Telegram Web Link
አትሌቶች የስልክ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል !

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ የሆኑ አትሌቶች የሳምሰንግ ስልክ በስጦታ መልክ እንደሚሰጣቸው ይፋ ሆኗል።

በፓሪስ ኦሎምፒክ እና ፓራኦሎምፒክ ተሳታፊ የሆኑ 17,000 አትሌቶች የሳምሰንግ አዲሱ “ Z Flip6 “ ሞዴል እንደሚያገኙ ታውቋል።

የሳምሰንግ ስልክ የማርኬቲንግ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ስቴቨን ቾይ “ አዲሱ ምርታችን በፓሪስ ኦሎምፒክ ለአትሌቶች በማቅረባችን ደስተኞች ነን “ ሲሉ ተናግረዋል።

ሳምሰንግ የአለምአቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አጋር በመሆን ከ 1988 የሲዮል ኦሎምፒክ ጀምሮ በመስራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ከጨዋታ ውጪ ነው !

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ምክንያት ኢንተር ሚያሚ ነገ ሌሊት ከፑኤብላ ጋር የሚያደርገው የሊግ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተገልጿል።

ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ሻምፒዮን በሆነችበት የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ውድድር በቀኝ እግሩ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በአሁን ሰዓት ከጉዳቱ በማገገም ላይ እንደሚገኝ የኢንተር ሚያሚ ዋና አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድርን በመምራት ላይ የሚገኘው ኢንተር ሚያሚ ነገ ሌሊት 9:00 ሰዓት ከፑኤብላ ጋር ይጫወታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን - የካፍ 'B' ላይሰንስ ስልጠና 🇪🇹

ዋናው ስፖርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር ያዘጋጁትና በትላንትናው ዕለት ፍፃሜውን ያገኘው የካፍ የB ዲፕሎማ የአንደኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና አጋር ስለነበር ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
በኦሎምፒክ ውድድር ሀገራት በስንት አትሌት ይወከላሉ ?

የ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ሲያደርግ ሶማሊያ ፣ ቤሊዝ ፣ ሌችተንስታይን እና ትንሿ ደሴት ናኡሩ በውድድሩ በአንድ አትሌት ብቻ እንደሚወከሉ ተገልጿል።

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር 10,500 አትሌቶች በ205 ልዑካን ቡድን ተከፋፍለው እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ።

በውድድሩ ላይ ብዙ ተሳታፊ አትሌቶች ያላት ሀገር አሜሪካ ስትሆን አጠቃላይ 592 አትሌቶች በመድረኩ ይወክሏታል ተብሏል።

አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ በበኩሏ በ571 አትሌቶች ስትወከል በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ከሚሳተፉ አትሌቶች ሀምሳ በመቶ የሚሆኑት ሴት አትሌቶች መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TeamEthiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት አምርቶ በስፍራው ይገኛል።

ብሔራዊ ልዑክ ቡድናችን በሀገር ባህላዊ አልባሳት ደምቆ የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ለመካፈል ወደ ስፍራው አቅንቷል።

የ20 ኪሜ የርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50ሜ የነጻ ቀዘፋ የውሀ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ ሰንደቅ ዓላማችንን በመያዝ ይመሩታል።

ብሔራዊ ልዑክ ቡድናችን የመክፈቻው ፕሮግራም ከጀመረ በኋላ ተራ ቁጥር 65ኛ ላይ ስንገኝ የሰንደቅ ዓለማችንን ይዘው የሚታዩ ይሆናል።

ቪድዮ ምንጭ ፦ ሲሳይ ዮሐንስ ( የፕሬስ አታሽ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ዝግጅት በደመቅ ሁኔታ መካሄዱን ሲቀጥል እውቋ አሜሪካዊት የሙዚቃ አቀንቃኝ ሌዲ ጋጋ ስራዋን አቅርባለች።

በጀልባዎች ላይ በመሆን በአይነቱ ልዩ የሆነ ትዕይንት በተለያዩ አርቲስቶች እየተካሄደ ይገኛል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የመክፈቻ ዝግጅቱ ለብዙሃን ተደራሽ ለማድረግ በፓሪስ ጎዳናዎች ከ80 በላይ ግዙፍ ስክሪኖች በቀጥታ እያሳየ ይገኛል።

በተጨማሪም በሁሉም የአለም ሀገራት የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን ሚልዮኖች እየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል።

የመክፈቻ ዝግጅቱን በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የቪድዮ ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

የ ኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ብሔራዊ ልዑክ ቡድኑ በጀልባ በመሆን የሀገራችን ኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላም እያውለበለበ በስነ ስርዓቱ ላይ ተሳትፏል።

በቪዲዮ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የቪድዮ ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በዘንድሮው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለአሸናፊዎች የሚሰጡ ሜዳልያዎች ከኤፍል ታወር በተወሰደ እውነተኛ የብረት ቁራጭ ያጌጡ መሆናቸው ተገልጿል።

በሜዳልያዎቹ መሐል ላይ እንደሚቀመጥ የተገለፀው የኤፍል ታወር ብረት ቁራጭ 18 ግራም እንደሚመዝን ተዘግቧል።

በዘንድሮው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ እና ፓራ ኦሎምፒክ ውድድር በድምሩ 5,084 ሜዳልያዎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በራሽፎርድ ሙሉ እምነት አለኝ " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በእንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ሙሉ እምነት እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" በማርከስ ራሽፎርድ እተማመናለሁ " የሚሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " እሱ ከሁለት አመት በፊት እንዳደረገው ከሰላሳ በላይ ግቦች ማስቆጠር እንደሚችል ሙሉ እምነት አለኝ " ብለዋል።

" ጥሩ ዝውውሮች አድርገናል ሁሉም ዝግጁ ሲሆኑ የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ የሚችል ቡድን ይኖረናል ፣ ቡድኔ የተቻላቸውን ያህል ጠንካራ እንዲሆን እፈልጋለሁ።" ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Anderlecht - St. Truiden
Dender - Royale Union SG
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
" ቡድኑ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉት " አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዛሬ ሌሊት የወዳጅነት ጨዋታውን ከሪያል ቤቲስ ጋር አድርጎ በዶምኒክ ስቦዝላይ ብቸኛ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታው ጥሩ ነገሮችን መመልከታቸውን ከድሉ በኋላ የገለፁት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት " ልናሻሽላቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውንም ከጨዋታው ተረድተናል " ብለዋል።

" ቡድናችን ኳስን ተቆጣጥሮ ነበር የተጫወተው " ያሉት አሰልጣኙ አሁን ላይ ያለ ተፈጥሯዊ አጥቂ ነው አየተጫወትን ያለነው በውድድሩ ግን በትክክለኛ አጥቂ እንጫወታለን ሲሉ ተናግረዋል።

ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በአሜሪካ የሚገኘው ሊቨርፑል ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን የፊታችን እሮብ ሌሊት 8:30 ሰዓት ከአርሰናል ጋር ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፔፕ ጋርዲዮላ ሲቲን ሊለቁ እንደሚችሉ ገለጹ ! ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው የውድድር አመት መጨረሻ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። " ማንችስተር ሲቲን ለመልቀቅ ተቃርቢያለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው አመት እዚሁ ለመቆየት አስቢያለሁ ከዛ በኋላ ለመልቀቅ የምቃረብ ይሆናል በማለት ተናግረዋል። በሚቀጥለው የውድድር አመት መጨረሻ ውላቸው የሚጠናቀቀው…
" ሲቲን ለመልቀቅ ተቃርቤያለሁ እንጂ እለቃለሁ አላልኩም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በክለቡ አዲስ ኮንትራት ሊፈርሙ እንደሚችሉ በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል።

" እኔ ሲቲን ለመልቀቅ ታቃረብኩ እንጂ እለቃለሁ አላልኩም " የሚሉት ፔፕ ጋርዲዮላ " በሲቲ ለስምንት አመት ቆይቻለሁ ተጨማሪ ስምንት አመት ስለማልቆይ ነው ለመልቀቅ ተቃርቤያለሁ ያልኩት " ብለዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም " ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ኮንትራት የማራዘም እድሌን ሙሉ ለሙሉ አልዘጋሁትም " ሲሉ አስረድተዋል።

ኤደርሰን በማንችስተር ሲቲ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ያረጋገጡት ፔፕ ጋርዲዮላ " ኤደርሰን ቁልፍ ተጨዋቻችን ነው እንደ እሱ አይነት ተጨዋች መተካት ከባድ ነው።"ብለዋል።

" ባለፉት ስድስት አመታት ሊጉን አምስት ጊዜ አሸንፈናል እንደ እውነቱ ከሆነ ሁሉም ሰው እኛን ለማስቆም ይጥራል በድጋሜ ለማሸነፍ በሙሉ ሀይላችን እንሰራለን " ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 17:14:23
Back to Top
HTML Embed Code: