Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

🇪🇹 ዋናው ስፖርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ልዩ የካፍ 'B' ላይሰንስ የአሰልጣኞች ስልጠና አጋር በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜናዎችን በቀላሉ በSMS እናግኝ! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!

በElite ስፖርት በሽ ዜናዎች⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" እዚህ እንድደርስ የረዱኝን ሁሉ አመሰግናለሁ " ቀነኒሳ በቀለ

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ " ESPN " አፍሪካ ሚዲያ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተብሎ መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሚዲያው ለሰጠው እውቅና ትልቅ ክብር እንዳለው በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ሲገለፅ " እንደዚህ አይነት ክብር ማግኘት ያስደስታል በአትሌቲክስ ህይወቴ የረዱኝኝን ሁሉ አመሰግናለሁ " ብሏል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በአትሌቲክስ ህይወቱ ሶስት የኦሎምፒክ ፣ አምስት የአለም ሻምፒዮና እንዲሁም አስራ አንድ የአለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳልያ እና ሌሎች ድሎች ባለቤት ነው።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለን በመከተል ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ካሜሮናዊው እግርኳስ ተጨዋች ሳሙኤል ኢቶ በምርጫው ከእግርኳስ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

ሚዲያው ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ምርጫውን ያደረገው እ.ኤ.አ. ከ 2000 ወዲህ የስፖርት ህይወታቸውን በጀመሩ ስፖርተኞች መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳንቾ ከወራት በኋላ ለዩናይትድ እየተጫወተ ነው !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ማንችስተር ዩናይትድ ከሬንጀርስ ጋር እያደረገ በሚገኘው የወዳጅነት ጨዋታ ከወራት በኋላ በክለቡ ማልያ ተሰልፎ በመጫወት ላይ ይገኛል።

ኤሪክ ቴንሀግ ስለ ሳንቾ በሰጡት አስተያየት " ሁሉም ጥፋት ያጠፋል " ሲሉ " ዩናይትድ ጥሩ ተጨዋች ያስፈልገዋል ሳንቾ ደግሞ ምርጥ ተጨዋች ነው ፣ መመለሱ ጥሩ ነገር ነው።"ብለዋል።

በትላንትናው ዕለት ክለቡን በይፋ የተቀላቀለው ሌኒ ዮሮ በበኩሉ የማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

" ሌኒ ዮሮን በማስፈረማችን በጣም ደስተኞች ነን እሱ ትልቅ አቅም ያለው ተጨዋች ነው።" ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ስለ አዲሱ ፈራሚያቸው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የወዳጅነት ጨዋታውን አሸነፈ !

ማንችስተር ዩናይትድ ከስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ ጋር ያደረገውን ሁለተኛ የቅድመ ውድድር ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለማንችስተር ዩናይትድ የማሸነፊያ ግቦችን አማድ ዲያሎ እና ጆ ሁጊል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በጨዋታው ጄደን ሳንቾ እና አዲሱ ፈራሚ ሌኒ ዮሮ ተሰልፈው መጫወት ችለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በአሜሪካ ከአርሰናል ጋር ሶስተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በአሜሪካ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሌኒ ዮሮ

የማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ሌኒ ዮሮ በዛሬው የወዳጅነት ጨዋታ ባሳየው እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ዛሬ ባደረግኩት እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ በዚህ እንደምቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ " ያለው ሌኒ ዮሮ " የቡድኑ ስሜት ደስ ይላል እሮብ አሜሪካ ሄደን ሶስት ጨዋታዎች እናደርጋለን ፣ ሁሉንም ለማሸነፍ የቻልነውን እናደርጋለን " ብሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሜሪካ ቆይታው ከአርሰናል፣ ሪያል ቤቲስ እና ሊቨርፑል ጋር በተከታታይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ የሜሲን የዋንጫ ድል ያከብራል !

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኢንተር ሚያሚ ዛሬ ሌሊት ከቺካጎ ጋር በሚያደርጉት የሊግ ጨዋታ የሊዮኔል ሜሲን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ድል እንደሚያከብሩ አስታውቋል።

የምሽቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ ኢንተር ሚያሚ የሊዮኔል ሜሲን አርባ አምስተኛ ዋንጫውን እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።

ዛሬ ሌሊት 8:30 ሰዓት በሚደረገው ጨዋታ አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ምክንያት ይሳተፋል ተብሎ አይጠበቅም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Viborg - Brondby
El Daklyeh - Zamalekለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•Macbook PRO 512GB/18GB
M3 Pro Chip 275,000 Birr

•Macbook PRO 512/8GB
M3 Chip 185,000 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
" ዴምቤሌ የሚጫወተው ለራሱ ብቻ ነበር " ሳምፖውሊ

የቀድሞ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጌ ሳምፓውሊ በአውሮፓ ዋንጫው የፈረንሳይ ድክመት አንዱ የዴምቤሌ ለግሉ ብቻ መጫወት እንደነበር ገልጸዋል።

" ዴምቤሌ ለራሱ ብቻ ነው የሚጫወተው " ያሉት ሳምፓውሊ የቡድን አጋሮቹን እንዴት ማገዝ እንዳለበት አያውቅም ነበር ለራሱ መጫወት ነው የሚያውቀው ምባፔም ትንሽ እንደዛ ነበር በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ተጨዋቹ ማርሴይን ሊቀላቀል ነው !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው ማርሴይ ዴንማርካዊውን አማካይ ፔር ኤሚል ሆይቤርን ከቶተንሀም ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ቶተንሀም ከዝውውሩ 13 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ከማርሴይ እንደሚያገኙ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በሀላፊነት የሾመው ማርሴይ በተጨማሪም የአርሰናሉን የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲ ኒኪታህ ለማስፈረም ይፋዊ ጥያቄ አቅርበዋል።

ማርሴይ ከቀናት በፊት እንግሊዛዊውን ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዩናይትድን ወደነበረበት መመለስ እንፈልጋለን " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድኑን ከአስር አመታት በፊት ወደነበረበት ደረጃ መመለስ እንደሚፈልጉ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" ይህንን ክለብ ከአስር አመታት በፊት የነበረበት ደረጃ መመለስ እንፈልጋለን " ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለቡን ፕርሚየር ሊጉን የሚያሸንፍ እና ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ የሚችል ማድረግ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ርቀት መጓዝ እንዳለብን እናውቃለን ነገርግን ቡድኑን ማሻሻል አለብን በማለት አሰልጣኙ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አል ናስር ለኤደርሰን የዝውውር ጥያቄ አቀረበ ! የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ለማንችስተር ሲቲ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። አል ናስር ለዝውውሩ 30 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሲያቀርቡ ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል። ማንችስተር ሲቲ ኤደርሰንን ከለቀቀው ከ 50 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚፈልግ የተገለፀ…
የኤደርሰን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ የማንችስተር ሲቲውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገልጿል።

ሌላኛው የሳውዲ ክለብ አል ናስር በቅርቡ ለማንችስተር ሲቲ ያቀረበው 30 ሚልዮን ዩሮ ውድቅ ሲደረግበት ሀሳባቸውን በመቀየር የአትሌቲኮ ፓራኔንሱን ግብ ጠባቂ ቤንቶ በ18 ሚልዮን ዩሮ አስፈርመዋል።

ማንችስተር ሲቲ አሁንም ግብ ጠባቂውን ለመልቀቅ እስከ 60 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ እንደሚፈልጉ ማሳወቃቸው ተገልጿል።

ኤደርሰን ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማምራት ዝግጁ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አል ኢትሀድ ዝውውሩ ከባድ ቢሆንም ለመሞከር መወሰናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ ! ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም ከአያክስ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአርሰናል ቤት የአራት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። መድፈኞቹ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ…
አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ከአያክስ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

መድፈኞቹ የ 18ዓመቱን ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ በማድረግ በአራት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አርሰናል ለግብ ጠባቂው ቶሚ ሴትፎርድ ዝውውር አንድ ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 19:25:11
Back to Top
HTML Embed Code: