Telegram Web Link
#EURO2024

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እና የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ከጨዋታው አስቀድሞ በስታዲየሙ ውስጥ ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች በስታዲየሙ ውስጥ ቁሳቁሶችን ሲወራወሩ መስተዋላቸው ተነግሯል።

አሁን ላይ በስታዲየሙ የተፈጠረውን ግጭት በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ገብተው ማረጋጋታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ዛሬ ከቱርክ አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል።

ጆርጅያ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት በታሪክ ትልቁ የሆነውን የ 8ለ0 ድል እንዲሁም በታሪክ ትልቁ የሆነውን የ 7ለ1 ሽንፈት አስመዝግበው በአውሮፓ ዋንጫው ቀርበዋል።

በቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ዊሊ ሳኞል የሚመራው የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን በ3-5-2 አሰላለፍ በመስመር በኩል ባሏቸው ተመላላሾች ጫና ፈጥሮ መጫወትን ይመርጣሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
26 ' ቱርክ 1-0 ጆርጅያ

ሙልዱር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
33 ' ቱርክ 1-1 ጆርጅያ

ሙልዱር ሚካውታድዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ቱርክ 1-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
66 ' ቱርክ 2-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ
አርዳ ጉለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+6' ቱርክ 3-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ
አርዳ ጉለር
አክቱርኮግሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቱርክ ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለቱርክ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን አርዳ ጉለር ፣ ሙልዱር እና አክቱርኮግሉ ከመረብ ሲያሳርፉ ለጆርጅያ ሚካውታድዜ አስቆጥሯል።

ቱርካዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አርዳ ጉለር በትልቅ ውድድር ላይ ለቱርክ ብሔራዊ ቡድን ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቅዳሜ ጆርጂያ ከቼክ እንዲሁም ቱርክ ከፖርቹጋል ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፖርቹጋል ከ ቼክ ሪፐብሊክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ ግብ አስቆጣሪያችን ነው " ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቡድኑ ውስጥ ያለው ትልቅ ስም ስላለው ብቻ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ሮናልዶ ከእድሜው መግፋት ጋር በተያያዘ መጠራት አልነበረበትም ለሚሉ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ " ሮናልዶ ቡድኑ ውስጥ ያለው ለጥቅም ነው ማንም ሰው ስም ስላለው አልተጠራም።

ሮናልዶ ለአል ናስር በተጠናቀቀው አመት በሀምሳ አንድ ጨዋታዎች ሀምሳ ግቦች አስቆጥሯል ፣ እሱ ግብ አስቆጣሪያችን ነው።"በማለት ከተጨዋቻቸው ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ሩበን ዲያስ በበኩሉ ሮናልዶ በቡድኑ መካተቱ እንዳስደሰተው የገለፀ ሲሆን " ሮናልዶ መነሳሳትን እና ሁሉም ነገር እንደሚቻል ማሳያ ነው።

ሮናልዶ አምበላችን ነው አሁንም ማሸነፍ ይፈልጋል እኛም እስከመጨረሻው እንከተለዋለን።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የማድሪድ ድጋፍ የበለጠ አነሳስቶኛል " አርዳ ጉለር

ቱርክ ጆርጂያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ወሳኝ ግብ ያስቆጠረው እና የጨዋታው ኮከብ በመባል የተመረጠው አርዳ ጉለር ሪያል የማድሪድ ድጋፍ እንደጠቀመው ተናግሯል።

" አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከጨዋታው በፊት መልዕክት ልከው መልካም ምኞታቸውን ገልፀውልኛል " ያለው አርዳ ጉለር ከሪያል ማድሪድ የተደረገልኝ ድጋፍ ትልቅ መነሳሳት ፈጥሮልኛል በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፖርቹጋል ምድቡን ብቻ ሳይሆን ውድድሩን ልታሸንፍ ትችላለች " ቶማስ ሱሴክ

የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን አምበል ቶማስ ሱሴክ ፖርቹጋል የዘንድሮውን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ማሸነፍ ትችላለች የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።

" ፖርቹጋል ምድቡን ብቻ ሳይሆን ውድድሩን ማሸነፍ ትችላለች " የሚለው ቶማስ ሱሴክ ባለፉት አመታት ጥራት እንዳላቸው አሳይተዋል ሮናልዶ ኮከባቸው ነው ባለፉት ሀያ አመታት የፖርቹጋል ትልቁ ኮከብ እሱ ነው ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፖርቹጋል 0 - 0 ቼክ ሪፐብሊክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
61 ' ፖርቹጋል 0 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ፕሮቮድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
69 ' ፖርቹጋል 1 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 ' ፖርቹጋል 1 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ

- ፖርቹጋል በጆታ አማካኝነት ያስቆጠረችው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ፖርቹጋል 2 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ
ኮንሴካኦ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ውድድሯን በድል ጀምራለች !

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ፍራንሴስኮ ኮንሴካኦ እና ፕሮቮድ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቼክ ህራናክ ከመረብ አሳርፏል።

ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ፔፔ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የተሳተፈ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስድስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች በመሳተፍ በውድድሩ ታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች መሆን ችሏል።

በቀጣይ ቅዳሜ በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ፖርቹጋል ከቱርክ እንዲሁም ቼክ ከጆርጅያ ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 02:39:23
Back to Top
HTML Embed Code: