Telegram Web Link
የፈረንሳዩ ክለብ ሊፈርስ መሆኑ ተገለጸ !

በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረው ቦርዶ በፈረንሳይ እግርኳስ ሊጎች መወዳደር የሚያስችለውን ፍቃድ ማደስ እንደማይፈልግ ለፈረንሳይ እግርኳስ ማህበር ማሳወቁ ተገልጿል።

የስድስት ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊው ቦርዶ በገጠመው ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ምክንያት ወደ ፈረንሳይ ሶስተኛ ሊግ ለመውረድ በመገደዱ ምክንያት ላለመቀጠል መወሰኑ ተነግሯል።

ከሳምንት በፊት በሊቨርፑል ባለቤቶች ባለቤትነት ሊያዝ የነበረው ክለቡ " FSG " ግዢውን ማቋረጣቸውን ተከትሎ ወደ ፈረንሳይ ሶስተኛ ሊግ ወርዷል።

አሁን ላይ ክለቡ ፍቃዱን እንደማያድስ እና ተጨዋቾቹ ውላቸው እንደሚቋረጥ የልምምድ ማዕከላቸውም እንደሚዘጋ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ትክክለኛውን ተጨዋች እስከምናገኝ እየጠበቅን ነው " አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ለማስፈረም ትክክለኛ ተጨዋቾችን እያፈላለገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዝውውር መስኮቱ እስካሁን ምንም ተጨዋች ያላስፈረሙት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዝውውር መስኮቱ መጨረሻ ዝውውሮችን እንደሚፈፅሙ ተናግረዋል።

" የሊቨርፑል ደረጃ ትልቅ በመሆኑ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች አፈላልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው " ያሉት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቢሆንም ቡድኑን በሁሉም ቦታዎች ለማጠናከር እየጣርን ነው ብለዋል።

" አሁንም በጣም ጥሩ ቡድን ነው ያለን በቀጣይ የምናልመውን ነገር ለማሳካት ተጨዋች ባናስፈርምም ያለን ስብስብ ከበቂ በላይ ነው ፣ በቀጣይ ወር ምንም ተጨዋች ካላስፈረምን የሚገርም ይሆናል።" አርኔ ስሎት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በማራኪ እና አዝናኝ ጨዋታዎች አሸናፊ ይሁኑ, እጅግ ብዙ የማሸናፍ አጋጣሚዎች ከቤቲካ ፋስታ
betika.com.et/et/betika-fasta
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ጉዳፍ ፀጋይ በሁለት ርቀቶች ትወዳደራለች !

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ በ 5000, 10,000 እና 15000ሜ እንደምተወዳደር የተነገራለት ጉዳፍ ፀጋይ በሁለት ርቀቶች ብቻ እንደምትወዳደር ተገልጿል።

እንደ ባለቤቷ እና አሰልጣኟ ህልፍ ይህደጎ መልዕክት አትሌቷ በ ኦሎምፒኩ 1500 እና 5000ሜ ብቻ ሀገራችንን እንደምትወክል ገልጿል።

አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ ለውሳኔው የ ኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ወቅሷል።

“ የሀገሯን ስም ከፍ ለማድረግ በሶስት ርቀት የመወዳደር ብቃትና አቅም ቢኖራትም በአንዳንድ የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አካለት ጫና በሁለት ርቀቶች ብቻ ትወዳደራለች” አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሜቴ በኦሎምፒክ ውድድሮች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የውድድሩን የመክፈቻ ዝግጅት ከስታዲየም ውጪ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።

የመክፈቻ ዝግጅቱን በፓሪስ ከተማ ታዋቂ በሆነው ሴይን ወንዝ ላይ በጀልባዎች አትሌቶችን በማድረግ ለማካሄድ እቅድ መያዙ ተነግሯል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ይህን ልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም ከግብ ለማድረስ 10,500 አትሌቶችን የሚያጓጉዙ 94 ጀልባዎችን ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

አትሌቶቹ የፓሪስ ታሪካዊ ቦታዎችን በጀልባ ሆነው የሚመለከቱ ሲሆን በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይፋዊው የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

በተጨማሪ በተለያዩ ጀልባዎች ላይ በመሆን በአይነቱ ከባድ ነው ብለው በራሳቸው አንደበት የተናገሩለትን ደማቅ ትዕይንት እንደሚቀርብ ተነግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ካናዳ ተጋጣሚዋን በመሰለል ቅሬታ ቀረበባት ! የካናዳ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት በኦሎምፒክ መክፈቻ ጨዋታ የሚገጥመውን የኒውዝላንድ አቻው በመሰለል ቅሬታ እንደቀረበበት ተገልጿል። የኒውዝላንድ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ሰኞ የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ ሲያደርገው የነበረውን ልምምድ በድሮን ሊሰልሉ ሞክረዋል በማለት ለፈረንሳይ ፖሊስ ማሳወቁ ተነግሯል። ድሮኑን ሲጠቀሙ የነበሩ ሰራተኞች…
ካናዳ የኦሎምፒክ ቡድኗን አሰልጣኝ አገደች !

የካናዳ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሀገሪቱን ሴቶች እግርኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ከኦሎምፒክ ቡድኑ ማገዱን አስታውቋል።

ካናዳ አሰልጣኟን ያገደችው ከቀናት በፊት የትላንት ተጋጣሚዋ ኒውዝላንድን ልምምድ በድሮን ለመሰለል በተደረገው ሙከራ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የካናዳ እግርኳስ የበላይ ቦርድ ሁኔታውን መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ እስኪደርስ ታግደው እንደሚቆዩ ይፋ ሆኗል።

ካናዳ ትላንት ኒውዝላንድን 2ለ1 ስታሸንፍ ቡድኑን የመሩት ምክትል አሰልጣኝ አንዲ ስፔንስ ቡድኑን በጊዜያዊነት እንደሚረከቡ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለትልቅ ዋንጫ ለመፋለም ዝግጁ ነኝ " ማጓየር

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በቀጣይ የውድድር አመት ለትልቅ ዋንጫዎች ለመፋለም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።

ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲነገር የቆየው ሀሪ ማጓየር በቀጣይ አመት የማንችስተር ዩናይትድ ቡድን አካል መሆኑን መስማቱንም ገልጿል።

" እዚህ ለትልቅ ዋንጫ ለመፋለም ዝግጁ ነኝ " የሚለው ሀሪ ማጓየር ስለ ወደፊት ቆይታው ሲናገርም " የሰማሁት እዚህ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ የወደፊት የቡድኑ አካል መሆኔን ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አቡበከር ናስር ወደ ሜዳ ተመልሶ ግብ አስቆጥሯል !

ለረጅም ጊዜ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር በአሁን ሰዓት ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ በወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፎ በመጫወት ላይ ይገኛል።

አቡበከር ናስር በቅርቡ ከጉዳቱ በማገገም ማሜሎዲ ሰንዳውንስ በግሉ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ እንዲጀምር ማድረጉ ይታወሳል።

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ በዚህ ሰዓት ከኩዌቱ ክለብ አል አረቢ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ ላይ ሲገኝ በጨዋታው አቡበከር ናስር ተሰልፎ በመጫወት ላይ ይገኛል።

አቡበከር ናስር በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃዎች በፍፁም ቅጣት ምት ግብ በማስቆጠር ማሜሎዲ ሰንዳውንስን መሪ አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዚኮ በፓሪስ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተገለጸ !

የቀድሞ ብራዚላዊ ተጨዋች ዚኮ ለ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ፓሪስ ባመራበት ወቅት በዘራፊዎች ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

የብራዚል ኦሎምፒክ ብሔራዊ ልዑክ አባል በመሆን ወደ ፓሪስ ያመራው ዚኮ ዘራፊዎች 500,000 ዩሮ የሚገመት ንብረት እንደዘረፉት ተነግሯል።

ዘራፊዎቹ የቀድሞ ተጫዋቹ ሲጓዝበት የነበረውን ታክሲ በማስቆም ጥሬ ገንዘብ እና አልማዝ የያዘ ቦርሳውን መውሰዳቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በ#1Wedefit ውድድራችን ብዙዎች እየተሳተፉ ነው!!! ከመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃ ችሎታ እየታየ ነው! እናንተስ?!ማነው እኔ ነኝ ያለ ዘፋኝ?! 🎶🎙ዛሬውኑ ፈጠን ፈጠን እያልን እንቀላቀል እንጂ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷
#1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ
@Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! ፖስት እናድርግ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!
እንዳያመልጣችሁ!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit #FurtherAheadTogethe
የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክስ ዛሬ ምሽት ይጀምራል!

🇪🇹አረንጓዴ ጎርፉም ፓሪስ ደርሷል🇪🇹

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱን ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው! የመክፈቻ ዝግጅቱን ቀድሞ በነበረው   በ Variety 4 ቻናል አሁን  Olympics Africa ቻናል ቁጥር 229 ላይ ከምሽቱ 1፡30 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአትሌቶቻችንን በጎጆ ፓኬጅ በ350 ብር ይከታተሉ! 

እናሸንፈለን ድሉን እናያለን💚🧡❤️

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#Paris2024 #LikeAChamp #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ኤቨርተን በይፋ ተጨዋች አስፈርሟል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ዴንማርካዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጄስፐር ሊንድስትሮምን ከናፖሊ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ኤቨርተን ተጫዋቹን በ22.5 ሚልዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት 2.5 ሚልዮን ዩሮ በመክፈል ማስፈረማቸው ተገልጿል።

" ኤቨርተንን በመወከሌ በጣም ደስተኛ ነኝ ፣ ኤቨርተን ትልቅ ታሪክ ያለው ትልቅ ክለብ ነው እዚህ በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ።"ሲል ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ባለፈው አመት ሊጉን አለማሳካታችን የሚያናድድ ነበር " ቶማስ ፓርቴ

ጋናዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ ቡድናቸው ባለፈው አመት ሊጉን አለማሸነፉ የሚያም መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ባለፈው አመት ሊጉን አለማሳካታችን የሚያም ነበር " ያለው ቶማስ ፓርቴ " በቀጣይ ያለፈውን አመት ስህተት ከመድገም መቆጠብ አለብን በማለት አሳስቧል።

ቶማስ ፓርቴ አያይዞም በቀጣይ የውድድር ዘመን ከጉዳት ነፃ ሆኜ ለመጫወት የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ ማን ይይዛል ?

የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚይዙ አትሌቶች መታወቃቸውን ልዩ ስፖርት በዘገባው አስነብቧል።

የ20 ኪሜ የርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50ሜ የነጻ ቀዘፋ የውሃ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ በመክፈቻው ሰንደቅ ዓላማችንን በመያዝ ልዑኩን የሚመሩ ይሆናል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ፕሮግራም ዛሬ ከምሽት ከ2:30 ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ይወዳደራል !

ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን ውድድር ለመወከል ተመርጦ የነበረው አትሌት ሲሳይ ለማ ከኦሎምፒክ ውጪ ሆኗል።

አትሌት ሲሳይ ለማ በውድድሩ የማይካፈለው በጡንቻ መሳሳብ ህመም ምክንያት በፈቃዱ ራሱን ከቡድኑ በማግለሉ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ አትሌት ሲሳይ ለማን በመተካት በተጠባባቂነት ተይዞ የነበረው አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ኢትዮጵያን ወክሎ እንደሚወዳደር ታውቋል።

በተጨማሪም አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት ዴሬሳ ገለታ በማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከቴንሀግ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን " ማጓየር

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሀሪ ማጓየር ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ የሚባል መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" የቴንሀግ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን በመካከላችን ትልቅ መከባበር አለ " የሚለው ሀሪ ማጓየር የአምበልነት ሚናው ከእኔ መወሰዱ የሚያናድድ ነው ነገርግን የእግርኳስ አንድ አካል ነው " በማለት ተናግሯል።

" በክለቡ ውስጥ ላለ ሁሉም ሰው አሁን አስደሳች ወቅት ነው ፣ ክለቡ በድጋሜ በትክክለኛው መንገድ በመጓዝ ላይ ነው ፣ ለክለቡ እንደሚያስብ እና እንደሚመለከተው ሰው ዬህንን ማየት ያስደስተኛል።" ማጓየር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ትልቁ የፈረንሳይ ባቡር መስመር መቋረጡ ተገለጸ !

የ2024 ኦሎምፒክ ውድድርን የምታዘጋጀው ፈረንሳይ ፓሪስ ትልቁ ፈጣን የባቡር መስመር በደረሰበት ጥቃት አግልግሎት መቋረጡ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የባቡር መስመሩን ከአገልግሎት ውጪ ለማድረግ ሶስት ቦታዎች ኬብሎችን የማበላሸት ጥቃት መፈፀሙን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

በዚህም ምክንያት በርካታ ተጓዦች የኦሎምፒክ ውድድርን ከምታዘጋጀው ፓሪስ ጋር የሚገናኙ ጉዞዎቻቸው ሊስተጓጎል እንደሚችል ተገልጿል።

የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን ደህንነት ለመጠበቅ የፈረንሳይ ወታደሮችን ጨምሮ 45,000 የፀጥታ አካላት እንደሚሰማሩ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከዚህ በፊት ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 19:20:11
Back to Top
HTML Embed Code: