Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ፓትሪክ ቬራ በሀላፊነት ሊሾም ነው ! ፈረንሳዊው የቀድሞ የክሪስታል ፓላስ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ የጣልያኑን ክለብ ጂኖኣ በሀላፊነት ሊረከብ መሆኑ ተገልጿል። የ 47ዓመቱ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ከጂኖኣ ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሱ ሲገለፅ በዚህ ሳምንት በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ተነግሯል። ጂኖኣ ከጣልያናዊው አሰልጣኝ አልቤርቶ ጊላርዲኖ ጋር ለመለያየት መወሰኑ ተገልጿል። አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ…
እርስ በርስ የማይጣጣሙት ፓትሪክ ቬራ እና ባሎቴሊ !

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ የጣልያኑን ክለብ ጂኖኣ በሀላፊነት ለመምራት ከስምምነት መድረሱ መዘገቡ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ከጣልያናዊው የፊት መስመር አጥቂ ማርዮ ባሎቴሊ ጋር ለሶስተኛ ጊዜ አብረው የመስራት እድል ይኖራቸዋል።

ፓትሪክ ቬራ ከዚህ በፊት በማንችስተር ሲቲ ተጨዋችነት እና ኒስ አሰልጣኝነት ጊዜያት ከማርዮ ባሎቴሊ ጋር መስራት ችለው ነበር።

ማርዮ ባሎቴሊ ከዚህ በፊት የፓትሪክ ቬራ አጨዋወት እሱ ሜዳ ላይ ምርጥ አቋሙን እንዳያሳይ እንዳገደው ሲገልፅ ነበር።

ባሎቴሊ ከዚህ በፊት በባደረገው ንግግሩም “  ከእሱ ጋር በግል ችግር የለብኝም በስፖርታዊ ነገር ከእሱ ጋር አልስማማም ይህ ባይሆን ኒስን አለቅም ነበር “ ብሏል።

ፓትሪክ ቬራ በበኩሉ " ባሎቴሊ ለቡድን ስፖርት አልተፈጠረም ከእሱ ጋር መስራት ለእኔ ከባድ ነው “  በማለት ተናግሮ ነበር።

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
ዱሳን ቭላሆቪች ለሚላን ጨዋታ ይደርሳል ?

ሰርቢያዊው የጁቬንቱስ የፊት መስመር ተጨዋች ዱሳን ቭላሆቪች ሀገሩ ሰርቢያ  ከዴንማርክ ጋር በነበራት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ነበር።

ተጨዋቹ በተደረገለት የህክምና ምርመራ ከባድ ጉዳት እንዳላጋመው መታወቁን ክለቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አረጋግጧል።

ይሁን እንጂ ዱሳን ቭላሆቪች ባለበት መጠነኛ ጉዳት ጁቬንቱስ የፊታችን ቅዳሜ ከኤሲ ሚላን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የመድረስ እድሉ የጠበበ መሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
ቪኒሰስ ጁኒየር ዶክመንተሪ ሊሰራለት ነው  !

የአሜሪካው ግዙፍ የሚዲያ ተቋም ኔትፍሊክስ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር  የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም መስራቱን አስታውቋል።

ዘጋቢ ፊልሙ የሎስ ብላንኮዎቹን የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የህይወት ውጣ ውረድ እና የእግርኳስ ህይወት እንደሚዳስስ ተገልጿል።

የ 24ዓመቱ ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ዘጋቢ ፊልም በ 2025 ለህዝብ ለእይታ እንደሚቀርብ ተነግሯል።

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
ታንዛኒያ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋገጠች !

በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ታንዛኒያ ለ 2025 ሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፏን አረጋግጣለች።

ታንዛኒያ ከጊኒ ጋር ያደረገችውን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ለአፍሪካ ዋንጫው አልፋለች።

ከኢትዮጵያ ጋር የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ምሽት የምታደርገው ዲሞክራቲክ ኮንጎ የምድቡ መሪ ሆና ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን ማረጋገጧ ይታወሳል።

ከምድቡ ጊኒ እና ኢትዮጵያ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

የጊኒ ብሔራዊ ቡድን ከ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማይሳተፍ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ምሽት 1:00 ያደርጋል።

ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዩጋንዳ ፣ ታንዛኒያ እና ሱዳን ለ 2025 ሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው።

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ !

1:00 ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከ ኢትዮጵያ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
“ ኔይማር አምስት ባሎን ዶር ይገባዋል “ ቡፎን

ጣልያናዊው ታሪካዊ ግብ ጠባቂ ቡፎን በእግርኳስ ህይወቱ አብሯቸው ከተጫወታቸው ተጨዋቾች ሁሉ ምርጡ ኔይማር መሆኑን ገልጿል።

“ ኔይማር ሜዳ ላይ ካየኋቸው ሁሉ ምርጡ ተጨዋች ነው “ የሚለው ቡፎን እሱ በእግርኳስ ህይወቱ አምስት ባሎን ዶር ይገባዋል ብሏል።

" ሜዳ ላይ ከዚዳን ሊዮኔል ሜሲ ፣ ሮናልዶ እና ኢኔስታ እንዲሁም በርካቶች ጋር ተጫውቻለሁ ነገርግን ኔይማር ምርጡ ነው።" ቡፎን

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
5 ' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-0 ኢትዮጵያ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
15 ' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-0 ኢትዮጵያ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
32 ' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-0 ኢትዮጵያ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
37 ' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-1 ኢትዮጵያ

በረከት ደስታ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከኮንጎ ጋር እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1ለ0 እየመራ እረፍት ወጥቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የመሪነት ግብ በረከት ደስታ ከመረብ አሳርፏል።

⚽️ የመጀመርያው አጋማሽ የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመርያው አጋማሽ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች 50%-50% የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
63' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-1 ኢትዮጵያ

               በረከት ደስታ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
80' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 0-1 ኢትዮጵያ

               በረከት ደስታ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
90+2' ዲሞክራቲክ ኮንጎ 1-1 ኢትዮጵያ

               በረከት ደስታ

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
90+4 ‘ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 1-2 ኢትዮጵያ

               በረከት ደስታ
መሐመድ ኑር ናስር

@Tikvahethsport         @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ድል አድርገዋል !

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች በረከት ደስታ እና መሐመድ ናስር ከመረብ አሳርፈዋል።

ዋልያዎቹ በማጣሪያው አራት ጨዋታዎች ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተው በአንዱ ማሸነፍ ችለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአራት ነጥቦች የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።

ከምድቡ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ታንዛኒያ ለአፍሪካ ዋንጫው ሲያልፉ ኢትዮጵያ እና ጊኒ ለውድድሩ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሮድሪ የባሎን ዶር ሽልማቱን ያስመለክታል !

የዘንድሮው የባሎን ዶር አሸናፊ ሮድሪ የፊታችን ቅዳሜ ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም በሚያደርጉት ጨዋታ ሽልማቱን በኢትሀድ ስታዲየም እንደሚያስመለክት ተገልጿል።‌‌

ተጨዋቹ ሽልማቱን ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ በስታዲየሙ እንደሚያሳይ እና ከደጋፊዎች ጋር ደስታውን እንደሚጋራ ተዘግቧል።

ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ ባሎን ዶር ያሸነፈ የመጀመሪያው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች መሆኑ ይታወቃል።

ሮድሪ በቅርቡ ባጋጠመው የ " ACL " ጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ ይገኛል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ከልጅነቴ ጀምሮ በስቃይ ነው የኖርኩት “ ቪንሰስ ጁኒየር

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ከልጅነቱ ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መኖሩን ተናግሯል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ማህበራዊ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረገው ቪንሰስ ጁኒየር በቆይታው የተለያዩ ጉዳዮችንም አንስቷል።

“ ከተወለድኩ ጀምሮ በጭንቀት እና ጫና ውስጥ ነው የኖርኩት “ የሚለው ቪንሰስ ጁኒየር አስቸጋሪ ከሆነ ቦታ ስለመጣሁ ብዙ ስቃይ ደርሶብኛል በማለት ተናግሯል።

ስፔን ውስጥ ስለደረሰበት የዘረኝነት ጥቃት ያነሳው ቪንሰስ “ ስፔን ውስጥ በጣም ብዙ ጉዳት ደርሶብኛል “ ያለ ሲሆን ችግሩ አሁንም በተወሰነ መልኩ መቀጠሉን አስታውሷል።

“ አሁን ስፔን ውስጥ ዘረኝነትን በሚፀየፉ ሰዎች እና ክለቦች ትልቅ እርዳታ ሁኔታው ተሻሽሏል። “ ቪንሰስ ጁኒየር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አሊሰን ቤከር ልምምድ ሰርቷል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ካጋጠመው ጉዳት በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ዛሬ ከክለቡ ከ 21ዓመት በታች ቡድን ጋር በመሆን ልምምድ መስራቱ ተነግሯል።

አሊሰን ቤከር አጋጥሞት በነበረው ጉዳት ምክንያት ለአንድ ወር ያክል ከሜዳ ርቆ መቆየቱ ይታወቃል።

በተጨማሪም የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሀርቬይ ኤሊዮት በዛሬው ልምምድ ላይ መሳተፉ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ ከአሰልጣኙ ጋር ሊለያይ ነው !

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኢንተር ሚያሚ ከአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ ጋር ሊለያይ መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ በግል ጉዳይ ምክንያት ኢንተር ሚያሚን ለመልቀቅ ማሰባቸውን ጊቭሚ ስፖርት አስነብቧል።

አሰልጣኙ ባለፈው አመት ኢንተር ሚያሚን ተረክበው የሊግ ካፕ እና የሰፖርተርስ ሺልድ ዋንጫን አሳክተዋል።

ኢንተር ሚያሚ በቅርቡ በአታላንታ ዩናይትድ ተሸንፎ ከሜጀር ሊግ ሶከር ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ተሰናብተዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/11/20 00:16:56
Back to Top
HTML Embed Code: