Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። ለስፔን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ማርክ ጉዩ በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል። ተጨዋቹ በባርሴሎና ኮንትራቱ ውስጥ ያለው…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈርሟል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ለስፔን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ማርክ ጉዩ በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

የ 18ዓመቱን ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከፊርማው በኋላ " ፕርሚየር ሊግ ውስጥ መጫወት ህልሜ ነበር " ያለ ሲሆን ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በደስታ እንቅልፍ አልተኛሁም ፣ ለቼልሲ በመፈረሜ ተደስቻለሁ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
34 ' ፈረንሳይ 0 - 0 ቤልጅየም

- አድሬን ራብዮ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ፈረንሳይ ሩብ ፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ በቅጣት ጨዋታው የሚያልፈው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፈረንሳይ 0 - 0 ቤልጅየም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዳን አሽዎርዝ ዩናይትድን መቀላቀል ይፈልጋሉ ! በማንችስተር ዩናይትድ እየተፈለጉ የሚገኙት የ 52ዓመቱ የኒውካስል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ የዩናይትድን ጥያቄ እንደሚቀበሉ ማረጋገጣቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደ ትልቅ እድል እንደተመለከቱት የተገለፀው ዳን አሽዎርዝ ስራውን በይፋ ለመቀበል መዘጋጀታቸውም ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ከኒውካስል ዩናይትድ…
ማንችስተር ዩናይትድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሾመ !

ማንችስተር ዩናይትድ የኒውካስል ዩናይትዱን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ በሀላፊነት ለመሾም ከኒውካስል ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 52ዓመቱ ሀላፊ ዳን አሽዎርዝ በቀጣይ የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና በሀላፊነት እንደሚረከቡ ይፋ ሆኗል።

ኒውካስል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድ ለሀላፊው ውል ማፍረሻ አቅርበውት የነበረውን 10 ሚልዮን የሚደርስ ክፍያ መቀበሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84 ' ፈረንሳይ 1 - 0 ቤልጅየም

ቨርቶንገን ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረንሳይ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የፈረንሳይን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቨርቶንገን በራሱ መረብ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

አድሬን ራብዮ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በሩብ ፍፃሜው በቅጣት ለፈረንሳይ ግልጋሎት የማይሰጥ ይሆናል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው ከፖርቹጋል እና ስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች አሸናፊ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፖርቹጋል ከ ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መጥፎ እድል አብሮን ነበር " ዴብሮይን

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቡድናቸው እድለኛ እንዳልነበረ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ጥሩ መጫወት ብንችልም ያገኘነውን አጋጣሚ መጠቀም አልቻልንም " ያለው ዴብሮይን ያልሆነ ኳስ ተቆጥሮብናል በዛሬው ጨዋታ መጥፎ እድል ነበረን እጅግ ያበሳጫል ሲል ተደምጧል።

" በግል በውድድሩ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ ቡድኑን ለማገዝ ሁሉንም ነገር ሰጥታቻለሁ ፣ ያገኘኋቸውን የግብ እድሎች አልተጠቀምኩም ይህ አለመታደል ነው ነገርግን ሁሉንም ሰጥቻለሁ።" ዴብሮይን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ የፈረንሳይ ምርጥ አጥቂ ሆኗል " ቼሊኒ

የቀድሞ ጣልያናዊ ተከላካይ ጆርጂዮ ቼሊኒ በአውሮፓ ዋንጫው በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ " የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ምርጥ አጥቂ ሆኗል " በማለት ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግሯል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በጨዋታ ምንም ግብ ሳያስቆጥር ሩብ ፍፃሜ መድረስ የቻለ በውድድሩ ታሪክ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን ሆኗል።

ፈረንሳይ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች ካስቆጠረቻቸው ሶስት ጎሎች ሁለት ግቦቿ በተቃራኒ ተጨዋቾች በራስ ላይ ሲቆጠሩ አንድ ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ዴቪድ ራያን በቋሚነት አስፈርሟል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውሰት ከብሬንትፎርድ ያስፈረሙትን ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ኮንትራት የመግዛት አማራጫቸውን ተጠቅመው ቋሚ ማድረጋቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለግብ ጠባቂው የዝውውር ሒሳብ በውሉ ውስጥ ተካቶ የነበረውን የመግዛት አማራጭ ሒሳብ 27 ሚልዮን ፓውንድ መክፈላቸው ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊው ዴቪድ ራያ አሁን ላይ በይፋ የአርሰናል ተጨዋች መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫው አስራ ስድስት የግብ ሙከራዎች አድርጎ ግብ ያላስቆጠረ የመጀመሪያው ተጨዋች ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
105 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
112 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- የስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማጃዝ ኬክ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የመለያ ምት ተጀምሯል !

🇵🇹 ፖርቹጋል

🇸🇮 ስሎቬንያ

ውጤት በዚሁ ፖስት ላይ " Update " ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በመለያ ምት 3ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ዲያጎ ኮስታ የተመቱበትን ሶስት የመለያ ምቶች በሙሉ መመለስ ችሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር አርብ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/25 07:23:35
Back to Top
HTML Embed Code: