Telegram Web Link
" የዩናይትድ አካል መሆን ትልቅ ሀላፊነት ነው " ኦናና

ካሜሮናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚደረጉ ጨዋታዎች ሁሉ ቀላል እንዳልሆኑ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚደረጉ ጨዋታዎች ሁሉ ቀላል አይደሉም "የሚለው አንድሬ ኦናና ምክንያቱም ስታዲየሙ እና ክለቡ ትልቅ ታሪክ አላቸው የዩናይትድ አካል መሆን ታላቅ ሀላፊነት ነው።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶም ሂተን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ይቀላቀላል !

የማንችስተር ዩናይትዱ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን ለቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን እንደሚቀላቀል ተገልጿል።

የ 38ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን የሚቀላቀለው ግብ ጠባቂዎችን በልምምድ ወቅት እገዛ ለማድረግ መሆኑ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለአውሮፓ ዋንጫው በግብ ጠባቂነት ጆርዳን ፒክፎርድ ፣ አሮን ራምስዴል እና ዲን ሄንደርሰንን መጥራቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማሊ ብሔራዊ ቡድን የጉዞ መስተጓጎል ገጥሞታል !

የማሊ ብሔራዊ ቡድን ነገ ደቡብ አፍሪካ ላይ ከሜዳው ውጪ ከማዳጋስካር ጋር ለሚያደርገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለማምራት የሀገሪቱ የአየር ንብረት አስቸጋሪ እንዳደረገበት ተገልጿል።

ብሔራዊ ቡድኑ ባለፈው ቅዳሜ ሰባት ሰዓት የሚፈጅ ቀጥታ በረራ ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ምክንያት በረራውን ሶስት ጊዜ ለመሰረዝ መገደዱ ተነግሯል።

ብሔራዊ ቡድኑ አሁን ላይ በመደበኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዞ አዲስ አበባ ላይ አርፎ ወደ ጆሀንስበርግ ለማምራት ጉዞውን መጀመሩ ተዘግቧል።

በተመዘገበ ስታዲየም እጦት ምክንያት ደቡብ አፍሪካ ላይ ለሚደረገው ጨዋታ የማሊ ብሔራዊ ቡድን ነገ ጠዋት ጆሀንስበርግ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ በአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር መሳተፍ አይፈልግም ! ሪያል ማድሪድ ቀጣይ አመት በሚጀምረው አዲሱ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር እንዲሳተፍ ከፊፋ የቀረበለትን ግብዣ እንደማይቀበል አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተናግረዋል። ፊፋ ሪያል ማድሪድ በአለም ክለቦች ዋንጫ በሚያደርገው አንድ ጨዋታ 20 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ እና ክፍያው እስከ ውድድሩ መጨረሻ እንደሚቀጥል እንዳሳወቀ ተገልጿል። " በውድድሩ…
ማድሪድ በአለም ክለቦች ዋንጫ ይሳተፋል !

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ቀጣይ አመት በሚጀምረው አዲሱ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር #እንደሚሳተፍ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አረጋግጧል።

" በውድድሩ ስለመሳተፋችን ተጠራጥረን አናውቅም "  ያለው ክለቡ በመግለጫው "  አሁንም መሳተፋችንን እንቀጥላለን በውድድሩ በመሳተፋችን እና ዋንጫውን ለደጋፊዎቻችን በማምጣታችንም ኩራት ይሰማናል " ብሏል።

ሪያል ማድሪድ በውድድሩ " መሳተፍ አይፈልግም " የሚል አስተያየት ሰጥተው የነበሩት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በበኩላቸው " ስለ ውድድሩ የሰጠሁት ቃለ ምልልስ በፈለግኩት መልኩ አልተተረጎመልኝም " ሲሉ አስተባብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ!  🤩

⭐️የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!    

💸እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።

አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው -             👉ln.run/k_QQW
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
🔥🔥 ለባልትና ቤቶች 🔥🔥
🫓🫓 ለወፍጮ ቤቶች 🫓🫓

አዲስ እና ዘመናዊ በኖርማል ቆጣሪ የሚሰራ ድንጋይ አልባ ዘመናዊ ማሽን ይዘንልዎ መጣን
ሩዝ፣ሽምብራ፣ገብስ አሳምሮ ይከካል ይፈትጋል ያበጥርራል
በሰአት  4 ኩንታል ይሰራል

ማንኛውም እህል፣ እንዲሁም ዛላ በርበሬን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ይፈጫል

የስፔር ፓርት ችግር እንዳያስቦ
ለበለጠ መረጃ መልእክት ይላኩልን
0951906772
@balagertech
https://www.tg-me.com/balager_technologies
TIKVAH-SPORT
የቫሌንሽያ ደጋፊዎች የእስር ቅጣት ተላለፈባቸው ! ባለፈው አመት ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሽያ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ብራዚላዊው ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ላይ የዘረኝነት ጥቃት ያደረሱ የቫሌንሽያ ደጋፊዎች ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል። የሀገሪቱ ፍርድቤት የዘረኝነት ጥቃቱን ባደረሱ ሶስት የቫሌንሽያ ደጋፊዎች ላይ የስምንት ወራት እስር ቅጣት እንደወሰነባቸው ተነግሯል። በተጨማሪም ለሁለት የውድድር አመታት…
" ፍርዱ ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች ነው " ቪንሰስ

ባለፈው አመት የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ብራዚላዊው ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ጥቃት አድራሾቹ ከተላለፈባቸው የቅጣት ውሳኔ በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ሀሳቡን አጋርቷል።

" ብዙዎች ክሱን እንድተወዉ እንዲሁም የማደርገው ነገር ትርጉም እንደሌለው እና ጨዋታ ላይ እንዳተኩር ነግረውኛል " ያለው ቪንሰስ በመልዕክቱ " እኔ ግን ሁልጊዜ እንደምለው የዘረኝነት ሰለባ አይደለሁም ዘረኞችን የምጋፈጥ እንጂ " ብሏል።

ቪንሰስ ጁኒየር ቀጥሎም " ስፔን ውስጥ የተጀመረው የመጀመሪያ ፍርድ የእኔ ብቻ አይደለም የመላው ጥቁር ህዝቦች ነው " ያለ ሲሆን ላሊጋው እና ሪያል ማድሪድን ለድጋፋቸው አመስግኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሼዝኒ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ነው !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ፖላንዳዊውን የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ ለማስፈረም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የቀድሞ የአርሰናል ግብ ጠባቂ ሼዝኒ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር በቀረበለት በአመት 16 ሚልዮን ፓውንድ የሚያስገኝ የሁለት አመት ኮንትራት መስማማቱ ተነግሯል።

በጁቬንቱስ ቤት የአንድ አመት ኮንትራት የሚቀረው ሼዝኒ በቀጣይ ክለቦቹ ከስምምነት የሚደርሱ ከሆነ ከአውሮፓ ዋንጫው በፊት ዝውውሩን እንደሚያጠናቅቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናይጄሪያ ሽንፈት አስተናግዳለች !

በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ከቤኒን አቻው ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ዘ ሱፐር ኤግል በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ያደረጋቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ ሶስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት አጠናቆ በአንዱ ተሸንፎ በሶስት ነጥቦች እና አንድ የግብ እዳ የምድቡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጌርኖት ሮር የሚመራው የቤኒን ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቦቹን ሰባት በማድረስ ምድቡን በበላይነት መምራት ጀምሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፍራንክ ዲ ዮንግ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነ !

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፍራንክ ዲ ዮንግ ከቀጣዩ የ2024 ጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ተጨዋቹ ከአውሮፓ ዋንጫው ውጪ የሆነው ከዚህ በፊት አጋጥሞት ከነበረው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ ምክንያት እንደሆነ እና በቀጣይ ወደ ባርሴሎና እንደሚመለስ ተነግሯል።

" በአውሮፓ ዋንጫው ባለመሳተፌ በጣም አዝኛለሁ ፣ ከጉዳት ለማገገም ባለፉት ሳምንታት ብዙ ነገር አድርገናል ነገርግን እንዳለመታደል ሆኖ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል።" ሲል ፍራንክ ዲ ዮንግ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
❇️SMART ያልሆኑ TVዎን  SMART ለማረግ  ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው
ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የለያዩ የፊል የኳስ ቻናሎች እላዩ ላይ የተጫነበት በአጭር ጊዜ በሚቋይ ቅናሽ
3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ቶተንሀም ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከፈረንሳዊው አማካይ ታንጎይ ንዶምቤሌ ጋር ያላቸውን ኮንትራት ለማቋረጥ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ያሳለፈው ታንጎይ ንዶምቤሌ በቶተንሀም ቤት የአንድ አመት ውል ይቀረዋል።

የ 27ዓመቱ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ከአምስት አመታት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ55 ሚልዮን ፓውንድ ቶተንሀምን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦማሪ ፎርሰን ዩናይትድን ሊለቅ ነው ! የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ፎርሰን በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል። በቅርቡ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለው ኦማሪ ፎርሰን በነፃ ዝውውር ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ተነግሯል። የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም በርካታ…
ኦማሪ ፎርሰን ወደ ጣልያን ሴርያ ሊያመራ ነው !

የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ፎርሰን ክለቡን በነፃ ዝውውር በመልቀቅ የጣልያኑን ክለብ ሞንዛ ለመቀላቀል መቃረቡ ተገልጿል።

በዚህ ክረምት በማንችስተር ዩናይትድ ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀው ኦማሪ ፎርሰን ከሞንዛ የቀረበለትን የአራት አመት ውል መቀበሉ ተነግሯል።

የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰን ከማንችስተር ዩናይትድ አዲስ ውል ቢቀርበለትም ሳይቀበል መቅረቱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አላማችን ሊጉን እና ሻምፒየንስ ሊጉን ማሸነፍ ነው " ኤምሬ

የአስቶን ቪላው ዋና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር አመት አላማው የሚሳተፍባቸውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች ማሸነፍ መሆኑን ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በንግግራቸውም " አላማችን የፕርሚየር ሊጉን እና የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ወደ አስቶን ቪላ ማምጣት ነው ከባድ ነው ነገርግን እናልማለን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሴስኮን ማን ጥሩ የማስፈረም እድል አለው ?

ስሎቬንያዊውን የሌፕዚግ የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮን ለማስፈረም ታላላቅ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

አሁን ላይ ተጫዋቹን ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት አርሰናል ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ መሆናቸው ይታወቃል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ ከሚገኙ ክለቦች መካከል የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዝውውሩን የማሳካት እድሉ ከሌሎቹ የበለጠ መሆኑ ተነግሯል።

መድፈኞቹ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆናቸው እና በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የተረጋጋ ቡድናቸው ተጫዋቹን ለማግኘት ሊያግዛቸው እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሴስኮን ማን ጥሩ የማስፈረም እድል አለው ? ስሎቬንያዊውን የሌፕዚግ የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮን ለማስፈረም ታላላቅ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። አሁን ላይ ተጫዋቹን ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት አርሰናል ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ መሆናቸው ይታወቃል። ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ ከሚገኙ ክለቦች መካከል የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል…
ቤንጃሚን ሴስኮ ውሉን ለማራዘም ተስማማ !

ስሎቬንያዊው የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮ በታላላቅ ክለቦች ሲፈለግ ቢቆይም በቡንደስሊጋው ክለብ ሌፕዚግ ለመቆየት መወሰኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ የቀረበለትን ከበፊቱ የተሻሻ አዲስ ኮንትራት ለመቀበል ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።

ቤንጃሚን ሴስኮ ከፕርሚየር ሊግ ክለቦች አርሰናል ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለት እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አልቫሬዝ ሪያል ማድሪድን መቀላቀል ይፈልጋል !

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ክለቡን የሚለቅ ከሆነ መቀላቀል የሚፈልገው ሪያል ማድሪድን መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ባለፉት ወራት ከሌላ ክለብ የሚቀርብለትን የዝውውር ጥያቄ ለመቀበል ዝግጁ እንደነበር ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ሪያል ማድሪድ በዚህ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጁሊያን አልቫሬዝን ያስፈርማሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ ተጠቁሟል።

ተጨዋቹ ስለ ወደፊት ቆይታ በሰጠው አስተያየት " አሁን ላይ እረጋጋለሁ ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ደስተኛ ነኝ ነገርግን በቀጣይ የሚፈጠረውን አብረን እንመለከታለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፍራንክ ዲ ዮንግ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነ ! የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፍራንክ ዲ ዮንግ ከቀጣዩ የ2024 ጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ይፋ ተደርጓል። ተጨዋቹ ከአውሮፓ ዋንጫው ውጪ የሆነው ከዚህ በፊት አጋጥሞት ከነበረው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ ምክንያት እንደሆነ እና በቀጣይ ወደ ባርሴሎና እንደሚመለስ ተነግሯል። " በአውሮፓ ዋንጫው ባለመሳተፌ በጣም አዝኛለሁ…
ኔዘርላንድ ሌላኛውን ተጨዋች በጉዳት አጥታለች !

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ኩፕሜነርስ በጉዳት ምክንያት ከቀጣዩ የ2024 ጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ተጨዋቹ ከአውሮፓ ዋንጫው ውጪ የሆነው ከትላንቱ ከአይስላንድ ጨዋታ በፊት በነበረው ዝግጅት ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በቀጣይ የቦርስያ ዶርትመንዱ ተጨዋች ማትሰን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፈረንሳይ ሊግ የቴሌቪዥን መብቱን ለመሸጥ ተቸግሯል !

የፈረንሳይ ሊግ ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን የቴሌቪዥን መብቱን የሚገዛው የጨዋታ አስተላላፊ ተቋም ለማግኘት መቸገሩ ተገልጿል።

ሊጉ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ #አንድ ቢልዮን ዩሮ ለማግኘት እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በግማሽ ወርዶ እስከ 500 ሚልዮን ዩሮ ለማግኘት ማለሙ እየተገለፀ ይገኛል።

የሊጉ ክለቦች ከቴሌቪዥን መብት የሚያገኙትን ክፍያ እስካሁን ባለማወቃቸው የቀጣዩን የውድድር አመት በጀት ለማዘጋጀት እንደተቸገሩ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 02:34:27
Back to Top
HTML Embed Code: