Telegram Web Link
አዳማ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር አዳማ ከተማ ከወልዋሎ አ.ዩ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግብ አሜ መሐመድ ፣ ነቢል ኑሪ እና ኤሊያስ ለገሰ ማስቆጠር ችለዋል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በውድድር ዘመኑ ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣1️⃣ አዳማ ከተማ :- 15 ነጥብ
1️⃣8️⃣ ወልዋሎ ዓ.ዩ :- 1 ነጥብ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ሊቨርፑል ጥሩ ከሆነ ያሸንፋል “ ሮይ ኪን

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሮይ ኪን ሊቨርፑል ዛሬ በጥሩ አቋማቸው ላይ ከሆኑ ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚያሸንፉ ገልጿል።

“ ሊቨርፑል በጥሩ አቋማቸው ላይ ከሆኑ ማንችስተር ዩናይትድን በቀላሉ ያሸንፋሉ “ ሲል ሮይ ኪን የጨዋታ ግምቱን አስቀምጧል።

ሮይ ኪን አክሎም ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስር “ በጣም አስከፊ ደረጃ ላይ ናቸው “ በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ጋርናቾ እና ማይኖ ዩናይትድን ሊለቁ ይችላሉ !

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የዝውውር መስኮቶች ተጨዋቾች ሽያጭ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ሲገለፅ ነበር።

ክለቡ በቀጣይ በሚያደርገው የተጨዋቾች ሽያጭ አይነኬ የሚባሉ ተጨዋቾችን ዝርዝር መያዙ ተነግሯል።

ለሽያጭ ከማይቀርቡ እና አይነኬ ከሚባሉ ተጨዋቾች መካከል አሌሀንድሮ ጋርናቾ እና ኮቢ ማይኖ #አለመኖራቸውን ዴቪድ ኦርንስቴን ተናግሯል።

በሌላ በኩል ማርከስ ራሽፎርድ ከሳውዲ አረቢያ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ መባሉ ሀሰተኛ መሆኑን የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ዴቪድ ኦርንስቴን ገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት :- ኪሊያን ምባፔ አንቶኒዮ ሩዲገር ቫልቬርዴ ጁድ ቤሊንግሀም እና ሮድሪጎ የወርሀ ህዳር የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport    …
“ ደጋፊዎች ስለመረጡኝ አመሰግናለሁ “ ምባፔ

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የታኅሣሥ ወር የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

“ ደጋፊዎች ድምፅ ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ ወሩ ለእኔ ምርጥ ነበር ለቡድናችንም ጥሩ ጊዜ ነበር “ ሲል ኪሊያን ምባፔ ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ አክሎም ቡድናቸው በቀጣይ ሁሉንም ነገር ማሸነፍ እንደሚፈልግ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 1:30 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:30 ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስቦዝላይ ለምን ከጨዋታው ውጪ ሆነ ?

ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የሊቨርፑል ተጨዋች ዶምኒክ ስቦዝላይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ ነው።

ተጨዋቹ ከጨዋታው ውጪ የሆነው ባጋጠመው ህመም ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ኢብራሂም ኮናቴ ከጉዳት ወደ ቡድኑ ሲመለስ ፌዴሪኮ ቼሳ በበኩሉ ተጠባባቂ ሆኖ የሚጀምር ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ደፋር መሆን አለብን “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው የሊቨርፑል ጨዋታ ደፋር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየትም “ ደፋር መሆን አለብን ፤ ቀለል አድርገን እግርኳስ መጫወት አለብን “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ በእግርኳስ ሁሉም ነገር ይቻላል ጥቃቅን ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን “ ሲሉ ሩበን አሞሪም አክለው ገልጸዋል።

ስለ ራሽፎርድ አስተያየታቸውን የሰጡት አሞሪም “ እሱ አሁንም እንደታመመ ነው ለጨዋታው ዝግጁ አይደለም " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዩናይትድ ውስጥ ለምን እንዳለን ማሳየት አለብን “ ማርቲኔዝ

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በዛሬው የሊቨርፑል ጨዋታ ራሳቸውን ማሳየት እንደሚፈልጉ ተናግሯል።

“ ጨዋታዎች ስትሸነፍ በራስ መተማመን ይጠፋል ነገርግን በጥልቀት እየሰራንበት ነው “ ሲል ማርቲኔዝ ተናግሯል።

ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ አክሎም “ በአሰልጣኙ እና ቡድኑ እተማመናለሁ “ ያለ ሲሆን “ ዛሬ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ለምን እንዳለን ማሳየት አለብን “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዩናይትድ ጥሩ ተጨዋቾች አሉት " አሊሰን

የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ቡድናቸው በጨዋታው ትኩረት እንዲያደርግ እና እንዳይዘናጋ አሳስቧል።

“ ዩናይትድ በርካታ ጥሩ ተጨዋቾች አሉት “ ያለው አሊሰን " አሁን ላይ ጥሩ ላይሆኑ ይችላሉ ነገርግን እግርኳስ እንዴት በፍጥነት እንደሚቀየር እናውቃለን " ብሏል።

" ራሳችን ላይ ማተኮር አለብን ፣ በሊጉ ሁሉም ጨዋታዎች ጠንካራ ናቸው ለፍልሚያ መዘጋጀት አለብን ጨዋታው በምንፈልገው መንገድ እንደሚጠናቀቅ ሙሉ ተስፋ አለን።" አሊሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
7'

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
14 '

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 '

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 '

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
44 '

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በሳምንቱ ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመርያው አጋማሽ በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ዲያጎ ዳሎት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ሊቨርፑል 55% - 45% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 '

ሊቨርፑል 0 -0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/10 13:02:07
Back to Top
HTML Embed Code: