Telegram Web Link
የቱርክ ደጋፊዎች የኦስትሪያን ተጨዋቾች ለመረበሽ ሞክረዋል !

የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ቱርክ ከኦስትሪያ ጋር ምሽት 4:00 በሌፕዚግ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ከጨዋታው አስቀድሞ ዛሬ ሌሊት የቱርክ ደጋፊዎች የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወዳረፉበት ሆቴል በማምራት ርችት እና ተቀጣጣይ ነገሮችን በማጮህ ለመረበሽ መሞከራቸው ተገልጿል።

በአውሮፓ ዋንጫው በደጋፊዎቻቸው ከደመቁ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አንዷ የሆነችው ቱርክ ሁለተኛዋ የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር የሚል ስም አግኝታለች።

ውድድሩ በሚዘጋጅበት ጀርመን ሀገር ከ #ሶስት ሚልዮን በላይ የቱርክ የዘር ሀረግ ያላቸው ነዋሪዎች መኖራቸው ይነገራል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከያዛቸው ሀያ ስድስት ተጨዋቾች መካከልም ሀካን ካልሀኖግሉ እና ከናን ይልዲዝን ጨምሮ አምስት ተጨዋቾቻቸው የተወለዱት ጀርመን ውስጥ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ ወጣት ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

ማንችስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን ወጣት የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሪሰን ማይልስ ከሳውዝሀምፕተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

የ 15ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሪሰን ማይልስ አርሰናልን ጨምሮ በታላላቅ የሊጉ ክለቦች የሚፈለግ ቢሆንም ማንችስተር ሲቲዎች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል።

የእንግሊዝ ከ 16ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነው ሀሪሰን ማይልስ በሳውዝሀምፕተን ያለው ኮንትራት መጠናቀቁ ተገልጿል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ ከቶተንሀም ጋር የተለያየውን የ19ዓመት አማካይ ዊልሆፍት ኪንግ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopianPL 🇪🇹

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ2017 ዓ.ም የውድድር አመት የዝውውር መስኮት የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

የዝውውር መስኮቱ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ተከፍቶ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም እንደሚዘጋ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

አሸናፊውን እስከ መጨረሻ መርሐ ግብር ያላሳወቀው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመት የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ከሌስተር ሲቲ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን በ30 ሚልዮን ፓውንድ በስድስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ተደርጓል። ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቀ በይፋ በቀድሞ አሰልጣኙ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራውን…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ከሌስተር ሲቲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን 30 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ በማድረግ ለተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ባለው በስድስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ " የቼልሲ ተጨዋች መሆን የሚደንቅ ነው ሁሉም ሰው ለመጫወት እየተመኘ የሚያድገው ክለብ ነው በጣም ተደስቻለሁ ለሁሉም ሰው ማድረግ የምችለውን ለማሳየት ጓጉቻለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ቀያይ ሴጣኖች የግብ ጠባቂያቸው ቶም ሂተንን ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

እንግሊዛዊው የ 38 ዓመት ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ተገልጿል።

" በልጅነት ክለቤ ውስጥ በመቆየቴ ደስተኛ ነኝ በጥሩ አቋም እንዳለሁ ይሰማኛል በሚቀጥለው አመት ቡድኑ የሚያስፈልገውን ነገር ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።"ሲል ቶም ሂተን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ዴሊትን ለማስፈረም ንግግር ጀመረ ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ይፋዊ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ የ 24ዓመቱን ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም በአያክስ ቤት እያለ ጀምሮ ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል። ማትያስ ዴሊት አሁን ላይ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2027 የሚደርስ ኮንትራት…
ዴሊት ዩናይትድን መቀላቀል እንደሚመርጥ አሳወቀ !

ኔዘርላንዳዊው የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ፍቃደኛ መሆኑን ማሳወቁ ተዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከባየር ሙኒክ ጋር በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 24ዓመቱን ተጨዋች ማትያስ ዴሊት 50 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ ገንዘብ ለማስፈረም ተስፋ አድርገው ድርድር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ኔዘርላንድ ከ ሮማንያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማን ወደ ሩብ ፍፃሜ ያቀናል?

የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች መርሃ ግብር:

⚽️ Romania vs Netherlands ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት | 7፡00 PM
⚽️ Austria vs Turkey ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

🤔 ማን ይሆን ሩብ ፍፃሜ ላይ የሚደርሰው? መልሶቻችሁን ከስር አጋሩን!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#EURO2024

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በኦስትሪያ ከተሸነፈበት በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጎ ሮማንያን የሚገጥሙ ይሆናል።

የፒኤስጂው አማካይ ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመለስ አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በፊት መስመር እና ተከላካይም ለውጥ አድርገዋል።

የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ከሴሎቫኪያ ጋር አቻ ከተለያየበት የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የሁለት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጓል።

በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የአሸናፊነት ግምቱን አግኝቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 '

ኔዘርላንድ 1-0 ሮማንያ

ጋክፖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ኔዘርላንድ 1-0 ሮማንያ

ጋክፖ

- የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ በአውሮፓ ዋንጫው ሶስተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
65 '

ኔዘርላንድ 1-0 ሮማንያ

ጋክፖ

- ኮዲ ጋክፖ ለኔዘርላንድ ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮ የነበረ ቢሆንም ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84 '

ኔዘርላንድ 2-0 ሮማንያ

ጋክፖ
ማለን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኔዘርላንድ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የኔዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ዶንዬል ማለን 2x እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ በአውሮፓ ዋንጫው ሶስተኛ ግቡን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች አንዱ ሆኗል።

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው የቱርክ እና ኦስትሪያን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ቱርክ ከ ኦስትሪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለመጨረሻ ጨዋታ ሽንፈት ምላሽ ሰጥተናል " ጋክፖ

ኔዘርላንድ ሮማንያን ባሸነፈችበት የምሽቱ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ኮዲ ጋክፖ ቡድናቸው ከቀናት በፊት በኦስትሪያ ላጋጠመው ሽንፈት ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።

ጥሩ ጨዋታ እና ጥሩ ግቦችን አስቆጥረናል በማለት የተናገረው ኮዲ ጋክፖ " ለኦስትሪያ ሽንፈት ይህ ጥሩ ምላሽ ነው ፣ ሮማንያ ግብ ታስቆጥራለች የሚል እምነት አልነበረንም " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 16:35:18
Back to Top
HTML Embed Code: