Telegram Web Link
የእረፍት ሰዓት ውጤቶች !

በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመት 1,223 ግቦች ሲቆጠሩ ይህም በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የተቆጠሩበት የውድድር አመት ሆኗል።

ከዚህ በፊት 1,222 ግቦች ተቆጥረውበት ሪከርዱን ይዞ የነበረው የ1992/93 የውድድር አመት ነበር።

የክሪስታል ፓላሱ ተጨዋች ማቴታ ከቴሪ ሄንሪ በመቀጠል በሰባት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ የሜዳ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ ሁለተኛው ፈረንሳዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት ባደረጋቸው ሀምሳ ጨዋታዎች ሀያ አምስት ግቦች አስቆጥሮ አስራ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
49 '

ቼልሲ 2 - 1 በርንማውዝ

ካይሴዶ ኡናል
ስተርሊንግ

ማንችስተር ሲቲ 2 - 1 ዌስትሀም

ፎደን                 ⚽️ኩዱስ

አርሰናል 1 - 1 ኤቨርተን 

  ⚽️ቶሚያሱ       ጉዬ

ሊቨርፑል 2 - 0 ዎልቭስ

ማክ አሊስተር

ኳንሳህ

ብራይተን 0 - 0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
58 '

ማንችስተር ሲቲ 3 - 1 ዌስትሀም

ፎደን                 ⚽️ኩዱስ
ሮድሪ

አርሰናል 1 - 1 ኤቨርተን 

  ⚽️ቶሚያሱ       ጉዬ

ሊቨርፑል 2 - 0 ዎልቭስ

ማክ አሊስተር

ኳንሳህ

ቼልሲ 2 - 1 በርንማውዝ

ካይሴዶ           ኡናል
ስተርሊንግ

ብራይተን 0 - 0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
65 '

ማንችስተር ሲቲ 3 - 1 ዌስትሀም

ፎደን                 ⚽️ኩዱስ
ሮድሪ

አርሰናል 1 - 1 ኤቨርተን 

  ⚽️ቶሚያሱ       ጉዬ

ሊቨርፑል 2 - 0 ዎልቭስ

ማክ አሊስተር

ኳንሳህ

ቼልሲ 2 - 1 በርንማውዝ

ካይሴዶ           ኡናል
ስተርሊንግ

ብራይተን 0 - 0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70'

ብራይተን 0 - 1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዳሎት

ማንችስተር ሲቲ 3 - 1 ዌስትሀም

ፎደን                 ⚽️ኩዱስ
ሮድሪ

አርሰናል 1 - 1 ኤቨርተን 

  ⚽️ቶሚያሱ       ጉዬ

ሊቨርፑል 2 - 0 ዎልቭስ

ማክ አሊስተር
ኳንሳህ

ቼልሲ 2 - 1 በርንማውዝ

ካይሴዶ           ኡናል
ስተርሊንግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90‘

አርሰናል 2 - 1 ኤቨርተን 

  ⚽️ቶሚያሱ       ጉዬ

ብራይተን 0 - 2 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዳሎት


ማንችስተር ሲቲ 3 - 1 ዌስትሀም

ፎደን                 ⚽️ኩዱስ
ሮድሪ

ሊቨርፑል 2 - 0 ዎልቭስ

ማክ አሊስተር

ኳንሳህ

ቼልሲ 2 - 1 በርንማውዝ

ካይሴዶ           ኡናል
ስተርሊንግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ 2023/2024 ሻምፒዩን ሆነ።

ቡድኑ በተከታታይ ለ4 ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማንሳት አዲስ ታሪክ ጽፏል።

ዘንድሮ እስከ ዛሬው የመጨረሻ መርሐ ግብር ከ #አርሰናል ጋር አንገት ለአንገት የተናነቀው ሲቲ 91 ነጥብ በመሰብሰብ ነው ዋንጫውን ያሸነፈው።

እጅግ ብርቱ እና ጠንካራ አመትን ያሳለፈው አርሴናል 89 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል።

አርሰናል ባለፈው አመትም ለዋንጫ ተቃርቦ ዋንጫውን ማግኘት ሳይችል መቅረቱ አይዘነጋም ዘንድሮም በሁለት ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ሳያገኝ ቀርቷል።

ሊቨርፑል አመቱን በ3ኛነት ሲያጠናቅቅ አስቶን ቪላ 4 ፣ ቶተንሃም 5 እንዲሁም ቼልሲ 6 ሆነው ጨርሰዋል።

ባለ ብዙ ታሪኩ ማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ በጣም ደካማ የተባለ አመትን በማሳለፍ በታሪኩ ዝቅተኛ የተባለውን #ስምንተኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል።

ኖርዌያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ ለተከታታይ አመታት የፕርሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቀ ጫማውን አሸንፏል።

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል ፣ ሊቨርፑል እና አስቶን ቪላ ሲሳተፉ ቶተንሀም በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ቼልሲ በኮንፈረንስ ሊግ ተሳታፊ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ሉተን ታውን ፣ በርንሌይ እና ሼፍልድ ዩናይትድ ከፕርሚየር ሊግ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ መውረዳቸው ተረጋግጧል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በመላው ዓለም በብዙ ሚሊዮን ተመልካችን ማግኘት የቻለ ጠንካራ የእግር ኳስ ውድድር ሲሆን በሀገራችን #በኢትዮጵያም ሚሊዮኖች በተለይ ወጣቶች ውድድሩን ይከታተሉታል

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremiereLeague

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲን በሀላፊነት እየመሩ ስድስተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተከታታይ አራተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን በማሳካትም አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰባት የውድድር አመት ውስጥ ስድስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳክተዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ ቤት ምን አሳኩ ?

6️⃣ ፕርሚየር ሊግ

4️⃣ ካራባኦ ካፕ

2️⃣ ኤፌ ካፕ እና ኮሚኒቲ ሺልድ

1️⃣ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

1️⃣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ፣ የፊፋ ክለቦች ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የሰራነውን ታሪክ ለመናገር ከባድ ነው “ ፊል ፎደን

የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የዘንድሮው ውድድር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ፊል ፎደን “ ማንም ቡድን ያለደረገውን አድርግናል “ ሲል ከዋንጫ ድሉ በኋላ ተናግሯል።

ለአራተኛ ተከታታይ አመት ሊጉን ማሸነፋቸውን “ የሰራነውን ታሪክ ለመናገር ከባድ ነው ፣ ታሪክ ሰርተናል “ ብሏል።

“ ይህን ለማድረግ አመቱን ሙሉ ለፍተናል ፣ ለክለቡ እና ለደጋፊው ምን ማለት እንደሆነ ተመልክታችኋል “ ፊል ፎደን

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን ስድሰተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አንዳንዴ እግር ኳስ ፍትሀዊ አይደለችም “ ሀቨርትዝ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጫዋች ካይ ሀቨርትዝ የሊጉን ዋንጫ ማጣታቸው እንዳስከፋው በመግለፅ በቀጣይ ዓመት ጠንክረው እንደሚመጡ አሳስቧል።

“ አንዳንዴ እግር ኳስ ፍትሀዊ አይደለችም ነገር ግን ሁኔታውን በፀጋ መቀበል አለብን “ ያለው ሀቨርትዝ አሁን ካለን ነገር የተሻለ ነገር እንደሚገባን ይሰማኛል “ ብሏል።

ለመላው የክለቡ ደጋፉዎች ባስተላለፈው መልዕክት “ በቀጣይ ዓመት የተሻለ ጠንካራ ቡድን እና ያለውን የሚሰጥ ክለብ እንደምንሆን ልነግራችሁ እወዳለሁ “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በውጤቱ ሁላችንም አዝነናል “

የመድፈኞቹ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ የሊጉን ዋንጫ ባለማሸነፋቸው ማዘኑን ገልጿል።

“ እውነት ለመናገር በውጤቱ ሁላችንም አዝነናል “ ያለው ኦዴጋርድ “ የቡድን አጋሮቼ ባሳዩት ነገር ኩራት ይሰማኛል “ በማለት ተናግሯል።

ክለቡ መቀየሩን የገለፀው ኦዴጋርድ “ ሁሉም ደጋፊ በእኛ እምነት አላችሁ ፣ በቀጣይ ሁሉንም ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን “ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ባደረግነው ነገር አትደሰቱ የተሻለ እናደርጋለን "

የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የክለቡ ደጋፊዎች በቀጣይ የተሻለ ስኬት እንዲጠብቁ እና የተመዘገበው ውጤት በቂ ነው ብለው እንዳያስቡ ተናግረዋል።

ባስመዘገብነው ውጤት ደስተኛ መሆን የለባችሁም ሲሉ ለደጋፊው መልዕክት ያስተላለፉት ሚኬል አርቴታ " ምክንያቱም እኛ ትልቅ ነገር ነው ማሳካት የምንፈልገው ድጋፋችሁን ቀጥሉ በቀጣይ እናደርገዋለን " በማለት ተናግረዋል።

ሚኬል አርቴታ ለደጋፊው ያስተላለፉትን መልዕክት በጎል ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

የ 2023/24 የውድድር ዘመን የፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ በይፋ ተረክበዋል።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉
https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቲያጎ ሲልቫ የቼልሲ ደጋፊዎችን ተሰናብቷል !

ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ ያሳወቀው ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በዛሬው ዕለት በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ደጋፊውን በእምባ ታጅቦ ተሰናብቷል።

ቲያጎ ሲልቫ ለደጋፊው ባደረገው ንግግርም " ህልሜ ልጆቼ ለቼልሲ ሲጫወቱ መመልከት ነው ፣ ቼልሲን እና እናንተ ደጋፊዎችን አመሰግናለሁ እወዳችኋለሁ " ሲል ተናግሯል።

የ 39ዓመቱ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በቼልሲ ቤት ባሳለፋቸው አራት አመታት ውስጥ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የአለም ክለቦች ዋንጫ ድሎችን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 15:26:35
Back to Top
HTML Embed Code: