Telegram Web Link
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
" የመጨረሻ አውሮፓ ዋንጫዬ ነው " ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመጨረሻው መሆኑን በሰጠው አስተያየት አሳውቋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአውሮፓ ዋንጫን ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ከስምንት አመት በፊት ማሳካት ችሏል።

የ 39ዓመቱ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በአስራ አራት ግቦች የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጨዋች ነው።

በምሽቱ ጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት በመሳቴ የፖርቹጋልን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለት የተናገረው ሮናልዶ " ግብ ጠባቂያችን አድኖናል " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#CopaAmerica2024

በኮፓ አሜሪካ ውድድር የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር አሜሪካ በዩራጓይ 1ለ0 መሸነፏን ተከትሎ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።

በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ ፓናማ ቦሊቪያን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ምድቡን ዩራጓይ አንደኛ እንዲሁም ፓናማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

በሩብ ፍፃሜው ዩራጓይ ከመጨረሻው ምድብ ሁለተኛ እንዲሁም ፓናማ አንደኛ ደረጃን ይዞ ከሚያጠናቅቅው ቡድን ጋር ይገናኛሉ።

የኮፓ አሜሪካ የመጨረሻው ምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲደረጉ :-

ሌሊት 10:00 - ብራዚል ከ ኮሎምቢያ

ሌሊት 10:00 - ኮስታሪካ ከ ፓራጓይ ጋር ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ ወደ ልምምድ ተመልሷል !

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ካጋጠመው መጠነኛ ጉዳት በማገገም ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ሐሙስ ሌሊት 10:00 ከኢኳዶር ጋር በምታደርገው የኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መድረሱ አሁንም አጠራጣሪ መሆኑ ተነግሯል።

ሊዮኔል ሜሲ ከቀናት በፊት አርጀንቲና ከፔሩ ጋር ያደረገችው የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እንዳመለጠው የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁዋን ጋርሽያ ወደ አርሰናል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዚህ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ከአሮን ራምስዴል ጋር የሚለያዩ ከሆነ አዲስ ግብ ጠባቂ እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ አሮን ራምስዴል ከለቀቀ ለመተካት የሚመለከቱት ግብ ጠባቂ ስፔናዊው የእስፓኞል ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ እንደሚሆን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች በውሰት የነበረውን ዴቪድ ራያ በቋሚነት ማስፈረማቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ተጨዋች ለማስፈረም አነጋግረዋል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም እንግሊዛዊውን ወጣት የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ከሊድስ ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። የ 18ዓመቱ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ቶተንሀምን መቀላቀል እንደሚፈልግ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ክለቦቹ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሊድስ ዩናይትድ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከብሬንትፎርድ የቀረበላቸውን…
ቶተንሀም ተጨዋች በይፋ አስፈርመዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም እንግሊዛዊውን ወጣት የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ከሊድስ ዩናይትድ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 18ዓመቱ ተስፈኛ ተከላካይ አርቼ ግሬይ በቶተንሀም ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ቶተንሀም ለዝውውሩ 40 ሚልዮን ፓውንድ ማውጣታቸው ሲገለፅ ተጨዋቹ በቶተንሀም የአስራ አራት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተጠቁሟል።

ቶተንሀም አርቼ ግሬይን ከሌሎች የሜዳ ክፍሎች በበለጠ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድርጎ ለማጫወት ማሰቡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BiniyamGirmay🇪🇷

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ ነህ፤ ለአፍሪካ እና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን " ሲሉ አወድሰውታል።

ቢኒያም ፤ " ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን " ሲል ተናግሯል።

ኤርትራዊው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት " የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ " የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ኤርትራውያን በተለይ በብስክሌት ግልቢያ በዓለም መድረክ በእጅጉ ይታወቃሉ።

#Eritrea
#NBC_Sport
#BBC
@tikvahethiopia
ዩናይትድ የተጫዋቾቹን መግቢያ እያደሰ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ የኦልድትራፎርድ ስታዲየም ተጨዋቾች ወደ ሜዳው የሚገቡበትን ስፍራ በአዲስ መልክ ለማደስ ስራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የስታዲየም መግቢያው የማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋቾችን በማካተት እድሳት እንደሚደረግለት ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የስታዲየም መግቢያውን ለማሻሻል ያሰቡት አካባቢውን ለማዘመን እና በጨዋታ ቀን ተጨዋቾቹን ለማነሳሳት ይጠቅማል በሚል መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆሽዋ ዚርክዜ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ?

የጣልያኑ ክለብ ቦሎኛ ሀላፊ ሳርቶሪ ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል የሚል እምነት እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

በኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከተወካዮቹ ጋር አሁን ላይ በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የሴርያው ክለብ ኤስ ሚላን በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

አሁን ላይ በአውሮፓ ዋንጫው ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘው ተጨዋቹ በቦሎኛ የውል ማፍረሻው 40 ሚልዮን ዩሮ መሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 ልዩ ቅናሹ 1 ሳምንት ብቻ ቀረው!

👉🏾 በዋናው አዲስ ቦት እስከ ሐምሌ 1 በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽ ያግኙ።

🤖 @WanawSportBot 🤖

👉🏾 #እንዳያመልጥዎ፣ ዛሬውኑ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
በቀላሉ በራስዎ የጨዋታ ቀመር አሽናፊነትዎን ይስሩ!

አሁኑኑ https://betika.com.et/et/combo-bet ላይ አሸናፊነትን ይጀምሩ!
አሸናፊነት በእጅዎ ነው!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
የቱርክ ደጋፊዎች የኦስትሪያን ተጨዋቾች ለመረበሽ ሞክረዋል !

የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ቱርክ ከኦስትሪያ ጋር ምሽት 4:00 በሌፕዚግ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ከጨዋታው አስቀድሞ ዛሬ ሌሊት የቱርክ ደጋፊዎች የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወዳረፉበት ሆቴል በማምራት ርችት እና ተቀጣጣይ ነገሮችን በማጮህ ለመረበሽ መሞከራቸው ተገልጿል።

በአውሮፓ ዋንጫው በደጋፊዎቻቸው ከደመቁ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አንዷ የሆነችው ቱርክ ሁለተኛዋ የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር የሚል ስም አግኝታለች።

ውድድሩ በሚዘጋጅበት ጀርመን ሀገር ከ #ሶስት ሚልዮን በላይ የቱርክ የዘር ሀረግ ያላቸው ነዋሪዎች መኖራቸው ይነገራል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከያዛቸው ሀያ ስድስት ተጨዋቾች መካከልም ሀካን ካልሀኖግሉ እና ከናን ይልዲዝን ጨምሮ አምስት ተጨዋቾቻቸው የተወለዱት ጀርመን ውስጥ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ ወጣት ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

ማንችስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን ወጣት የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሪሰን ማይልስ ከሳውዝሀምፕተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

የ 15ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀሪሰን ማይልስ አርሰናልን ጨምሮ በታላላቅ የሊጉ ክለቦች የሚፈለግ ቢሆንም ማንችስተር ሲቲዎች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል።

የእንግሊዝ ከ 16ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነው ሀሪሰን ማይልስ በሳውዝሀምፕተን ያለው ኮንትራት መጠናቀቁ ተገልጿል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ ከቶተንሀም ጋር የተለያየውን የ19ዓመት አማካይ ዊልሆፍት ኪንግ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopianPL 🇪🇹

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ2017 ዓ.ም የውድድር አመት የዝውውር መስኮት የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

የዝውውር መስኮቱ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም ተከፍቶ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም እንደሚዘጋ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

አሸናፊውን እስከ መጨረሻ መርሐ ግብር ያላሳወቀው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመት የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ከሌስተር ሲቲ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን በ30 ሚልዮን ፓውንድ በስድስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ተደርጓል። ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቀ በይፋ በቀድሞ አሰልጣኙ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራውን…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ከሌስተር ሲቲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን 30 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ በማድረግ ለተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ባለው በስድስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ " የቼልሲ ተጨዋች መሆን የሚደንቅ ነው ሁሉም ሰው ለመጫወት እየተመኘ የሚያድገው ክለብ ነው በጣም ተደስቻለሁ ለሁሉም ሰው ማድረግ የምችለውን ለማሳየት ጓጉቻለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ቀያይ ሴጣኖች የግብ ጠባቂያቸው ቶም ሂተንን ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

እንግሊዛዊው የ 38 ዓመት ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ተገልጿል።

" በልጅነት ክለቤ ውስጥ በመቆየቴ ደስተኛ ነኝ በጥሩ አቋም እንዳለሁ ይሰማኛል በሚቀጥለው አመት ቡድኑ የሚያስፈልገውን ነገር ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።"ሲል ቶም ሂተን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ዴሊትን ለማስፈረም ንግግር ጀመረ ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ይፋዊ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ የ 24ዓመቱን ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም በአያክስ ቤት እያለ ጀምሮ ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል። ማትያስ ዴሊት አሁን ላይ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2027 የሚደርስ ኮንትራት…
ዴሊት ዩናይትድን መቀላቀል እንደሚመርጥ አሳወቀ !

ኔዘርላንዳዊው የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ፍቃደኛ መሆኑን ማሳወቁ ተዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከባየር ሙኒክ ጋር በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 24ዓመቱን ተጨዋች ማትያስ ዴሊት 50 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ ገንዘብ ለማስፈረም ተስፋ አድርገው ድርድር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/24 19:04:47
Back to Top
HTML Embed Code: