Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ በሜዳው የፍፃሜ ጨዋታውን ያስመለክታል ! ሪያል ማድሪድ ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ለንደን ተጉዘው መመልከት ላልቻሉ ደጋፊዎች በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እንዲመለከቱ ማዘጋጀቱ ተገልጿል። ክለቡ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ሜዳ ላይ ግዙፍ የጨዋታ መመልከቻ ስክሪኖችን በማዘጋጀት ለደጋፊዎቹ ክፍት እንደሚያደርግ አሳውቋል። ጨዋታውን በስታዲየሙ ተገኝቶ…
የበርናቦ ስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ ጨመረ !

ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም በስክሪን ለመመልከት የትኬት ዋጋ መናሩ ተገልጿል።

የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ለመታደም የመግቢያ ትኬቶች በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር 275 ዩሮ በመሸጥ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ጨዋታውን ለመመልከት እስከ 80,000 የሚደርሱ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ሊገኙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የእኛም ተጨዋቾች ፕሮፌሽናል ናቸው " - ገብረ መድህን ኃይሌ

👉🏻 “ አንድ ተጫዋች ቀንሰን ሰኞ እንጓዛለን “

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከሜዳው ውጪ በሚያደርጋቸው የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች ዙሪያ የቡድኑ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ለማጣሪያ ጨዋታዎቹ ጥሪ ቀርቦላቸው በዝግጅት ላይ ከሚገኙ ተጨዋቾች መካከል ብሔራዊ ቡድኑ #አንድ ተጨዋች በመቀነስ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና አሰልጣኙ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ በቆይታቸው ወቅት ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል :-

- " የተጋጣሚያችን ተጨዋቾች በታላላቅ ሊጎች መጫወታቸው ጫና አይፈጥርብንም ይህን መላመድ ይገባናል የእኛም ተጫዋቾች ፕሮፌሽናል ናቸው።

- በዝግጅታችን ወቅት የአሸናፊነት ስነልቦና እና የማዋሀድ ስራ ላይ ስንሰራ ቆይተናል።

- መድህን አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው በተከታታይ እያሸነፈ ነው ለብሔራዊ ቡድኑ በራስ መተማመን ይጨምራል ፣ የአሸናፊነት መንፈስ ተፅዕኖ በተጨዋች ብቻ ሳይሆን በአሰልጣኝም ይኖራል።

- ኢትዮጵያ መድህን መሰረታዊ ለውጥ ነው ያመጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቀጣይ መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለሁ።

- ሱራፌል ዳኛቸው  ያለበትን ወቅታዊ አቋም ማወቅ ስላልቻለን በዚህ ጥሪ ልንዘለው ችለናል።

- አቤል ያለው ግብፅ ነው የሚጫወተው የተጫወተባቸው ጊዜያት ብዙ አልነበሩም የተጫወተው ጥቂት ደቂቃ ነው አለመጫወቱ ራሱ ተፅዕኖ አለው።"ብለዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ስፍራው መቼ ይጓዛል ?

ብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን ሰኞ የማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ወደሚያደርግበት ጊኒ ቢሳው እንደሚያቀኑ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ከፉልሀም በነፃ ዝውውር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ኒውካስል ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ መቃረባቸው ተዘግቧል።

ቼልሲን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቶሲን አዳራብዮ የክለቡ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው እንደሚሆን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ ተጨዋቾች ስንት ትኬቶች ያገኛሉ ?

የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ለምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ሁለት ነፃ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም #ሰላሳ በገንዘብ የሚቀርቡ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች አጠቃላይ ሰላሳ ሁለት ትኬቶች ለተጨዋቾቹ እንደሚቀርብላቸው ተነግሯል።

እያንዳንዱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ለስታዲየም መግቢያ ትኬቶች 12,300 ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ሲገለፅ ሁሉንም ትኬቶች ለቤተሰባቸው እና ጓደኞቻቸው መስጠታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዛሬ ምሽት የሚደረገውን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ግዮን ሆቴል ከልዩ ምግብ እና መጦጦች እንዲሁም በዓለምአቀፍ ዲጄ ከታጀበ ሙዚቃ ጋር በ360 ዲግሪ ስክሪኖች ጨዋታውን ሊያስመለክታችሁ እናንተን  እየጠበቀ ይገኛል!።

ይህንን ድንቅ ጨዋታ ከሄኒከን ጋር እየተዝናን አብረን እንመልከት!
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Dortmund - Real Madrid
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
TIKVAH-SPORT
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳኩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ኮቢ ማይኖ እና ዲያጎ ዳሎት የአመቱ የመጨረሻ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport    …
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች  ኮቢ ማይኖ የአመቱ የመጨረሻ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ጥሩ የውድድር አመት ያሳለፈው ኮቢ ማይኖ በአመቱ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የማንችስተር ዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLFinal

የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ እና ቦርስያ ዶርትመንድ መካከል ምሽት 4:00 ሰዓት በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

ጨዋታውን የተመለከቱ መረጃዎች ምን ይመስላሉ ?

- ጨዋታውን ስሎቬኒያዊው የ 42ዓመት ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

- ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አሜሪካዊው አቀንቃኝ ሊኒ ክራቪትዝ በዌምብሌይ ስታዲየም ምሽቱን የሚያደምቅ ይሆናል።

- አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የጨዋታውን ኮከብ ተጨዋች ይመርጣሉ።

- 86,000 ተመልካቾች በዌምብሌይ ስታዲየም እንደሚገኙ ሲጠበቅ ሁለቱ ክለቦች እያንዳንዳቸው ሀያ አምስት ሺህ ትኬቶች ተሰጥቷቸዋል።

- በጨዋታው ሪያል ማድሪድ ነጭ ማልያቸውን ለብሰው ወደ ሜዳ ሲገቡ ቦርስያ ዶርትመንድ በበኩላቸው ቢጫ መለያቸውን ይለብሳሉ።

- የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በጨዋታው " እስከመጨረሻው ቡድኑን እናምናለን " የሚል የድጋፍ ፅሁፍ ያስመለክታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- ዋንጫውን የሚያሸንፈው ክለብ 20 ሚልዮን ዩሮ የሚያገኝ ሲሆን ሁለተኛ ይዞ የሚያጠናቅቀው ክለብ 15.5 ሚልዮን ዩሮ የበረከትለታል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የርገን ክሎፕ ዌምብሌይ ይገኛሉ !

ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የቀድሞ ክለባቸው ቦርስያ ዶርትመንድ ዛሬ ምሽት ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርገውን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ እንዲታደሙ እንደጋበዛቸው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ዛሬ ምሽት የፍፃሜ ጨዋታውን ለመመልከት ዌምብሌይ ስታዲየም እንደሚገኙ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እ.ኤ.አ 2013 ዶርትመንድ ለመጨረሻ ጊዜ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰበትን ጨዋታ በአሰልጣኝነት መምራታቸው አይዘነጋም።

በወቅቱ በተመሳሳይ በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ባየር ሙኒክ ሻምፒዮን እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የመጣነው ማድሪድ ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት አይደለም  " ቴርዚች

የቦርስያ ዶርትመንዱ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቡድናቸው በምሽቱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ ለመፎካከር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

" በከፍተኛ ደረጃ ለመፎካከር ዝግጁ ነን " ያሉት አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች እዚህ ያለነው ሪያል ማድሪድ ተጨማሪ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሲያሸንፍ ለመመልከት አይደለም " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 በፍፃሜው #ይገምቱ#ይሸለሙ! 🎁

🏆 በዛሬው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ማን አሸንፎ ዋንጫውን ያነሳ ይሆን?

🇩🇪 የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ወይስ የስፔኑ ሪያል ማድሪድ 🇪🇸

💬 ግምትዎን በቲክቶክ ገፃችን (https://vm.tiktok.com/ZMjJy6QCA/) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የዋንጫውን አሸናፊ ክለብ እና ውጤት እስከ ግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #3 ተከታታዮቻችን የዋናውን የጂም ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 ሁሉንም የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ለተጨዋቾች ክፍያ መብዛት ተጠያቂ አይደለሁም " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለቡ ለተጨዋቾች ለሚያወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ተጠያቂ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቾች ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣ ነው ተብሎ የሚቀርበው ትችት " ትክክል ነው ገንዘቡ ከፍተኛ ነው " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ ነገርግን ተጠያቂው " እኔ አይደለሁም " ሲሉ አስረድተዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቀጥለውም ወደ ክለቡ ለመግባት ተቃርበው የነበሩ ትልልቅ ተጨዋቾችን ጨምሮ ከተጨዋቾች ጋር ድርድር ያደረገው ክለቡ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ዶርትመንድ ከ ሪያል ማድሪድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TkvahGoal

የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርጉት ዶርትመንድ ደጋፊዎች ወደ ዌምብሌይ ስታዲየም በማምራት ላይ ናቸው።

በስታዲየሙ አካባቢ ያለውን የደጋፊዎች ድባብ በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ቱርክ ሊያመሩ ነው ! ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የቱርክ ሱፐር ሊጉን ክለብ ፌነርባቼ በሀላፊነት ለመረከብ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ስማቸው ከሳውዲ አረቢያ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፌነርባቼን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከወራት በፊት ከሴርያው ክለብ ሮማ ከተሰናበቱ ወዲህ…
" ወደ ፌነርባቼ መሄድ እፈልጋለሁ " ጆዜ ሞሪንሆ

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በቀጣይ ወደ ቱርክ ሱፐር ሊጉ ክለብ ፌነርባቼ እንደሚያመሩ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በአሁን ሰዓት የሪያል ማድሪድ እና ቦርስያ ዶርትመንድን ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ለመከታተል ዌምብሌይ ስታዲየም ይገኛሉ።

ስለ ቀጣይ ማረፊያቸው የተጠየቁት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ " ሁኔታዎች ሙሉ ለሙሉ አልተጠናቀቁም ነገርግን ወደ ፌነርባቼ መሄድ እፈልጋለሁ " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ህመም አጋጥሞት እንደነበር ተገለጸ !

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ባለፉት ሁለት ቀናት መጠነኛ ህመም አጋጥሞት እንደነበር ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር ባለፉት ሁለት ቀናቶች ለህመሙ መድሀኒት ሲወስድ እንደነበረ ሲገለፅ በዛሬው ዕለት ጤናው መሻሻሉ ተነግሯል።

ቪንሰስ ጁኒየር በምሽቱ ጨዋታ የሪያል ማድሪድን የፊት መስመር የሚመራ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 03:16:44
Back to Top
HTML Embed Code: