Telegram Web Link
#Paris2024         #TeamEthiopia🇪🇹

የ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መካሄዱን ሲቀጥል የአትሌቲክስ ውድድር በዛሬው ዕለት ጅማሮውን የሚያደርግ ይሆናል።

ከደቂቃዎች በኋላ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የ 20ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር መካሄዱን ሲጀምር ሀገራችን በምስጋና ዋቁማ የምትወከል ይሆናል።

የ 20ዓመቱ አትሌት ምስጋና ዋቁማ ኢትዮጵያ ባልተለመደ ርቀት ጥሩ ውጤት እንደምታስመዘገብ ህልም እንዳለው አስቀድሞ ገልጿል።

አትሌት ቀነኒስ በቀለን አርአያው እና ጀግናው አድርጎ የሚመለከተው አትሌት ምስጋናው ዋቁማ የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ተሳትፎውን ከደቂቃዎች በኋላ ያደርጋል።

አትሌቱ በዚህ ርቀት ከሳካቸው ስኬቶች መካከል :-

1⃣ኛ - የ 2024 የአፍሪካ ሻምፒዮና እንዲሁም የአፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት

1⃣ኛ - የ 2023ቱ የአፍሪካ ከ 20ዓመት በታች የ 10ኪ.ሜ እርምጃ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት

1⃣0⃣ኛ - በ2024ቱ የአለም የ 20ኪ.ሜ እርምጃ ውድድር ተጠቃሾቹ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024         #TeamEthiopia🇪🇹

ኢትዮጵያዊው አትሌት ምስጋና ዋቁማ ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የፓሪስ ኦሎምፒክ የ 20ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

አትሌት ምስጋና ዋቁማ 1:19:31 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በስድስተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ውድድሩን ኢኳዶራዊው አትሌት ፒንታዶ በበላይነት ሲያጠናቅቀው ብራዚላዊው ቦንፊርም የብር ስፔናዊው አትሌት አልቫሮ ማርቲን የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆነዋል።

የ 20ዓመቱ አትሌት ምስጋና ዋቁማ በውድድሩ የኢትዮጵያን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሜዳሊያ ጠብቄ ነበር " አትሌት ምስጋና ዋቁማ

ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ የ 20ኪ.ሜ እርምጃ ውድድር በመወከል ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው አትሌት ምስጋና ዋቁማ ሜዳልያ ጠብቆ እንደነበር ተናግሯል።

ውድድሩ የአየር ንብረት ለውጥ ቢኖሩትም አሪፍ እንደነበር የገለፀው አትሌት ምስጋና ዋቁማ " ሜዳልያ ውስጥ እንደምሆን ነበር ያሰብኩት አልተሳካልኝም " ሲል ከውድድሩ በኋላ ገልጿል።

በርቀቱ የኢትዮጵያን ሪከርድ በማስመዝገብ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ የጨረሰው አትሌቱ “ ሜዳልያ የማሳካት እቅድ ነበረኝ “ ያለው " ሆኖም እግዚአብሔር ያለው ነው የሚሆነውና በኦሎምፒክ ደረጃ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ውጤቱ ደስ ብሎኛል " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፓሪስ ኦሎምፒክ ቅሬታዎች ቀጥለዋል !

ስድስተኛ ቀኑን የያዘው የፓሪሱ የ2024 ኦሎምፒክ ውድድር የሚቀርቡ ቅሬታዎች አሁንም መቀጠላቸውን በስፍራው የሚገኙ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ለውድድር በፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶች መንደር የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በቆይታቸው ደስተኛ ባለመሆናቸው የተለያዩ ቅሬታዎችን በማቅረብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አትሌቶቹ ካቀረቧቸው ቅሬታዎች መካከልም :-

- የመኝታ አልጋ እና ፍራሽ አለመመቻቸት

- የምግብ ጥራት ጉድለት እና ማነስ

- የማረፊያ ክፍል መጥበብ እና በጋራ እንዲጠቀሙ መደረግ

- የማረፊያ ክፍሉ አየር መቆጣጠሪያ አለመኖር እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት የታላቋ ብሪታኒያ አትሌቶች ልዑክ ቡድን የራሱን ሼፍ መቅጠሩ እና ካረፈበት ማረፊያ ተጨማሪ ጉዞ አድርጎ ለመመገብ መወሰኑ ተገልጿል።

ሮማንያዊቷ የጠረጴዛ ቴኒስ ተጨዋች ዞክስ ስለ ማረፊያ ክፍሉ አስተያየቷን ስትሰጥ " ክፍሉ የአየር መቆጣጠሪያ ባለመኖሩ በር ከፍተን ነው የምንተኛው ፣ በጣም ጠባብ ክፍል ውስጥ ለሁለት ተጋርተናል።"ብላለች።

የታላቋ ብሪታኒያ ልዑክ ቡድን ሀላፊ በበኩላቸው  " የቀረበው ምግብ ጥራት ጉዳይ አጠራጣሪ ነው በቂ ምግብም እየቀረበ አይደለም " ብለዋል።

አሜሪካዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ኮኮ ጉፍ በበኩሏ በአንድ ክፍል ውስጥ አስር አትሌቶች መኖራቸውን እና በክፍሉ ውስጥ ሁለት መፀዳጃ ቤት ብቻ መኖሩን በማህበራዊ ሚዲያ ገልፃለች።

አሜሪካዊያን አትሌቶች በፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶች መንደር በተደረገላቸው አቀባበል በስፋት ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC (HP Victus)

🔸
Core 17 12th Gen
RTX 3050 TI (4GB)
104,000 Birr

🔹Core 17 13th Gen
RTX 4050 TI (6GB)
119,000 ETB

🔸Core 17 13th Gen
RTX 4060 (8GB)
139,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
ውበትና ጥራትን የተላበሱ የስፖርት አልባሳት #ከዋናው!

👉🏾 #ይዘዙን፣ ውበትን ይላበሱ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
“ ፌዴሬሽን ውስጥ ፆታዊ ትንኮሳም አለ “ ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድር በመጣ ቁጥር አለመግባባት የሚታይበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አትሌት ምርጫ ውስጥ ወገንተኝነት እና ፆታዊ ትንኮሳ መስተዋሉን ገልጿል።

አትሌቶች ምርጫ ላይ የሚስተዋለው ጭቅጭቅ " ወጥ የሆነ ህግ “ ባለመቀመጡ የመጣ ነው የሚለው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ " ህጉ በስርዓት ቢሆን ሁሉም አትሌት ተጠቃሚ በሆነ ነበር " ሲል ይገልጻል።

በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ደራርቱ ቱሉ ላይ “ ምንም ቅሬታ የለኝም ጥፋት አላየሁባትም “ ሲል የገለፀው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እሷ ከተከፋው ጋር ነች በሌሎቹ ላይ ግን ምን #እንደሚሰራ ስለማይ እርግጠኛ አይደለሁም ብሏል።

ህጉ ሲወጣ አሰልጣኞች መሳተፋቸው ለእነሱ በሚጠቅማቸው መልኩ ስላመቻቹት ጭቅጭቅ አይጠፋም ሲል ቀነኒሳ በቀለ ተናግሯል።

በዚህም ምክንያት በወገንተኝነት ፣ በቅርርብ ፣ በግል ፀብ ምክንያት አትሌቶች እንዳይመረጡ እያደረገ ነው በማለት አትሌቱ አስረድቷል።

“ በፌዴሬሽኑ ውስጥ አትሌቶች ምርጫ ፆታዊ ፍላጎትን ማስፈፀሚያ “ እየሆነ ስለመምጣቱም የገለፀው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ " ፆታዊ ትንኮሳም አለ ሁሉም መፅዳት አለበት “ ሲል አሳስቧል።

በፌዴሬሽኑ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት አትሌቶች አይምሩ አይባልም ነገርግን የተማሩ ሰዎችንም በማምጣት እና በመተጋገዝ እንዲሁም ህጎችን በማስተካከል መስራት ያስፈልጋል ሲል ቀነኒሳ በቀለ ተናግሯል።

በኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክለው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን ሲገልፅ “ በራሴ እተማመናለሁ ፤ የተቻለኝን አድርጌ ለሀገሬም ለራሴም ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ " ብሏል።

መረጃው ከሸገር ስፖርት ፕሮግራም ጋር ካደረገው ቆይታ የተወሰደው ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኦሎምፒክ ተወዳዳሪዋ ነብሰጡር  !

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የተሳተፈችው ግብፃዊቷ ተወዳዳሪ ነዳ ሓፊዝ የሰባት ወር ነብሰጡር እንደሆነች በማህበራዊ ትስስር ገጿ ገልፃለች።

ነዳ ሓፊዝ ግብፅን በኦሎምፒክ ሴቶች የግል " Sabre " ውድድር በመወከል እስከ ጥሎ ማለፍ መድረስ ስትችል በጥሎ ማለፍ ውድድር ተሸንፋ ከውድድሩ ወጪ ሆናለች።

" በውድድር መድረኩ ለእናንተ ሁለት ተጋጣሚ ቢታያችሁም ሶስት ነበርን የሰባት ወር ነብሰጡር ነኝ።"ስትል ነዳ ሓፊዝ በማህበራዊ ትስስር ገጿ ስለ ሆኔታዋ አስረድታለች።

ሶስተኛ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን ያደረገችው ነዳ ሓፊዝ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ግን ለእሷ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ተናግራለች።

የ 26ዓመቷ ነዳ ሓፊዝ የህክምና ዶክተር መሆኗ ሲገለፅ እንዲሁም ከዚህ በፊት የጂምናስቲክ ስፖርተኛ እንደነበረች ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ውሃ ዉስጥ ማሰብ የማልፈልገውን ነገር አይቻለሁ "

በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ትርያትሎን ተወዳዳሪዎች የውድድሩ አንድ አካል የሆነውን የዋና ውድድር ያደረጉበት የሴይን ወንዝ ጥራት እንዳበሳጫቸው ገልፀዋል።

የወንዙ ውሃ ጥራት ማነስ ብዙ ጥያቄዎች ሲያስነሳ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን የወንዶች ትርያትሎን ውድድርም በዚሁ ምክንያት በተደጋጋሚ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል።

በወንዙ 1.5 ኪ.ሜ ዋኝታ ውድድሯን ያደረገችው ቤልጂዬማዊት ጆሊን ቨርሜይለን ከውድድሩ በኋላ በከፍተኛ ንዴት " ወንዙ ውስጥ ማሰብ የማልፈልገውን ነገር አይቻለሁ " ብላለች።

“ ወንዙ ለመቶ አመታት የቆሸሸ ነው አዘጋጆቹ ለተወዳዳሪዎች ጤንነት ቅድሚያ እንሰጣለን ያሉት በምን አግባብ ነው “ ስትል ተወዳዳሪዋ ብስጭቷን ገልፃለች።

ተወዳዳሪዋ አክላም “ ከወንዙ ውስጥ ምንም ላለመጠጣት ጥረት አድርጌ አልተሳካልኝም ብዙ ውሃ ጠጥቻለሁ በቀጣይ ልታመምም ላለልታመምም እችላለሁ "ብላለች።

ለአንድ መቶ አመታት ያህል መዋኘት ታግዶ የቆየው የፓሪሱን ሴይን ወንዝ ለውድድሩ ንፁህ ለማድረግ ፈረንሳይ 1.2 ቢልዮን ፓውንድ ወጪ አድርጋ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒኪታህ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ !

እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲ ኒኪታህ አርሰናልን በመልቀቅ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ማርሴይ በበኩሉ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከአርሰናል ጋር ከስምምነት ለመድረስ በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በሀላፊነት የሾመው ማርሴይ ቡድኑን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ፈጣን ድል አስመዘገበች !

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች 66 ኪሎ ግራም ቦክስ ውድድር አልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማኔ ኬሊፍ ጣልያናዊቷን አንሄላ ካርኒ በ46 ሰከንድ ውስጥ መርታት ችላለች።

ጣልያናዊቷ ቦክሰኛ አንሄላ ካሪኒ ከተጋጣሚዋ በተሰነዘረባት የመጀመሪያ ቡጢ አፍንጫዋን ከፍተኛ ህመም እንደተሰማት እና መቀጠል እንዳልፈለገች ገልፃለች።

አንሄላ ካሪኒ ተጋጣሚዋን ለመጨበጥ እንኳን ፍቃደኛ ሳትሆን መወዳደሪያውን በእንባ ታጅባ ለቃ ስትሄድ ተስተውላለች።

በኋላም አስተያየቷን የሰጠችው አንሄላ ካሪኒ “ እንደዚህ አይነት ቡጢ አጋጥሞኝ አያውቅም ፤ በጣም ነው ያመመኝ ለአሰልጣኜ ከዚህ በላይ መቀጠል እንደማልችል ነግሬዋለሁ" ብላለች።

አልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ ኢማኔ ኬሊፍ በ2023 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከስርዓተ ፆታ ትክክለኛነት ጋር በተገናኛ ሳትሳተፍ ቀርታ ነበር።

በዚህም ምክንያት በማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃውሞ የነበረ ሲሆን የአልጄሪያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ የውጪ ሚዲያዎች እያደረጉ ያሉትን መሰረተ ቢሲ ፕሮፖጋንዳ እናወግዛለን ሲል መግለጫም አውጥቷል።

የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጂዮርጂዮ ሜሎኒ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት " ተመጣጣኝ ግጥሚያ አልነበረም አትሌቶች ከሚመጥናቸው ጋር መወዳደር መብት አላቸው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ውሀ የሚያቀብለኝ ባለመኖሩ አዝኛለሁ “ ምስጋና ዋቁማ

“ ከዚህ ቀደም የነበረው አሰራር ተቀይሯል “ አቶ ቢልልኝ መቆያ

ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ወክሎ ዛሬ ጠዋት የእርምጃ ውድድሩን ያደረገው አትሌት ምስጋና ዋቁማ በውድድሩ ወቅት ውሀ የሚያቀብለው በማጣቱ ቅር መሰኘቱን ገልጿል።

አትሌቱ ከጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ ጋር በነበረው ቆይታ “  ውሀ የሚያቀብለኝ አጥቼ ነበር “ ሲል የተናገረ ሲሆን " የሌሎች ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ ስር ውሀ አቀባይ አለ የእኛ ጋር ግን ማንም የሚያቀብል ሰው አልነበረም " ብሏል።

" በሁኔታው አዝኛለሁ " ሲል የገለፀው አትሌት ምስጋና ዋቁማ በኋላ ላይ ግን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሀላፊዎችን እንዳገኛቸው ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የቴክኒክ እና ህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ “ ከዚህ ቀደም የነበረው አሰራር ተቀይሯል “ ሲሉ አስረድተዋል።

ሀላፊው በስፍራው ለተገኘ ሚድያ በሰጡት አስተያየት አክለውም  “ ትናንት አዘጋጆቹ ውሀ የሚያቀብል ሰው እንዲፈቀድልን ጠይቀን በአዲሱ ህግ ራሱ አትሌቱ እንዲያነሳ ተወስኗል “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ክሪስታል ፓላስ ጥያቄው በማርሴ ተቀባይነት አገኘ ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር ለማስፈረም ከማርሴይ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል። ክሪስታል ፓላስ ተጫዋቹን ለማስፈረም ያቀረበው 15 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ በማርሴይ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል። ተጨዋቹ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በግል ከስምምነት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ…
ክሪስታል ፓላስ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር ከማርሴይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

እስማኤል ሳርን ባለፈው አመት በ13 ሚልዮን ዩሮ ያስፈረሙት ማርሴይ አሁን ላይ ለክሪስታል ፓላስ በ15 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ መሸጣቸው ተገልጿል።

ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር በክሪስታል ፓላስ ቤት የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አልሞ መተኮስ ከተፈጥሮ ያገኘሁት ፀጋ ነው " ዩሱፍ ዲኬክ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በ10 ሜትር አልሞ መተኮስ ውድድር ለሀገሩ ቱርክ የብር ሜዳልያ ያስገኘው አልሞ ተኳሽ ዩሱፍ ዲኬክ በማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ነበር።

ዩሱፍ ዲኬክ በውድድሩ ወቅት ከሌሎች አልሞ ተኳሾች በተለየ መልኩ አጋሽ መሳሪያዎችን ሳይጠቀም አንድ እጁን ኪሱ ከቶ ሲተኩስ መስተዋሉ እውቅናን አትርፎለታል።

ሌሎች አልሞ ተኳሾች ውድድራቸውን በሚያደርጉበት ወቅት ለውድድሩ የሚጠቅም የአይን መነፅር ፣ የጆር መከላከያ እና ሌሎች መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ።

የ 51ዓመቱ አልሞ ተኳሽ ዩሱፍ ዲኬክ ስለ ሁኔታው ተጠይቆ ሲያስረዳ " እኔ አጋዥ መሳሪያ አስፈልጎኝ አያውቅም " ሲል “ አልሞ መተኮስ ከተፈጥሮ የተሰጠኝ ፀጋ ነው " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከጋርዲዮላ ጋር በመልክ ብቻ ነው የምንመሳሰለው " ኢንዞ ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር የሚመሳሰሉት በመልክ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።

የፔፕ ጋርዲዮላ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው የሰሩት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ “ ፀጉር ስለሌለን እና ተመሳሳይ ፂም ስላለን እንድ አይነት አጨዋወት ይኖረናል ማለት አይደለም “ ብለዋል።

ብዙዎች ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ማነፃፀራቸው እንደፈተናቸው የጠቆሙት አሰልጣኙ " የጋርዲዮላን አጨዋወት እወደዋለሁ ነገርግን ከእኔ ጋር አይመሳሰልም “ ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ ጥሩ ከሚባሉት ሲቲ እና አርሰናል የሚለየን የቆዩ አሰልጣኞች በመያዛቸው ነው " የሚሉት ኢንዞ ማሬስካ " በትክክለኛው መንገድ እንደምንሆን እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም ከቼልሲ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ከቡድናቸው ጋር በመሆን እንደ ካርሎ አንቾሎቲ ድላቸውን ማክበር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦሊቬ ጅሩ ሎስአንጀለስን ለመቀላቀል ተስማማ ! ፈረንሳዊው የኤሲ ሚላን የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ሎስአንጀለስ እግር ኳስ ክለብን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። በጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ቤት ያለው ውል ቀጣይ ክረምት የሚጠናቀቀው ኦሊቬ ጅሩ ለሎስአንጀለስ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል። @tikvahethsport    …
ኦሊቬ ጅሩ በይፋ ሎስአንጀለስን ተቀላቅሏል !

በቅርቡ ከኤሲ ሚላን ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ የአሜሪካውን ሎስ አንጀለስ እግርኳስ ክለብ በነፃ ዝውውር መቀላቀሉ በይፋ ተገልጿል።

ኦሊቬ ጅሩ የአሜሪካውን ክለብ ሎስ አንጀለስ በአንድ አመት ኮንትራት የተቀላቀለ ሲሆን በውሉ ውስጥ ለተጨማሪ አንድ አመት የማራዘም አማራጭ መካተቱ ተነግሯል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ በሎስ አንጀለስ ቤት ዘጠኝ ቁጥር መለያ እንደሚለብስ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ክሬግ ሼክስፒር ህይወታቸው አለፈ !

የቀድሞ የሌስተር ሲቲ ምክትል አሰልጣኝ ክሬግ ሼክስፒር በዛሬው ዕለት ህይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ክሬግ ሼክስፒር ሌስተር ሲቲ እ.ኤ.አ 2016 ሳይጠበቅ ታሪካዊውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ሲያሳካ የክላውዲዮ ራኔሪ ምክትል አሰልጣኝ ነበሩ።

የአሰልጣኝ ክሬግ ሼክስፒር ቤተሰቦች " አሰልጣኝ ክሬግ በ60ዓመቱ በቤተሰቦቹ መሐል ዛሬ ጠዋት ህይወቱ አልፏል " ሲሉ በአሰልጣኞች ማህበር በኩል አሳውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የነጠላ ሜዳ ቴኒስ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ተለይተው ታውቀዋል።

በሩብ ፍፃሜው የአለም ቁጥር ሁለቱ ኖቫክ ጆኮቪች እንዲሁም የአለም ቁጥር ሶስቱ ካርሎስ አልካራዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል።

የ 21ዓመቱ ካርሎስ አልካራዝ ከኖቫክ ጆኮቪች በኋላ በኦሎምፒክ ነጠላ ቴኒስ ግማሽ ፍፃሜ የደረሰ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኗል።

በግማሽ ፍፃሜው እነማን ይገናኛሉ ?

- ኖቫክ ጆኮቪች ( ሰርቢያ ) ከ ሎሬንዞ ሙሴቲ ( ጣልያን )

- ካርሎስ አልካራዝ (ስፔን ) ከ አልያሲሜ ( ካናዳ )

በሜዳ ቴኒስ ጥንድ ውድድር ታላቋ ብሪታኒያን ወክሎ ከዳን ኢቫንስ ጋር የተጣመረው አንዲ መሪ በአሜሪካኖቹ ቶሚ ፓውል እና ታይለር ፍሪትዝ ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

በኦሎምፒክ ታሪክ በነጠላ ቴኒስ ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ያሳካው ብቸኛ ተጨዋች አንዲ መሪ የመጨረሻ የቴኔስ ውድድሩ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 11:14:32
Back to Top
HTML Embed Code: