Telegram Web Link
“ ይህ የሪያል ማድሪድ ታሪክ ነው “

አስራ አምስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ድላቸውን የተጎናፀፉት ሪያል ማድሪድ የቡድን አባላት ከድሉ በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከተሰጡ አስተያየቶች መካከልም ፡-

- “ አስራ ስድስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስለማሸነፍ ከአሁኑ እያሰብን እንገኛለን “ ናቾ

- “ ይህ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሪያል ማድሪድ ታሪክ ነው “ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ

- “ እድለኛ ከሆንኩኝ ከሪያል ማድሪድ ጋር ስድስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን አነሳለሁ “ ካማቪንጋ

- “ ይህ ቡድን ቤተሰብ ነው ፣ የስኬታችን ዋነኛ ሚስጥር ይህ ነው። አስራ ስድስተኛው የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ቀጣይ አመት ማሸነፍ እንፈልጋለን። “ ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ

- “ ወደ ሪያል ማድሪድ ስመጣ አንድ ህልም ነበረኝ ቢያንስ አንድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ ነበር።” ሉካ ሞድሪች

- “ ይህ ቀን በህይወቴ ከተደሰትኩባቸው ቀናቶች መካከል አንዱ ነው ፣ ህልሜ እውን ሆኗል “ ሲል አምበሉ ናቾ ተናግሯል።

ቶኒ ክሩስ ፣ ሉካ ሞድሪች ፣ ናቾ እና ዳኒ ካርቫሀል በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ስድስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 🇪🇹

ዋናው ስፖርት በድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከግንቦት 25 ጀምሮ የሚካሄደው የድሬዳዋ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ውድድር ተሳታፊ ክለቦች የስፖርት ትጥቅ አጋር በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

⚽️ #ውድድር ካለ #ዋናው አለ! ⚽️

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የሆሴሉ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ?

የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት የት እንደሚሆን እስከአሁን አለማወቁን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

በቀጣይ በወደፊቱ ቆይታው ዙሪያ ለንግግር እንደሚቀመጥ ባለፈው ክረምት በውሰት ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ሆሴሉ ተናግሯል።

ሪያል ማድሪዶች ተጫዋቹን በቋሚ ዝውውር ለማስፈረም 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" 150 ሚልዮን ዩሮ ከቀረበልን ራሴ እልከዋለሁ "

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ፕሬዝዳንት ፓውሎ ስካሮኒ ለፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራፋኤል ሊያኦ ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ከቀረበላቸው ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ፓውሎ ስካሮኒ በንግግራቸውም " ለራፋኤል ሊያኦ 150 ሚልዮን ዩሮ የሚያቀርቡልን ከሆነ እኔው ራሴ ነኝ አዘጋጅቼ ወደ እነሱ የምልክላቸው " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የተጨዋቾቹን ውል ሊያራዝም ነው ! የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ እድሚያቸው የገፋ ታሪካዊ ተጨዋቾቻቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። ሎስ ብላንኮዎቹ ሁለቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋቾች ሉካ ሞድሪች እና ቶኒ ክሩስ በሚቀጥለው የውድድር አመት በቡድናቸው ውስጥ ለማቆየት ማሰባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ካርሎሎ አንቾሎቲ ተጨዋቾቹ በስብሰባቸው ውስጥ እንዲቆይ…
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተቃርቧል !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ የክሮሽያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ኮንትራት ለማራዘም መስማማታቸው ተገልጿል።

የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል።

ሉካ ሞድሪች ከምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ድል በኋላ አስተያየቱን ሲሰጥ በሪያል ማድሪድ ቤት ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ ገልፆ ነበር።

ተጨዋቹ ትልቅ ገንዘብ የሚያስገኙ የዝውውር ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም ውድቅ በማድሪድ በሪያል ማድሪድ ቤት ለመቆየት መወሰኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🥁ተጀመረ ተጀመረ ተተተጀመረ!🔥
በነጻ ውርርዶች ደንበኞችን ሊያንበሸብሽ የአቪዬተር ሻሞ ተጀመረ!
በየቀኑ እስከ 4 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው ሻሞዎች እርስዎን ይጠብቃሉ!
በውርርዶች እያሸነፉ ከሻሞው የድርሻዎን ይቅለቡ!
አሁን ነው መብረር!
የእርስዎን የውርርድ ሻሞዎች እዚህ ጋር ይቅለቡ!
👉 https://ln.run/As9wm
የሻሞውን ህግ እና ደንቦች ለማንበብ፣
ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👉 ln.run/sGGe-
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ቱርክ ሊያመሩ ነው ! ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የቱርክ ሱፐር ሊጉን ክለብ ፌነርባቼ በሀላፊነት ለመረከብ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ስማቸው ከሳውዲ አረቢያ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፌነርባቼን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከወራት በፊት ከሴርያው ክለብ ሮማ ከተሰናበቱ ወዲህ…
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ አቀባበል ይደረግላቸዋል !

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የቱርክ ሱፐር ሊጉን ክለብ ፌነርባቼ ለሚቀጥሉት ሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን አኑረዋል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ዛሬ ከሰዓት በፌነርባቼ ስታዲየም ሳራኮግሉ የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት ይፋዊ የፊርማ ስነስርዓት እንደተዘጋጀላቸው ተገልጿል።

ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ኢስታንቡል በማምራት ላይ መሆናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፉልሀም ስሚዝ ሮውን ማስፈረም ይፈልጋል !

ፉልሀም እንግሊዛዊውን የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ በቀጣይ የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ከሚመለከቷቸው ተጨዋቾች ቀዳሚው ኤሚል ስሚዝ ሮው እንደሚሆን ተዘግቧል።

ፉልሀም ተጨዋቹን ለማስፈረም የዝውውር መስኮቱ ሲከፍት ጥያቂያቸውን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ ኮንትራት ሊያራዝሙ መሆኑ ተገልጿል።

የ 32ዓመቱ ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል።

ሉካስ ቫስኩዌስ በዚህ አመት ለሪያል ማድሪድ በሰላሳ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን የላሊጋ ፣ ሻምፒየንስ ሊግ እና ስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር ይሳተፋል ? የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ስብስቡ ውስጥ ማካተት እንደሚፈልግ ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትዶች በበኩላቸው እስካሁን አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር እንዲሳተፍ መፍቀድ አለመፍቀዳቸውን አለማሳወቃቸው ተነግሯል። @tikvahethsport    …
አሌሀንድሮ ጋርናቾ ወደ ኦሎምፒክ አያመራም !

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሀገሩን ለመወከል እንደማያመራ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በቀጣዩ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እንዲሳተፍ ፍቃድ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ተነግሯል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ በቀጣይ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን በኮፓ አሜሪካ ውድድር የሚወክል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጉንዶጋን ቡድኑን በአምበልነት ይመራል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢልካይ ጉንዶጋን በቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት እንዲመራ መመረጡ ታውቋል።

በተጨማሪም ጆሹዋ ኪሚች እና ቶማስ ሙለር ሁለተኛ እና ሶስተኛ አምበል በመሆን በአውሮፓ ዋንጫው የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን እንደሚመሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ የተጨዋቾቿን ግልጋሎት አታገኝም !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት በሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ የወሳኝ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል።

ለአውሮፓ ዋንጫ ዝግጅት ላይ የምትገኘው እንግሊዝ ነገ ምሽት ከቦስኒያ እና ሄርዜጎቪና ጋር የወዳጅነት ጨዋታዋን የምታደርግ ሲሆን ቡካዩ ሳካ እና ጆን ስቶንስ ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።

ቡካዩ ሳካ በጡንቻ ጉዳት እንዲሁም ጆን ስቶንስ ዘግይቶ ቡድኑን በመቀላቀሉ ምክንያት ጨዋታው እንደሚያልፋቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የቱርክ እግርኳስ እንዲሻሻል መርዳት እፈልጋለሁ " ሞሪንሆ

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በዛሬው ዕለት የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ዋና አሰልጣኝ በመሆን በይፋ በሀላፊነት ተሾመዋል።

የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት በስታዲየሙ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ " እግርኳስ ፍቅር ነው ለእሱ ደግም ከዚህ የተሻለ ቦታ ፈፅሞ አይገኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

የቱርክ እግርኳስ እንዲሻሻል ማገዝ እንደሚፈልጉ ለደጋፊው ባደረጉት ንግግር የገለፁት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ " ነገርግን ቅድሚያ የምሰጠው ለፌነርባቼ ነው አሁን ህልማችሁ ህልሜ ሆኗል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Germany - Ukraine
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
2024/10/03 23:20:27
Back to Top
HTML Embed Code: