Telegram Web Link
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ሲቲ እና ኤቨርተን

1ኛ. @Z_warrior9
2ኛ. @Hassumi_9
3ኛ. @Emmiye21

የቼልሲ እና ፉልሀም ጨዋታ

1ኛ. @Miku1121
2ኛ. @Kirada
3ኛ. @Jesse175

የማንችስተር ዩናይትድ እና ዎልቭስ

1ኛ. @eliabte
2ኛ. @Tuyeetinsae
3ኛ. @Bili7Lili

የሊቨርፑል እና ሌስተር ሲቲ

1ኛ. @Hamido505
2ኛ. @usernamemother
3ኛ. @RGT_810

የአርሰናል እና ኤፕስዊች ታውን ጨዋታ

1ኛ. @Ifahawwina
2ኛ. @TeTesfu
3ኛ. @Joh11_21

🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሽልማቱ በነገው ዕለት የሚደርሳቸው ይሆናል።

@tikvahethsport
“ 2025 የዋንጫ አመት ይሆናል “ ራይስ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አማካይ ዴክላን ራይስ ቡድናቸው በ 2025 ዋንጫ ለማሸነፍ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።

“ 2025 ዋንጫዎችን የምናሸንፍበት አመት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን “ ሲል ዴክላን ራይስ ተናግሯል።

ቡድኑ ዋንጫ ለማሸነፍ ጨዋታዎችን ማሸነፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለፀው ራይስ “ በመጨረሻ ምንም ባናሳካም ምንም ማለት አይደለም “ ብሏል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
“ ለደጋፊዎቹ ጥሩ ምለሻ መስጠት እፈልጋለሁ “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ለክለቡ ደጋፊዎች ጥሩ ነገር መስጠት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

“ ከደጋፊዎቹ የምጠብቀው ነገር የለም “ ያሉት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እዚህ የመጣሁት የማንንም ድጋፍ ልጠይቅ አይደለም በማለት ተናግረዋል።

“ ደጋፊዎች ያላቸውን ሁሉ እየሰጡን ነው ትልቅ ድጋፍ ይሰጡናል ተሸንፈንም እያበረታቱን ነው “ ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

" ለደጋፊዎቹ ከእነሱ ምንም ነገር ሳልጠይቅ ጥሩ ነገር ልሰጣቸው እፈልጋለሁ " አሞሪም

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በቀጣይ ጨዋታ አለመኖሩን ተከትሎ ሀሪ ማጓየር አምበልነቱን ይቀበል እንደሆነ የተጠየቁት ሩበን አሞሪም “ አምበሉን በጨዋታው ቀን ታዩታላችሁ " ብለዋል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ልዩ ውርርዶች ከቀመረኛው!
የቀመረኛው የእለቱ ጥቆማዎች!
ዛሬም አሸናፊ የውርርድ ጥቆማዎች ለእርስዎ!

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
በጠንካራ አቋም ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ዌስትሃምን አሸንፎ መሪነቱን ያጠናክራል? እስቲ ኮመንት ላይ ውጤቱን እንገምት! በዕለታዊ 1.1 ጊባ የዳታ ጥቅል የኳስ ጨዋታውን ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል!

በM-PESA ላይ ስንገዛ
እለታዊ 1.3 ጊባ በ30 ብር ብቻ! 

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" ሳላህ ባሎን ዶር ያሸንፋል " ጄሚ ካራገር

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራገር መሐመድ ሳላህ የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት ያሸንፋል የሚል ትልቅ ግምት እንዳለው ተናግሯል።

“ መሐመድ ሳላህ የባሎን ዶር እና የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት የማሸነፍ ትልቅ እድል አለው “ ሲል ጄሚ ካራገር ተናግሯል።

ጄሚ ካራገር አክሎም ደጋፊዎች በመሐመድ ሳላህ ጉዳይ ምንም ቢሉኝ ከእኔ የበለጠ የእሱ አድናቂ አይገኝም በማለት ተናግሯል።

የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊው ከሪያል ማድሪድ ፣ ሊቨርፑል ፣ ኢንተር ሚላን እና ባየር ሙኒክ መካከል አንዱ እንደሚሆን ጄሚ ካራገር ግምቱን አስቀምጧል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ዩናይትድ የቀድሞ ተጨዋቾቹን ድጎማ አቋርጧል !

ማንችስተር ዩናይትድ ለቀድሞ የክለቡ እግርኳስ ተጨዋቾች ማህበር ያደርግ የነበረውን የገንዘብ ድጎማ ማቋረጡ ተገልጿል።

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ማህበር አነስተኛ ገቢ ላላቸው የቀድሞ የክለቡ ተጨዋቾች የሚረዳ ማህበር እንደነበር ተነግሯል።

ክለቡ ለማህበሩ በአመት 40,000 ፓውንድ ይረዳ እንደነበር ሲገለፅ ነገርግን አሁን ላይ መክፈል ማቋረጡን ቴሌግራፍ ዘግቧልደ

እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ የማንችስተር ዩናይትድን አነስተኛ ድርሻ ከተቆጣጠሩ ወዲህ የክለቡን ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሱ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
🎁🎄🎁🎄 እንኳን አደረሳችሁ🎁🎄🎁🎄

🆕አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል 📲 ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📣 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞 0929008292

✉️ inbox @bina27

📌 አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
“ ተስፋ አልቆርጥም እዚሁ እቆያለሁ “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አሁን ባጋጠመን ችግር ተስፋ አልቆርጥም እዚሁ እጋፈጠዋለሁ በማለት ተናግረዋል።

ክለቡ በትልቅ ችግር ውስጥ በመሆኑ ምክንያት “ ተስፋ አልቆርጥም “ ያሉት ጋርዲዮላ “ እዚህ መሆን እፈልጋለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ ተጨዋቾች እያደረጉ በሚገኙት ነገር ደስተኛ ነኝ ሰባት ተጨዋቾች ቢጎዱም እንኳን ሁሉም ሰው ጠንክሮ ኤየሰራ ነው።“ ጋርዲዮላ

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም “ የማንችስተር ሲቲን ደጋፊዎችን አንገት ማስደፋት አልፈልግም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

“ አሁን እያሳላፍን ያለነው ችግር ባለፉት አመታት የነበረን ስኬት ምን ያህል ከባድ እንደነበር እንድንገነዘብ አድርጎናል ምርጥ ስምንት አመታት ነበሩን።“ ጋርዲዮላ

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
“ ሜዳልያችሁ እንዳይበላሽ በቆምጣጤ ዘፍዝፉት “

በመላው አለም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የኦሎምፒክ ውድድር ከወራት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ በበርካታ ውዝግቦች ታጅቦ መካሄዱ ይታወቃል።

አሁን ላይ በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎች የተበረከቱ ሜዳልያዎች ከወዲሁ ቀለማቸው እየለቀቀ እና እየተበላሹ መሆኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ በርካታ አትሌቶች ያገኙት ታሪካዊ ሜዳልያ በመበላሸቱ ቅሬታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ሲያቀርቡ ተስተውለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን ከሰጡ አትሌቶች መካከል ፈረንሳዊው ዋናተኛ ንዶዬ ብሮዋርድ አንዱ ሲሆን ሜዳልያውን “ ፓሪስ 1924 " ሲል ገልፆታል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ ሜዳልያ ባለቤት የነበረው ቦክሰኛ ኢማኑኤል ራዬስ ፕላ በበኩሉ ሜዳልያው እንዳይበላሽ ጠቃሚ ቪዲዮ መመልከቱን እና የእሱ ጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ሌሎች አትሌቶች ቢጠቀሙ ሲል መፍትሔ ያለውን የተናገረው ቦክሰኛው “ ቆምጣጤ እና ውሀ አድርጋችሁ አስቀምጡት ኢንተርኔት ላይ አይቼ ለእኔ ስርቶልኛል “ ብሏል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ኢንተር ሚላን የሊጉን መሪነት ተረከበ !

ኢንተር ሚላን ከካግሊያሪ ጋር ያደረገውን ጣልያን ሴርያ አስራ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ ፣ ባስቶኒ እና ሀካን ካልሀኖግሉ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ የሚመራው ኢንተር ሚላን ባለፉት አስራ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠመውም አስሩን ማሸነፍ ችሏል።

ኢንተር ሚላን ማሸነፉን ተከትሎ የጣልያን ሴርያን መሪነት ከአታላንታ መረከብ ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ ኢንተር ሚላን :- 40 ነጥብ
1️⃣8️⃣ ካግሊያሪ :- 14 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

እሁድ - ቬኔዝያ ከ ኢንተር ሚላን

እሁድ - ሞንዛ ከ ካግሊያሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from Can PlayStation (CAN PlayStation Manager)
ታላቅ የገና ስጦታ
Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ  ቸምረው መቀየር ይችላሉ)

PlayStation 4 Slim በቅናሽ ዋጋ ከCan PlayStation ይግዙ

Ps4 Slim
Dubai used
2 Orginal jestic
5 installed
<Fc25
<Batman
<rocket league
<Formula one
<EA football 25 installed
Storage 500gb
HD quality resolution
Version 12.00
Full accessories
1 years guarantee

ዋጋ=37,000

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

11:00 ናፖሊ ከ ቬኔዝያ

11:30 ሌስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ሲቲ

12:00 ኤቨርተን ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

12:00 ቶተንሀም ከ ዎልቭስ

2:00 ጁቬንቱስ ከ ፊዮሬንቲና

2:15 ዌስትሀም ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

4:45 ኤሲ ሚላን ከ ሮማ

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማቶቻችን የማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሽልማታችን 10:00 ፣ 1:00 ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ብቻ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኢንተር ሚላን የሊጉን መሪነት ተረከበ ! ኢንተር ሚላን ከካግሊያሪ ጋር ያደረገውን ጣልያን ሴርያ አስራ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ ፣ ባስቶኒ እና ሀካን ካልሀኖግሉ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። በአሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ የሚመራው ኢንተር ሚላን ባለፉት አስራ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አልገጠመውም አስሩን ማሸነፍ…
አታላንታ ሊጉን እየመራ አመቱን አጠናቀቀ !

የጣልያን ሴርያ መሪው አታላንታ ትላንት ምሽት ከላዝዮ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ይህንንም ተከትሎ አታላንታ በሴርያው ከአስራ አንደኛ ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥለዋል።

በአሰልጣኝ ጋስፔሪኒ የሚመራው አታላንታ በሴርያው ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ ምንም ጨዋታ አልተሸነፈም።

አታላንታ በአርባ አንድ ነጥቦች አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለውን ኢንተር ሚላን በአንድ ነጥብ በልጠው ሴርያውን መምራታቸውን ቀጥለዋል።

አታላንታ የጣልያን ሴርያን እየመሩ 2024 ማጠናቀቅ ችለዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር አታላንታ ከዩዲኔዜ ላዝዮ ከሮማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ?

1️⃣ አታላንታ :- 41 ነጥብ
4️⃣ ላዝዮ :- 35 ነጥብ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ልምምዱን ለደጋፊው ክፍት ያደርጋል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዛሬ በስታዲዮ ዮሃን ክራይፍ የሚያደርጉትን ልምምድ ለተመልካች ክፍት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ባርሴሎናዎች 6,000 ተመልካች መያዝ በሚችለው ስታዲዮ ዮሃን ክራይፍ በየአመቱ ልምምዳቸውን በደጋፊዎቻቸው ፊት የማድረግ ባህል አላቸው።

ስታዲየሙ በደጋፊዎች እንደሚሞላ ሲጠበቅ ሁሉም የሚገኘው ጊቢ ለበጎ አድራጎት አላማ እንደሚውል ተነግሯል።

ተጨዋቾቹ ከልምምድ በኋላ ከደጋፊዎች ጋር ጊዜ እንደሚኖራቸው እና በመቀጠልም ወደ ሆስፒታል አምርተው ህፃናትን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፋብዮ ቬራ ወደ አርሰናል ይመለስ ይሆን ?

በውሰት ለፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ በመጫወት ላይ የሚገኘው ፋብዮ ቬራ የውሰት ውሉን በማቋረጥ ወደ አርሰናል ሊመለስ እንደሚችል ተገልጿል።

የ 24ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፋብዮ ቬራ ትላንት ምሽት ጨዋታውን ካደረገው የፖርቶ ስብስብ ውጪ ተደርጎ ነበር።

አርሰናል የፋብዮ ቬራን የውሰት ኮንትራት በማቋረጥ ወደ ቡድናቸው ሊመልሱት እንደሚችሉ ተዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖርቶ አሰልጣኝ ቪቶር ብሩኖ “ ፋብዮ ቬራን እናምነዋለን በሚቀጥለው ሳምንት በድጋሜ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ፋቢዮ ቬራ ባለፈው ክረምት የቀድሞ ክለቡ ፖርቶን በውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ መቀላቀሉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜና በስልካችን! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!

በElite ስፖርት በሽ ዜናዎች⚡️

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ፔፕ ጋርዲዮላ 500ኛ ጨዋታቸውን ይመራሉ !

ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ቀን 11:30 ከሌስተር ሲቲ ጋር የፕርሚየር ሊግ መርሐግብሩን የሚያደርግ ይሆናል።

በጨዋታው ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ 5️⃣0️⃣0️⃣ኛ የማንችስተር ሲቲ ጨዋታቸውን የሚመሩ ይሆናል።

“ ማንችስተር ሲቲን ለአምስት መቶ ጨዋታዎች በመምራቴ ኩራት ይሰማኛል “ ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

በቀጣይ ማንችስተር ሲቲን ለተጨማሪ 500 ጨዋታዎች መምራት የማይታሰብ ነው ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/03 23:48:10
Back to Top
HTML Embed Code: