Telegram Web Link
ቡናማዎቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አንተነህ ተፈራ እና አብዱልከሪም ወርቁ ከመረብ ሲያሳርፉ ያሬድ ዳርዛ ለኢትዮጵያ መድን አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ መድን ከሰባት ተከታታይ ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ኢትዮጵያ ቡና አምስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 50 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 37 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
58 ' ጆርጂያ 1 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ሚካውታድዝ ሺክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የጆርጂያን ግብ ሚካውታድዝ ከመረብ ሲያሳርፍ ፓትሪክ ሺክ ቼክ ሪፐብሊክን አቻ ማድረግ ችሏል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቱርክ :- 3 ነጥብ

2️⃣ ፖርቹጋል :- 3 ነጥብ

3️⃣ ቼክ ሪፐብሊክ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ጆርጂያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሮብ ጆርጂያ ከፖርቹጋል እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ ከቱርክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ቱርክ ከ ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔥 #በፍፁም እንዳያመልጥዎ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
Photo
አርዳ ጉለር ለምን ከአሰላለፍ ውጪ ሆነ ?

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ወጣቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አርዳ ጉለር ከደቂቃዎች በኋላ በሚደረገው የፖርቹጋል ጨዋታ ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

አርዳ ጉለር ጨዋታውን በቋሚነት ለመጀመር መቶ በመቶ ብቁ አለመሆኑን የቱርክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቪንሴንሶ ሞንቴላ ገልፀው ነበር።

የ 19ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አርዳ ጉለር ቱርክ ጆርጂያን ባሸነፈችበት የመጀመሪያ ጨዋታ ድንቅ ግብ ማስቆጠር ሲችል የጨዋታው ኮከብ በመባልም መመረጥ ችሏል።

በጆርጅያ ጨዋታ በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃዎች ተቀይሮ የወጣው አርዳ ጉለር ባለፈው ሐሙስ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሳይሰራ ቀርቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ላይ ግብ አላስቆጠረም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሶስት ጊዜ የተጫወተ ሲሆን እ.ኤ.አ 2012 ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።

ሮናልዶ በምሽቱ ጨዋታ ሁለት መቶ ዘጠኝ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2 ' ቱርክ 0 - 0 ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 ' ቱርክ 0 - 0 ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
23 ' ቱርክ 0 - 1 ፖርቹጋል

ሲልቫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 ' ቱርክ 0 - 2 ፖርቹጋል

               ሲልቫ
አካይዲን ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
44 ' ቱርክ 0 - 2 ፖርቹጋል

               ሲልቫ
               አካይዲን ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ቱርክ 0 - 2 ፖርቹጋል

               ሲልቫ
               አካይዲን ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ከነዓን ማርክነህ 2x ፣ ምንይሉ ወንድሙ እና በሀይሉ ግርማ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለሲዳማ ቡና ብርሀኑ በቀለ አስቆጥሯል።

መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ያለውን ነጥብ እኩል ሀምሳ ሰባት በማድረስ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

2️⃣ መቻል :- 57 ነጥብ

1️⃣2️⃣ ሲዳማ ቡና :- 34 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

እሁድ - መቻል ከ አዳማ ከተማ

ሐሙስ - ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 ' ቱርክ 0 - 3 ፖርቹጋል

               ሲልቫ
               አካይዲን ( በራስ ላይ )
ፈርናንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 ' ቱርክ 0 - 3 ፖርቹጋል

               ሲልቫ
               አካይዲን ( በራስ ላይ )
               ፈርናንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።

ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን በርናርዶ ሲልቫ ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና አካይዲን ( በራስ ላይ ) ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሰባት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በውድድሩ ታሪክ አዲስ ሪከርድ ማስመዝገብ ችሏል።

በተጨማሪም ሮናልዶ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በአጠቃላይ ውድድሮች ሰላሳ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የሉዊስ ፊጎን ሪከርድ መጋራት ችሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ራፋኤል ሊያኦ በተከታታይ ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ያመልጠዋል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ፖርቹጋል :- 6 ነጥብ

2️⃣ ቱርክ :- 3 ነጥብ

3️⃣ ቼክ ሪፐብሊክ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ጆርጂያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሮብ ጆርጂያ ከፖርቹጋል እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ ከቱርክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ቤልጅየም ከ ሮማንያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 22:03:31
Back to Top
HTML Embed Code: