Telegram Web Link
ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረከበ !

ማንችስተር ሲቲ ከፉልሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ጆስኮ ግቫርዲዮል 2x ፣ ፊል ፎደን እና ጁሊያን አልቫሬዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኬቨን ዴብሮይን አንድ መቶ አስራ አንደኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ ታሪክ ብዙ አመቻችቶ ያቀበለ ሶስተኛው ተጨዋች ሆኗል።

የማንችስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ግቫርዲዮል ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አምስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን በውድድር ዘመኑ አስራ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ሲያስቆጥር አጠቃላይ በውድድር አመቱ ሰላሳ ስድስት የግብ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 85 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ፉልሀም :- 44 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ - ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ

እሁድ - ሉተን ታውን ከ ፉልሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት እድሜ የቀረው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር በአጓጊነቱ ሲቀጥል በዛሬው ዕለት ማንችስተር ሲቲን ወደ መሪነት አምጥቷል።

ለረጅም ጊዜ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የቆየው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከዋንጫ ፉክክሩ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር የሚለያዩት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሊቨርፑል ቆይታቸውን አንድ የእንግሊዝ ፕርሚየር ዋንጫን በማሸነፍ ለማጠናቀቅ ተገደዋል።

ወቅታዊ የዋንጫ ተፎካካሪዎች ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 85 ነጥብ ( 58 ንፁህ ግብ )

2️⃣ አርሰናል :- 83 ነጥብ ( 60 ንፁህ ግብ )

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

- ማንችስተር ሲቲ :- ቶተንሀም እና ዌስትሀም

- አርሰናል :- ማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን

ሊጉን ማን ያሳካዋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነአቻ  ውጤት አጠናቀዋል።

የሀዋሳ ከተማን ግብ ታፈሰ ሰለሞን ከመረብ ሲያሳርፍ ደስታ ደሙ ሲዳማ ቡናን አቻ ማድረግ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 33 ነጥብ

1️⃣1️⃣ ሲዳማ ቡና :- 31 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል

እሁድ - አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፍፁም ቅጣት ምቱን መውሰድ ፈልጌ ነበር " ግቫርዲዮል

ለማንችስተር ሲቲ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ተከላካዩ ግቫርዲዮል ሀትሪክ ለመስራት የፍፁም ቅጣት ምቱን እንዲመታ ጠይቆ እንደነበር ገልጿል።

" ፍፁም ቅጣት ምቱን ለመምታት ጠይቄ ነበር ተነጋግረንበታል ፣ ነገርግን ሁላችንም ማን መምታት እንዳለበት እናውቃለን አልቫሬዝ ግቡን በማስቆጠሩ ደስተኛ ነኝ።"ሲል ግቫርዲዮል ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
25 '

ኒውካስል 0 - 1 ብራይተን

                 ቬልትማን

ዌስትሀም 0 - 1 ሉተን ታውን

                   ሎኮንጋ

ቶተንሀም 0 - 0 በርንሌይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
27 '

ቶተንሀም 0 - 1 በርንሌይ

ላርሰን

ኒውካስል 0 - 1 ብራይተን

                 ቬልትማን

ዌስትሀም 0 - 1 ሉተን ታውን

                   ሎኮንጋ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
40'

ቶተንሀም 1 - 1 በርንሌይ

ፖሮ               ላርሰን

ኒውካስል 0 - 1 ብራይተን

                 ቬልትማን

ዌስትሀም 0 - 1 ሉተን ታውን

                   ሎኮንጋ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ቶተንሀም 1 - 1 በርንሌይ

ፖሮ               ላርሰን

ኒውካስል 1 - 1 ብራይተን

ሎንግስታፍ             ቬልትማን

ዌስትሀም 0 - 1 ሉተን ታውን

                   ሎኮንጋ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተከላካይ ማተኮር ያለበት መከላከል ላይ ነው " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የቡድናቸው ተከላካዮች የበለጠ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው ግብ ማስቆጠር ላይ ሳይሆን መከላከሉ ላይ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

" የተከላካዮች ስራ መከላከል እንጂ ግብ ማስቆጠር አይደለም " ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ ግብ ቢያስቆጥሩ ምንም ችግር የለውም ነገርግን ለእነሱ በጣም አስፈላጊው መከላከል ላይ ማተኮር ነው ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
65 '

ቶተንሀም 1 - 1 በርንሌይ

ፖሮ               ላርሰን

ኒውካስል 1 - 1 ብራይተን

ሎንግስታፍ             ቬልትማን

ዌስትሀም 1 - 1 ሉተን ታውን

ፕራውስ                   ሎኮንጋ

በጨዋታዎቹ የሚቆጠሩ ግቦችን በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:30 ኖቲንግሃም ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
81 '

ቶተንሀም 2 - 1 በርንሌይ

ፖሮ               ላርሰን
ቫን ዴቪን

ዌስትሀም 3 - 1 ሉተን ታውን

ፕራውስ                   ሎኮንጋ
ሱሴክ
ኤርቲ

ኒውካስል 1 - 1 ብራይተን

ሎንግስታፍ             ቬልትማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲደረጉ ቶተንሀም በርንሌይን 2ለ1 ዌስትሀም ሉተን ታውንን 3ለ1 መርታት ችለዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ፔድሮ ፖሮ እና ቫንዴቪን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኒውካስል ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኤቨርተን ሼፍልድ ዩናይትድን 1ለ0 ሲያሸን ክሪስታል ፓላስ ዎልቭስን 3ለ1 እንዲሁም ብሬንትፎርድ በርንማውዝን 2ለ1 አሸንፈዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

5️⃣ ቶተንሀም :- 63 ነጥብ

6️⃣ ኒውካስል :- 57 ነጥብ

9️⃣ ዌስትሀም :- 52 ነጥብ

ወቅታዊ ሙሉ የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንሌይ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ወረደ !

በአሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ የሚመራው በርንሌይ በቶተንሀም 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ መውረዱን አረጋግጧል።

በርንሌይ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ተመልሶ ወርዷል።

በርንሌይ ሼፍልድ ዩናይትድን በመከተል ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን ያረጋገጠ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 ' ኖቲንግሃም 0 - 1 ቼልሲ

ሙድሪክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
15 ' ኖቲንግሃም 1 - 1 ቼልሲ

ቦሊ                  ሙድሪክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/25 23:20:18
Back to Top
HTML Embed Code: