Telegram Web Link
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ይለያሉ !

ዛሬ ምሽት በስፔን ኔርጃ ሀገራችን ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት የመምረጫ ውድድር እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከምሽቱ የመምረጫ ውድድር በኋላ ኢትዮጵያን በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር 10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶች ተለይተው ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ምሽት የ800ሜ እና 1500ሜ ወንዶች የኦሎምፒክ ሚኒማ ለማሟላት የሙከራ ውድድሮች እንደሚደረጉ ታውቋል።

ውድድሮቹ ስንት ሰዓት ይደረጋሉ ?

ምሽት 2:25 - 800ሜ ወንዶች

ምሽት 2:40 - 10000ሜ ሴቶች

ምሽት 3:15 - 10000ሜ ወንዶች

ምሽት 3:50 - 1500 ወንዶች

ምንጭ :- ብዙአየሁ ዋጋው

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ተጠባቂው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት አዘጋጇ ሀገር ጀርመን ከስኮትላንድ ጋር በምታደርገው የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል።

- በውድድሩ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን በአማካይ 28.2 እድሜ ትልቅ እድሜ ያለው ብሔራዊ ቡድን በመሆን የሚቀርብ ይሆናል።

- የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በ25.3 አመት በአማካይ የውድድሩ ወጣት እድሜ ያለው የቡድን ስብስብ ይዞ የሚካፈሉ ይሆናል።

- የ 17ዓመቱ ስፔናዊው የባርሴሎና ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ ተሰልፎ የሚጫወት ከሆነ በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

- የ 41ዓመቱ ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ፔፔ በውድድሩ ተሰልፎ የሚጫወት ከሆነ በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመሆን አዲስ ሪከርድ ያስመዘግባል።

- ከፔፔ የተሻለ ግብ የማስቆጠር እድል ያለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ በትልቅ እድሜው ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጨዋች መሆን ይችላል።

- ሮሜሎ ሉካኩ ለሀገሩ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ከሌሎች ተጨዋቾች የበለጠ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ አለው ሉካኩ በጨዋታ በአማካይ 0.74 ግብ ያስቆጥራል።

- የአውሮፓ ዋንጫውን ከሚያስተናግዱ የጀርመን ስታዲየሞች ግማሹ የጀርመን ሁለተኛ ሊግ ክለቦች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
በኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ !

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ በተያዘው እቅድ መሠረት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገልጸዋል።

አቶ ቀጄላ መርዳሳ ከዚህ በፊት በሀገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

አሁን ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የጥናት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ውድድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ታሪካዊ ዳራ በተጠበቀ መልኩ ለማዘጋጀት መታቀዱም ተነግሯል።

መሟላት ስለሚገባቸው ስታዲየሞች ያስረዱት ሚኒስትሩ ብሔራዊ ስታዲየም እና ባሕር ዳር ስታዲየምን ጨምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

ምንጭ :- EBC

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024 🇩🇪

በአሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን የሚመራው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከስኮትላንድ ጋር በሀገሪቱ ሁለተኛ ግዙፍ ስታዲየም የባየር ሙኒኩ አሊያንዝ አሬና የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታውን ያደርጋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ዶርትመንድን ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ያደረሱትን ማትስ ሁሜልስ እና ካሪም አዴይሚን ባልተጠበቀ መልኩ በስብሰባቸው ሳያካትቱ ለውድድሩ ቀርበዋል።

አሰልጣኙ በባየር ሙኒክ ቤት ያሰለጠኑት የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሊዮን ጎሬዝካን እንዲሁ በስብስባቸው ውስጥ ያላከተቱ ሌላኛው ተጨዋች ነው።

ጁሊያን ኔግልስማን የመሐል ሜዳውን እንዲመሩ የብራይተኑን ፓስካል ግሮስ እና የባየር ሊቨርኩሰኑን ሮበርት አንድሪችን መርጠዋል።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ቁልፍ በሆኑ የሜዳ ክፍሎች በቡንደስሊጋው ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀው ስቱትጋርት ተከላኩዩን ዋልዴማር አንቶን እና የክንፍ ተጫዋቹን ክሪስ ፉሪች በስብሰባቸው አካተዋል።

የአውሮፓ ዋንጫው ውድድር ፍፃሜ ከአንድ ወር በኋላ በርሊን በሚገኘው የሀገሪቱ ግዙፍ ስታዲየም ኦሎምፒያስታዲዮን የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የልምምድ ማዕከሉን ሊያድስ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ የክለቡን ልምምድ ማዕከል ካሪንግተን ለማደስ ከሚቀጥለው ሳምንት በኋላ ስራ እንደሚጀመር ይፋ አድርጓል።

ለክለቡ ልምምድ ማዕከል እድሳት 50 ሚልዮን ፓውንድ መመደቡ በይፋ ሲገለፅ ማዕከሉን ዘመናዊ እና ለተጨዋቾች እና ሰራተኞቹ ምቹ ለማድረግ መታሰቡ ተነግሯል።

ለልምምድ ማዕከሉ የሚወጣው 50 ሚልዮን ፓውንድ የክለቡን አነስተኛ ድርሻ የገዙት ሰር ጂም ራትክሊፍ ለክለቡ መሰረት ልማት ካዘጋጁት የ300 ሚልዮን ዶላር ውስጥ እንደሆነ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሉካኩ ወደ ሳውዲ መሄድ እንደሚፈልግ ገለጸ ! ቤልጂየማዊው የፊት መስመር አጥቂ ሮሜሎ ሉካኩ የሳውዲ አረቢያ እግርኳስ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሆኑን በሰጠው አሰሰተያየት ገልጿል። " አንድ ቀን ሳውዲ አረቢያ መጫወት እፈልጋለሁ " የሚለው ሮሜሎ ሉካኩ እዛ እግርኳስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ አውቃለሁ ብዙ ተጨዋቾች ወደዛ መሄድ ይፈልጋሉ።"በማለት ተናግሯል። " የሳውዲ አረቢያ እግርኳስ በፍጥነት…
ሳውዲ አረቢያ ሉካኩን ማስፈረም ትፈልጋለች ?

ሳውዲ አረቢያ በያዝነው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩን ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥተው #እንደማይንቀሳቀሱ ተገልጿል።

አሁን ላይ በቼልሲ ኮንትራት ያለው ሮሜሎ ሉካኩ በቅርቡ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዶ መጫወት እንደሚፈልግ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር።

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ባለፈው ክረምት ሮሜሎ ሉካኩን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ተጨዋቹ ባለመፈለጉ ሳይሳካ መቅረቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥በጉጉት የሚጠበቀው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ይጀመራል!

⚽️ Germany vs Scotland ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በSS Football 225 በ ጎጆ ፓኬጅ

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር 350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Turning any art into lasting metal prints!

Custom prints available in various sizes:
A4
A3
A2

Order now by calling 0912689730 or 0913336591.

Follow us for more
Telegram: @silverpoint_printss
Instagram: https://www.instagram.com/silverpoint_prints/
TikTok: https://www.tiktok.com/@silverpoint.prints
ዶርትመንድ ከተጨዋቹ ጋር ተለያየ !

የቡንደስሊጋው ክለብ ዶርትመንድ ከጀርመናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትስ ሁሜልስ ጋር ከአስራ ሶስት አመታት በኋላ መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 35ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትስ ሁሜልስ በዶርትመንድ ቤት ያለው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ በነፃ ክለቡን ይለቃል።

ማትስ ሁሜልስ ከዶርትመንድ ጋር ሁለት የቡንደስሊጋ እንዲሁም ሌሎች የጀርመን ፖካል እና ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ u-20 ፕርሚየር ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ተለዩ !

የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲደረጉ ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ቡና ከ 20ዓመት በታች ቡድን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻውን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሰዋል።

የመቻል ከ 20ዓመት በታች ቡድን በበኩሉ የኢትዮ ኤሌክትሪክ አቻውን በተመሳሳይ በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረስ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡና ከ 20ዓመት በታች ቡድን እና የመቻል አቻው የፊታችን እሁድ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ረፋድ 5:00 ሰዓት የፍፃሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በደረጃ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የፊታችን እሁድ በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ጠዋት 3:00 ሰዓት ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስፔን የተጨዋቿን ግልጋሎት አታገኝም !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከክሮሽያ ጋር በሚያደርገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የተከላካዩ አይመሪክ ላፖርቴን ግልጋሎት እንደማያገኝ ተገልጿል።

አይመሪክ ላፖርቴ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው የተገለፀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ልምምድ አለመስራቱ ተነግሯል።

በነገው ጨዋታ የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ናቾ የመሐል ተከላካይ ሆኖ በቋሚነት ሊጀምር እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግብ አብዱ ሙተለቡ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው መቻል ማሸነፉን መውጣቱን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ማጥበብ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

2️⃣ መቻል :- 54 ነጥብ

7️⃣ ፋሲል ከነማ  :- 40 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ሲዳማ ቡና ከ መቻል

- ሻሸመኔ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን ማን ሊያሸንፍ ይችላል ?

ፍፃሜውን ሊያገኝ የተቃረበው የ2016 ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ለዋንጫው አሸናፊነት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና መቻልን አፋጦ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊጉን በሀምሳ ሰባት ነጥቦች በበላይነት ሲመራ መቻል በሶስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሻሸመኔ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን

- መቻል :- ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ

የሊጉ ሻምፒዮን ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሬስ ኔልሰን አርሰናልን መልቀቅ ይፈልጋል !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሬስ ኔልሰን በዚህ ክረምት ሌላ የሚፈልገው ክለብ ካገኘ መመልከት እንደሚፈልግ ለአርሰናል ማሳወቁ ተገልጿል።

በጥር ወር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለሬስ ኔልሰን የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት መድፈኞቹ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለመሸጥ የሚገደዱ ከሆነ 20 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

በአርሰናል ቤት ብዙም የመጫወት እድል ያላገኘው የ 24ዓመቱ ተጨዋች ሬስ ኔልሰን ባለፈው ክረምት የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይታወሳል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም ዌስትሀም ዩናይትድ ፣ ኖቲንግሃም ፣ ፉልሀም እና ክሪስታል ፓላስ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከሀላፊነታቸው ለቀቁ ! ጀርመናዊው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል። አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን በይፋ አስታውቀዋል። የ 41ዓመቱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቦርስያ ዶርትመንድን እየመሩ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ እንደነበሩ…
ዶርትመንድ ኑሪ ሳሂን በአሰልጣኝነት ሾመ !

ከጀርመናዊው አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ጋር የተለያየው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዶርትመንድ ቱርካዊውን የቀድሞ ተጨዋቻቸው ኑሪ ሳሂንን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ለቦርስያ ዶርትመንድ በሁለት መቶ ሰባ አራት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት የቻለው ኑሪ ሳሂን ባለፈው አመት በኤዲን ቴርዚች የአሰልጣኝ ቡድን ውስጥ ተካቶ ሰርቷል።

የ 35ዓመቱ የቀድሞ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኑሪ ሳሂን ቦርስያ ዶርትመንድን ለሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ጥያቄ አቀረበ !

ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመሐል ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ለማስፈረም ለኤቨርተን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር የመጀመሪያ 35 ሚልዮን ፓውንድ ማቅረባቸው ተነግሯል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በበኩሉ የቀረበው የዝውውር ሒሳብ ከሚጠበቀው በታች ነው ብለው እንደሚያምኑ ሲገለፅ ውድቅ ለማድረግ ማሰባቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ#ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን?

🇩🇪 ጀርመን ወይስ ስኮትላንድ 🇸🇪

💬 ግምትዎን #በቴሌግራም ገፃችን (https://www.tg-me.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የጂም ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !

በ2016 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ተመስገን ደረሰ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር አመቱ #ስምንተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፈረሰኞቹ ካለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በአንዱ ነው በአምስቱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይተዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 43 ነጥብ

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ  :- 40 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

- ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ የመጣነው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ነው " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ቡድናቸው በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ትልቅ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀቱን ተናግሯል።

ነገ ከስፔን ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት አስተያየቱን የሰጠው ሉካ ሞድሪች " በአለም ዋንጫ እንዳደረግነው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንፈልጋለን ወደዚህ የመጣነው ትልቅ ውጤት አልመን ነው " ብሏል።

በአውሮፓ እና አለም ዋንጫ ውድድሮች ዙሪያ እየተሰጡ ስለሚገኙ አስተያየቶች የተጠየቀው ሞድሪች " ሁለቱን ላወዳድር አልፈልግም ነገርግን አለም ዋንጫ ከባድ ይመስለኛል አለም ዋንጫ የአለም ምርጥ ቡድኖችን የሚያገናኝ ብቸኛው ውድድር ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 11:21:27
Back to Top
HTML Embed Code: