Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው! Lecce - Atalanta
Bayer Leverkusen - Augsburg
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና

10:30 ባየር ሊቨርኩሰን ከ ኦግስበርግ

10:30 ዶርትመንድ ከ ዳርምስታድት

10:30 ሆፈንሄም ከ ባየር ሙኒክ

12:00 ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል

3:45 ቶሪኖ ከ ኤሲ ሚላን

*የጀርመን ቡንደስሊጋ የመጨረሻ ሳምንት ሙሉ የጨዋታ መርሐ ግብሮች ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወደ ፕርሚየር ሊግ ማን ያድጋል ?

የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሲካሄዱ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ክለብ በመሆን ለማደግ ለሚደረገው ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚ ክለቦች ተለይተዋል።

በጥሎ ማለፉ ሊድስ ዩናይትድ ኖርዊች ሲቲን እንዲሁም ሳውዝሀምፕተን ዌስትብሮምን በደርሶ መልስ የድምር ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሰዋል።

ሊድስ ዩናይትድ ከሳውዝሀምፕተን ጋር በዌምብሌይ ስታዲየም የፍፃሜ ጨዋታቸውን በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ 11:00 ሰዓት የሚያደርጉ ይሆናል።

ሌስተር ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ቀደም ብለው በቀጥታ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደጉ ክለቦች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ የትኬት ዋጋ መጨመሩን ገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር አመት የተዘጋጁ የጨዋታ መግቢያ ትኬቶች ላይ ጭማሬ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ሰማያዊዎቹ በጨዋታ መግቢያ ትኬቶች ላይ አምስት በመቶ ( 5% ) ጭማሬ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።

በአሜሪካዊው ባለቤት ቶድ ቦህሊ የሚመሩት ቼልሲዎች የትኬት ዋጋ ሲጨምሩ ከአስራ ሶስት የውድድር አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሜሲ የፈረመበት ወረቀት በጨረታ ተሸጠ !

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለባርሴሎና የፈረመበት ጊዜያዊ ወረቀት በጨረታ መሸጡ ተገልጿል።

ከሀያ አራት አመታት በፊት የሊዮኔል ሜሲ እና የባርሴሎና ሀላፊዎች መተማመኛ ትሆን ዘንድ በካፌ ውስጥ የተፈረመችው ውል በቅርቡ በበይነ መረብ ለጨረታ ቀርባ ነበር።

የጨረታው መነሻ ዋጋ 300,000 ሺ ፓውንድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በመጨረሻም ወረቀቱ 762,400 ሺ ፓውንድ መሸጡ ተገልጿል።

በወቅቱ ከዚህች የወረቀት ስምምነት አንድ ወር በኋላ ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎናን በይፋ በመቀላቀል በክለቡ በርካታ ታሪኮችን በመፃፍ በአለም እግርኳስ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠርም ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ ዛሬ ይጠናቀቃል !

አሸናፊውን ክለብ እስከመጨረሻው ሳምንት መርሐ ግብር ያላሳወቀው የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ ውድድር ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል።

ሊጉን የቼልሲ ሴቶች ቡድን እና የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ ሁለት ነጥብ በሁለት የግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን እየመሩት ይገኛሉ።

ሁለቱ ክለቦች አስካሁን ካደረጓቸው ሀያ አንድ ጨዋታዎች በተመሳሳይ አስራ ሰባት አሸንፈው ሶስት ተሸንፈው አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ሊጉ ዛሬ አሸናፊውን ሲለይ መሪው ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ አመሻሽ 11:00 ያደርጋሉ።

የቼልሲ ሴቶች ቡድን ዛሬ የእንግሊዝ ሱፐር ካፕ ዋንጫን የሚያሸንፍ ከሆነ ለ #አምስተኛ ተከታታይ አመታት የሊጉ ሻምፒዮን በመሆን ወርቃማ ታሪክ ይፅፋል።

ሊጉን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል ? የዘንድሮ የውድድር ዓመት የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ እና ወጣት ተጫዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በአመቱ ምርጥ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ :- - ፊል ፎደን ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ አሌክሳንደር አይሳክ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ኮል ፓልመር ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ኦሊ ዋትኪንስ እና ቫን ዳይክ ተካተዋል። በወጣት ምርጥ ተጫዋች እጩ ውስጥ ስምንት ተጫዋቾች…
ፊል ፎደን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ !

በነገው ዕለት ፍፃሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።

ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለማንችስተር ሲቱ አስራ ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር ስምንት ለግብ የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን ሁለት ሀትሪክም ሰርቷል።

ፊል ፎደን ከሸልማቱ በኋላ " ይህንን ትልቅ ትርጉም ያለው ሽልማት እንዳሸነፍ ድምፅ የሰጡኝን ሁሉ አመሰግናለሁ ፣ ሽልማቱ በጣም የምኮራበት ስኬት ነው ፣ ሁሉንም የማንችስተር ሲቲ አባላትም አመሰግናለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፊል ፎደን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ ! በነገው ዕለት ፍፃሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል። ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለማንችስተር ሲቱ አስራ ሰባት…
#PremiereLeague

ፊል ፎደን ከ2015/16 የውድድር አመት ጄሚ ቫርዲ ካሸነፈ ወዲህ የፕርሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት ያሸነፈ የመጀመሪያው እንግሊዛዊ ተጨዋች ሆኗል።

ባለፉት አምስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመታት የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።

ባለፉት አምስት አመታት እነማን አሸነፉ ?

- ኬቨን ዴብሮይን :- 2019/20 የውድድር አመት

- ሩበን ዲያስ :- 2020/21 የውድድር አመት

- ኬቨን ዴብሮይን :- 2021/22 የውድድር አመት

- ኤርሊንግ ሀላንድ :- 2022/23 የውድድር አመት

- ፊል ፎደን :- 2023/24 የውድድር አመት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 WANAW 🤝 EFF 🇪🇹

THE GREEN, YELLOW AND RED JERSEY JOURNEY
!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
#Tecno #Camon30Pro5G

የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ።

አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ብለዋል።

#Camon30Et  #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ባየር ሊቨርኩሰን ሊጉን ሳይሸነፍ ያጠናቅቅ ይሆን ?

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዋንጫን ቀደም ብሎ ማሸነፉን ያረጋገጠው ባየር ሊቨርኩሰን ዛሬ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ከኦግስበርግ ጋር የውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደርጋል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሊቨርኩሰን ዛሬ ከኦግስበርግ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ሽንፈት የማይገጥመው ከሆነ ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ ሊጉን በማሳካት ወርቃማ ታሪክ የሚፅፍ ይሆናል።

ባየር ሊቨርኩሰን በዚህ አመት በቡንደስሊጋው ሰላሳ ሶስት ጨዋታዎች ሲያደርግ ሀያ ሰባቱን አሸንፎ በስድስቱ አቻ ተለያይቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ ሜሰን ግሪንውድን ማስፈረም ይፈልጋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ እንግሊዛዊውን የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ናፖሊ አሁን ላይ በሜሰን ግሪንውድ ዝውውር ዙሪያ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል።

የውድድር አመቱን በላሊጋው ክለብ ሄታፌ በውሰት ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ በክረምቱ ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአሰልጣኝ ዣቪ የባርሴሎና ቆይታ ? ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ከክለቡ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። አሰልጣኝ ዣቪ ከቀናት በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጡት አስተያየት ከባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ጋር አለመግባባት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረ ተዘግቧል። ዣቪ ከቀናት በፊት ቡድናቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ለመፎካከር…
" የተለወጠ አዲስ ነገር የለም " ዣቪ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር የተፈጠረ አዲስ ነገር አለመኖሩን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" አሁን ላይ ምንም የተቀየረ ነገር የለም ክለቡ በእኔ ላይ እምነት አለው ፣ ፕሬዝዳንቱ እና ዴኮ አዎንታዊ መልዕክት ነው የላኩልኝ ስለሚወጡ መረጃዎች ግድ የለኝም ትኩረት የማደርገው እቅዱ ላይ ነው።" ሲሉ ዣቪ ተናግረዋል።

" ይህ ቡድን ትልቅ አቅም አለው በሚቀጥለው የውድድር አመት ዋንጫ ለማሸነፍ ጥረት እናደርጋለን እቅዳችን ግልጽ ነው።" ዣቪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጄሱስ ናቫስ ከሲቪያ ጋር ሊለያይ ነው ! ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሲቪያ ጋር እንደሚለያይ አስታውቋል። ጄሱስ ናቫስ በሲቪያ ቤት በቆየባቸው አመታት ስድስት መቶ ሰማንያ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። የ 38ዓመቱ ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ ከሲቪያ ጋር ዘጠኝ የተለያዩ ዋንጫዎችንም ማሸነፍ ችሏል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄሱስ ናቫስ በሲቪያ ቤት ለመቀጠል ወሰነ !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሲቪያ ጋር እንደሚለያይ አሳውቆ የነበረው ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ አሁን ላይ በክለቡ ለመቀጠል ከስምምነት መድረሱን ገልጿል።

ተጨዋቹ ከሲቪያ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እስከ ታህሳስ ወር ለሲቪያ እንዲጫወት እና በአዲሱ አመት በክለቡ ውስጥ በሚፈልገው ሌላ ሚና መስራት እንዲችል መስማማታቸው ተዘግቧል።

ጄሱስ ናቫስ ከአሁን በኋላ እስከ ታህሳስ ወር ከሲቪያ ክፍያ እንደማይቀበል እና ደሞዙን ለክለቡ ፋውንዴሽን እንደሚለግስ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ስቴፋኦ ዊሊያን ከብራዚሉ ክለብ ፓልሜይራስ ለማስፈረም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ የተጨዋቹ አቋም እየታየ የሚጨምር ክፍያን ጨምሮ አጠቃላይ 57 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ክፍያ ሊያሶጣቸው እንደሚችል ተነግሯል።

የ 17ዓመቱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ስቴፋኦ ዊሊያን በቼልሲ ቤት የሰባት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የፈረሰኞቹን ግብ በረከት ወልዴ ሲያስቆጥር የሀድያ ሆሳዕናን የአቻነት ግብ ዑመድ ኡኩሪ ከመረብ አሳርፏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለፉትን ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በአራቱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

4️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 40 ነጥብ

8️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 35 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

እሁድ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TkvahGoal

የ 2023/24 የውድድር አመት የጀርመን ቡንደስሊጋ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብሮች በአሁን ሰዓት በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

እረፍት | ባየር ሊቨርኩሰን 2-0 ኦግስበርግ

እረፍት | ሆፌንሄም 1 - 2 ባየር ሙኒክ

እረፍት | ዶርትመንድ 2-0 ዳርምስታድት

ጨዋታዎቹን እና አጫጭር ቪዲዮችን በጎል ቻናላችን መከታተል ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቤርቶ ዲዘርቢ ብራይተንን ሊለቁ ነው !

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከፕርሚየር ሊጉ ክለብ ብራይተን ጋር ሊለያዩ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ከሁለት አመታት ቆይታ በኋላ ከብራይተን ጋር በጋራ ስምምነት እንደሚለያዩ ክለቡ አስታውቋል።

የ  42ዓመቱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ነገ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የብራይተን የመጨረሻ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሊቨርኩሰን ወርቃማ ታሪክ ፃፈ !

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዋንጫን ቀደም ብሎ ማሸነፉን ያረጋገጠው ባየር ሊቨርኩሰን ከኦግስበርግ ጋር ያደረገውን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባየር ሊቨርኩሰንን የማሸነፊያ ግቦች ቪክቶር ቦኒፌስ እና ሮበርት አንድሪክ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮው የውድድር አመት ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫውን በማሳካት አዲስ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን በዚህ አመት በቡንደስሊጋው ሰላሳ አራት ጨዋታዎች ሲያደርግ ሀያ ስምንቱን አሸንፎ በስድስቱ አቻ ተለያይቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 11:26:30
Back to Top
HTML Embed Code: