Telegram Web Link
90+8'

ክሮሽያ 1 - 1 ጣልያን

ሞድሪች ዛካኚ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
ጣልያን ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታ ስፔን አልባንያን 1ለ0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ክሮሽያ ከጣልያን ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ፌራን ቶሬስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ሉካ ሞድሪች ማስቆጠር ሲችል ለጣልያን ዛካኚ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መታደግ ችሏል።

ጣልያን አቻ መውጣቷን ተከትሎ ስፔንን በመከተል አስራ ስድስቱን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አራት ግቦችን በማስቆጠር የኢቫን ፔሪሲችን ታሪክ መጋራት ችሏል።

የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" እግርኳስ ሁልጊዜም ጨካኝ ነች " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ምሽት በመጨረሻ ደቂቃ ግብ አስተናግዶ አቻ ከተለያየበት ጨዋታ በኋላ ሉካ ሞድሪች " እግርኳስ ጨካኝ ነች " ሲል ገልጿል።

" የተቆጠረብን ግብ አይገባንም ነበር " ያለው ሉካ ሞድሪች እግርኳስ ሁልጊዜም ጨካኝ እና ምህረት የለሽ ነች ፣ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም አሸንፈን ባለማለፋችን በጣም አዝኛለሁ።"ሲል ተደምጧል።

የጨዋታው ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ሉካ ሞድሪች በቀጣይ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ያገል እንደሆን ሲጠየቅ " አሁን ትክክለኛው ጊዜ አይደለም " ሲል መልሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ህንድ ያለውን አካዳሚ መዝጋቱ ተገለጸ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በህንድ ዴልሂ እና ሙምባይን ጨምሮ በአራት ከተሞች ያላቸውን የታዳጊዎች አካዳሚ ለመዝጋት መወሰናቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና አካዳሚውን ለመዝጋት የወሰኑት ከተከፈተበት እ.ኤ.አ 2010 ወዲህ ባለፉት አስራ አራት አመታት አንድም ጥሩ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ሊገኝ ባለመቻሉ መሆኑ ተነግሯል።

ባርሴሎና በአራት ከተሞች አካዳሚውን የከፈተባት የደቡብ እስያዋ ሀገር ህንድ የ 1.4 ቢልዮን ህዝብ ብዛት ባለቤት ነች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምድቡ መሪ መሆን እንፈልጋለን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው የምሽቱን የኦስትሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አሸንፎ የምድቡ መሪ መሆን እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

" ጨዋታውን ማሸነፍ እና የምድቡ መሪ መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ሮናልድ ኮማን " ነገርግን ተጋጣሚ ማክበር እና ኳስ ተቆጣጥረን መጫወት አለብን ካልሆነ ኦስትሪያ ያስቸግራሉ አውሮፓ ዋንጫው በፉክክር የተሞላ ነው።"ብለዋል።

አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቀጥለውም እስካሁን በውድድሩ ላይ ለዋንጫ የማጫቸው ብዙ ቡድኖች አላየሁም በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉዊስ ዲያዝ ሊቨርፑልን ሊለቅ ይችላል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአዲሱ አሰልጣኝ አሬኔ ስሎት እቅድ ውስጥ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተጨማሪም አየርላንዳዊው ግብ ጠባቂ ኮሚን ኬለር በቀጣይ የውድድር አመት በአሰልጣኝ አሬኔ ስሎት እቅድ ውስጥ መሆኑ ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑል ለሉዊስ ዲያዝ 50 ሚልዮን ፓውንድ እንዲሁም ለግብ ጠባቂ ኮሚን ኬለር 25 ሚልዮን ፓውንድ ከቀረበለት ለመሸጥ ሊያስብበት እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሽሊ ያንግ በኤቨርተን መቆየት ይፈልጋል ! እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ በመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ቤት በሚቀጥለው የውድድር አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል። ኤቨርተን ባለፈው አመት በነፃ ዝውውር ቡድናቸውን የተቀላቀለውን አሽሊ ያንግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በክለቡ ለማቆየት የአንድ አመት ውል ማቅረባቸው ተገልጿል። የ 38ዓመቱ የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ መጫወት እስከቻለ…
አሽሊ ያንግ በኤቨርተን ቤት ውሉን አራዝሟል !

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ በመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ቤት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 38ዓመቱ የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ በኤቨርተን ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ተገልጿል።

በክለቡ እንዲቆይ ሲጠየቅ ለመቀበል አለማንገራገሩን የገለፀው አሽሊ ያንግ ከፊርማው በኋላ እዚ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔥 #ይፍጠኑ፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ናቾ ከሪያል ማድሪድ ጋር ሊለያይ ነው ! ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚለያይ ተገልጿል። በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ናቾ ፈርናንዴዝ ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ ሪያል ማድሪድን የሚለቅ ይሆናል። ሪያል ማድሪድ በዚህ አመት የላሊጋ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ናቾ በታሪክ ስኬታማው…
ሪያል ማድሪድ ከናቾ ጋር መለያየቱ ይፋ ሆነ !

የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ ከስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ ጋር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ናቾ ፈርናንዴዝ ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያይተዋል።

ናቾ በሪያል ማድሪድ ቤት ሶስት መቶ ስልሳ አራት ጨዋታዎች ሲያደርግ #ስድስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ አጠቃላይ ሀያ ስድስት ዋንጫዎች አሳክቷል።

ናች ፈርናንዴዝ በቀጣይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በይፋ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ ማልያውን እንደሚሰጠኝ ተሰፋ አደርጋለሁ "ክቫራትስኬሊያ

የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ህቪቻ ክቫራትስኬሊያ ፖርቹጋላዊውን ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ መግጠም ለእሱ ህልሙ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ሮናልዶን መግጠም ለእኔ ህልሜ ነበር " ያለው ክቫራትስኬሊያ " እሱ በአውሮፓ አይጫወትም ነገርግን አሁን እኛ ምድብ ይገኛል አንዳንድ ጊዜ ህልሞችም እውን ይሆናሉ " ሲል ተደምጧል።

ተጨዋቹ ቀጥሎም በነገው የፖርቹጋል እና ጆርጂያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ " የሮናልዶን ማልያ ይዤ መሄድ እፈልጋለሁ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሩድ ቫን ኔስትሮይ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ? የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ እንዲካተት ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል። ኔዘርላንዳዊ የቀድሞ የፊት መስመር ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች አድርጎ አንድ መቶ ሀምሳ ግቦች አስቆጥሯል። ሩድ ቫን ኔስትሮይ…
ኤሪክ ቴንሀግ ውላቸውን ለማራዘም ተቃርበዋል !

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ለማቆየት መወሰኑ እና ውላቸውን ለማራዘም ንግግር መጀመሩ እንደተገለፀ ይታወሳል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የአሰልጣኞች ቡድን ለውጥ እንደሚያደርጉ ሲገለፅ የክለቡ ቀድሞ ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይን ለማምጣት ጥረት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ደምቀዋል! ፉክክሩም አይሏል! ማን ወደ ጥሎ ማለፍ ይገባል?

🤔 የእናንተን አስተያየት ከስር አጋሩን!

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
የጨዋታ አሰላለፎች !

1:00 ፈረንሳይ ከ ፖላንድ

1:00 ኔዘርላንድ ከ ኦስትሪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ ያለነው ለማሸነፍ ነው " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው ከደቂቃዎች በኋላ ከኦስትሪያ ጋር የሚያደርገውን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጸዋል።

" እዚህ ያለነው ለማሸነፍ ነው " ያሉት አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን " ምድቡን በበላይነት መርተን ማለፍ እንፈልጋለን የፈረንሳይን ውጤት መመልከት አልፈልግም ምክንያቱም እኛ የምንገባው ለማሸነፍ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/28 20:01:34
Back to Top
HTML Embed Code: