Telegram Web Link
እጥፍ ድርብ አሸናፊነት!

በቤቲካ ያሸነፉትን ገንዘብ በACCA እስከ 300% ከፍ ያድርጉ!

አሁኑኑ Betika.et ላይ አሸናፊነትን ይጀምሩ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
አትሌቶቻችን የቀድሞውን ታሪክ መድገም ይችላሉ?

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን ዛሬ ከምሽቱ 4፡20 በፓሪሱ ኦሎምፒክስ 10000 ሜትር ፍፃሜ ይሳተፋሉ!

💥በወንዶች 10000ሜ ሀገራችንን ወክለዉ የሚሳተፉ አትሌቶቻችን

ሰለሞን ባረጋ
በሪሁ አረጋዊ
ዮሚፍ ቀጀልቻ ናቸው።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#Paris2024 #LikeAChamp #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Paris2024                #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የማጣሪያ እና ፍፃሜ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የ10,000 ወንዶች #ፍፃሜ እንዲሁም 1,500 ወንዶች ፣ 800 እና 5,000 ሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋል።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ቀን 6:05 :- 1,500ሜ ወንዶች ማጣሪያ ( አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ፣ ሳሙኤል ተፈራ እና ኤርሚያስ ግርማ )

- ምሽት 1:10 :- 5,000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ( አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ )

- ምሽት 2:45 :- 800ሜ ሴቶች ማጣሪያ ( አትሌት ሀብታም አለሙ ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ፅጌ ዱጉማ )

- ምሽት 4:20 :- 10,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ( አትሌት ሰለሞን ባረጋ ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፓሪስ ኦሎምፒክ ቅሬታዎች ቀጥለዋል ! ስድስተኛ ቀኑን የያዘው የፓሪሱ የ2024 ኦሎምፒክ ውድድር የሚቀርቡ ቅሬታዎች አሁንም መቀጠላቸውን በስፍራው የሚገኙ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ለውድድር በፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶች መንደር የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በቆይታቸው ደስተኛ ባለመሆናቸው የተለያዩ ቅሬታዎችን በማቅረብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። አትሌቶቹ ካቀረቧቸው ቅሬታዎች መካከልም :- …
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሰባተኛ ቀኑ ላይ ሲደረስ በውድድሩ የሚስተዋሉ አነጋጋሪ ጉዳዮችም በየዕለቱ ቀጥለው ተስተውለዋል።

ገና ከጅምሩ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር አሁንም ቅሬታዎች ቀጥለዋል።

በፓሪስ ኦሎምፒክ እስካሁን ምን አይነት ቅሬታዎች ቀረቡ ?

- በመክፈቻው ዝግጅት ላይ የቀረበው ድርጊት የእምነት ተቋማትን ማስቆጣት

- ከፍተኛ የደህንነት ስጋት መኖር 

- የመዋኛ ገንዳዎች መስፈርት አላመሟላት

- የህንድ ተወዳዳሪዎች በምግብ ጥራት ጉድለት ምክንያት ቁርሾ ውስጥ በሚገኙት የፓኪስታን ምግብ ቤት ለመመገብ መገደድ

- ቤት አልባ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ስደተኞች ከፓሪስ ወደ ሌላ ስፍራ ተጉዘዋል።

- የአዘርባጃን ጁዶ ተወዳዳሪ የፈረንሳይ ተጋጣሚውን ካሸነፈ በኋላ ባንዲራውን ይዞ ደስታውን እንዳይገልፅ መከልከል

- የፓሪስ የህዝብ ትራንስፖርት ዋጋ በእጥፍ ከ2.15 ዩሮ ወደ 4 ዩሮ ጭማሪ ማሳየት

- የአርጀንቲና እግርኳስ ተጨዋቾች እንዲሁም ብራዚላዊው የቀድሞ ተጨዋች ዚኮ በፓሪስ ዝርፊያ መፈፀም ተጠቃሾቹ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማክ ቶሚናይ የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ ?

ስኮትላንዳዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስኮት ማክ ቶሚናይ ከፉልሀም የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለታል።

ፉልሀም ስኮት ማክ ቶሚናይን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም 20 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የቀረበው የዝውውር ሒሳብ የማንችስተር ዩናይትድን ፍላጎት ያላሟላ መሆኑ ሲገለፅ ምናልባት ቀያዮቹ ሴጣኖች በ25 ሚልዮን ፓውንድ ሊስማሙ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹ ክለቡን እንዲለቅ ግፊት እንደማያደርጉ እና የፌርፕሌይ ህጉን ለማስተካከል ጥያቄ ከቀረበ እንደሚመለከቱ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሲቲን ማሸነፍ የሚችል ቡድን እየሰራን ነው “ ቴን ሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቀጣይ ሳምንት በሚደረገው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ የሚችል ቡድን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

እረፍት ላይ የነበሩት ጋርናቾ እና ማርቲኔዝ በቀጣይ ቀናት ወደ ልምምድ እንደሚመለሱ የገለፁት ኤሪክ ቴንሀግ " በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ የሚችል ቡድን እየሰራን ነው “ ብለዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቀጥለውም ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ከተገለጸው ስኮት ማክ ቶሚናይ ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን እና እሱ በቡድናቸው ትልቅ ተጽዕኖ እንዳለው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒውካስል የተጫዋቹን ውል ማራዘም ይፈልጋል !

ኒውካስል ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን ኮንትራት ማራዘም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን ከእረፍት ሲመለስ ኮንትራቱን ለማራዘም ንግግር ለመጀመር ማሰባቸው ተነግሯል።

ኒውካስል ዩናይትድ ተጨዋቹ በመጀመሪያ አመቱ በክለቡ ላሳየው ጥሩ ብቃት መሸለም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

በተጨማሪም ተጫዋቹን ለረጅም ጊዜ ለማስፈረም ሲከታተል የቆየውን ሊቨርፑል ፍላጎት ማጥፋት እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ጥያቄ አቀረበ !

ማንችስተር ዩናይትድ የባየር ሙኒኮቹን ተጨዋቾች ማትያስ ዴሊት እና ናስር ማዝራዊ ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ባየር ሙኒክ የማንችስተር ዩናይትድን የመጀመሪያ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ በማድረግ የተሻለ ሒሳብ መጠየቃቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሁለቱንም ተጨዋቾች ለማስፈረም ከባየር ሙኒክ ጋር የሚያደርጉትን ንግግር አሁንም አጠናክረው መቀጠላቸው ተዘግቧል።

ሁለቱም ተጨዋቾች በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት እንደሚቀርብላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024              #TeamEthiopia 🇪🇹

የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር 1,500ሜ ወንዶች ሩጫ ውድድር ማጣሪያ ከደቂቃዎች በፊት ሲደረግ ሁለት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው አትሌት ኤርሚያስ ግርማ 3:35.21 በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

በመጀመሪያው ምድብ ተወዳድሮ የነበረው አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል በሚያስችለው ደረጃ ማጠናቀቅ ሳይችል ቀርቷል።

በሶስተኛ ምድብ የተወዳደረው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

የ1500ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 ሰዓት የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
“ ውሀ ማቀበል ተራ ስራ ነው “ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

“ ለኢትዮጵያ ብቻ የወጣ ህግ ካለ ጠይቀን እንረዳለን “

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በትላንቱ የኦሎምፒክ የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያን ለወከለው አትሌት ምስጋና ዋቁማ ውሀ አለመቅረቡ እንዳሳዘነው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

“ ውሀ ማቀበል ተራ ስራ ነው “ ሲል የገለፀው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ " ሲጀመር ረጅም ርቀት ነው የተወዳደረው ውሀ ሳይሆን የስፖርት መጠጥ ነበር ሊቀርብለት የሚገባው " በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእርምጃ ውድድር ከሩጫም በበለጠ ከባድ መሆኑን ያስረዳው የቀድሞ አትሌት " ይህ ሁሉ ሰው ሄዶ ውሀ እንኳን አለማቀበሉ አሳዝኖኛል ፣ የሄዱት ፓሪስን ለማየት ከሆነ እሱን ማወቅ አለብን “ ብሏል።

" ውሀ መስጠት የሚፈቀድባቸው ቦታዎች አሉ ጠረጴዛ ተቀምጧል ፤ የተሰጠው ምክንያት አግባብ አይደለም ፤ ለኢትዮጵያ ብቻ ተብሎ የወጣ ህግ ካለ " IOC " ን ጠይቀን እንረዳለን።" ኃይሌ

“ አትሌት ምስጋና ዋቁማ ወርቅ ያመጣ ያህል ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል " ሲል በውጤቱ እጅግ መደሰቱን የገለፀው ኃይሌ የተመዘገበው ያልጠበቀው ውጤት እንደነበርም ገልጿል።

መረጃው ከሸገር ስፖርት የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ካደረገው ቆይታ የተወሰደ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Apple AirPods & Samsung Earbuds

Brand New:
AirPods 2 - 15,500 ETB
AirPods 3 - 24,000 ETB
AirPods Pro 2 - 29,000 ETB


Buds Pro 2 - 16,000ETB
Buds 2 - 11,000ETB

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
የሳፋሪኮም #1Wedefitን የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን በመቀላቀል የምናገኛቸው ሽልማቶች ምንድን ናቸው?

💵 እስከ 400,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት!
🏕10 ምርጥ ተወዳዳሪዎች በቡት ካምፕ የመግባት እድል!
🎵በዳኞቻችን ምርጫ ለምርጥ 6 የ150,000 ብር ሽልማትና ነጠላ ዜማ የመልቀቅ እድል!

በመወዳደር ተሸላሚ ይሁኑ፤ ይሄ እድል እንዳያመልጣችሁ የ #1Wedefit የዲጂታል ሙዚቃ ውድድር ላይ በመሳተፍ ቤተሰብ በመሆን ታለንቶን ያሳዩን።
እንዝፈን! ፖስት እናድርግ! እናሸንፍ!
መልካም ዕድል!
" አርሰናል ስመጣ ብዙ እድሜያቸው የገፋ ተጨዋቾች ነበሩ " ኤዱ ጋስፐር

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር ከአምስት አመታት በፊት መድፈኞቹን ሲረከቡ በርካታ ተጨዋቾች እድሚያቸው የገፋ እንደነበሩ ገልጸዋል።

" እኔ አርሰናል ስመጣ በርካታ ተጨዋቾች እድሜያቸው ከ 27ዓመት በላይ ነበሩ ነገርግን የሚከፈላቸው ገንዘብ ከፍተኛ ነው ሜዳ ላይ የሚሰጡት ነገር ጋር አይገናኝም ነበር " ሲሉ ኤዱ ጋስፐር ተናግረዋል።

ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎት ባይሰጡም ከፍተኛ የደጋፊ ድጋፍ ነበራቸው በማለት የገለፁት ኤዱ ጋስፐር ክለቡን ለመጥቀም እነሱን ማሰናበት ነበረብን ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የህይወቴ ምርጡ ውሳኔ ዩናይትድን መልቀቄ ነው " ፔሬራ

ብራዚላዊው የፉልሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች አንድሬስ ፔሬራ በህይወት ዘመኑ የወሰነው ምርጥ ውሳኔ ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቁ መሆኑን ገልጿል።

ከማንችስተር ዩናይትድ አካዳሚ የተገኘው እና በክለቡ ዋናው ቡድን የተጫወተው አንድሬስ ፔሬራ " ማንችስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ የወሰንኩት የህይወቴ ምርጡ ውሳኔ ነው " ብሏል።

አሁን ላይ እየተጫወተ የሚገኝበት ፉልሀም ብዙ ያልተነገረለት ጠንካራ መሆኑን ያስረዳው አንድሬስ ፔሬራ " ጥሩ እግርኳስ እንጫወታለን ትልቅ ቡድኖችንም አሸንፈናል " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ለሴት ተጨዋቾቹ ልዩ ፖሊሲ ቀረፀ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ሴት ተጨዋቾቹ እና የቡድኑ አባላት በእርግዝና ወቅት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አዲስ ፖሊሲ መቅረፁን ይፋ አድርጓል።

ኤሲ ሚላን ሴት ተጨዋቾቹ በክለቡ በሚኖራቸው የመጨረሻ አመት ኮንትራት እርግዝና ካጋጠማቸው ውላቸው በቀጥታ በተመሳሳይ ክፍያ ለተጨማሪ አንድ አመት እንደሚታደስ ተገልጿል።

በተጨማሪም ለተጨዋቾቹ በእርግዝና ወቅት እንዲሁም ለሚወለደው ህፃን ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ኤሲ ሚላን ለሴት ነብሰጡር ተጨዋቾች የቀጥታ አንድ አመት ውል የሚሰጥ የመጀመሪያው የአውሮፓ ክለብ መሆን ችለዋል።

ከአመታት በፊት በሴት እግርኳስ ተጨዋቾች ዙሪያ በተደረገ ጥናት ቃለመጠይቅ ከተደረገላቸው ተጨዋቾች መካከል 2% የሚሆኑት ልጅ ሲኖራቸው 47% ቤተሰብ ለመመስረት ከእግርኳስ እንደሚወጡ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ምንም ጥሩ ብንሰራ እንተቻለን “ ቴን ሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ምንም ጥሩ ነገር ቢሰሩ ከመገናኛ ብዙሃን ትችት እንደሚቀርብባቸው በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ባለፈው አመት ከእንግሊዝ መገናኛ ባዙሃን ከፍተኛ ጫና እንደተደረገባቸው የገለፁት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ " በሊጉ እንደ እኛ የተተቸ ክለብ የለም ምንም ጥሩ ብንሰራ እንተቻለን " ብለዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም " ሁሉም ስለእኛ ጥሩ ያልሆነ ነገር ነው የሚያወሩት ፤ ይህ እኛን ይበልጥ እንድንሰራና ጠንካራ ቡድን እንድንሆን ያደርገናል እንጂ በጭራሽ ከአላማችን አያስቀረንም " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ስሚዝ ሮው የህክምና ምርመራውን አጠናቀቀ ! እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው ወደ ፉልሀም የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ያደረገውን የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ኤሚል ስሚዝ ሮው የፉልሀም ሪከርድ በሆነ 37 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ክለቡን እንደሚቀላቀል ተነግሯል። ፉልሀም የ 24ዓመቱን ተጫዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው በአምስት አመት ኮንትራት ያስፈርሙታል…
ስሚዝ ሮው በይፋ ፉልሀምን ተቀላቀለ !

በአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው ከአርሰናል ማስፈረሙን በይፋ አስታውቋል።

ፉልሀም ተጨዋቹን ቅድሚያ በሚከፈል 27 ሚልዮን ፓውንድ እና እየታየ በሚጨመር 7 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ማስፈረማቸው ተገልጿል።

ኤሚል ስሚዝ ሮው በፉልሀም የአምስት አመት ኮንትራት ከፈረመ በኋላ በሰጠው አስታያየት " ለወደፊቱ የእግርኳስ ህይወቴ ትክክለኛ እርምጃ ነው ከአሰልጣኙ ጋር ስለ እቅዱ በደንብ ተነጋግሬያለሁ " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 13:20:37
Back to Top
HTML Embed Code: