Telegram Web Link
አልባንያ ተጨዋቿ የጨዋታ ቅጣት ተጣለበት !

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሚርሊንድ ዳኩ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች አገዳ እንደተጣለበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈበት አልባንያ ከቀናት በፊት ከክሮሽያ ጋር ካደረገችው ጨዋታ በኋላ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ ሰርቢያዊያን እና መቄዶኒያዊያንን መሳደቡን ተከትሎ ነው።

በተጨማሪም የአልባንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ50,000 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሁን ሁሉም ስዊዘርላንድን የበለጠ ያከብራል " ዣካ

የስዊዘርላንድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ከትላንቱ የጀርመን ጨዋታ በኋላ ቡድናቸው የበለጠ ይከበራል የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም " ቀጣይ ጨዋታችን እና ተጋጣሚያችንን በጉጉት እየጠበቅን ነው ከትናንቱ የጀርመን ጨዋታ በኋላ ሁሉም ሰው ለስዊዘርላንድ የበለጠ ክብር እንደሚሰጥ ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮነር ጋራገር በአርኖልድ ቦታ ሊሰለፍ ነው !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌቱ ቡድኑ ከስሎቬኒያ ጋር በሚያደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የአሰላለፍ ለውጥ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በጨዋታው በመሐል ሜዳ ክፍሉ አሌክሳንደር አርኖልድን በኮነር ጋላገር ተክተው ለማሰለፍ ማሰባቸው ተነግሯል።

የሊቨርፑሉ ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች በአማካይ ስፍራ ተሰልፎ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ተቃውሞዎች ሲቀርቡበት ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሆሴሉ ለሪያል ማድሪድ በቋሚነት ይፈርማል ! ሪያል ማድሪድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ ለሚቀጥለው የውድድር አመት በቋሚነት ለማስፈረም መወሰናቸው ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ሆሴሉን ባለፈው ክረምት በውሰት 500,000 ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት ሲሆን ተጫዋቹም በወሳኝ ጨዋታዎች ግብ በማስቆጠር ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎት መስጠት ችሏል። ሪያል ማድሪዶች ተጫዋቹን በውሉ…
ሆሴሉ ሪያል ማድሪድን ሊለቅ ነው !

ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለመቀጠል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በሆሴሉ የውሰት ውል ውስጥ የተካተተውን አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ በቋሚነት ለማስፈረም መወስናቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ሆሴሉ ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣታቸውን ተከትሎ ሎስ ብላንኮዎቹን ለመልቀቅ ማሰቡ ተገልጿል።

ሆሴሉ በቀጣይ የኳታሩን ክለብ አል ሀራፋ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 በጥራት የተዘጋጁ #ቢብሶች!

🔥 አሁኑኑ #ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
" በእግርኳስ ካሰብኩት በላይ ማሳካት ችያለሁ " ሜሲ

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ካሰበው በላይ ስኬታማ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" አመታት እየሄዱ እንደሆነ እና በእግርኳስ ውስጥ የቀሩኝ አመታት ጥቂት መሆናቸውን አውቃለሁ " ያለው ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቴ ካለምኩት በላይ ማሳካት ችያለሁ " ብሏል።

የኢንተር ሚያሚው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በዛሬው ዕለት 37ኛ አመት የልደት ቀኑን በማክበር ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤምሬትስ ካፕ የሚደረግበት ቀን ተገለጸ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት የሚያዘጋጀው ኤምሬትስ ካፕ የተሰኘው  ውድድር ነሐሴ 5 እንደሚካሄድ ተገልጿል ።

አርሰናል የዚህን አመት የኤምሬትስ ካፕ ጨዋታ እሁድ ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ሊዮን ጋር እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል።

በተጨማሪም መድፈኞቹ ከሊዮን ጨዋታ አራት ቀናት ቀደም ብለው ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሌቨርኩሰን ጋር በኤምሬትስ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ስዊዘርላንዳዊው የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም ተመልሶ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
" ኪሊያን ምባፔ መጫወት ይፈልጋል "

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ የቡድኑ አምበል ኪሊያን ምባፔ ካጋጠመው ጉዳት እየተሻለው መሆኑን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ አያይዘውም ኪሊያን ምባፔ በነገው የፖላንድ ጨዋታ ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና በጨዋታው መሰለፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ ጨዋታዎች የሚያደርገው የፊት ጭምብል ለመተንፈስ አስቸጋሪ ባይሆንበትም እይታውን በመጠኑ ሊቀንሰው እንደሚችል አሰልጣኙ አያይዘው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አልባንያ ከ ስፔን

4:00 ክሮሽያ ከ ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#EURO2024

በምሽቱ የጣልያን እና ክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ 38,000 ተመልካች በሚይዘው የሌፕዚግ ስታዲየም 25,000 ገደማ የክሮሽያ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢቫን ፔርሲችን ተጠባባቂ ያደረገችው ክሮሽያ የአጥቂ አማካዩ ክራማሪችን በፊት መስመር ቦታ ላይ አሰልፋለች።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ያለ ተፈጥሯዊ አጥቂ ሲገቡ 4-6-0 የሆነ የጨዋታ አሰላለፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የክሮሽያ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው የ3-5-2 የጨዋታ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
13 '

አልባንያ 0-1 ስፔን

ቶሬስ

ክሮሽያ 0-0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
31 '

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#እረፍት

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
54 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
77 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

*ወቅታዊ የምድቡ ደረጃ ሰንጠረዥ

1️⃣ ስፔን :- 9 ነጥብ

2️⃣ ክሮሽያ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ጣልያን :- 3 ነጥብ

4️⃣ አልባንያ :- 1 ነጥብ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
2024/07/01 00:44:49
Back to Top
HTML Embed Code: