Telegram Web Link
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from WANAW SPORT
❤️ ለቤተሰብዎ ውበት የተዘጋጁ ማልያዎችን እነሆ!

👉🏾 #አሁኑኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሀገራት አዲስ ተጨዋቾችን መጥራት ይችላሉ ?

ሀገራት በቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀሟቸውን የሀያ ስድስት ተጨዋቾች ስብስብ ባሳለፍነው አርብ ለዩኤፋ ማስገባታቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ሀገራት እስከ ውድድሩ መጀመሪያ ጨዋታ ተጨዋቾቻቸው ጉዳት ወይም ህመም ካጋጠማቸው ሌላ ተጨዋች እንዲጠሩ እንደተፈቀደላቸው ተነግሯል።

ይህ የሚሆነው ተጨዋቾቹ በውድድሩ መካፈል እንደማይችሉ ዩኤፋ በሚመድባቸው እንዲሁም በብሔራዊ ቡድኑ ሀኪሞች ከተረጋገጠ እንደሆነ ተገልጿል።

ከእዚህ የትኞቹ ብሔራዊ ቡድኖች ይጠቀማሉ ?

በጉዳት ምክንያት ፍራንክ ዲ ዮንግ እና ኩፕሜነርስን ያጣው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በሌላ ተጨዋች ለመተካት ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በተጨማሪ ሉክ ሾውን ጨምሮ የሌሎች ተጨዋቾቹ የአካል ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚገኘው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከውሳኔው ይጠቀማል ተብሎ ይጠበቃል።

የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ትላንት ምሽት በጉዳት ተቀይሮ የወጣው አጥቂያቸው ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በውድድሩ መድረስ አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ ሌላ ተጨዋች የመጥራት መብት ያገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቡድናችን ባለ ትልቅ ተሰጥኦ ነው " ሮናልዶ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቡድናቸው ስብስብ ትልቅ ተሰጥኦ ባላቸው ተጨዋቾች የተሞላ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" የተጨዋቾች ወርቃማ ትውልድ ለእኔ ዋንጫዎችን ማሸነፍ የሚችል ነው " የሚለው ሮናልዶ ይህ የፖርቹጋል ቡድን ባለ ትልቅ ተሰጥኦ ነው ከአውሮፓ ዋንጫው ጀምሮ ዋንጫዎችን እንደሚያሸንፍ ተስፋ አለኝ ብሏል።

" በስድስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች የተሳተፈ ቀዳሚው ተጨዋች በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል ፣ በእግርኳስ ያሳካሁት አንድ ሌላ ምዕራፍ ነው።"ሮናልዶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ! 🤩

⭐️የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!

💸እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።

አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው - 👉ln.run/k_QQW
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
ላውረንት ኮስሎኒ በሀላፊነት ተሾሟል !

ከአመት በፊት በይፋ ራሱን ከፕሮፌሽናል እግርኳስ ያገለለው የቀድሞ ፈረንሳዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ላውረንት ኮስሎኒ በአዲስ ሀላፊነት መሾሙ ተገልጿል።

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተከላካይ ላውረንት ኮስሎኒ የፈረንሳዩ ክለብ ሎርየንት ስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን በሀላፊነት መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 38ዓመቱ ላውረንት ኮስሎኒ ከዚህ በፊት የሎርየንት ታዳጊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ ይገኝ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው ኒኮሎ ባሬላን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 27ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኒኮሎ ባሬላ በኢንተር ሚላን ቤት ለተጨማሪ አምስት አመታት መቆየት የሚያስችለውን ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ጣልያናዊው ተጨዋች ኒኮሎ ባሬላ በአዲሱ ኮንትራት በአመት ሰባት ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ታሪክ ፅፏል !

ፖርቹጋል ከአየርላንድ ጋር ያደረገችውን የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ግቦችን እንዲሁም ጇ ፊሊክስ ቀሪውን ጎል አስቆጥረዋል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተከታታይ ለሀያ አንድ አመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ላለፉት ሀያ አንድ አመታት በየአመቱ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን ግቦች አንድ መቶ ሰላሳ ማድረስ ችሏል።

ክርስትያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር አመት ባደረጋቸው ሀምሳ ስምንት ጨዋታዎች ሀምሳ ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት ግምገማ ያደርጋል ! የኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳካው ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት የድህረ የውድድር ዘመን ግምገማ ለማድረግ እቅድ መያዛቸው ተገልጿል። ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የወደፊት ቆይታ ዙሪያ የመጨረሻ ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት አሰልጣኙ የሰሩትን ስራ ለመገምገም ማሰቡ ተነግሯል። አሰልጣኙ ከኤፌ ካፕ ዋንጫ ድላቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት ጨዋታው የመጨረሻቸው…
ኤሪክ ቴንሀግ በዩናይትድ ቤት ይቆያሉ !

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ካደረገው የድህረ ውድድር አመት ግምገማ በኋላ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በክለቡ እንዲቀጥሉ ከውሳኔ መድረሱ ተዘግቧል።

በሚቀጥለው አመት ውላቸው የሚጠናቀቀው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው የክለቡን ውሳኔ መቀበላቸው እና በሀላፊነት ለመቀጠል መስማማታቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም በዛሬው ዕለት ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
❇️SMART ያልሆኑ TVዎን  SMART ለማረግ  ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው
ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የለያዩ የፊል የኳስ ቻናሎች እላዩ ላይ የተጫነበት በአጭር ጊዜ በሚቋይ ቅናሽ
3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሊቨርፑል ምን አይነት ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል ?

አሰልጣኝ አርኔ ስሎትን በሀላፊነት የሾመው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ቅድሚያ የሚሰጠው ለመሐል ተከላካይ መሆኑ ተገልጿል።

ሊቨርፑሎች በመቀጠልም የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ጥሩ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች የሚያገኙ ከሆነ ለማስፈረም እንደሚሰሩ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ሊቨርፑል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ተጨማሪ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ማቀዳቸው ሲገለፅ ከአሜሪካ ጉዞ በኋላ አንፊልድ ላይ ለመጫወት ማሰባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በእግርኳስ ብዙ አመት አይቀረኝም " ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ብዙ አመታት ስለማይቀሩት አሁን ላይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች መደሰት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ሮናልዶ በንግግሩም " በእግርኳስ ውስጥ ብዙ አመታት አይቀሩኝም ስለዚህ አሁን መደሰት አለብኝ ፣ ለእግርኳስ ልዩ ፍቅር አለኝ ሁሉም ጨዋታዎች ልዩ ናቸው።

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፖርቹጋልን መወከል የተለየ ኮራት ይሰማሃል በሀያ እድሜዎች ላይ እንዳለሁ ሁሉ አሁንም ህልሜ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በእንግሊዝ ጨዋታ አነስተኛ አልኮል ያለው መጠጥ ይቀርባል !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው መጀመሪያ እሁድ ከሰርቢያ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በስታዲየሙ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ እንደሚቀርብላቸው ተገልጿል።

በውድድሩ ከሚደረጉት ጨዋታዎች ሁሉ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ የሚቀርብበት ብቸኛው ጨዋታ እንደሚሆንም ተነግሯል።

ይህ የሆነው 40,000 ገደማ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ይታደማሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጨዋታ ከተቃራኒ ደጋፊዎች ጋር አለመግባባት ይፈጠራል በሚል ፍራቻ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በውድድሩ አሻራዬን ማስቀመጥ እፈልጋለሁ " ምባፔ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ ቡድናቸው በበቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለመፃፍ ጀርመን መድረሱን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" በአውሮፓ ዋንጫው አሻራዬን ሜዳ ላይ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ " የሚለው ኪሊያን ምባፔ ታሪክ ለመፃፍ ጀርመን ደርሰናል ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ለውድድሩ ዝግጁ ነን በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
✈️ አውሮፓ እንሂድ

🏆 የአውሮፓ ታላላቅ ተጫዋቾች ለሃገራችው ዋንጫ ለማሸነፍ ጉዞ ወደ ጀርመን ጀምረዋል!

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በወር ከ350 ብር ጀምሮ በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3XdLqsP

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
📯 አስቀድመው ተዘጋጅተው የሚወስዷቸው ማልያዎች ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይዘዙን፣ አማራጩን ይጠቀሙ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ፈርናንዶ ሳንቶስ በሀላፊነት ተሾመዋል !

ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ የ አዘርባጃን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን በሀላፊነት መሾማቸው ይፋ ተደርጓል።

የ 69ዓመቱ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በቅርቡ ከቱርኩ ክለብ ቤሺክታሽ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸው አይዘነጋም።

ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው መነሳት በኋላ የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን እና ቤሺክታሽ አሰልጣኝ በመሆን ተሾመው የነበሩት አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በሀላፊነት ብዙም ሳይቆዩ ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ዋንጫውን መክፈቻ ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን አርብ የሚደረገውን ተጠባቂ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር መክፈቻ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በጀርመን እና ስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ቱርፒን በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል።

የመክፈቻ ጨዋታው አርብ ምሽት 4:00 ሰዓት በባየር ሙኒኩ ፉባል አሬና ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ወጣት ተጨዋች ሊያስፈርም ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወጣቱን እንግሊዛዊ የፊት መስመር አጥቂ ሪያን ማክአይዶን ከቼልሲ ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው እና ዝውውሩን እያጠናቀቁ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የ 16ዓመቱ አጥቂ ሪያን ማክአይዶ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ቼልሲን ይለቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ በእንግሊዝ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 04:39:29
Back to Top
HTML Embed Code: