Telegram Web Link
" በዚህ እድሜዬ ስለ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ " ዴብሮይን

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ከሳውዲ አረቢያ የሚቀርቡለትን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ጥያቄዎች ለመመልከት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በማንችስተር ሲቲ ቤት የአንድ አመት ውል የቀረው ኬቨን ዴብሮይን " በዚህ እድሜዬ ለሁሉም ጥያቄዎች ክፍት መሆን አለብኝ በዚህ የእግርኳስ የመጨረሻ ጊዜ ላይ ስለ ትልቅ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ።"በማለት ተናግሯል።

ቤልጂየማዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በአስተያየቱ አሁን ያለበት የእግርኳስ መጨረሻ እድሜ ብዙ ገንዘብ ስለማግኘት የማሰቢያ መሆኑን ጠቁሟል።

" ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሁለት አመታት ብጫወት የማይታመን ገንዘብ ማግኘት እችላለሁ ምናልባት ለአስራ አምስት አመታት ስጫወት ያገኘሁት ያንን ላያክል ይችላል።" ዴብሮይን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው 10 ቀናት በቻ ቀሩት!

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር!  ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ካሴሚሮ የክለብ ባለቤት መሆኑ ተገለፀ !

ብራዚላዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካሴሚሮ የስፔን ሶስተኛ ሊግ ተወዳዳሪ የሆነውን ማርቤላ እግርኳስ ክለብ ከፍተኛ ድርሻ መግዛቱ ተገልጿል።

ካሴሚሮ ባደረገው ንግግርም " ማርቤላን መቀላቀሌ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው ፣ በቀጣይ በጋራ ክለቡን ትልቅ ቦታ ለማድረስ እንደምናልም ጥርጥር የለውም።"ሲል ተደምጧል።

በቀጣይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሊለያይ እንደሚችል እየተነገረ የሚገኘው ካሴሚሮ በአዲሱ ክለቡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል እንደሚሆን ይፋ ሆኗል።

ክለቡ ከቀናት በፊት ከታችኛው እርከን ወደ ስፔን ሶስተኛ ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አምራባት በዩናይትድ መቆየት ይፈልጋል "

ሞሮኳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሶፍያን አምራባት በቀጣይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት መቆየት እንደሚፈልግ የፊዮሬንቲና ዳይሬክተር ፕሬድ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በንግግራቸውም " ሶፍያን አምራባት ፕርሚየር ሊግ ውስጥ መቆየት ይፈልጋል ማንችስተር ዩናይትድ ምንም ነገር አልነገሩንም ከፊዮሬንቲና ጋር እንዲቆይ እንፈልጋለን ነገርግን እሱ ሌላ አቅም ያለው ይመስለኛል።"ብለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሶፍያን አምራባትን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ከፊዮሬንቲና ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በዚህ ክረምት የሲቲ የዝውውር ሁኔታ ምን ይመስላል ?

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የኬቨን ዴብሮይን እና በርናርዶ ሲልቫ ቆይታ አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ በዝውውር መስኮቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች በቅድሚያ እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲዎች በተጨማሪም #የቀኝ የፊት መስመር ተጨዋች ለመመልከት በዝውውር መስኮቱ ለመግባት በአጀንዳነት መያዛቸውን ታማኝ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ሲቲ በዝርዝራቸው ውስጥ የያዟቸው አማካዮች የውል ማፍረሻው £100 ሚልዮን የሆነው የኒውካስል ተጨዋች ብሩኖ ጉማሬስ ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ፓኩዌታ እና ጆሹዋ ኪሚች መሆናቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲ የግብ ጠባቂዎችን እንዲሁም ካይል ዎከርን የወደፊት ሁኔታ ተመልክተው በቦታው ተጨዋቾች ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ተዘግቧል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ካይል ዎከር ክለቡን የሚለቅ ከሆነ ማንችስተር ሲቲ የቀድሞ ተጨዋቻቸው ጄርሚ ፍሪምፖንግን ከባየር ሌቨርኩሰን ለማስፈረም እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከአለም ዋንጫ አውሮፓ ዋንጫ ከባድ ነው " ምባፔ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና አዲሱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ አስቸጋሪ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

አንድ ጊዜ የአለም ዋንጫን ያሳካው ኪሊያን ምባፔ ሲናገርም " ከአለም ዋንጫ ውድድር ይልቅ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ እጅግ አስቸጋሪ ነው።"በማለት ተናግሯል።

ስለ ሪያል ማድሪድ ፊርማው ያነሳው ኪሊያን ምባፔ " በጣም ደስተኛ ነኝ መመልከት ትችላላችሁ ለህልሜ ክለብ ልጫወት ነው ቢያንስ አምስት አመት ማድሪድ ውስጥ እሆናለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምባፔ ማድሪድ መግባቱ ጥሩ ዜና አይደለም " ላፖርታ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ቡድናቸው እያደረገ ባለው ሂደት እና የክለቡ አካዳሚ ተጨዋቾች እምነት እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

በአንድ የመገናኛ ብዙሀን ቃለ ምልልስ ያደረጉት የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በቆይታቸውም የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ምን አሉ ?

- " በሚቀጥለው የውድድር አመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ ባሉን ተጨዋቾች ሊጉንም ማሳካት እንችላለን።

- እኛ ከአካዳሚያችን በሚወጡ ተጨዋቾች እናምናለን ባለን ነገር ደስተኛ ነን ፣ ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን ማስፈረሙ እንደ ባርሴሎና ደጋፊ ጥሩ ዜና አይደለም።

- ዣቪን ማሰናበት ከወሰንኳቸው ውሳኔዎች ሁሉ በጣም ከባዱ ነበር ሜሲ ፣ ቡስኬት እና ጆርዲ አልባ ላይም ተፈጥሯል የክለቡን ጥቅም ግዴታ ማስቀደም አለብኝ።

- ጇ ፊሊክስ እና እና ካንሴሎ ለተጨማሪ የውድድር አመት በባርሴሎና እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን።

- በእኛ በኩል ለዳኞች ምንም አይነት ክፍያ አልከፈልንም ሪያል ማድሪድ በዳኞች የሚወደደው ክለብ ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቨርቹዋል ጨዋታዎች የሚጨበጡ ሽልማቶች, ዳጎስ ያሉ የገንዘብ ሽልማቶችን በቤቲካ ቨርቹዋል!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
አስቶን ቪላ ከቼልሲ ጋር ንግግር ጀመረ !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የሰማያዊዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮነር ጋላገር ለማስፈረም ከቼልሲ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምት የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን በቋሚ ዝውውር ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የ 24ዓመቱ ተጨዋች ኮነር ጋላገር አድናቂ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ሊለያይ ይችላል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጥሩ ሒሳብ የሚቀርብለት ከሆነ ፖላንዳዊውን የመስመር ተጨዋች ያኩብ ኪውዮርን ሊሸጥ እንደሚችል ተገልጿል።

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን የ 24ዓመቱ ፖላንዳዊ የመስመር ተጨዋች ያኩብ ኪውዮር ፈላጊ መሆናቸው ተዘግቧል።

ፖላንዳዊው ተጨዋች ያኩብ ኪውዮር ከአመት በፊት ከጣልያኑ ክለብ ስፔዚያ አርሰናልን መቀላቀሉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል በቀጣይ ምን ማስፈረም ይፈልጋል ? የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር አጥቂ ለማስፈረም በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም መድፈኞቹ የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ሲዘገብ ሶስተኛ ግብ ጠባቂም ለማስፈረም ከሚመለከቱት የሜዳ ክፍል አንዱ መሆኑ ተነግሯል። አርሰናል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመለከተው…
የአርሰናል ባለቤቶች ለዝውውር ትልቅ ገንዘብ ያቀርባሉ !

የተጠናቀቀው የ2023/24 የውድድር ዘመን ለሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ሌላኛው አትራፊ አመት እንደነበር ተገልጿል።

መድፈኞቹ በውድድር አመቱ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሩብ ፍፃሜ መድረሳቸውም አይዘነጋም።

አርሰናሎች በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ብቻ ከ90 ሚልዮን ዩሮ በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የመድፈኞቹ ባለቤቶች በዚህ ክረምት ቡድኑን ለማጠናከር ትልቅ የዝውውር ገንዘብ ያዘጋጃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ከፉልሀም በነፃ ዝውውር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል። ኒውካስል ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ መቃረባቸው ተዘግቧል። ቼልሲን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቶሲን አዳራብዮ የክለቡ…
ፉልሀም ከተጨዋቹ ጋር መለያየቱን ይፋ አደረገ !

ፉልሀም በክለቡ ያለው ኮንትራቱ ከተጠናቀቀው እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ጋር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ቼልሲን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጨዋቹ በትላንትናው ዕለት የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ቼልሲ ቶሲን አዳራብዮን በነፃ ዝውውር የክለቡ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤንጃሚን ሴስኮ ወዴት ያመራ ይሆን ?

በታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘው ስሎቬንያዊው የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮ በሚቀጥሉት ቀናት ቀጣይ ማረፊያውን እንደሚመርጥ ተገልጿል።

የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ ተጨዋቹን በክለቡ ለማቆየት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አዲስ ኮንትራት እንዳቀረቡለት ተነግሯል።

በተጨማሪም የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ከታላላቅ ክለቦች ጋር በመፎካከር አመታዊ 30 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ቢያቀርቡለትም ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

አርሰናል ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ቤንጃሚን ሴስኮን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ራሽፎርድን አርሰናል ዉስጥ ብመለከተው ደስ ይለኛል " ሳኛ

የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ባካሪ ሳኛ እንግሊዛዊውን የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በአርሰናል ማልያ መመልከት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" ራሽፎርድን አርሰናል ዉስጥ ብመለከተው ደስ ይለኛል " የሚለው ባካሪ ሳኛ " የአርሰናል የፊት መስመር ማርከስ ራሽፎርድ ቢጨመርለት ለተጋጣሚው እችግ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ሆኖ ይቀርባል።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን ሊረከቡ ነው ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከቶተንሀም ጋር ከተለያዩ በኋላ ለቤተሰባቸው ቅርብ ለመሆን የጣልያን ክለብ የማሰልጠን…
ናፖሊ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን በሀላፊነት ሾመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይፋ ሆኗል።

" የናፖሊ አሰልጣኝ በመሆኔ ደስታ ተሰምቶኛል ክለቡን ለማሳደግ እና ቡድኑን ለማሻሻል ያለኝን ሁሉ እንደምሰጥ ቃል እገባለሁ።"ሲሉ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቀጣዩ የሲቲ አላማ ለአምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ነው "

የማንችስተር ሲቲው ሊቀመንበር ኸልዱን አል ሙባረክ በክለቡ የውድድር አመት ሁኔታ ዙሪያ በክለቡ ሚዲያ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

ሊቀመንበሩ በቃለ ምልልሳቸው የማንችስተር ሲቲን ያለፉት አመታት ስኬትን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ከእነዚህም መካከል :-

- " የፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን እንደምናሸንፍ ያወቅኩት ነሀሴ ወር ላይ ከአርሰናል ጋር ኤምሬትስ ስታዲየም በተሸነፍንበት ጨዋታ ነው።

- በቀጣይ የውድድር አመት የማንችስተር ሲቲ አላማ የሚሆነው የፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ነው።

- በእንግሊዝ እግርኳስ ታሪክ ባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ሊጉን ለተከታታይ አራት ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ክለብ የለም ይህንን ስታውቅ ማንችስተር ሲቲን ማድነቅ ትጀምራለህ።

- ስለ ፔፕ ጋርዲዮላ ቆይታ በጋራ የምንወስነው ውሳኔ ነው የሚሆነው ለእኛም ለጋርዲዮላም የሚስማማ ውሳኔ እንወስናለን።

- የቀረቡብን 115 ክሶች የሚያበሳጩ ናቸው ነገርግን ሰዎች በክስ ሂደቱ ሳይሆን ከመጨረሻው ውሳኔ በኋላ በእኛ ላይ እንዲፈርዱ እንፈልጋለን የመጨረሻው ፍርድ እስከሚታወቅ ረጅም ጊዜ ይወስዳል።

- በፕርሚየር ሊጉ ባለፉት አመታት በእኛ ደረጃ የሚገኝ ቡድን ፈልገህ ማግኘት አትችልም።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 #ሁለት ቀናት ብቻ ቀሩት

⚽️ ለእግር ኳስ ቡድንዎ ልዩ የሽያጭ ብስራት ⚽️

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ ዛሬውኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ኦማሪ ፎርሰን ዩናይትድን ሊለቅ ነው ! የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ፎርሰን በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል። በቅርቡ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለው ኦማሪ ፎርሰን በነፃ ዝውውር ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ተነግሯል። የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም በርካታ…
ጆኒ ኢቫንስ በዩናይትድ ሊቆይ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ንግግር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በተመሳሳይ ውሉን ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

የክለቡ አካዳሚ ውጤት የሆነው ብራንደን ዊሊያምስ በበኩሉ ከክለቡ ጋር ከአመታት በኋላ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል።

ማንችስተር ዩናይትድን ሊለቅ እንደሚችል ሲነገር የቆየው የፊት መስመር ተጨዋቹ ኦማሪ ፎርሰን በበኩሉ አዲስ ኮንትራት እንደቀረበለት ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰን የቀረበለትን ኮንትራት ውድቅ በማድረግ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 15:47:53
Back to Top
HTML Embed Code: