Telegram Web Link
💻HP ,& DELL ላፕቶፖች ላይ  
ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ
አዳዲስ እና ያገለገሉ
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱ

Links 1, https://www.tg-me.com/youtrading1

Call us 0922354242

You Trading, we are located at bole medanalem infront of Selam city Mall , Lamir bldg 1st floor 109D  https://maps.app.goo.gl/MA9GjVtfjmedFD8fA?g_st=i
በወር 20,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
             🚴‍♀️  ብስክሌት
             🏍   ሞተር
             🛵   E-bike  ካልዎት ምን ይጠብቃሉ  ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን  ብስክሌት ፥ ሞተረ  እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የሥራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-
ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://www.tg-me.com/DriversRegistration_bot
ወይም
☎️ +251923344444 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
ጀርመን ተጨዋቿ ጉዳት አጋጥሞታል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን እና ዌስትሀም ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ኒክላስ ፉልክሩግ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ተጨዋቹ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ በመልቀቅ ወደ ለንደን መመለሱን የጀርመን እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቱ ጀርመን ዛሬ ምሽት ከኔዘርላንድ ጋር የምታደርገው ተጠባቂ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ምባፔን በምን መልኩ ይጠቀማል ?

ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ እንደ ዘጠኝ ቁጥር ተጨዋች እንደሚመለከቱት ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ኪሊያን ምባፔ ቦታው ላይ ካሳየው ነገር አንፃር በአለም ላይ ከእሱ የተሻለ ምርጥ የዘጠኝ ቁጥር ተጨዋች የለም የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔ የመሐል ተከላካዮችን በመለያየት በቀላሉ ግብ ማስቆጠር ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ተዘግቧል።

ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔ በተወሰነ ትእቢተኛ ተጨዋች ይሆናል ብለው ጠብቀው እንደነበረ ሲገለፅ ይሁን እንጂ ፍፁም ተቃራኒ ሆኖ እንዳገኙት ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ በቀጣይ ባሎን ዶር ያሸንፋሉ ያላቸውን ጠቅሷል !

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሚቀጥሉት አመታት ባሎን ዶር ማሸነፍ ይችላሉ ያላቸውን ተጨዋቾች ጠቅሷል።

“ ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ ጥቂት አመታት ባሎን ዶር ማሸነፍ ይችላል “ ሲል የተደመጠው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጁድ ቤሊንግሀም ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ላሚን ያማልም እድል አላቸው። ብሏል።

" ሪያል ማድሪድ ምርጥ አሰልጣኝ እና ፕሬዝዳንት አለው ጠንካራ ቡድንም አላቸው ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ ብዙ ጥሩ ነገሮችን ያደርጋል።" ሲል ሮናልዶ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ማድሪድ እድለኛ ሳይሆን በታሪክ ምርጡ ክለብ ነው “ ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድ በርካታ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያሳካው በእድል አለመሆኑ ተናግሯል።

“ ብዙዎች ሪያል ማድሪድ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ እድለኛ ነው ሲሉ ይሰማል “ የሚለው ሮናልዶ “ ነገርግን ሪያል ማድሪድ እድለኛ አይደለም በእግርኳስ ታሪክ ምርጡ ክለብ ነው “ ብሏል።

“ አሁንም ደግሜ እናገራለሁ ማንችስተር ዩናይትድን አሁንም እወደዋለሁ ምርጡ ሁሉ እንዲገጥመው ምኞቴ ነው።" ሮናልዶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🌼 አዲስ ዓመት፣ አዲስ ግብ፣ አዲስ ስንቅ! 🌼

እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

Instagram | Facebook | TikTok

ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የለንደን ደርቢ ጨዋታ 💥

⚽️ ደማቁ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ! አርሰናል የለንድን ተቀናቃዩን ቶተንሀም እሁድ መስከረም 5 ከሰዓት 10፡00 ሰዓት በቶተንሃም ሜዳ ይገናኛሉ!

🤔 አርሰናል እያሳየ የለውን ብቃት መቀጠል ይችላል? የእናንተን ግምት ያጋሩን
 
👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

👉 የዲኤስቲቪን ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
ያማል የወሩ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ተብሏል !

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ከ 23ዓመት በታች ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የወሩ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በወሩ ውስጥ ለባርሴሎና አንድ ግብ አስቆጥሮ አራት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ትኬቶችን ሸጦ አጠናቋል !

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ከባየረ ሙኒክ ጋር ለሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የተዘጋጁ ትኬቶች ተሸጠው መጠናቀቃቸውን አሳውቋል።

ቪላ ፓርክ ላይ ለሚደረገው የ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ የተዘጋጁ ትኬቶች ከወዲሁ ጨዋታው ሃያ ሁለት ቀናት እየቀረው መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

አስቶን ቪላ ከአርባ አንድ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 ዋናው × ላይቤሪያ 🇱🇷

እናት ኢትዮጵያ በልጆችዋ ለአፍሪካዊያውያን ታላላቅ ነገሮችን አበርክታለች። እኛም #ዋናዎቹ እንደቀደምት አባቶቻችን የሀገራችንን ስም የስፖርት አልባሳትን በማቅረብ በአህጉራችን ከፍ እያደረግን እንገኛለን።
ሀሳቡ ሰፊ ተግባሩ ግዙፍ የሆነው የስፖርት ትጥቅ አቅራቢነታችን በአፍሪካ አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Instagram | Facebook | TikTok

ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አርሰናል እሁዱ ምን አይነት ማልያ ይለብሳል ?

አርሰናል በእሁዱ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ከሜዳ ውጪ የሚጠቀሙትን የሜዳ ውጪ ጥቁር ማልያ ለብሰው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የክለቡን ባህላዊ ቀይ እና ነጭ የሜዳ ማልያ ለመልበስ ጥያቄ ቢያቀርቡም በአወዳዳሪው አካል ተቀባይነት አለማግኘቱ ተነግሯል።

አርሰናል ተቀባይነት ያላገኘው ቀዩ ማልያ ነጭ ቀለም ጎልቶ ስለሚታይ ከቶተንሀም ማልያ ጋር ይጋጫል በሚል መሆኑ ተዘግቧል።

አርሰናል በሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ከቀዩ ማልያ ውጪ ሲጫወት ከሰላሳ ስምንት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ታንዛኒያ ጊኒን አሸንፋለች ! 

በ 2025 የሞርኮ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኙት ታንዛኒያ እና ጊኒ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።

የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1ኛ. ኮንጎ :- ስድስት ነጥብ
2ኛ. ታንዛኒያ :- አራት ነጥብ
3ኛ. ኢትዮጵያ :- አንድ ነጥብ
4ኛ. ጊኒ :- ምንም ነጥብ


የምድቡ ቀጣይ ጨዋታዎች ?

- ኢትዮጵያ ከ ጊኒ

- ኮንጎ ከ ታንዛኒያ

የ 2025 ሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ቀጣይ ጥቅምት ወር ውስጥ ይካሄዳሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናታን አኬ ጉዳት አጋጥሞታል !

ኔዘርላንድ ከጀርመን ጋር እያደረገች በምትገኘው የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ የማንችስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናታን አኬ ጉዳት አጋጥሞታል።

ተጨዋቹ በጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት በእርዳታ ታግዞ ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል።

በናታን አኬ ምትክ የአርሰናሉ የኋላ መስመር ተጨዋች ጁሪየን ቲምበር ተቀይሮ ወደ ሜዳ ገብቷል።

ጨዋታውን ጀርመን 2ለ1 በሆነ ውጤት በመምራት ላይ ትገኛለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#NationsLeague

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ግቦችን ለኔዘርላንድ ሬንደርስ እና ዱምፍሪስ ማስቆጠር ሲችሉ ለጀርመን ኡንዳቭ እና ጆሽዋ ኪሚች ከመረብ አሳርፈዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ከፊንላንድ አቻው ጋር ያደረገውን የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ በሀሪ ኬን ሁለት ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ሀሪ ኬን ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ አስረኛው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ኬን በጨዋታው ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 67ኛ እና 68ኛ ግቦቹን በማስቆጠር ጥሩ ምሽት ማሳለፍ ችሏል።

ኖኒ ማዱኬ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ባደረገበት ምሽት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
-የጤና ያድርግልን።

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

#TikvahEthiopiaFamily
#ቲክቫህኢትዮጵያቤተሰቦች

@tikvahethsport
አሜሪካ በይፋ አሰልጣኝ ቀጠረች !

አሜሪካ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከኮፓ አሜሪካ የምድብ ስንብት በኃላ አሰልጣኝ እያፈላለጉ ይገኙ የነበሩት አሜሪካዎች ፖቼቲኖን እስከ 2026 የአለም ዋንጫ ድረስ በሀላፊነት ሾመዋል።

ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ብሔራዊ ቡድኑን እየመሩ በቀጣይ ወር በወዳጅነት ጨዋታ ከፓናማ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማርቲን ኦዴጋርድ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ “

በሀገራት የኔሽን ሊግ ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው የመድፈኞቹ እና ኖርዌይ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ “ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ “ ሲል ቦምጋርትነር ተደምጧል።

“ ማርቲን ኦዴጋርድን ከልቤ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ “ የሚለው ቦምጋርትነር “ ይህን አስደናቂ ተጫዋች ለመጉዳት አውቄ ያደረኩት አይደለም “ ብሏል።

በማህበራዊ ትስስር ገፁ መልዕክቱን ያስተላለፈው ቦምጋርትነር ኦዴጋርድ በቶሎ እንዲያገግም ምኞቱን አያይዞ ገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/01 22:40:38
Back to Top
HTML Embed Code: