Telegram Web Link
“ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ያሳለፍኩት ከባዱ አመት ነበር “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ያለፈው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ያሳለፉት ከባዱ አመት እንደነበር ተናግረዋል።

“ ይህ ቀላል ስራ አይደለም በጣም ከባድ ሀላፊነት ነው " ያሉት ኤሪክ ቴን ሀግ “ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ያሳለፍኩት በጣም ከባዱ የውድድር ዘመን ነበር “ ሲሉ ገልጸውታል።

" አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከዘጠኝ አመታት ቆይታ በኃላ አቅሜን ጨርሳለሁ ብለው ሊቨርፑልን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አከብረዋለሁ " ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የኤፌ ካፕ ዋንጫን ሲያሳኩ በሊጉ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስሚዝ ሮው በቀጣይ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው በፕርሚየር ሊግ ክለቦች ክሪስታል ፓላስ እና ፉልሀም እየተፈለገ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ፉልሀም በቅርቡ ያቀረቡት የዝውውር ጥያቄ በአርሰናል ተቀባይነት አለማግኘቱ ይታወሳል።

አሁን ላይ ክሪስታል ፓላስ ኤሚል ስሚዝ ሮውን ለማስፈረም ለአርሰናል የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ተዘግቧል።

የአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታው ቡድን አርሰናል በቀጣይ ቡድኑን ለማጠናከር ጥሩ ጥያቄ ከቀረበ ለመሸጥ ካሰባቸው ተጨዋቾች መካከል ኤሚል ስሚዝ ሮው አንዱ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሴስክ ፋብሪጋስ ውሉን ሊያራዝም ነው ! የጣልያኑን ክለብ ኮሞ በሀላፊነት እየመራ የሚገኘው ስፔናዊው አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስ በክለቡ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም መቃረቡ ተገልጿል። ሴስክ ፋብሪጋስ ቡድኑን እየመራ በዚህ አመት ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጣልያን ሴርያ ውድድር ማሳደጉ አይዘነጋም። የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ ተጨዋች ሴስክ ፋብሪጋስ በተጨማሪም በክለቡ የአክስዮን…
ሴስክ ፋብሪጋስ በዋና አሰልጣኝነት ተሾሟል !

የጣልያኑን ክለብ ኮሞ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እየመራ ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ወደ ሴርያው ማሳደግ የቻለው ሴስክ ፋብሪጋስ አሁን ላይ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሟል።

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስ ኮሞን ለሚቀጥሉት አራት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ በይፋ ተገልጿል።

የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ ተጨዋች ሴስክ ፋብሪጋስ ከፊርማው በኋላ " አመቱን በዋና አሰልጣኝነት መጀመሬ አስደስቶኛል የክለቡ ባለድርሾች ስላመኑኝ አመሰግናለሁ " በማለት ተናግሯል።

ሴስክ ፋብሪጋስ እንዲሁም የቀድሞ ፈረንሳዊ ኮከብ ቴሪ ሄንሪ በኮሞ እግርኳስ ክለብ የአነስተኛ አክስዮን ድርሻ ባለቤት ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🤯 400,000 ብር?? በዛ ላይ ደግሞ አስቡት የእናንተ ሙዚቃ በመላው ኢትዮጵያ ሲደመጥ...እናንተ ችሎታው ይኑራችሁ የቀረውን በእኛ ጣሉት! አሁኑኑ የአንድ ደቂቃ ቪዲዮአችንን እንላክ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷
#1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ
@Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ዩኤፋ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አደረገ !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ከቀናት በፊት በማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ሮድሪ እየተመሩ ያሰሙትን ዝማሬ እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኤፋ ምርመራውን የከፈተው ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማድሪድ ውስጥ በምታክብርበት ወቅት ተጨዋቾቹ " ጂብላርታር ስፔን ነው " እያሉ እንግሊዞች ላይ ቀልደዋል በሚል መሆኑ ተነግሯል።

በሰዓቱ ሮድሪ በድምፅ ማጉያ ዝማሬውን ሲያሰማ ሞራታ በበኩሉ " የእንግሊዝ ቡድን አጋሮች አሉህ " ብሎ ሲጠይቀው የሚደመጥ ሲሆን ሮድሪ " ግድ የለኝም " ሲል ተደምጧል።

የጂብላርታር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቀናት በፊት በጉዳዩ ላይ ቅሬታውን ለአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አስገብቶ ነበር።

ዩኤፋ በተለይም ዝማሬውን ያሰማውን ሮድሪ እንዲሁም የቡድኑ አምበል ሞራታን በመመርመር ላይ መሆኑን አስታውቋል።

በስፔን ደቡባዊ ጫፍ የምትገኘው ጂብላርታር ከ18ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር የነበረች ሲሆን ስፔኖች እንድትመለስ እንደሚፈልጉ ይነገራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በኒውካስል መቆየት እፈልጋለሁ " ኤዲ ሀው

ስማቸው ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የኒውካስል ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲ ሀው በክለቡ መቆየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

" በኒውካስል ዩናይትድ መቆየት እፈልጋለሁ " የሚሉት አሰልጣኝ ኤዲ ሀው " ነገርግን ለመቆየት ነገሮች ለእኔም ለክለቡም ትክክለኛ መሆን አለባቸው " ብለዋል።

ስማቸው ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስለመያያዙ የተጠየቁት አሰልጣኝ ኤዲ ሀው " እኔ ክለቡን እና ደጋፊውን እንዲሁም አሁን ያለንበትን ነገር እወደዋለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ኒውካስል ዩናይትድን ከተረከቡ በኃላ ባለፈው የውድድር አመት ክለቡን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አንድ ሙከራ ብቻ ነበር የተሞከረብን " አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዛሬ በልምምድ ማዕከሉ ከፕሬስተን ጋር በዝግ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ የነበረ ሲሆን ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አዲሱ የሊቨርፑል አሰልጣኝ አርኔ ስሎት " ውጤቱ የፈለግነው አልነበረም ነገርግን ሁሉም ተጨዋቾች ብቁ ሆነው ቆይተዋል።

ወጣት ተጨዋቾችን ጨምሮ አብዛኞቹ ተጨዋቾች የመጫወቻ ጊዜ አግኝተዋል ይህ በጣም ጥሩ ነው ፣ አንድ የግብ ሙከራ ብቻ አስተናግደናል እሱም ግብ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

በወዳጅነት ጨዋታው ሀያ ስድስት የሊቨርፑል ተጨዋቾች ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጊኒ በወዳጅነት ጨዋታ አርጀንቲናን አሸንፋለች !

የጊኒ ከ 23ዓመት በታች ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ከአርጀንቲና አቻው ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በአሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ የሚመራው የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ኒኮላስ ኦታሜንዲ ፣ ቲያጎ አልማዳ እና ሩሊን በቋሚነት አሰልፏል።

ጊኒ በፓሪሱ ኦሎምፒክ ውድድር ከፈረንሳይ ፣ ኒውዝላንድ እና አሜሪካ ጋር ስትደለደል አርጀንቲና ከሞሮኮ ፣ ኢራቅ እና ዩክሬን ጋር ተደልድላለች።

አፍሪካ በዘንድሮው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በወንዶች በጊኒ ፣ ሞሮኮ ፣ ግብፅ እና ማሊ ብሔራዊ ቡድኖች ትወከላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ተስፈኛው የአርሰናል ታዳጊ ወደ ዩናይትድ ? የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለማምራት ካሪንግተን ተገኝቶ መነጋገሩ ተገልጿል። በሚያስቆጥራቸው በርካታ ግቦች መነጋገሪያ የነበረው ኦቢ ማርቲን ከአርሰናል የቀረበለትን ውል እስካሁን አለመቀበሉ ተነግሯል። ታዳጊው በመድፈኞቹ እንዲቆይ በቅርቡ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አግኝተው አነጋግረውት…
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም እያነጋገረ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ የአርሰናሉን ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቺዶ ኦቢ ማርቲን አርሰናል በክለቡ እንዲቆይ ያቀረበለትን ጥያቄ አለመቀበሉ እና ክለቡን ለመልቀቅ መወሰኑ ታውቋል።

ተጨዋቹ በዚህ ሳምንት ካሪንግተን ተገኝቶ እንደነበር መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን ቀያዮቹ ሴጣኖች በአሁን ሰዓት ተጫዋቹን ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲ ወጣቱን የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እጥፍ ድርብ አሸናፊነት!

በቤቲካ ያሸነፉትን ገንዘብ በACCA እስከ 300% ከፍ ያድርጉ!

አሁኑኑ Betika.et ላይ አሸናፊነትን ይጀምሩ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
አል ኢትሀድ ለተጫዋቹ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ዌስትሀም ዩናይትድ ንጎሎ ካንቴን ለማስፈረም ያቀረቡትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለንጎሎ ካንቴ ዝውውር 15 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ቢያቀርቡም በአል ኢትሀድ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ተነግሯል።

አል ኢትሀድ የ33 አመቱን ንጎሎ ካንቴ የመሸጥ ፍላጎት #የሌላቸው ሲሆን ዌስትሀም ዩናይትድ አሁንም ከስምምነት ላይ ለመድረስ በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ንጎሎ ካንቴን ለማስፈረም 25  ሚሊየን ፓውንድ እና ከዛ በላይ የዝውውር ሒሳብ እንደሚያስፈልጋቸውም ተጠቁሟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ግሪንውድን ስለሰጡን ዩናይትድን እናመሰግናለን “ ዲ ዘርቢ

ጣልያናዊው የማርሴይ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ አዲሱን ፈራሚያቸው ሜሰን ግሪንውድ ታላቅ ተጨዋች ማድረግ እንደሚፈልጉ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“ ስለ ግሪንውድ የሚሰማው ሁሉም ነገር ስላለፈው ነገር ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ እሱን ታላቅ ተጨዋች ማድረግ እና ቡድኑን በእሱ ላይ መገንባት እንፈልጋለን ብለዋል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ቀጥለውም ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ስለሸጠላቸው ማመስገን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆኢል ማቲፕ ወደ ባየር ሌቨርኩሰን ?

የወቅቱ የጀርመን ቡንደስሊጋ አሸናፊ ባየር ሌቨርኩሰን ካሜሮናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆኢል ማቲፕ ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ጆኢል ማቲፕ ከሊቨርፑል ጋር ከስምንት የውድድር አመታት ቆይታ በኋላ በውድድር አመቱ መጨረሻ መለያየቱ አይዘነጋም።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሌቨርኩሰን የ 32ዓመቱን ተከላካይ ጆኢል ማቲፕ በነፃ ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። መድፈኞቹ ለተጨዋቹ ባቀረቡት እስከ 2029 የሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። አርሰናል በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከቦሎኛ ጋር ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ…
አርሰናል ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረቡ ተገለጸ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ከዚህ በፊት ተጨዋቹን እስከ 2029 በሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም በግል መስማማታቸው ይታወቃል።

አርሰናል ክለቡ ጋር ጥሩ ንግግር ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቀጣይ ተጫዋቹን የማስፈረም ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዴሊትን የማስፈረም ሀሳብ ከእኔ አልመጣም “ ኤሪክ ቴን ሀግ

የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስሙ ከክለቡ ጋር በስፋት እየተያያዘ ስለሚገኘው የባየር ሙኒክ ተከላካይ ማትያስ ዴሊት አስታያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ከሁለት አመት በፊት ማትያስ ዴሊትን ለማስፈረም እፈልግ ነበር ነገርግን እሱ ባየር ሙኒክን ተቀላቅሏል " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ አሁን ግን እሱን የማስፈረም ሀሳቡ ከእኔ የመጣ አይደለም ሲሉ አረጋግጠዋል።

" ማትያስ ዴሊትን በደንብ እንደማውቀው አልክድም ነገርግን ወደዚህ ይመጣ እንደሆነ በቀጣይ የሚታይ ጉዳይ ነው " ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ማትያስ ዴሊትን ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር መስማማት ቢችሉም ከባየር ሙኒክ ጋር በዝውውር ሒሳብ ዙሪያ እስከ አሁን ከስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻለ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄደን ሳንቾ በዩናይትድ ስብስብ ውስጥ ተካቷል !

በዛሬው ዕለት ከሬንጀርስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርገው ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን ተጨዋች ጄደን ሳንቾ በስብስቡ ውስጥ ማከተቱን ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም አዲሱ ፈራሚ ሌኒ ዮሮ በማንችስተር ዩናይትድ የቡድን ስብስብ ተካቶ ወደ ስኮትላንድ ማምራቱ ይፋ ሆኗል።

ሁለቱም ተጨዋቾች ምሽት 12:00 ሰዓት ከሬንጀርስ ጋር በሚደረገው ሁለተኛ የቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፈው ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር አለመግባባት ውስጥ የነበረው ጄደን ሳንቾ ለመጨረሻ ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ተሰልፎ የተጫወተው ከአመት በፊት እንደነበር ይታወሳል።

በዛሬው የማንችስተር ዩናይትድ ስብስብ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ ሀሪ ማጓየር ፣ አንቶኒ እና ሊንድሎፍ አለመካተታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረቡ ተገለጸ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ከዚህ በፊት ተጨዋቹን እስከ 2029 በሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም በግል መስማማታቸው ይታወቃል። አርሰናል ክለቡ ጋር ጥሩ ንግግር ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቀጣይ…
#Update

አርሰናሎች ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ማስፈረም ከጣልያኑ ክለብ ቦሎኛ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር መስማማታቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ከእረፍት በተመለሰ በኋላ ለክለቡ ቦሎኛ ሀላፊዎች አርሰናልን በመቀላቀል ህልሙን እንዲያሳካ እንዲለቁት ጥያቄ ማቅረቡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጃሬድ ብራንዝዌት ኤቨርተንን ላይለቅ ይችላል ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አስቶን ቪላ ማምራት በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር ሊያስቀረው እንደሚችል ተገልጿል። አማዱ ኦናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ለአስቶን ቪላ ለመሸጥ የተቃረበው ኤቨርተን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ካልቀረበላቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት ላይሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል። …
ኤቨርተን ተጫዋቹን እንደማይሸጥ አሳወቀ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ተከላካያቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ለማንችስተር ዩናይትድ ማሳወቁ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚፈልጉት የተጠየቀው የዝውውር ሒሳብ የሚቀንስ ከሆነ ብቻ መሆኑ ተዘግቧል።

ኤቨርተን በበኩሉ ተጫዋቹን ለመሸጥ ሊያስብ የሚችለው የጠየቀው 70 ሚልዮን ፓውንድ ከቀረበለት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል የወዳጅነት ጨዋታውን አሸንፏል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዛሬ በልምምድ ማዕከሉ ከሊግ አንዱ ክለብ ሌይተን ኦሪየንት ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ተገልጿል።

ለመድፈኞቹ ግቦቹን ጋብሬል ጄሱስ እና ስሚዝ ሮው ማስቆጠራቸው ተገልጿል።

አርሰናል ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ በአሜሪካ ከበርንማውዝ ጋር የቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 21:23:46
Back to Top
HTML Embed Code: