Telegram Web Link
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም ከ 4️⃣5️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቼልሲን በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጆ ስታዲየም አሸንፎታል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ከ 2️⃣9️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሎል።

የአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካው ቡድን ቼልሲ ከአስራ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ ተሸንፏል።

በዘንድሮው የውድድር አመት ቶተንሀም ከሳውዝሀምፕተን እና ዎልቭስ በመቀጠል ሶስተኛው ብዙ የሊግ ጨዋታ የተሸነፈው ክለብ ሆኗል።

ኖቲንግሀም ፎረስት በ1️⃣8️⃣ ጨዋታዎች 3️⃣4️⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ቶተንሀም ከ 2️⃣3️⃣ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቦክሲንግ ደይ መርሐግብር ያደረገውን ጨዋታ ተሸንፏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
5 ' ዎልቭስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
18 '

ዎልቭስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
25 '

ዎልቭስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
“ በዋንጫ ፉክክሩ እንደሌለን ተናግረናል “ ፓልመር

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር ቡድናቸው ገና በማደግ ላይ ያለ መሆኑን ገልጿል።

“ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ እንደሌለን ሁሉም ሰው ከጀምሩ ሲናገር ነበር “ ሲል ፓልመር ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ ተናግሯል።

“ እኛ እንደ ቡድን በማደግ እና በመሻሻል ላይ ነው የምንገኘው ሁሉንም ጨዋታዎች እንደማናሸንፍ እናውቅ ነበር።“ ኮል ፓልመር

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
እረፍት

ዎልቭስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
“ ወደ ዩናይትድ የምናቀናው በትልቅ በራስ መተማመን ነው “  ኤዲ ሀው

የኒውካስል ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ቡድናቸው በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ በራስ መተማመን ይዞ እንደሚገጥመው ተናግረዋል።

ከዛሬው ድል በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ኤዲ ሀው “ ሰኞ ወደ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም የምናቀናው ትልቅ በራስ መተማመን እና በቃት ይዘን ነው “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ኤዲ ሀው አክለውም ዛሬ አስቶን ቪላን ያሸነፉበትን ጨዋታ “ በቀጣይ ምን ማሻሻል አለብን የሚለውን ለማወቅ በድጋሜ እመለከተዋለሁ “ ብለዋል።

“ አይሳክ የማይታመን አቅም ያለው ተጨዋች ነው እሱን በማስፈረሜ ደስተኛ ነኝ ወድጄዋለሁ እሱ በምንም አለውጠውም።“ ኤዲ ሀው

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
51 '

ዎልቭስ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ

- የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

- ዎልቭስ አስቆጥረው የነበረው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport @kidusoyoftahe
59 '

ዎልቭስ 1-0 ማንችስተር ዩናይትድ

ኩንሀ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ሌስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የሊቨርፑል እና ሌስተርን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 5:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
78 '

ዎልቭስ 1-0 ማንችስተር ዩናይትድ

ኩንሀ

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
90+8'

ዎልቭስ 2-0 ማንችስተር ዩናይትድ

ኩንሀ
ህዋንግ

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ !

ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የበዓል ሰሞን መርሐግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የዎልቭስን የማሸነፊያ ግብ ህዋንግ እንዲሁም ኩንሀ ከማዕዘን ምት በቀጥታ ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ስምንተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር አመቱ በሁሉም ውድድሮች ሶስተኛ ቀይ ካርዱን ተመልክቷል።

ፈርናንዴዝ ከ 1️⃣9️⃣ አመታት በኋላ በአንድ የውድድር ዘመን ሶስት ቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሆኗል።

ማኑኤል ኡጋርት የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት ምክንያት ቀጣዩ የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነታቸው አምስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣4️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 22 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ዎልቭስ :- 15 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሁድ - ቶተንሀም ከ ዎልቭስ

ሰኞ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ቡድኑ ደካማ ነው “ ሩበን አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ ቡድናቸውን “ ደካማ “ ሲሉ ገልጸውታል።

“ ጨዋታዎችን ከተሸነፍክ እና ምንም ጨዋታ ካላሸነፍክ ወደኋላ እየተጓዝክ ነው “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ስለ ቡድናቸው ሁኔታ ተናግረዋል።

“ ከባድ ሁኔታ ላይ ነን “ የሚሉት ሩበን አምሪም የአስቸጋሪው ሁኔታ ማብቂያ መቼ እንደሆነ እንደማያውቁ ገልጸዋል።

ስለ ዛሬው ቡድናቸው የተናገሩት አሰልጣኙ “ ከኋላ መስመር እስከ ፊት መስመር ደካማ ቡድን ነው " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
10 '

ሊቨርፑል 0-1 ሌስተር ሲቲ

አንድሬ አዬው

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
2024/12/28 16:26:55
Back to Top
HTML Embed Code: