Telegram Web Link
ኦባምያንግ ለሀገሩ ጥሪ ቀረበለት !

ለፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ እየተጫወተ የሚገኘው የፊት መስመር ተጨዋቹ ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ ከሀገሩ ጋቦን ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።

ኦባምያንግ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ የጋቦን ብሔራዊ ቡድንን በቀጣይ በሚደረጉ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚወክል ይሆናል።

ጋቦን በሚቀጥለው ወር ከአይቮሪኮስት እና ጋምቢያ ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤቨርተን በድጋሜ ነጥብ ተቀነሰባቸው ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ጥሰው በመገኘታቸው ምክንያት በአመቱ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የነጥብ ቅነሳ ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል። በቅርቡ ስድስት ነጥቦች የተቀነሰባቸው ኤቨርተኖች አሁን ላይ በሌላ ህግ ጥሰት #ሁለት ነጥቦች እንደተቀነሱባቸው ተነግሯል። ይህንንም ተከትሎ ኤቨርተን በሀያ ሰባት ነጥቦች ከወራጅ ቀጠናው በሁለት…
ኤቨርተን የጠየቀውን ይግባኝ ማንሳቱን ገለፀ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ጥሰው በመገኘታቸው ምክንያት በአመቱ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የነጥብ ቅነሳ ቅጣት እንደተጣለባቸው ይታወሳል።

ከዚህ በፊት ስድስት ነጥቦች የተቀነሰባቸው ኤቨርተኖች ቀጥሎም ሁለት ነጥቦች ተቀንሶባቸው የነበረ ሲሆን ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ጠይቀው ነበር።

አሁን ላይ በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ኤቨርተን የነጥብ ቅነሳው በቀጣይ በሊጉ በሚኖራቸው ደረጃ ለውጥ ስለማያመጣ የጠቁትን ይግባኝ ማንሳታቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኮል ፓልመር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል ! ወደ ፍፃሜው በመቃረብ ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሚያዝያ ወር ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል። ኮል ፓልመር በወሩ ውስጥ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሰባት…
#TikvahGoal

እንግሊዛዊው ተጨዋች ኮል ፓልመር ኤቨርተን ላይ ያስቆጠረው የመክፈቻ ግብ የፕርሚየር ሊጉ የሚያዚያ ወር ምርጥ ግብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ኮል ፓልመር በአንድ ወር የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች እና ምርጥ ግብ ሽልማትን ያሸነፈ በሊጉ ታሪክ የመጀመሪያው የቼልሲ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የወሩን ምርጥ ግብ በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቾቹ ወደ ልምምድ ተመልሰዋል !

ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ ከአርሰናል ጋር ከሚያደርገው የሊግ ጨዋታ በፊት በሰራው ልምምድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ማክ ቶሚናይ መሳተፋቸውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ገልፀዋል።

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሜሰን ማውንት ሌላ ጉዳት ማስተናገዱን እና ልምምድ እንዳልሰራ አሰልጣኙ አሳውቀዋል።

አርጀንቲናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በበኩሉ በጨዋታው እንዲሳተፍ መጠየቁን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እሁድም የሲቲ ደጋፊ ነኝ " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ነገ ከፉልሀም ጋር ከሚያደርገው የሊግ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቆይታቸው ምን አሉ ?

- " እሁድ በሚደረገው የሊግ ጨዋታ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ አይደለሁም እኔ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊ ነኝ።

- ሙሉ ቡድናችን ለፉልሀም ጨዋታ ዝግጁ ነው ምንም ጉዳት የለብንም ጥሩ የህክምና ቡድን አለን በሚሰሩት ነገር ደስተኛ ነኝ።

- ፉልሀም በሜዳቸው ነው የሚጫወቱት ጨዋታው ቀላል ይሆናል ብዬ አልጠብቅም እኛን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር ያደርጋሉ።

- ሮድሪ የግል ሽልማቶች ውስጥ እጩ አለመሆኑ ግድ አይሰጠውም እሱ ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ያለውን ዋጋ ያውቃል እኛ እሱ ምን ያህል ምርጥ እንደሆነ እናውቃለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የአቋማችን መውረድ መንስኤ ጉዳት ነው " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው በዘንድሮው የውድድር አመት እያሳየ የሚገኘው ደካማ አቋም ምክንያቱ ጉዳት መሆኑን ገልጸዋል።

" በወሳኝ የሜዳ ክፍሎች ብዙ ጉዳት ሲኖሩ የትኛውም ቡድን ጥሩ መንቀሳቀስ አይችልም " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ " በዚህ አመት ያሳየነው ደካማ አቋም ምክንያቱ ያጋጠሙን ጉዳቶች ናቸዉ " በማለት ተናግረዋል።

" የእሁዱን የአርሰናል ጨዋታ ለማሸነፍ የየትኛውንም ተጨዋች ጤንነት አደጋ ላይ በመጣል በድጋሜ ማጣት አልፈልግም።"ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አክለው ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ብሩክ ሙሉጌታ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ ተከታታይ ሶስተኛ ሽንፈታቸን ሲያስተናግዱ ያለፉትን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በአራቱ ተሸንፈዋል።

ኢትዮጵያ መድን ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች በአሸናፊነት በመወጣት ነጥባቸውን ከወራጅ ቀጠናው ክለቦች ከፍ ማድረግ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 39 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 28 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

አርብ - ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

ቅዳሜ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሶስተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ብሔራዊ ቡድኑ የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሶስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ኬንያ ናይሮቢ ላይ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም የሚያደርግ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታውን በደርሶ መልስ ውጤት የሚያሸንፈው ቡድን በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር ከጅቡቲ እና ብሩንዲ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሊጉን እንደምናሸንፍ ውስጤ ነግሮኛል " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ እንደሚያሸንፍ እየተሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል።

" የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ እንደምናሸንፍ ውስጤ እየነገረኝ ነው " ያሉት ሚኬል አርቴታ ይህ ስሜት ሁሉም እንዲሰማው እፈልጋለሁ ዋንጫውን እንደምናሳካው ሙሉ ተስፋ አለኝ ብለዋል።

" እኛ ማንችስተር ሲቲን ለማስቆም እየተጓዝን ነው ሁልጊዜ እነሱን ለመፎካከር ስንሞክር እየተሻሻልን እንገኛለን በዚህ አመት ድንቅ ነገር አድርገናል እሁድ ዩናይትድ ላይ ተመሳሳይ እንደምናደርግ ተስፋ አደርጋለሁ።" አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጂሮና ስታዲየማቸው ፍቃድ አገኘ !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ጂሮና በቀጣዩ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ጨዋታቸውን በሜዳቸው ሞንቲሊቪ እንዲያደርጉ ፍቃድ ማግኘታቸውን አሳውቀዋል።

ስታዲየሙ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን የጥራት መስፈርት አያሟላም የሚል ስጋት የነበረባቸው ጂሮናዎች አሁን ላይ እንደተፈቀደላቸው ተነግሯል።

ጂሮና በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ቦታን ማረጋገጣቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ከፍ ብለው በረው ዕድልዎን ይጨብጡ! በአቪዬተር እስከ 500,000 ብር በሰከንዶች ወስጥ ያሸንፉ! አሁኑኑ ለመጫወት ሊንኩን ይጫኑ https://betika.com.et/et/aviator !
🔥 አርሰናሎች የ20 ዓመት የዋንጫ ጥማታቸውን ሊቆርጡ መድፋቸውን እያገላበጡ ወደ የፕሪሚየር ሊግ አፋፉ ተቃርበዋል።

አፋፉ ላይ ደግሞ ቀያዮቹ ቆመዋል!

⚽️ እሁድ ከምሽቱ 12፡30 ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ብቻ!

ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…

👉 ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
ብራዚል ስብስቧን አሳወቀች !

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ2024 የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ ይፋ አድርገዋል።

ካሴሚሮ ፣ ጋብሬል ጄሱስ ፣ ሪቻርልሰን ፣ ማቲውስ ኩንሀ እና ብሬመር በስብስቡ ውስጥ ሳይካተቱ የቀሩ ተጨዋቾች ናቸው።

የአል ሂላሉ የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር በበኩሉ በጉዳት ምክንያት በስብስቡ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናከረ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ሱሌይማን ሀሚድ እና ፉዓድ ፈረጃ ማስቆጠር ሲችሉ ለወልቂጤ ከተማ ሳምሶን ጥላሁን ከመረብ አሳርፏል።

ወልቂጤ ከተማዎች ያለፉትን አራት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 50 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ወላይታ ድቻ ከ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ወልቂጤ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የአርሰናል ተጨዋቾች እየደወሉልኝ ነው " ሌኖ

የፉልሀሙ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ የቀድሞ የቡድን አጋሮቹ የአርሰናል ተጨዋቾች በነገው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ለማስቆም የቻለውን እንዲያደርግ ደውለው እንደጠየቁት ገልጿል።

" የአርሰናል ተጨዋቾች ደውለው ነገ በሁሉም መንገድ ማንችስተር ሲቲን ለማስቆም የቻልኩትን እንዳደርግ ጠይቀውኛል " ያለው ሌኖ " እኔም መልሼ ስጋት እንዳይገባችሁ ለማስቆም ያለንን ሁሉ እንሰጣለን ብያቸዋለሁ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ ፒኤስጂን እንደሚለቅ በይፋ አሳወቀ !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

ፈረንሳዊው ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ለፒኤስጄ 306 ጨዋታዎች አድርጎ ሁለት መት ሀምሳ አምስት ግቦችን አስቆጥሮ 108 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ኪሊያን ምባፔ በፒኤስጂ ቤት ምን አሳካ ?

6️⃣ የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ

3️⃣ ኮፕ ዴ ፍራንስ

3️⃣ የአሸናፊዎች ዋንጫ

2️⃣ የሊግ ካፕ

4️⃣ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት

5️⃣ የፈረንሳይ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣረ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ ፒኤስጂን እንደሚለቅ በይፋ አሳወቀ ! ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል። ፈረንሳዊው ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ለፒኤስጄ 306 ጨዋታዎች አድርጎ ሁለት መት ሀምሳ አምስት ግቦችን አስቆጥሮ 108 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ኪሊያን ምባፔ በፒኤስጂ ቤት ምን አሳካ ? 6️⃣
" ሀገሬን መልቀቅ ቢከብድም አዲስ ፈተና ያስፈልገኛል " ምባፔ

ፒኤስጂን በውድድር ዘመኑ መጨረሻ እንደሚለቅ በይፋ ያሳወቀው ኪሊያን ምባፔ ከሰባት አመታት በኋላ አዲስ ፈተና አስፈልጎት ለመልቀቅ መወሰኑን በማህበራዊ ገፁ ባሰራጨው መልዕክት ገልጿል።

" ሀገሬን እና የማውቀውን የፈረንሳይ ሊግ ለቆ መሄድ በጣም ከባድ ነው "ያለው ኪሊያን ምባፔ በመልዕክቱ " ነገርግን ከሰባት አመት በኋላ አዲስ ፈተና አስፈልጎኛል " በማለት ተናግሯል።

" ሁሉንም የፒኤስጂ ዜናዎች በቅርበት እከታተላለሁ ሁሉንም ጨዋታዎች እመለከታለሁ እዚህ በመጫወቴ እድለኛ መሆኔን ለሁሉም እነግራለሁ።" ምባፔ

ኪሊያን ምባፔ እሁድ በፓርክ ዴ ፕሬንስ የመጨረሻ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ሲያሳውቅ ክለቡ የሽኝት መርሐግብር ያዘጋጅለታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኪሊያን ምባፔን ሙሉ የስንብት መልዕክት በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ኢንተር ሚላን ከፍሮሲኖን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ፍራቴሲ ፣ አርናቶቪች ፣ ቡቻናን ፣ ማርቲኔዝ እና ማርከስ ቱራም ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢንተር ሚላን በውድድር አመቱ የሰበሰባቸውን የሊግ ነጥቦች ወደ ዘጠና ሁለት ነጥቦች ከፍ ማድረግ ችሏል።

ፍሮሲኖን በበኩሉ ከወራጅ ቀጠናው በሁለት ነጥቦች ርቆ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች አስራ ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሻምፒዮኑ ክለብ ኢንተር ሚላን በቀጣይ እሁድ ከላዝዮ ጋር የሊግ መርሐግብሩን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፋብሪጋስ ቡድኑን ወደ ሴርያው አሳድጓል !

በስፔናዊው አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስ የሚመራው የጣልያኑ ክለብ ኮሞ ከታችኛው ሊግ ወደ 2024/25 የጣልያን ሴርያ ውድድር ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

የሴስክ ፋብሪጋሱ ቡድን ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጣልያን ሴርያ ውድድርን መቀላቀል ችለዋል።

ኮሞ ትልቅ ሀብት ባላው ተቋም ባለቤትነት ከተያዙ የጣልያን ክለቦች አንዱ መሆኑ ሲገለፅ በክለቡ ውስጥ ቴሪ ሄንሪ እና ሴስክ ፋብሪጋስ የአክስዮን ድርሻ እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 60,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
2024/09/28 22:18:53
Back to Top
HTML Embed Code: