Telegram Web Link
የፈረንሳይ ሊግ ፍፃሜውን አገኘ !

የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት የፈረንሳይ ሊግ ትላንት ከተደረጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብሮች በኋላ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ፒኤስጂ ለሶስት ተከታታይ አመታት ሊጉን በማሳካት ቀደም ብሎ ሊጉን በበላይነት ማጠናቀቁን ማረጋገጡ ይታወሳል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በሀያ ሰባት ግቦች የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጨዋች በመሆን አጠናቋል።

ኪሊያን ምባፔ ለስድስት ተከታታይ አመታት የፈረንሳይ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጨዋች በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።

በሚቀጥለው የውድድር አመት ፒኤስጂ ፣ ሞናኮ ፣ ብረስት እና ሊል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

እንዲሁም ኒስ በዩሮፓ ሊግ ኦሎምፒክ ሊዮን ደግሞ በኮንፈረንስ ሊግ ከፈረንሳይ ሊግ የሚሳተፉ ይሆናል።

ሎርየንት እና ክሌርመንት ፉት ከሊጉ በቀጥታ መውረዳቸው ሲረጋገጥ ሜትዝ በሊጉ ለመቆየት የማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋል።

የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ወደ ደቡብ ኮርያ ያመራል !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ቶተንሀም ለሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር አመት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ወደ ደቡብ ኮርያ እንደሚያመራ ይፋ ተደርጓል።

ቶተንሀም በደቡብ ኮርያ የቅድመ ውድድር ቆይታው ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ እንዲሁም ሌሎች ክለቦች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በቀጣይ በዩሮፓ ሊግ የሚሳተፈው ቶተንሀም ከደቡብ ኮርያ በተጨማሪም ወደ ጃፓን በማምራት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚያደርግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ከአዲዳስ ጋር ስምምነት ፈፀመ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ አስቶን ቪላ ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ አዲዳስ ይፋዊ የክለቡ ትጥቅ አቅራቢ ተቋም በመሆን ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን በማግኘት ድንቅ የውድድር አመት ያሳለፈው አስቶን ቪላ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲዳስን የመጫወቻ እና ልምምድ ማልያ እንደሚለብስ ተገልጿል።

ክለቡ ከእውቁ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ ብራንድ አዲዳስ ጋር ለበርካታ አመታት የሚቆይ የውል ስምምነት መፈፀሙን አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምንሄደው ኤፌ ካፑን ለማሸነፍ ነው " ኦናና

የማንችስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ቡድናቸው ቀጣይ ሳምንት ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገውን የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል።

የኤፌ ካፕ ዋንጫው ጥሩ አመት ላላሳለፉት ቀያዮቹ ሴጣኖች አስፈላጊ መሆኑን ያነሳው አንድሬ ኦናና " እኛ ማንችስተር ዩናይትዶች ነን ወደ ፍፃሜው የምናመራው ለማሸነፍ ነው " ሲል ተደምጧል።

የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ 11:00 ሰዓት በዌምብሌይ ስታዲየም በማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Bologna - Juventus
Salernitana - Verona
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
#Tecno #Camon30Pro5G

ቪድዮዎች  እና ምስሎችን በከፍተኛ ጥራት ማንሳት እንዲያስችል Sony Imx890 የካሜራ ሴንሰርን የተገጠመለት አዲሱ Tecno Camon Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ

#Camon30Et #Camon30pro5GEt  #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ክሮሽያ ስብስቧን አሳውቃለች !

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ጀርመን በምታዘጋጀው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

የ 38ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦለታል።

ሉካ ሞድሪች በእግርኳስ ህይወቱ አምስተኛ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩን የሚያደርግ ይሆናል።

ሙሉ ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮማን ጉዳት እንዳጋጠመው ተገለጸ !

ፈረንሳዊው የባየር ሙኒክ የፊት መስመር ተጨዋች ኪንግስሌይ ኮማን በድጋሜ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ተጨዋቹ በልምምድ ወቅት የጉልበት ጉዳት እንዳጋጠመው ሲገለፅ የጉዳት መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ በይፋ የታወቀ ነገር የለም።

ኪንግስሌይ ኮማን ለቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከቀረበላቸው የፊት መስመር ተጨዋቾች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፖቼቲኖ እንደማይቀጥሉ ሰምቻለሁ " ፈርዲናንድ

የቀድሞ እንግሊዛዊ የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንድ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከቼልሲ ጋር እንዳማይቀጥሉ መስማቱን ገልጿል።

ሪዮ ፈርዲናንድ ከውስጥ ሰምቼዋለሁ እንዳለው መረጃ ከሆነ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በሚቀጥለው አመት " በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤት አይቀጥሉም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባምላክ ተሰማ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ይመራሉ !

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ የሚደረግ የአፍሪካ አህጉር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ እንዲመሩ በፊፋ ተመርጠዋል።

ባምላክ ተሰማ በምድብ ሶስት የሚገኙት የቤኒን እና ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድኖች የሚያደርጉትን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩ ታውቋል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ ሰኞ ሰኔ 3/2016 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል።

በተጨማሪም አልጄሪያ ከጊኒ ጋር የምታደርገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሰስተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ተሰማ ሊመሩ እንደሚችሉ እየተገለፀ ይገኛል።

አልጄሪያ ለጨዋታው የተመረጡ የጋቦን ዳኛ እንዲቀየሩ ፊፋን መጠየቋ ሲገለፅ ጨዋታውን ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት እንዲሁም ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኝነት እንደሚመሩ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቡንደስሊጋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ይፋ ሆነ !

በባየር ሌቨርኩሰን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጀርመን ቡንደስሊጋ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የባየር ሌቨርኩሰን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፍሎሪያን ዊርትዝ የጀርመን ቡንደስሊጋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል በአብላጫ ድምጽ መመረጡ ተገልጿል።

የ 21ዓመቱ ፍሎሪያን ዊርትዝ በውድድር አመቱ ባደረጋቸው ሰላሳ ሁለት ጨዋታዎች አስራ አንድ ግቦችን አስቆጥሮ አስራ አንድ ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲና ስብስቧን አሳውቃለች !

በአሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የሚመራው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ለሀያ ዘጠኝ ተጨዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ካደረገላቸው ከሀያ ዘጠኝ ተጨዋቾች ውስጥ ለቀጣዩ የ2024 ኮፓ አሜሪካ ውድድር ሶስት ተጨዋቾች እንደሚቀንስ ተገልጿል።

ለኮፓ አሜሪካ ውድድር ዝግጅት የሚጀምረው ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ሳምንታት ከኢኳዶር እና ጓቴማላ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በመስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🏆 #የ2016_የኢትዮጵያ_ሴቶች_ከፍተኛ_ሊግ_ሻምፒዮን 🏆

የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ በቂርቆስ ክፍለከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ዋናው ስፖርትም ለክለቡ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አስቶን ቪላ ሮስ ባርክሌይን ማስፈረም ይፈልጋል !

አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮስ ባርክሌይ ወደ ሻምፒዮን ሽፑ ከወረደው ሉተን ታውን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ከሉተን ታውን ጋር በግሉ ጥሩ የሚባል የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ሮስ ባርክሌይ አስቶን ቪላን መቀላቀል እንደሚፈልግ ተገልጿል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ ሮስ ባርክሌይ ቡድኑን ለማጠናከር ትክክለኛው ተጨዋች ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርኔ ስሎት ሊቨርፑልን እንደሚረከቡ ይፋ አደረጉ ! ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሚቀጥለው የውድድር አመት የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዛሬው እለት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን በመተካት የሊቨርፑል ቀጣይ አሰልጣኝ በመሆን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል። አሰልጣኙ በንግግራቸውም " በሚቀጥለው የውድድር አመት የሊቨርፑል…
ሊቨርፑል በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ምትክ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በትላንትናው ዕለት በይፋ ክለቡን ተሰናብተው ሊቨርፑልን መልቀቃቸው ይታወቃል።

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሶስት አመት ውል መፈረማቸው ሲነገር ከአስር ቀናት በኋላ ሊቨርፑልን ተረክበው ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቴንሀግ የሚቀጥል አይመስለኝም "ፈርዲናንድ

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንዴ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በሀላፊነታቸው ላይቆዩ እንደሚችሉ ተናግሯል።

" አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቀጣይ አመት በክለቡ ይቀጥላል ብዬ አልጠብቅም " ያለው ሪዮ ፈርዲናንድ የምፈልገው ይህንን ነው ማለቴ ሳይሆን የማስበው ይህ ነው በማለት ተናግሯል።

ሪዮ ፈርዲናንድ አያይዞም ማንችስተር ዩናይትድ በኤፌ ካፕ የሚያስመዘግበው ውጤት በአሰልጣኙ ቀጣይነት ላይ በ " INEOS " በኩል የሀሳብ ለውጥ ያመጣል ብሎ እንደማያምን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ቤት ይቆያል !

ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በሚቀጥለው አመት በሊቨርፑል ቤት እንደሚቀጥል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አረጋግጧል።

" ዋንጫ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን በሚቀጥለው አመት ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ደጋፊዎቻችን ይገባቸዋል ፣ ለዚህ በደንብ እንፋለማለን።"ሲል ሳላህ በማህበራዊ ጉፁ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/26 22:54:21
Back to Top
HTML Embed Code: