ማዳን ቢችልም ትርጉም አልባ እንደሆነበት ገልጿል።

“ ሁለቱን ኳሶች ማዳኔ ምንም ለውጥ አላመጣም ማሸነፍ አልቻልንም ፤ አሁን ወደ ማንችስተር መመለስ ከባድ ነው “ ሲል አንድሬ ኦናና ተናግሯል።

“ በሀዘን ነው ወደ ቤቴ የምሄደው “ ሲል ያለበትን ሁኔታ የገለፀው ኦናና ሶስት ነጥብ ማግኘት ነበረብን አንድ ነው ያገኘነው ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የሊቨርፑል እና በርንማውዝ ጨዋታ :-

1ኛ. @Abelabera12
2ኛ. @abulala10
3ኛ. @RG_81014

የጁቬንቱስ እና ናፖሊ ጨዋታ :-

1ኛ. @Mo0m67
2ኛ. Jo
3ኛ. @Neba63

የማንችስተር ዩናይትድ እና ክሪስታል ፓላስ ጨዋታ :-

1ኛ. @abulala10
2ኛ. @pavel2446
3ኛ. Mc alister

@tikvahethsport
“ ደስተኛ አይደለሁም ማሸነፍ ነበረብን “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ያስመዘገበው ውጤት እንዳላስደሰታቸው ከጨዋታው በኃላ ገልጸዋል።

“ ደስተኛ አይደለሁም ማሸነፍ ነበረብን “ ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ “ ከእረፍት በፊት ቢያንሰ አንድ ወይም ሁለት ግብ ማስቆጠር ነበረብን “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ሂላል በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐግብር አል ሂላል ከአል ኢትሀድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ሂላልን የማሸነፊያ ግቦች ሚትሮቪች 2x እና አል ዳውሳሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአል ኢትሀድ ካሪም ቤንዜማ አስቆጥሯል።

አል ሂላል በዘንድሮው የውድድር አመት ያደረጋቸውን አራት የሊግ ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ አል ሂላል :- 12 ነጥብ
2️⃣ኛ አል ኢትሀድ :- 9 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

አርብ አል ኢትሀድ ከ አል ካሊጅ

ቅዳሜ አል ሂላል ከ አል ኮሉድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ ነጥብ ተጋርቷል !

በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ ከኒውዮርክ ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የኢንተር ሚያሚን ግብ ሊዮናርዶ ካምፓና ሲያስቆጥር ጄምስ ሳንድስ ኒውዮርክ ሲቲን አቻ አድርጓል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ኢንተር ሚያሚ :- 64 ነጥብ
6️⃣ኛ ኒውዮርክ ሲቲ :- 41 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

ቅዳሜ ሌሊት ኢንተር ሚያሚ ከ ቻርሎቴ

ቅዳሜ ሌሊት  ኒውዮርክ ሬድ ቡልስ ከ ኒውዮርክ ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሎስ ብላንኮዎቹ ድል አድርገዋል !

በስፔን ላሊጋ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከእስፓኞል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ካርቫል ፣ ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር እና ኪሊያን ምባፔ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ባለፉት ስድስት የላሊጋ ጨዋታዎች ሶስት ግብ አስቆጥሮ አራት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 14 ነጥብ
1️⃣3️⃣ኛ. እስፓኞል :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ ሪያል ማድሪድ ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ

ማክሰኞ እስፓኞል ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 00:44:26
Back to Top
HTML Embed Code: