Telegram Web Link
ጁቬንቱስ ከቦሎኛ ነጥብ ተጋርተዋል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከቦሎኛ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቦሎኛን ግብ ሪካርዶ ካላፊዮሪ 2x እና ካስትሮ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጁቬንቱስ የአቻነት ግቦችን ቼሳ ፣ ሚሊክ እና ይልዲዝ አስቆጥረዋል።

ሶስት ለባዶ ሲመራ የቆየው ጁቬንቱስ በጨዋታው መጋባደጃ ደቂቃዎች በሰባት ደቂቃዎች ውስጥ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር አቻ መሆን ችለዋል።

ጁቬንቱስ ያለፉትን #ስድስት የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ቦሎኛ :- 68 ነጥብ

4️⃣ ጁቬንቱስ :- 68 ነጥብ

በሊጉ የመጨረሻ መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከሞንዛ እንዲሁም ቦሎኛ ከጂኖኣ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•MacBook Air, M1
•MacBook Pro, M1

•MacBook Air, M2
•MacBook Pro, M2

•MacBook, M1 Pro
•MacBook, M2 Pro

•MacBook, M1 Max
•MacBook, M2 Max

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ፎደን ባሎን ዶር ሊያሸንፍ ይችላል " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋቻቸው ፊል ፎደን የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት ሊያሸንፍ እንደሚችል ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸውም " ፊል ፎደን ከእንግሊዝ ጋር የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድርን ማሳካት ከቻለ የባሎን ዶር ሽልማት ሊያሸንፍ ይችላል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ፊል ፎደን በዚህ አመት ለማንችስተር ሲቲ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎም መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤንጃሚን ሴስኮ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ የፊት መስመር ተጨዋች ቤንጃሚን ሴስኮ በሳውዲ አረቢያ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ወኪሉ ገልጿል።

ወኪሉ አያይዞም ተጨዋቹ አሁን ላይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የመሄድ እቅድ እንደሌለው የገለጸ ሲሆን የፕርሚየር ሊግ እና ሴርያ ክለቦችም ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግሯል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በሚቀጥለው ክረምት ለማስፈረም በዝርዝራቸው ውስጥ ከያዟቸው አጥቂዎች አንዱ ቤንጃሚን ሴስኮ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፕርሚየር ሊግ ተፎካካሪነቱ ጠፍቷል " - አግቦላሆር

የቀድሞ እንግሊዛዊ የአስቶን ቪላ ተጨዋች ጋብሬል አግቦላሆር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በአሁን ሰዓት ተፎካካሪነቱን በማጣት በማንችስተር ሲቲ ቁጥጥር ስር መሆኑን ገልጿል።

" ማንችስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ አመታት ሊጉን በማሳካት የሚደንቅ ስኬት አስመዝግቧል " የሚለው የቀድሞ ተጨዋቹ ፕርሚየር ሊግ በአሁን ሰዓት ተፎካካሪነቱን አጥቶ " Farmers league " ሆኗል ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ወደ ፈረንሳይ አምርተዋል !

የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በዛሬው ዕለት ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ማምራታቸው ተገልጿል።

ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በፓሪስ ቆይታቸው ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በኦሎምፒክ ተሳታፊ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በቀጣዩ ኦሎምፒክ ፈረንሳዊ ተጨዋቾችን ለመላክ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ቀድሞ ያሳወቀ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው በውድድሩ ምርጥ ተጨዋቾች ማካተት እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

በተጨማሪም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቅርቡ ኪሊያን ምባፔ የኦሎምፒክ ቡድኑን እንዲመራ ቀጣይ ማረፊያው የሚሆነውን ክለብ እንደሚያነጋግሩ ጠቁመው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሄንደርሰን ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አይቀርብለትም !

እንግሊዛዊው የአያክስ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን በብሔራዊ ቡድኑ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት ስብሰባቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን ጥሪ እንደማይቀርብለት ተነግሯል።

በሌላ በኩል የሊቨርፑሉ ተጨዋች ከርትስ ጆንስ እና የበርንሌይ ግብ ጠባቂ ጄምስ ትራፎርድ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የቡድን ስብስብ ጥሪ ይቀርባላቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲን ሊለቅ ይችላል !

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች አሁን ላይ ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ከቀረቡለት በውድድር አመቱ መጨረሻ ለመመልከት ዝግጁ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tech – art leather ቴክኖሎጂ በመጠቀም እጅግ ዘመናዊ ዲዛይን የተላበሰው አዲሱ Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድረጉ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt  #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
📢 Calling all our international customers!

👉🏾 Get ready to elevate your game with our professional kits at WANAW SPORTSWEAR!

👉🏾 Enjoy our free worldwide #DHL_Delivery and affordable prices. Whether you're in Europe, Asia, or even the United States, we've got you covered!

🛍 Order now and experience the ultimate in comfort, style, and performance.

🔥 Don't miss out, join the WANAW FAMILY today!

📞  For orders and further information contact 0901138283, 0910851535 and 0913586742.

📲 You can also order via Telegram @Wanawsales by directly talking to our sales team or via our Telegram bot @WANAWSbot.

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የክሎፕ ሽኝት የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በተጠናቀቀበት ምሽት አብዛኞቹ የውድድሩ ተከታታዮች ከማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ድል ስነ-ስርዓት ይልቅ የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን ሽኝት ሲከታተሉ እንደነበር ተገልጿል።

ሰባ በመቶ የሚሆኑት የውድድሩ የብሪቲሽ የቴሌቪዥን ተከታታዮች እሁድ ምሽት የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን የሽኝት ስነ-ስርዓት ሲከታተሉ እንደነበር ተነግሯል።

በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች ከአርባ አራት በመቶ የሚሆኑ ተከታታዮች የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን የሽኝት ለመመልከት መምረጣቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤን ቺልዌል ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አይቀርብለትም !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ቤን ቺል ዌል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሪ እንደማያቀርብለት ተገልጿል።

ተጨዋቹ በዘንድሮው የውድድር አመት በጉዳት ምክንያት ለክለቡ ብዙም ግልጋሎት መስጠት ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል።

የክሪስታል ፓላሱ አማካይ አዳም ዋርተን እና የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢዜ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ሊቀርብላቸው እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶኒ ክሩስ ጫማውን እንደሚሰቅል ይፋ አደረገ !

ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ በይፋ ከእግርኳስ ራሱን እንደሚያገል አስታውቋል።

" በጣም ለረጅም ጊዜ አስቤበታለሁ ነገርግን ባለፉት ጥቂት ቀናት ይህ አመት ትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ተረድቻለሁ ብቸኛው ምርጫዬ እግርኳስን በሪያል ማድሪድ ማጠናቀቅ ነው።"ሲል ቶኒ ክሩስ ተናግሯል።

ቶኒ ክሩስ በማድሪድ ቤት ምን አሳካ ?

4️⃣ ሻምፒየንስ ሊግ

4️⃣ የላሊጋ ዋንጫ

4️⃣ ሱፐር ኮፓ

3️⃣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ

5️⃣ የክለብ አለም ዋንጫ

1️⃣ ኮፓ ዴ ላሬ ማሳካት ችሏል።

ቶኒ ክሮስ በተጨማሪም በእግርኳስ ህይወቱ አንድ የአለም ዋንጫ ፣ ሶስት የቡንደስሊጋ እና ሶስት የጀርመን ካፕ ድሎችን መጎናጸፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራሽፎርድ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆነ !

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱ ተገልጿል።

የ 26ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በዘንድሮው የውድድር አመት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ጥሩ የሚባል አመት ማሳለፍ አልቻለም።

ማርከስ ራሽፎርድ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስልሳ ጨዋታዎች ማድረግ ሲችል አስራ ሰባት ግቦችን ማስቆጠርም ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ እነማንን በስብስቧ ታካትታለች ?

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስባቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኙ ነባር የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾችን መቀነሳቸውን እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ማካተታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ናቸው።

በማንችስተር ሲቲ ቤት በዚህ አመት በቂ የጨዋታ ጊዜ ሳያገኝ አመቱን ያጠናቀቀው ጃክ ግሪሊሽ በአሰልጣኙ ስብስብ ውስጥ መካተቱ ተዘግቧል።

ከብሔራዊ ቡድኑ እነማን ተቀነሱ ?

- ጆርዳን ሄንደርሰን

- ማርከስ ራሽፎርድ

- ሪስ ጄምስ

- ቤን ቺልዌል

እነማን ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል ?

- ከርትስ ጆንስ                   - አዳም ዊርተን

- ጃሬል ኳንሳህ                  - ጃክ ግሪሊሽ

- ኢቫን ቶኒ                         - ኢዜ

- ጄምስ ትራፎርድ 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ስብስቧን አሳውቃለች !

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የሚመራው የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

የ 41ዓመቱ የፖርቶ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ፔፔ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።

በጉዳት ላይ የሚገኘው የባየር ሙኒክ ተጨዋች ራፋኤል ጎሬሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ሳይቀርብለት ቀርቷል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
እንግሊዝ እነማንን በስብስቧ ታካትታለች ? የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስባቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኙ ነባር የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾችን መቀነሳቸውን እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ማካተታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ናቸው። በማንችስተር ሲቲ ቤት በዚህ አመት በቂ የጨዋታ ጊዜ ሳያገኝ…
እንግሊዝ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች !

በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

ማርከስ ራሽፎርድ ከስብስቡ ውጪ የሆነው በእሱ ቦታ የተሻለ አመት ያሳለፉ ተጨዋቾች መኖራቸውን ተከትሎ መሆኑን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ሰባት ተጨዋቾችን በመቀነስ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ በይፋ አሰልጣኝ ሾመች !

በቀጣይ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታውን የሚያደርገው የጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን በይፋ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል።

ጊኒ ቢሳው ፖርቹጋላዊውን የፉልሀም ምክትል አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጋ በሀላፊነት መሾሟን አስታውቃለች።

የቀድሞ ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሉዊስ ቦ ሞርቴ በኤቨርተን እና ፉልሀም ቤት ከአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ጋር በምክትል አሰልጣኝነት ለስድስት አመታት ማገልገል ችለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ቢሳው ጋር ቢሳው ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/11/15 18:43:21
Back to Top
HTML Embed Code: